Thursday, May 16, 2013

የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሀመድ ኡመር የመንግስት ሰራተኞች የአባልነት ክፍያ በግዴታ እንደሚቆረጥባቸው ተናገሩ

የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሀመድ ኡመር የመንግስት ሰራተኞች የአባልነት ክፍያ በግዴታ እንደሚቆረጥባቸው ተናገሩ
ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ኢሳት እጅ በገባው የፕሬዚዳንቱን ሚስጢራዊ ንግግሮች በያዘው  ፊልም ውስጥ እንደተመለከተው ፣ አቶ አብዲ የኢህአዴግ አጋር ድርጅት የሆነው የሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሲ ፓርቲ ( ሶህዴፓ) አባላት በግዴታ የአባልነት መዋጮ እንዲከፍሉ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ” መንግስት በአንድ በኩል ገንዘብ ይሰጣል በሌላ በኩል ደግሞ ገንዘብ ከፋዩዋ በግዴታ ከሰራተኞች እየቆረጠች ትወስዳለች” ብለዋል አቶ አብዲ።

አቶ አብዲ ድርጅታቸው ሶህዴፓ 40 ሺ አባላት እንዳሉት ተደርጎ ሪፖርት የሚቀርበውም ውሸት ነው ብለዋል። ” 40 ሺ አባላት ቢኖሩን ኑሮ ጸረ ሰላም ሀይሎች እንዴት ኖሩ?” በማለት የጠየቁት አቶ አብዲ፣ ያሉትም አባላት ቢሆኑ ገንዘባቸው በግዴታ በመንግስት የሚወሰድባቸው እንጅ በሙሉ ልብ የአባልነት መዋጮ የሚከፍሉ አይደሉም” ሲሉ አክለዋል።

እርሳቸው የድርጅት አባል የሚሉት በራሱ ፈቃድ መዋጮ የሚከፍል እንጅ መንግስት አስገድዶ የሚቆርጥበትን አለመሆኑን ግልጽ አድርገዋል።

ኢሳት በተከታታይ በለቀቃቸው የቪዲዮ ማስረጃዎች ፕሬዚዳንቱ  “ ክልሉ እንዳደ ፣ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደደረ ተደርጎ በየጊዜው የሚቀርበው ሪፖርት ፍጹም ትክክል ያልሆነ ውሸት ነው።  ከአሁን በፊት ይቀርቡ የነበሩ ሪፖርቶችም እንዲሁ  ግምገማ ለማለፍ ተብሎ በውሸት ላይ ተመስርተው የተዘጋጁ መሆናቸውን ” መግለጻቸው ይታወሳል።

ፕሬዚዳንቱ ” ትግሬዎች፣ አማራ መልሶ ስልጣን እንዳይዝ ኦጋዴኖችን አስታጥቀው በጋራ አገሪቱን እንድንመራ ይፈልጉ ነበር፣ እኛ ግን እንደ አማራ ቆጥረናቸው ተኩስ ከፈትንባቸው፤ አማራ እና ትግሬ፣ አማራ እና ኦሮሞ መቼውንም አይታረቁም ፣ አይተባበሩም ስለዚህ የኦጋዴን ህዝብ ከትግሬ ጎን እንዲቆም፣ አማራ እና ትግሬን፣ አማራ እና ኦሮሞን አንድ አድርጎ አማራ እያለ መጥራቱን ያቁም” በማለት መናገራቸውም በሚስጢራዊ ቪዲዮው ውስጥ መጠቀሱ ይታወሳል።

በጉዳዩ ዙሪያ የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንትን ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም ፕሬዚዳንቱ ስብሰባ ላይ ናቸው በሚል ጸሀፊያቸው ልታገናኝን አልቻለችም
 ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ኢሳት እጅ በገባው የፕሬዚዳንቱን ሚስጢራዊ ንግግሮች በያዘው ፊልም ውስጥ እንደተመለከተው ፣ አቶ አብዲ የኢህአዴግ አጋር ድርጅት የሆነው የሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሲ ፓርቲ ( ሶህዴፓ) አባላት በግዴታ የአባልነት መዋጮ እንዲከፍሉ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ” መንግስት በአንድ በኩል ገንዘብ ይሰጣል በሌላ በኩል ደግሞ ገንዘብ ከፋዩዋ በግዴታ ከሰራተኞች እየቆረጠች ትወስዳለች” ብለዋል አቶ አብዲ።

... አቶ አብዲ ድርጅታቸው ሶህዴፓ 40 ሺ አባላት እንዳሉት ተደርጎ ሪፖርት የሚቀርበውም ውሸት ነው ብለዋል። ” 40 ሺ አባላት ቢኖሩን ኑሮ ጸረ ሰላም ሀይሎች እንዴት ኖሩ?” በማለት የጠየቁት አቶ አብዲ፣ ያሉትም አባላት ቢሆኑ ገንዘባቸው በግዴታ በመንግስት የሚወሰድባቸው እንጅ በሙሉ ልብ የአባልነት መዋጮ የሚከፍሉ አይደሉም” ሲሉ አክለዋል።

እርሳቸው የድርጅት አባል የሚሉት በራሱ ፈቃድ መዋጮ የሚከፍል እንጅ መንግስት አስገድዶ የሚቆርጥበትን አለመሆኑን ግልጽ አድርገዋል።

ኢሳት በተከታታይ በለቀቃቸው የቪዲዮ ማስረጃዎች ፕሬዚዳንቱ “ ክልሉ እንዳደ ፣ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደደረ ተደርጎ በየጊዜው የሚቀርበው ሪፖርት ፍጹም ትክክል ያልሆነ ውሸት ነው። ከአሁን በፊት ይቀርቡ የነበሩ ሪፖርቶችም እንዲሁ ግምገማ ለማለፍ ተብሎ በውሸት ላይ ተመስርተው የተዘጋጁ መሆናቸውን ” መግለጻቸው ይታወሳል።

ፕሬዚዳንቱ ” ትግሬዎች፣ አማራ መልሶ ስልጣን እንዳይዝ ኦጋዴኖችን አስታጥቀው በጋራ አገሪቱን እንድንመራ ይፈልጉ ነበር፣ እኛ ግን እንደ አማራ ቆጥረናቸው ተኩስ ከፈትንባቸው፤ አማራ እና ትግሬ፣ አማራ እና ኦሮሞ መቼውንም አይታረቁም ፣ አይተባበሩም ስለዚህ የኦጋዴን ህዝብ ከትግሬ ጎን እንዲቆም፣ አማራ እና ትግሬን፣ አማራ እና ኦሮሞን አንድ አድርጎ አማራ እያለ መጥራቱን ያቁም” በማለት መናገራቸውም በሚስጢራዊ ቪዲዮው ውስጥ መጠቀሱ ይታወሳል።

በጉዳዩ ዙሪያ የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንትን ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም ፕሬዚዳንቱ ስብሰባ ላይ ናቸው በሚል ጸሀፊያቸው ልታገናኝን አልቻለችም

Ethiopian editor questioned over story on Azeb Mesfin

Azib Mesfin's flower farm accused of environmental pollution
(CPJ) New York, May 15, 2013–Ethiopian police in Addis Ababa questioned an editor for several hours today in connection with a story published in October about the widow of the late Ethiopian leader Meles Zenawi, according to news reports.

Officers in the Ethiopian Federal Police Crime Investigation Department interrogated Ferew Abebe, the former editor-in-chief of the private Amharic-language weekly Sendek, about his sources for the October 10, 2012, story that said Azeb Mesfin, Meles’ widow, had refused to leave the Ethiopian national place nearly two months after the prime minister’s death, local journalists said. The story, which was widely covered in local and international press, cited government sources as saying that Meles’ successor, Hailemarian Desalegn, was unable to live in the palace.
 
Ferew refused to identify his sources and cited Ethiopian laws that guaranteed the rights of a journalist to keep sources confidential, local journalists said. According to the Ethiopian penal code, a court can compel journalists to reveal their sources if a crime has been committed against the constitutional order, national defense force, or security of the state, which constitutes clear and imminent danger.
 
Police released Ferew on a bond of 5,000 birrs (US$265) pending further investigation, according to the same sources.

On Monday, police also summoned a deputy editor for Sendek to question him about the same story, local journalists said. He was released without charge.

“Ethiopian police’s demand that Ferew Abebe reveal his sources for a story published seven months ago is intimidation and tramples on the protections afforded to journalists under Ethiopian law,” said CPJ Africa Advocacy Coordinator Mohamed Keita. “We call on authorities to abandon their long-standing pattern of vindicative persecution of journalists who raise questions about issues of public interest, such as the occupation of a public building by the former first lady.”
 
At least seven journalists are behind bars in Ethiopia, making the country the second leading jailer of journalists in Africa, according to CPJ research. Ethiopia trails only Eritrea among Africa’s worst jailers of journalists, CPJ research shows.

ልቅ የሆነ የሙስና ግንኙነት…



melaku_fenta
ልቅ የሆነ የሙስና ግንኙነት… (ትንሽ ወግ)
አቶ መላኩ ፈንታ መንግስት የሚያውቀው በሽታ አለብኝ እና በዋስ ልፈታ፤ አሉ አሉ፤…
እኔ ደግሞ እንዲህ አልኩ፤
ምን ነካዎ አቶ መላኩ፤ መንግስት በሚያውቀው በሽታዎ ነውኮ ዘብጥያ የወረዱት፤ እርግጥ ነው ይህንን በሽታ ከየትም አላመጡትም፤ ከመንግስትዎ ጋር ባደረጉት ጥንቃቄ የጎደለው እና ልቅ የሆነ የሙስና ግንኙነት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እርግጥ ነው መንግስታችን ራሱም የዚህ በሽታ ተጠቂ መሆኑ እሙን ነው፡፡ እርግጥ ነው በማራዘሚያ ብዛት እንጂ ሁሉም ባለስልጣኖቸች የዚህ ህመም ሰለባ መሆናቸውም ግልጽ ነው፡፡
ታድያ መንግስት የሚያውቀው በሽታ ስላለብኝ ማሩኝ ከማለት በሽታውን ያመጣሁት ከእነርሱ ነውና ሁሉም ይምጡ ማለት አይሻልዎትም ነበር… ሃሃ (በቅንፍም የምር ግን ምንድነው መንግስት የሚያውቀው በሽታ…)
አቶ ገብረዋህድ ገብረ መድን በቤተሰቦቼ ላይ ኢሰብአዊ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል… ሀገሪቱ ምን አይነት ሀገር እየሆነች ነው… ብለዋል አሉ፡፡
እኔ ደግሞ እንዲህ አልኩ፤
አቶ ገብረዋህድ ቆየችኮ እርስዎ በስልጣን ነጠላ ሰረዝ በዶላር ነጠላ ሰረዝ በፓውንድ እና በብር የሞቀ ቤትዎ ሆነው የውጪው ቅዝቃዜ አልታወቅዎትም እንጂ “ሀገሪቱ ምን አይነት ሀገር እየሆነች ነው…” የሚለውን ጥያቄ እኮ እነ አቶ አንዷለም አራቄ መጠየቅ ከጀመሩ ቆዩ፣ ሀገሪቷ ምን አይነት ሀገር እየሆነች ነው የሚለውን ጥያቄ እነ አቶ በቀለ ገርባ ጠይቀው ማንም መልስ አልሰጣቸውም፡፡
በቅርቡ እንኳ አቡበከር በቴሌቪዥን እጁን በካቴና ታስሮ ፖሊሶች ሲሳሳቁበት በአደባባ እያየን ሁላችንም በአንድ ድምጽ ሀገሪቷ ወዴት እየሄደች ነው… ብለን ጠይቀን ነበር፡፡ ግን እርስዎም ሆኑ ጓደኞችዎ ድምፃችን አልሰማችሁም፡፡
እነ ርዮት አለሙ እነ እስክንድር ነጋ እነ ውብሸት ታዬ በፍትህ እጦት እና በኢሰብአዊ አያያዝ ተማረው “ሀገሪቷ ምን አይነት በያይነቱ ሆነች…” ብለው ከጠየቁ ቆዩኮ… ታድያ ያኔ የት ነበሩ… (በቅንፍም ይቺን ነገር ሁሉም ባለስልጣን በየተራ ይያት ብለን እንመርቃለን)
ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሌሎችንም ሙሰኞች አጋልጡ ብሎ ስልክ ቁጥሩን ሰጥቶናል፡፡ አሉ
እኔ ደግሞ እንዲህ አልኩ፤
እኔ የምልህ ፀረ ሙስናዬ የምን ቁጥ ቁጥ ነው ብዬ… አጠቃላይ ኢህአዴግን በሙስና ብልግና ብጠቁም ለማሰር የሚያስችል ሰፊ ቃሊቲ አለህ… ከሆነ ዛሬውኑ እደውላለሁ…!

Wednesday, May 8, 2013

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ


ሰላማዊ ትግላችንን ከፍ አድርገን እንቀጥላለን!!!

Blue Party Ethiopia
ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ ጊዚያት በሐገራችን የሚፈፀሙ የተለያዩ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶችና ህገ ወጥ ድርጊቶች ኢንዲቆሙ ለመንግስት የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቢቆይም ከመንግስት የተሰጡት ምላሾች ግን ጥያቄዎቻችንን ማንቋሸሽና ማጣጣል ወይም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ማለፍ ሆኖ ቆይቷል፡፡

Blue Party Ethiopia
ፓርቲያችን ጥያቄዎችን የሚያቀርበው መንግስት አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው ቢሆንም ችግሮቹ እስካሁንም ሳይፈቱ አንዳንዶቹም እየተባባሱ ቀጥለዋል፡፡ በመሆኑም ፓርቲያችን ከዚህ በፊት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጥሪ ለመንግስት አቅርቦ መልስ ከተነፈጋቸው መካከል፤
1ኛ. ለፍትህና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን የሚታገሉ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባላትን በአሸባሪነት ስም ማሰርና ማሰቃየትን አጥብቀን የምንቃወም መሆኑንና እስረኞችንም እንዲፈታ የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን ምንም መልስ ያልተገኘ በመሆኑ፤

2ኛ. የዜጎችን ሰብዓዊና ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በመጣስ ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ኢሰብዓዊ በሆነ ድርጊት በታጠቁ ኃይሎች እንዲፈናቀሉ ማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመሆኑ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡና የተፈናቀሉት ዜጎችም በአስቸኳይ ወደየመኖሪያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ በመንግስትም ሆነ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸው የጠየቅን ቢሆንም አሁንም ገና የሚፈናቀሉ ዜጎችን ስም ዝርዝር በየማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ ተለጥፎ እያየን በመሆኑ፤
3ኛ. መንግስት በኃይማኖታችን ጣልቃ አይግባ፣ የእምነት ስርዓታችንና የሃይማኖት መሪዎቻችንን እምነታችንበሚፈቅደው ብቻ እናከናውን ያሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን በአሸባሪነት ወንጀል በመክሰስ በእስር እንዲማቅቁና ሰብዓዊ መብታቸው እንዲጣስ መደረጉ እንዲቆምና ያነሷቸውም የእምነት ነፃነት ጥያቄዎቻቸው እንዲከበር የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን የተገኘ መልስ ባለመኖሩ፤
4ኛ. መንግስት የኑሮ ዉድነትን፣ የሥራ አጥነትንና በሙስና የተዘፈቁ የመንግስት ሌቦችን የሚቆጣጠርባቸውን መንገዶችና ፖሊሲዎች በማዉጣት ሐገራችንን ከቀውስና ዜጎችንም ከሰቆቃ እንዲያወጣ በተደጋጋሚ ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ሰሚ አጥተው በመቆየታቸው እነዚህ ችግሮች እንዲፈቱ አሁንም አጥብቀን የምንጠይቅ መሆኑ እና ሌሎችም፤ በመንግስት ምላሽ የተነፈጓቸው ጥያቄዎቻችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብን ትኩረት የሚያገኙበትን መንገድ መፈለግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚሁ መሰረት ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች በሚገኙበት ድምፃችንን ለማሰማት ከግንቦት 15 – 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስና ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ከላይ ያነሳናቸውና ሌሎችም ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ ሰማያዊ ፓርቲ ለመጠየቅ ወስኗል፡፡ በመሆኑም እነዚህ ጥያቄዎች እንዲመለሱ የሚፈልግ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበራትና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በእነዚህ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ሚያዚያ 29 ቀን 2005 ዓ. ም
አዲስ አበባ

Monday, May 6, 2013

አባይ፤ የኢህአዴግ አባል ነውን!?



ethiopia
“አባይ ማደሪያ የለው ደሞዝ ይዞ ይዞራል…” የምትለው አባባል ከተፈጠረች እነሆ ሁለት አመት አለፋት፡፡ ግዜው ይሮጣል፡፡ ሶስት፣ አራት፣ እና አምስት አመትም እዝችው አጠገባችን ቁጭ ብለው የምናወራውን እየሰሙ ነው፡፡

ከሶስት አመት በፊት መንግስታችን የትራንስፎርሜሽን እቅድ የሚባል ወደ አስማት ቀረብ የሚል ዕቅድ አውጥቶ “ወተት በቧንቧ በየቤቱ እናቀብላለን” አይነት ነገር ሲነግረን ይቺ ነገር የየትኛው “እንትን” ውጤት ትሆን ብለን ስንጨነቅ ሰንበተን ነበር፡፡ ከዛ ወድያው ትራንስፎርሜሽኑን አባይ አጥለቀለቀው፡፡ ከዛስ…. ከዛማ ትራንስፎርሜሽን ተረስታ አባይ አባይ ይዘፈን ጀመር፡፡ ከዛስ…. ምን ከዛስ አለው… አባያችን ከእያንዳንዳችንን ኪስ ውስጥ ዘው ብሎ ገባ….ታ!
ሰላም ወዳጄ እንዴት ሰነበቱልኝ አውዳመቱ እንዴት አለፈ… እንኳንስ አውዳመቱ እና ስንቱ አያልፍም የተባለ ክፉ ቀን አልፏል… አሉኝ እንዴ! አዎ ጥሩ ነገር ብለውኛል፡፡ ቀጥሎም ገና ብዙ ቀኖች ያልፋሉ ዕድሜውን የሰጠን ሰዎችም ቁጭ ብለን እንታዘባለን፡፡ ስለዚህ ዕድሜውን ይለምኑ…! በቅጡ ካወጋን እኮ ሰነባበትን መሰል…! አንዳንድ ወዳጆቼም “በአነስተኛ እና ጥቃቅን ፅሁፎች አደከምከን እኮ” ሲሉ በውስጥ መስመርም በአደባባይም ተግሳጽ ልከውልኛል፡፡ ሰዉ ቀላል ተናጋሪ ሆኗል እንዴ…!
ለማንኛውም ዛሬ በአባይ ጉዳይ ላይ ትንሽ እናውጋ ብዬ ተከስቻለሁ…! ይቺ ፅሁፍ ለላይፍ መፅሄት እና እና ለ abetokichaw.com ድረ ገጽ ተብላ የተሰናዳች መሆኗንም እናገራለሁ፡፡ ከላይ በተንደረደርኩት መሰረት ስቀጥል እባክዎን ወዳጄ አብረውኝ ይዝለቁ ብዬ በመጋበዝ ነው፡፡
ለአባይ መዋጮ መዋጮ መባል የተጀመረ ሰሞን እኔ እሰራበት የነበረ የትምህርት ተቋም ከመንግስት ከፍተኛ አካላት ከፍተኛ ቁጥጥር ተጥሎበት ነበር፡፡ ቁጥጥሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአግባቡ ግልጋሎት ለህዝቡ እንዲሰጡ ተብሎ የተወሰደ ነበር፡፡ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እና አለቃችን በዚህ ቁጥጥር የተነሳ የእለት እንጀራችንን እንዳይቆጣጠር፣ እንዳይወሳሰብ፣ ብሎም እንዳይቋረጥ ተጨንቀን፡፡ ተጨንቀንም፤ መስሪያ ቤታችንን በማፀዳዳት ስንተጋ በነበረበት ወቅት፤ የአባይ መዋጮ ነገር እየጠነከረ መጣ… እናስ… እናማ አለቃችን መጀመሪያ የስራ ሃላፊዎችን ሰበሰበ ሰብስቦም ሰራተኛው በሙሉ የአንድ ወር ደሞዙን ለአባይ እንዲለቅ የማሳመን ስራ እንዲሰሩ ተማፀነ፡፡
ሃላፊዎቹም ወደ ሰራተኛው ሄደው “ዛሬ የአንድ ወር ደሞዛችንን ባንለቅ ነገ ሁሉንም ደሞዛችንን ስራችንንም ጭምር እንደምንለቅ” አስረዱን እኛም ነገሩ ሲገባን ቃል ገባን፤ “ከነገሩ ጦም ይደሩ” ነውና፤ “ከጠቀመው ይውሰደው” ብለን የአንድ የአንድ ወር ደሞዛችንን እነሆ በረከት አልን፡፡ አቶ በረከትመን አቶ መለስም ፈገግ አሉልን፤ ያኔም መንግስት በመስሪያ ቤታችን ላይ ያሰበውን የጥራት ቁጥጥር ተወልን “እንዳሻሽ ሁኚ” የሚለውን ሙዚቃም ጋበዘን እኛም በደስታ ደነስን….! ጥራት ምናባቱ ጥሪት ነው ዋናው! ለአባይ በሰጠነው ጥሪት የጥራት ቁጥጥሩ ቀረልን እስይ እልልል…. አለልን!
የአባይ መዋጮ ነገር በሁሉም መስሪያ ቤቶች በተለይም በግል ቤቶች እንዲሁ ነበር፡፡ መስሪያ ቤቶች ከመንግስት ጋር አጓጉል ከመሳፈጥ ብለው፤ ለስራ ሃላፊዎች መመሪያ ያስተላልፋሉ፤ የስራ ሃላፊዎች ደግሞ በአለቆቻቸው ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ብለው፤ ሰራተኞቻቸውን እጅህ ከምን ይላሉ፤ ሰራተኞችም ጠቅላላ ደሞዝ ከማጣ የአንድ ወር ደሞዜን ባጣ ይቀለኛል እና ይሁን ብለው ይለግሳሉ፡፡
ይህ በእንዲህ አንዳለ፤
ይቺ አባይ ትልቅ መሸቀያ ሆናለች፡፡ ደግሞ እኮ ሽቀላዋ ይሉኝታ አልባ መሆኗ ነው የሚገርመው፡፡ አንድ ወዳጄ አሁን ላለንበት “ግሎባል ዋርሚንግ” ስጋት ጭስ አልባ መሆን እንጂ ይሉኝታ አልባ መሆን ጠቀሜታ የለውም ብሎኛል፡፡ የኢህአዴግ ባለስልጣናቱ ግን በይሉኝታ አልባ ገንዘብ ስብሰባ ከሀገር ይወጡ እና አጓጉል የሆነ የቅስም ስብራት ሲደርስባቸው በንዴት የሚያወጡት ጭስ “ለግሎባል ዋርሚንጉ” ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን ልብ አላሉትም… ስለዚህ እኛ ልብ እናስብላለን
ሰሞኑን የአባይ ወሬ በከፍተኛ ደረጃ እየተርገበገበ ይገኛል፡፡ በተለይ ኢህአዴግን ወክለው ፌስ ቡኩን የተቀላቀሉ ተበካዮች… (ይቅርታ የፊደል ግድፈት አለ እናርማለን…) በፌስ ቡክ የኢህአዴግ ተወካዮች… ነጋ ጠባ አባይ አባይ እያሉ በጎርፍ ሊያስወስዱን ምንም አልቀራቸው፡፡ እኔ የምለው አንዳንድ ከእኛ የበለጡ የኢህአዴግ ካድሬዎችን ግን ልብ ብላችሁልኝ ከሆነ አባይ ራሱ በአንድ ለ አምስት አደረጃጀት ውስጥ የገባ የኢህአዴግ አባል አድርገው እኮ ነው የሚያዩት፡፡ እውነቱ ግን የታወቀ ነው፤ እንኳንስ ወንዙ እና ሰዉ እራሱ የኢህአዴግ አባል የሚሆነው ለአበሉ ብሎ ነው፡፡ (የዘንድሮ ኑሮ እንደሆነ በአበልም አልተቻለም!) እናም ያለ አበል የኢህአዴግ አባል የሚሆን ከተገኘ አስይዛለሁ… (በቅንፍም የማስይዘው ለፖሊስ ነው ብዬ ማብራሪያ እሰጣለሁ!) የምር ግን አንድ እኔ ነኝ ከአገር ተባርሬ እንኳ ኢህአዴግዬ እያልኩ የማቆላምጣት… እና አንድ እርሳቸው ነበሩ… እንጂ ሌሎቹ በሙሉ ለአበላቸው ሲሉ ነው…! ይቺ አስተያየት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝን እንኳ ሳይቀር ትመለከታለች፡፡ ድሮ የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት… ይባል አንደነበረው የአሁኑን የኢህአዴግ ሰራዊት ግን የሚወልደው የኑሮ ውድነቱ ነው፡፡ አባል ካልሆኑ መብል የለማ!
ታድያ አባይ ለየትኛው አበሉ ብሎ ነው በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ውስጥ የሚገባው…! የትኛው የኑሮ ውድነት አላስቆም አላስቀምጥ ብሎት “ከመሞት መሰንበት” ብሎ በአባልነት ይጠመቃል፡፡ በእውኑ ራሱ ጠማቂ ሆኖ ሳለ ይጠመቅ ዘንድስ እንዴት ይሆንለታል…!
ለማንኛውም አባይ ኢህአዴግ አይደለም፡፡ አባይ አንድነትም አይደለም፡፡ አባይ ኦነግም አይደለም አባይ ግንቦት ሰባትም አይደለም፡፡ አባይ ኢትዮጵያ ነው፡፡ አባይ ወንዝ ብቻም ሳይሆን ሀገር ነው፡፡ አባይ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀብት እና ጸጋ ነው፡፡
በቅርቡ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከአውሮፓ ሀገራት ዩሮ ከምድረ አሜሪካ ደግሞ ዶላራቸውን ከአረብ ሀገራትም ድርሃማቸውን አፈስፈስ! አድርገው ለመውሰድ ትልልቅ ቦርሳ ይዘው ሄደውም አልነበር…? ሲመለሱ ግን ትልቁ ቦርሳቸው ብቻ ሳይሆን አነርሱም ሽምቅቅ ብለው ተጣጥፈው እና አንሰው ነበር፡፡ “እኔን ያሳንሰኝ” አይባልም መቼም ከዚህ በላይ የት ልነስ…!
ለዚህ ዋነኛ ሰበቡ ውጪ ሀገር በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያጋጠማቸው ተቃውሞ ነው፡፡ ባለስልጣናቱ ኢትዮጵያ እንደተለመደው፤ “ታመጫለሽ አምጪ አለበለዛ ቤቱን ለቀሽ ውጪ” ማለት የሚሳካ መስሏቸው ቢሄዱም ኢትዮጵይውኑ “አንሰማችሁም” አሏቸው! እውነትም አላቸው፤ እነርሱ ስንት ጊዜ “ድምፃችን ይሰማ” ቢሉ እሺ ብሎ አንድም ቀን ያልሰማቸው መንግስት ገንዘብ አምጡ ሲላቸው እንዴት ሊሰሙት ይችላሉ…!
በውጪ ሀገር ያሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለይም ሀገር ቤት ከመንግስት መሬት ወስደው ቤት መስራት ያልጀመሩቱ… ከአባይ በፊት በርካታ መገደብ ያለባቸው ነገሮች አንዳሉ ጮክ ብለው እየተናገሩ ነው፡፡ ያ ማለት ግን አባይን መቃወም ማለት አይደለም፡፡ አባይ ይገደብ የሰብአዊ መብጥ ጥሰትም ይገደብ፡፡ አባይ ይገደብ እስርም ይገደብ፡፡ አባይ ይገደብ ስልጣንም ይገደብ፡፡ አባይ ይገደብ የእምነት ጣልቃ ገብነትም ይገደብ፡፡ አባይ የግደብ የፕሬስ አፈናውም ይገደብ፡፡ ያኔ የምናመነጨው ሃይል ለጎረቤት ሀገር ብቻ ሳይሆን ለመላው አለም ይበቃል… ስለዚህ ስሙን… ነው የሚሉት፡፡
ይህንን በቅጡ ያልሰሙ የኢህአዴግ የስጋ ዘመዶች ግን በአባይ ላይ ትንፍሽ የሚለውን ሁሉ የኢትዮጵያ ጠላት ማድረጋቸው ሳያንስ ራሱ አባይን በአንድ ለአምስት አደረጃጀት የታቀፈ የኢህአዴግ አባል አድርገውት ቁጭ አሉ! ይሄንን አባይ ቢሰማ ከአጠገቡ የበቀለች ዛፍ ላይ ይሰቀል ነበር፡፡
ከዚች ጋ የምትመሳሰል አንዲት ጨዋታ እነሆ እንደማሳረጊያ ትሁን!
ሰውዬው ሀገር ያስቸገረ ዘራፊ ነበር፡፡ ታድያ የሆነ ጊዜ በቁጥጥር ስር ይውል እና ስቅላት ሊከናወንበት ህዝብ የተሰበሰበበት አደባባይ በአንገቱ ሸምቀቆ ገብቶ ሳለ፤ ንጉሱ አንድ ዕድል ሰጡት “እስቲ እዚህ ከተሰበሰባችሁት ውስጥ እኔ ይሄንን ሰው ባል አድርጌ መክሬ ገስጬ እመልሰዋለሁ፤ የምትል ሴት ካለች ትምጣ” አሉ፡፡ ይሄን ጊዜ አንዲት በሀገሩ የታወቀች እና በዘርፈ ብዙ ችግቿ የምትተች ቢመክሯትም አልሰማ ያለች (ስናጠጋጋም እንደ ኢህአዴግ ያለች ሴትዮ እንበላት) በጥቅሉ በክፉ አመሏ የተነሳ ባል አጥታ ቁማ የቀረች ሴት፤ “እኔ አድነዋለሁ… እኔ መክረዋለሁ…” ብላ ወደ ንጉሱ ዘንድ ቀረበች፡፡ ወንጀለኛውም ወደ ሴትዮዋ ዘወር ብሎ ቢያይ ያውቃታል… አትሆነውም፡፡ አንገቱ ከገመድ ውስጥ ነው… በልቡም የእርሷ ባል ከመባልስ… አለና በአንደበቱ ደግሞ “አጥብቀው…!” አለ!
እና ወዳጄ ኢህአዴግዬ ያለውን ይበለኝ እንጂ ይህን ግን እነግርዎታለሁ፤
አባይ የማንም ባል የማንም አባልም አይደለም፡፡ እርሱ የኢትዮጵያ አብራክ ክፋይ ነው! የማይሆን ጋብቻ ከሚፈፅም…. “አጥብቀው” ብሎ ጥልጥል ቢል ይመርጣል፡፡ አባይ የኢትዮጵያ ነው፡፡ የኢትዮጵያውንን ድምፅ የማሰማ አባይን ሊደፍርም፣ ሊወሽምም፣ ሊያገባም፣ ሊያግባባም ይከብደዋል፡፡
ስናበቃም እንላለን…
ከባዱን ነገር እንደማመጥ እና እናቅልለው!
ወዳጄ ይበሉ ይቺን ታኸል ካወጋን የጤና ያድርግልን፤ ይበሉ ያሰናብቱኝ!
አማን ያሰንበተን!

Sunday, May 5, 2013

የወያኔ ልማት ሰዋዊ ሽታ የለውም

Official Site for Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracyየወያኔ ልማት ሰዋዊ ሽታ የለውም
ሀገራችንን አንቆ የሚገዛው ወያኔ ራሱን የልማት መንግስት ነኝ በሚል ራሱን በሚጠፋ ስእል ላይ አስቀምጦል። በየአመቱ የተጋነነ እና የሌለ ነጠላ የስታቲስቲክ ዜማ እየለቀቀ ያቀርባል። በዴሞክራሲያዊ መንገድ ህጋዊ መሰረት ማግኘት ስለተሳነው በልማታዊ መዝገብ ስም ለመገኘት አይን የአወጣ ሙከራ ያደርጋል።
 
የወያኔ ልማት ሰዋዊ ሽታ የለውም። ለዘረኛው መንግስት ልማት ማለት ብልጭልጫዊ ነገር ማሳየት እንጂ የሰውን፣ የህዝቡን ጉስቁል ኑሮ መቀየር ማሻሻል መሆኑን አያውቅም። አንድ ሺ አፈናቅሎ አንድ የስርአቱን አገልጋይ ቱጃር ያከብርና አገር ለማ ይለናል። የጋምቤላን አኙዋኮች ከአያት ቅድመ አያት መሬት አፈናቅሎ በርሃብ እየቆላ፣ የአረብና ህንድ የሩዝ ሁዳድ ስላደረገው ብቻ አገር ለማ ከበሮ ደልቁ ይለናል።
 
ወያኔ ልማት ለሰው መሆኑን ወይ አያውቀውም አሊያም ረስቶታል። በአዲስ አበባና በብዙ አካባቢዎች መንደርን እያፈረሰ የሚበትናቸው ዜጎች፤ ከእነሱ ጋር እድራቸው፣ ሰንበቴያቸው፣ ማህበራቸው፣ ማህበራዊ ህይወታቸው አብሮ እንደሚፈርስ ቢያውቅም ግድ የለውም። የወያኔ ልማት ሰውን ወደተራ እንስሳነት የሚያወርድ የወሮበላ ስራ ነው።
ህወሃት እንደ መንግስት ሱፍ ለብሶ፣ በሌላ በኩል እንደ ኢፈርት ባለቤትነቱ ወዛደር መስሎ ውል ይፈራረማል። ኢፈርት የሚገጣጥመውን መኪና ለመከላከያ ሚኒስተር ይሸጣል፤ እንደ መንግስት በህዝብ ስም እርዳታ ይቀበላል፣ እንደ ወሮበላ ዘራፊ ስማቸውን ቀይረው ወዲያውኑ ዘረፋውን ይጀምራል። ይህን የመሰለ የዘቀጠ ውንብድና በህዝብ ንብረት ላይ እየሰሩ ሌሎችን የወያኔ ግልገሎች ደግሞ ሌቦች፣ ኪራይ ሰብሳቢዎች እያሉ ሲሳደቡ አይናቸውን አያሹም።
 
የወያኔ አለቆች ድሃ ገበሬዎችን ከመኖሪያቸው ሲያፈናቅሉ ደን ስለጨፈጨፉ ነው የሚል የፈጠራ ክስ ይፈጥሩና የኤፈርት ኩባንያዎች ኢሉ አባቦር ውስጥ የያዩን ደን እየጨፈጨፉና እያጋዩ የሚሰሩትን የዝርፊያ ማእድን ቁፈራ ልማት ነው ይሉናል።
ወያኔ በሚገዛት ኢትዮጵያ ባለሀብት መሆንና ሀገር አልምቶ ራስን መጥቀም ገደብና መስመር አለው። ብዙ ኢንቨስተሮች የወያኔ ባለስልጣንን በአጋርነት፣ በሸሪክነት እንዲያስገቡ ይገደዳሉ። አሊያም ሀብቱን ላለመነጠቅ የፈለገ ሀብታም ልሁን ባይ የዳጎሰ ገንዘብ ለባለስልጣናቱ እጅ መንሻ ለኪስ ተጠይቀው ይሰጣሉ። በአንጻሩ የወያኔን የሀብታምነትን ቀይ መስመር ዘለው እምቢ ያሉ እስር ቤት የተጣሉ፣ የተሰደዱ በተለይ ወያኔ ከሚጠላው የጎሳ ወገን የሆኑ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ፣ የልማት ተስፈኞቹ በቃሊቲና በዝዋይ እስር ቤቶች ተጨናንቀዋል።
 
ዛሬ ዛሬ ጤፍ ጠፋ ተወደደ፣ ስኳር ጠፋ ምን እንሁን፣ መብራትና ውሃ ጠፋ ፈረቃው በዛብን ሲባሉ፤ መልሳቸው አስገራሚ እና አሳዛኝ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የጠፋው፣ የምትራቡት አገሪቱ እያደገች ስለሆነ ነው የሚል የማላገጥ መልስ ይሰጣሉ። የሚሉት እድገት ቁልቁል እንደካሮት እየጨመረ ያለውን ድህነት መሆኑን ማለታቸው ነው።
 
በኢትዮጵያ የነገሰው ደህነት፣ ከድህነቱ ጋር የተያያዘው መጠነ ሰፊ ተስፋ መቁረጥና ስደት ለወያኔ ምኑም አይደለም። ምናልባትም የአገሪቱን እድገት ያመጣው ነገር ነው በሚል መላምት የሆነ፣ የይሆናል ግምታቸውን ይሰጡናል።
 
የአደገችና የበለጸገችን ኢትዮጵያ ከመፍጠር ይልቅ በልማት ስም የግል ምቾታቸውንና ድሎቶቻቸውን ለማስጠበቅ፣ ብሎም የስልጣን ጊዚያቸውን ለማራዘም ሲሉ፤ ህዝብን ከቀዪው በማፈናቀል ለርሃብና ለስቃይ ለስደት እየዳረጉት ይገኛሉ።
 
ህወሃቶች የሀብት ክፍፍል በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በሚል የአካባቢውን ነዋሪ በማንነቱ ምክንያት አፈናቅለው የህወሃት አባላትንና ደጋፊዎችን የመጥቀም ስትራቴጂዎችን ቀርጸው ሰፊውን የህዝብ ጉልበት እንደ መዥገር መጠው፣ በቀዪው ያፈራውን ንብረትና ገንዘብ እንኳ ሳይሰበስብ ያፈናቅሉታል። ታዲያ የትኛው የልማት ስትራቴጂ ይሆን ህዝብን ማእከል ያደረገው?
የተማሩ ዜጎች በተማሩበት ሙያ ሰርተው በልማቱ ሂደት ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንዳይጠቅሙ አድረገው ራእያቸው በማጨለም በጨፍን የስርአቱ ባሪያ አገልጋይ አሊያም አጨብጫቢ እንዲሆኑ ሆነው ይቀረጻሉ፤ አሊያ ግን መጽዋት ጠባቂ ወይም ከሀገር እንዲሰደዱ ይደረጋሉ።
 
የወያኔ ልማት ህዝብ ህዝብም፣ ሰው ሰውም አይሸትም! ስለዚህም በአገር አልሚነት ስም ማንንም ማታለል አይችልም። ይህ የዝርፊያና የፈንጋይ የወያኔ ኢኮኖሚ ከራሳቸውና ከጉጅሌዎች ባለፈ ውጭ የሚጠቅመው ኢትዮጵያዊ አይኖርም።
 
ኢትዮጵያ ለሁሉም ልጆቿ የሚሆን የተፈጥሮ ጸጋ አላት። ምቹ የአየር ንብረት፣ ለም አፍርና በተስተካከለ መልከዓ ምድር የተቸረች ሀገር ነች። ልጆቿ ሁሉ የዚህ ጸጋ ባለቤት እንዳይሆኑ እና ዜጎቿ በእኩልነት ተጠቃሚ ሳይሆኑ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሆነው እንዲሰደዱ እያደረገ ያለው ወያኔ ነው። ወያኔ አልሚ ሳይሆን የልማት ፀርና የአንድነት ቀበኛ ነው።
 
በኢትዮጵያ ልማትም፣ እድገትም፣ እኩልነትም፣ ሰብአዊ ክብርም፣ ተስፋም፣ በሀገር መኩራትም እንዲኖር ወያኔ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መወገድ አለበት። ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለነዚህና ለእውነተኛ የሰበአዊ መብት መከበር፣ ሁሉም ዜጎች በሀገራቸው የትኛውም ቦታ በእኩልነት ሰርቶ የማደግ መሰረታዊ መብቶች፤ ህዝብን ማእከል ላደረገ እውነተኛ ልማት እና ሀገራችንን ከመፈራረስ አደጋ ለመታደግ ረጅሙን የትግል ጉዞ በአንድ ርምጃ ጀምሮአል፡፡ እርሰዎስ? ኑ! ተቀላቀሉን፡፡ ድህነት፣ ውርደት፣ ስደት እስከመቼ?
 
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Wednesday, May 1, 2013

ዜና ብስጭት፤ አቡነ ጴጥሮስን ጨክነው ሀሙስ ሊያነሷቸው ነው፡፡


922915_10151533427118930_1195238247_n
ለአመታት የፒያሳ ግርማ ሆነው የቆዩትእምቢ ባዩ አርበኛው አቡን ከነገ በስተያ ሀሙስ “ለቀላል ባቡር መንገድ ዝርጋታ” ተብሎ ሊነሱ መሆኑን ሸገር ራዲዮ ጣቢያ ነገረን፡፡

ቀጥሎ የኔ ብስጭታዊ ወሬ ይቀጥላል፤

…አንድ የተለከፈ መንገድ ቀያሽ ካላጣው ቦታ ለቅኝ ገዢዎች አልንበረከክም ብለው መስዋት የሆኑትን  አባትን ሀውልት “ካላፈረስኩ ባቡር መንገድ መዘርጋት አልችልም” ብሎ በቀየሰው መሰረት የአቡኑ ሀውልት መፍረስ እርግጥ ሆኗል፡፡

በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ “አቡን” ሆነው በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ “ለተሰዉት” “አቡነ” መለስ ሀውልት እየተገነባ ባለበት በዚህ ወቅት፣  የእውነተኛው ሰማህት እና የእውነተኛው አቡን ሀውልት ይፍረስ መባሉ ብዙዎችን ሲያበሳጭ ሰንብቷል፡፡

አፍራሽ ግብረ ሀይሉ ሀውልቱ ከፈረሰ በኋላ በቦታው ተመልሶ ይተከላል ቢልም ንግግሩን በጥርጣሬ የሚያዩት ብዙዎች ናቸው ከብዙዎቹ ውስጥ አንዱም እኔ ነኝ!

ነገሮች ግድ በሚሏቸው ሀገራት መንገድ በሚቀየስ ጊዜ ታሪካዊ ሀውልቶችን ይቅርና የዕድሜ ባለፀጋ ዛፎችን እንኳ ላለመጉዳት ጥረት ሲደረግ አይተን አቡነ ጴጥሮስን ካላፈረስኩ መንገድ አልሰራም የሚለው መሀንዲስ በተለይ ጣሊያናዊ ካልሆነ፤  ከአቡኑ ጋር ምን እንዳቀያየመው ወደፊት የሚጣራ ይሆናል፡፡

እኔ ደግሞ ረስተውት መስሎኝ ነበርኮ… ለካስ ሰዎቻችን መገንባት እንጂ ማፍፍረስ አይረሱምና!

ለማስታወስ ያህል፤

ባለፈው ወቅት በጣሊያን የግራዚያኔን ሀውልት መሰራት ተቃወሙ  ሰልፍ ያደረጉ ኢትዮጵያውን በገዛ መንግስታቸው ምን ሲደረግ ግራዚያኔን  ተቃወማችሁ… ተብለው ታስረው ነበር፡፡ ይሄንን አስታውሰን የአቡኑን መፍረስ አይተን ብስጭት ይነሰን….!?