Thursday, June 6, 2013

“ይህ መንግሥት አይመጥነንም”የ“ምርቃና” መግለጫ ለኢህአዴግ ድንጋጤ


shemelis2-
ሰሞኑን ኢትዮጵያ የዓለም መገናኛ አጀንዳ ሆናለች። ለዘመናት እጇን ኢትዮጵያ ላይ ተክላ የኖረችው ግብጽ የምትዝተው ዛቻና፣ በቅርቡ ተቋቁሞ ታላቅ ታሪክ በማስመዝገቡ የተረጋገጠለት ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ አጀንዳዎቹ ናቸው።
በወጣት አመራሮች የተገነባውና በርካታ ሴት አባላት እንዳሉት የሚነገርለት ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በዋናነት የተገኘው ድል የፍርሃት ደመና መገፈፉ ነው። አቶ መለስ ባስተላለፉት ትዕዛዝ በ1997 ዓ.ም ዜጎች አልመው በሚተኩሱ የአጋዚና ታማኝ የህወሃት አባሎች ደረትና አናታቸው እየተወጋ እንዲገደሉ ከተደረገ በኋላ የተቃውሞ ሰልፍ የማይታሰብ ሆኖ ላላፉት ስምንት ዓመታት ቆይቶ ነበር።
ከዳር እስከዳር ድምጽ አልባ ሆኖ የተሸነፈው ኢህአዴግ በጠመንጃ ፣ በወቅቱ የነበሩት የቅንጅት አመራሮች ታሪካዊና ሊረሳ የማይችል ስህተት ተዳምረው የህዝቡን ቅስም የሰበረው የ1997 ዓ ም ምርጫ ጣጣውና ቆፈኑ እንዲሁ በቀላሉ የሚለቅ እንዳልሆነ በወቅቱ አስተያየት ተሰጥቶ ነበር።
“ሁለት አስርት ዓመታት ወደኋላ ተመልሰናል” ተብሎ የተዘጋውን በር የበረገደው ሰማያዊ ፓርቲ ከህዝብ ባገኘው ድጋፍ አዲስ አበባን የተቃውሞ ጎርፍ አጎረፈባት። ሰላማዊ ሰልፉ ሰላማዊና የተሳካ እንደነበር ኢህአዴግ ራሱ ተናገረ። ህዝብ ተቃውሞውን ገልጾ የሶስት ወር ጊዜ ከሰጠ በኋላ ወደ ቤቱ ተመለሰ።
አዲስ አበባ አንድ ለአምስት፣ የጎንዮሽ፣ የሽቅብ፣ የህቡዕ፣ የገሃድ፣ የዘር፤ የታማኞች፣ የበጣም ታማኞች፣ የልማት፣ የአነስተኛ ስራ ፈጠራ፣ የጾታ፣ የዘር፣ የእድሜ፣ የተፈጥሮ ሁኔታ፣ የጥቅም ወዘተ የፈጠረው አደረጃጀት አፈር ድሜ መብላቱ ያስጨነቀው ኢህአዴግ ሰልፉ ተበትኖ ሲያበቃ ላንቃውን አላቀቀ።
እንደ ገበጣ ጠጠር በፈለገበት ጉድጓድ የሚወረውራቸውን ቅምጥ አሽከሮች ለመግለጫ አሰማራ። ለስምንት ዓመታት ታፍኖ የኖረ ህዝብ መቦረቁ አስደነገጠውና ከፊልም ክምችት ህግ መዝዞ ለመክሰስ ያመች ዘንድ ህጸጽ እንዲነቀስ አዘዘ። አቶ ሽመልስ ከፈረሹበት ፍራሽ ተነስተው በምርቃና የአፋቸውን ለሃጭ እንኳን በወጉ መቆጣጠር እያቃታቸው በሉ የተባሉትን ተፉ። አቶ ሬድዋንም ሰው በሌለበት የ2002 ምርጫ በስድብ አቶ መለስን በማስደሰታቸው ባገኙት ሃላፊነት ለጌቶቻቸው ምላስ ሆነው ህዝብ አወገዙ። እሳቸውም ተፉ።
አይ ጋዜጠኛነት – “አትነሳም ወይ”   
አንድ ህዝብ ለተቃውሞ ሲወጣ ሊያወግዝ፣ ሊዘልፍ፣ የፈለገውን ጉዳይ በማንሳት ሊራገም፣ ለተነሳበት ጉዳይ “ተነሱ” ብሎ በፍርሃትና ሚና ባለመለየት የተቀመጡትን ለመቀስቀስ፣ ለማበረታታት ነው። ከድሮ ጀምሮ አገርና ህዝብ እንዲተባበሩ ሲፈለግ፣ መሪዎች ሲገዝቱ በሠንደቅዓላማና የሁሉም ማተብ የሆነችውን አገር ስም በመጥራት ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ነው። ኢህአዴግም ቢሆን በጨነቀው ጊዜ ባወገዘውና በሚጠላው ሠንደቅ ሲነግድበት ታይቷል። አቶ መለስ “ጨርቅ” ብለው ባዋረዱት “ባንዲራ” እንዲገነዙ የፈቀደ ፓርቲም ነው። ታዲያ ከጥንት ጀምሮ ሰንደቅ ዓላማውን “ማተቤ” እያለ የሚጠራ ህዝብ የሰንደቁን flagስም እየጠራ “አትነሳም ወይ” በማለት ማዜሙ እንዴት ይበዛበታል? ደግሞስ ኢህአዴግና በዙሪያው የሰበሰባቸው አሽከር ባለስልጣኖቹ ስለ ሰንደቅ ክብር የመቆርቆር ሞራሉስ አላቸው?
ኢህአዴግን “ውሸትህ ሰለቸን” እያሉ ሲረግሙት ከነበሩት በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ሰዎች መካከል “ለምን አዲሱን ሰንደቅ ዓላማ ያዝክ” በሚል የሚጨቃጨቁ አስር የማይሞሉ ሰዎች በካሜራ አድኖ ሰልፉን “ህገ ወጥ” ለማስመሰል የዳዳው ጋዜጠኛ ሙያውንም ሆነ ራሱን ስለማርከሱ ጉልህ ማሳያ የሚነሳው እዚህ ላይ ነው።
ስለ ሰንደቅዓላማ ይነሳ ከተባለ ዜናው “በሰልፉ ላይ ባንዲራ ለምን አልወጣም? ሰንደቀዓላማውን የነፍሱ ያህል የሚያመልክ ህዝብ እንዴት አስቻለው? ሰንደቅዓላማ የተሸሸገበትስ ምክንያት ምንድን ነው?” የሚለውና ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ነበሩ።
በባድመ ጦርነት ወቅት በዳግም ጥሪ አገሩን ሊታደግ የመከላከያ ሰራዊትን የተቀላቀለው /የደርግ ሠራዊት ሲባል የነበረውን/ ወገን ኩርፊያ ለማስታገስ “የቀድሞውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ” በባላደራነት በመስጠት ኢህአዴግ የሰውን ልጅ ለማይጠቅም ጦርነት መማገዱን ለሚያወቁ ዜጎች ኢህአዴግ ስለ ሰንደቅ የመቆርቆር መብት እንደሌለው ይረዳሉ። እንዲህ ያለው “ድርጅታዊ ክህደትና ዓላማ ያለው አታላይነት” ዝም ተብሎ አስር ሰዎች ተሟገቱ ብሎ የክስ ማመቻቺያ ሪፖርት ማዘጋጀት ጋዜጠኛ አያስብልም። ሰዎቹ እነማን ናቸው? አንድ ባንዲራ ብቻ እንዴት ሊታይ ቻለ? ማን አመጣው? እንዴት መጣ? ብዙ መጠየቅ የሚቻልበት ጉዳይ ሆኖ ሳለ መታለፉ አስገራሚ ይሆናል። ለነገሩ ሰልፉን አስመልክቶ አቋም ይዞ የጻፈ የአገር ውስጥ ሚዲያም አላጋጠመኝም። ለለቅሶ ግጥምና ሙሾ የደረደሩ ጋዜጠኞች ለህዝባዊ ተቃውሞ የሰጡት ሽፋን ደረጃው ዝቅ ቢልም ከመወረፍ አያድናቸውም።
አትነሳም ወይ በሚል መፈክር ማውረድና የታሰሩ እስረኞች እንዲፈቱ መጠየቅ ህግን መተላለፍና የፍርድ ሂደት ላይ ተጽዕኖ መፍጠር እንደሆነ የሚዘግብ ዘጋቢ የሙያው ባለቤቶች ነን ለሚሉ ሁሉ አንገት የሚያስደፋ ነው። አቶ መለስ እንደ ቴአትር ቤት ድራማ ይጫወቱበት በነበረው ፓርላማ ፊት፣ በቀጥታ ስርጭት በሚተላለፍ ዝግጅት፣ በፖለቲካ እስረኞችና ተከሳሾች ላይ አስቀድመው ውሳኔ ሲሰጡና ብይን ያሰሙ በነበረበት አገር “እስረኞች ይፈቱ” ብሎ መጠየቅ ወንጀል ሆኖ “ህግ ተጥሷል” ሲያስብል መስማት ሞቶ መበስበስ ሲታሰብ የሚዘገንነውን ያህል ይቀፋል። ለዚያውም በአቶ ሽመልስ ከማል አንደበት ሲነገር።
“የስካር መግለጫ”
የአቶ በረከት ተላላኪ የሚባሉትና ለታይታ የሚኒስትር ታፔላ የተለጠፈባቸው አቶ ሽመልስ ሰልፉን አስመልክቶ መግለጫ ሲሰጡ ከንግራቸው በላይ መነጋገሪያ የሆነው በወቅቱ የነበሩበት የሙቀት ስሜት ነበር። አፋቸው ዳርና ዳር አረፋ ይደፍቃቸው ነበር። ሲያመነዥጉ የዋሉትን የጫት መጠንና አይነት መዘርዘር ቢከብድም ከፍራሽ ላይ ተጠርተው የችኮላ መግለጫ እንደሰጡ መደረጉን መሸሸግ አይቻልም። እዚህ ላይ “ምን አገባህ?” የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችል ይሆናል። ምን አልባትም የግል ጉዳይ እንደሆነ ተደርጎ ሊታይ ይችላል። እኔ እስከማወቀው ግን ሰክሮ የተከበረ ህዝብ ፊት መቅረብ፣ መናገር እስኪያቅት ድረስ አይን እያጉረጠረጡ ለህዝብ ማውራት አግባብ አይደለም። አንድ ኪሎ ጫት ከ100 ብር በላይ በሚሸጥበት ሁኔታ ቀን በቀን ጫት ማመንዠክ ከመንግሥት ሠራተኛ (ባለሥልጣንም ጭምር) ወርሃዊ ደመወዝ ጋር የሚመጣጠን ባለመሆኑ ለስርቆትና ሙስና ስለሚዳርግ የሚወገዝ ነው።
shemelisአንድ ክስተት ትዝ አለኝ፡፡ የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ቦሪስ ዪልሲን በአልኮሆል አፍቃሪነታቸው ብዙ የተባለባቸው ነበሩ፡፡ እርሳቸው ከሥልጣን ለቅቀው በስፖርተኛነታቸው የሚታወቁትና በጁዶ የጥቁር ቀበቶ ተሸላሚው ቭላዲሚር ፑቲን ሥልጣን ከያዙ ጥቂት ዓመታት በኋላ ግመገማዊ ጥናት ተደረገ፡፡ በውጤቱም በዘመነ ዪልሲን እጅግ አሻቅቦ የነበረው የሰካራም ቁጥር ፑቲን ሥልጣን ከያዙ በኋላ መቀነሱ ይፋ ሆነ፡፡ ኢትዮጵያስ ድሮና ዘንድሮ…?
ወደጉዳዬ ስመለስ እንግዲህ እኚህ ሰው (ሽመልስ) ናቸው “ህገወጥ” በማለት የህዝብን ቁጣ የፈረጁት። የሚላላኩለት ኢህአዴግ ህግ አክባሪ ሆነና ይህ የታፈነ ህዝብ ህገ ወጥ ተብሎ ተፈረጀ። ኢህአዴግና ፍርድ ቤት የተለያዩ አካላት ተደርገው ታዩና “የፍርድ ሂደት ላይ ጫና ለመፍጠር የተደረገ ሙከራ፣ ቀናውን የፍርድ ሂደት ለመበረዝ …” የተቃጣ ሰልፍ ሆኖ ቀረበ። ዳሩ ኢህአዴግ የሚሰበስባቸውን ሰዎች ለሚያውቁ፣ አቶ ሽመልስን በቅርብ ለሚያውቃቸው ጉዳዩ አይገርምም። ስርዓቱ የቆመው እንዲህ ባሉ ሰዎች መሆኑ ግን ያሳዝናል። አሁን ከሶስት ወር በኋላ በሚካሄደው ሰልፍ “የባለሥልጣኖች የጫትና የሺሻ ኮታ ይፋ እንዲሆን እንጠይቃለን” የሚል ጥያቄ ቢቀርብ ማን ቀርቦ “ሰልፉ ህግ መንግስቱን የሚጻረር፣ ጸረ ሰላም ሰልፍ ነው” ይል ይሆን?
“ይህ መንግስት አይመጥነንም”
selfለዚህ ጽሁፍ መነሻዬ ይህ ሃሳብ ነው። መንግስት ህዝብን ካልመጠነ ችግር ነው። የደህንነትና ፖሊስ ሃይል ህዝብን ከሚሰልል ይልቅ ከህዝብ ጋር ሆኖ አገርን በጋራ ሊጠብቅ እንደሚገባ የሚጠይቁ አገር ወዳዶች “የሚመጥናቸው መንግስት” አለማግኘታቸው አሳሳቢ ነው። 22 ዓመት ሙሉ ጥላቻ ቢሰበክም እርስ በርሱ ሳይጫረስ እዚህ ደረጃ መድረሱ የሚያናድዳቸው የኢህአዴግ አውራ መሪዎች “ዛሬም ድረስ አልረኩም” የሚሉ ሰልፉ ላይ ነበሩ። እነዚህ ሰዎች ሲሉ የነበሩት ጉዳይ ከመድረክ ተነሳ። “ይህ መንግስት አይመጥነንም” ሲባል ተጮኸ። ድጋፍ ተሰጠ። በማይመጥናቸው አገዛዝ መተዳደር የማይፈልጉ የፍርሃት ቀንበራቸውን ሰበሩ። ሰማያዊ ፓርቲ ይህን ገድል በልጅነቱ ሰራ።
ሰማያዊ ፓርቲ ሰዎች በሚጥናቸው ፓርቲ መተዳደር እስኪችሉ ድረስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት እንደሚከፍሉ ተናገረ። አሁንም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች አስተጋቡ “አዎ” አሉ። ይህ እውነት ነው። የማይመጥን አገዛዝ የሚወከለው አገዛዙ በሚሰበስባቸው ተላላኪዎቹ ነው። በማይመጥነው አገዛዝ መመራት ያንገሸገሸው ህዝብ ተቃውሞውን ገልጾ ሲገባ “ህገ ወጥ ነህ” የሚሉት አስቀድሞ በካርዱ፣ ከስምንት ዓመት በኋላ በድምጹ፣ በየጊዜው በተለያየ መልኩ የሚያወግዛቸው “ገለባ” ባለጊዜዎች ነው። አስቀድሞ አትመጥኑንም የተባሉ፣ ቢናገሩ ማን ያደምጣል? የተሻሉ የሚባሉ ባለስልጣናት ቢኖሩም ዝምታን እስከመረጡ ድረስ ለህዝብ የሚሰጡት ዋጋ የለምና አብረው ከመደመር አይድኑም።
“አለ ገና” – ተባለ!
ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጀው ሰማያዊ ፓርቲ እንዳስታወቀው ላቀረባቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች መልስ ካልተሰጠው ከሶስት ወር በኋላ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል። ሌሎች ፓርቲዎችም የሰማያዊ ፓርቲን ፈለግ ተከትለው በየክልሉና በሚታወቁ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ ለማዘጋጀት ዝግጅት ላይ እንደሆኑ አስታውቀዋል። በኦሮሚያ የኦህዴድ መፋዘዝን ተከትሎ የከረረ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ ይጠበቃል። እንደ ጠላት እየታየ የሚፈናቀለው የአማራ ክልል ተቃውሞ ማካሄድ ከጀመረ ከወረዳ ወረዳ የሚዘል እንደሚሆን ይታሰባል። በደቡብ ሲዳማ የተቃውሞ ሰልፍ ከጀመረ ከርሟል። በቅርቡ በተካሄደው የማሟያ ምርጫ ወቅት አምጾ ነበር። አሁንም በቋፍ ላይ ነው።

የተቀመጠበት መቀመጫ እንደ ምጣድ የጋለበት ኢህአዴግ አስቀድሞ ወደ ማስፈራራት የሮጠው አቶ መለስ  “በ97 የተፈጸመው ዓይነት ጥፋት ሁለተኛ አይታሰብም” በማለት የተናገሩትና ያስተላለፉት ትዕዛዝ “ኦርኔል” ስለታወሰው ነው “አለ ገና” መባሉ እንቅልፍ ስለነሳው ነው። ተቃውሞው ወደ ክልሎች ይዛወራል መባሉ ቅዠት ውስጥ ስለከተተው ነው። ሁሉም ወደ ፊት የሚታዩ ቢሆኑም ሰላማዊ ሰልፍ መፈቀዱ የሚመሰገን ነው። ተሰለፉ፣ ተቃወሙ ብሎ ፈቅዶ ለምን ጎነተላችሁኝ ብሎ ለክስና ለእስር መሯሯጥ ደግሞ ግለቱን የሚጨምር በመሆኑ ቢቀር የሚል የሚለውን ምክር እንደዜጋ ለመሰንዘር እወዳለሁ። ከሰሜን አፍሪካ ወደተነሳው የውሃ ፖለቲካ አውድማ ተምዘግዝገን ገብተናልና ቢያንስ ብሔራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር ወደሚያስችለን መንገድ ብናመራ ይበጃል። የአሁኑ ሰልፍና ተቃውሞ ጅምር ነው። ኢህአዴግ ከሰማ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው። ብሔራዊ መግባባት በመፍጠር አንድ የውስጥ ጉዳያችንን እንዝጋ:: ህዝብ ወሳኝ አካል እንዲሆን የፈሰሰውን ደም እናስብ። በፍርሃቻና በስካር መግለጫ በማስፈራራት ህብረት መፍጠር አይቻልምና። (የጎልጉል ሪፖርተር ካለበት የዘገበው)

Wednesday, June 5, 2013

Ethiopia to lease 42 percent of Gambella, the size of Netherlands East Africans told to resettle: Are these ‘land grabs’ or progress?


East Africans told to resettle: Are these ‘land grabs’ or progress?

In Ethiopia, a plan known as ‘villagization’ has freed up vast tracts for foreign corporations and brought a storm over methods of development at the World Bank.
A 15-hour drive west from Ethiopia’s capital past coffee forests and jigsaw fields brimming with cattle and people, the road leaves the high country and enters the Gambella region — an expanse of flatter bush and forest with rich grasslands and rivers.
The land is sparsely populated; locals are taller and darker than their upcountry compatriots. Most are of Nuer or Anuak ethnicity. The Nuer, whose statuesque men display parallel horizontal markings on their foreheads, herd cattle and grow maize in the water-blessed expanses.
Gambella, long ignored if not invisible, has recently become a battleground over development, modernization, and human rights – one creating a furor inside the World Bank, which approved programs worth $920 million in Ethiopia last year.
People use a new water pump in the village of Tegni in Gambella, Ethiopia.
People use a new water pump in the village of Tegni in Gambella, Ethiopia. The government cites Tegni as a successful example of its controversial resettlement scheme. PHOTO: William Davison
Ethiopia’s effort to resettle local farmers into main villages while also leasing land to foreign corporations or wealthy Ethiopians has put Gambella under scrutiny for charges of violent forced relocations.
Now the issue is coming to a head: Ethiopian authorities since 2010 have embarked on a plan known as “villagization” to move some 45,000 households. The plan takes scattered families and consolidates them into fewer settlements. It is sold as a scheme for better schools, clinics, cleaner water, and, authorities say, more democracy.

Sunday, June 2, 2013

የሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰሳማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ


ሟቹ የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ የዛሬ ስምንት አመት ገደማ ይመስለኛል በራሳቸው አንደበት ጋዜጠኛም ሳያስፈልጋቸው በቴሌቪዢን መስኮት ብቅ ብለው ማንም ሰው ከዛሬ ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ ማድረግ የማይችል መሆኑን አስረግጠው በማስፈራሪያ መልክ የተናገሩት፡፡

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ለረዥም ጊዜ /ላለፉት ስምንት/ ዓመታት ሰላማዊ ሰልፎች በሃገራችን ላይ ሳይደረጉ የህዝባችንም ድምፅ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ትእዛዝ ታፍኖ ቆይትዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ህገመንግስታዊ መብቱን በመጠቀም በዛሬው እለት የጠራው ሰልፍ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ በሰለማዊ መንገድ የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት እንዲሁም  ያለ አግባብ የታሰሩ የፖለቲካ የሀይማኖት እና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፤  ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በአግባቡ እንዲመለሱ እና አፈናቃዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የኑሮ ውድነቱ አስተማማኝ እልባት እንዲሰጠው እና ሌሎችንም በርካታ ጥያቄዎች ያቀረቡ ሲሆን

Titel: Demo. in Addis Abeba
Schlagwörter: Demo. blaue Partei, Äthiopien
Autor: Y. G.Egziabher ( DW Correspondent Addis Abeba
Datum: 02.06.2013

መንግስት እነኚህን የህዝብ ጥያቄዎች በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ካልመለሰ ድምፃቸውን በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚያሰሙ የፓርቲው አመራር ገልፀዋል፡፡

ሰልፉ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ጀምሮ እስከ ስምንት ሰዓት ድረስ እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ የተከናወነ ሲሆን ቀበና ከሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት አንስቶ በአራት ኪሎ በፒያሳ እና በቸርቸር ጎዳና ሄዶ መድረሻውን ኩባ አደባባይ ያደረገው ሰልፍ ባልተጠበቀ የህዝብ ቁጥር ብዛት በኢትዮጵያዊ ጨዋነት በሰላም ተጠናቋል፡፡

944521_502719046450298_831415286_n
እንግዲህ ወያኔዎች ከዚህ የሰላማዊ ሰልፍ ብዙ ልትማሩ የሚግባችሁ ይመስለኛል ህዝቡ ምን ያህል ድምፁ ታፍኖ እንደነ በረና እንደተማረረ ብሶቱን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ መግለጽ እንደሚፈልግ እንዲሁም በሃገራችን ውስጥ የስርአት ለውጥ እንደሚያስፈልገን መገንዘብ ይኖርባችኌል፡፡ በመሆኑም በጠመንጃ አፈሙዝ፤ በዘር በሃይማኖት ከፋፍሎ የአንድ የብሄር የበላይነትን አጉልቶ ሌላውን ብሄር በማሳነስ ሃገር መግዛት አይቻልምና  ሃገራችን የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት የሚከበርባትና ሁሉም ዜጋ በሃገሩ ሳይሸማቀቅ አንገቱን ቀና አድርጎ የሚኖርባት አንዲት ኢትዮጵያ እንድትኖረን እንፈልጋለንና ሃገራችንን ብትለቁልን በሚል የግል አስተያየቴን በመስጠት ሰማያዊ ፓርቲዎችን በርቱ ተበራቱ እኛም ከጎናችሁ ነን ለማለት እወዳለሁ፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር

ሄለን ንጉሴ  

Thursday, May 30, 2013

የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ


የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ
የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛ ጉባኤ ቅዳሜ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓም ተጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከተካሄደ በኋላ ህዝባዊ ትግሉን ወደፊት የሚያራምዱ ዉሳኔዎችን ካሳለፈ በኋለ ባለፈዉ ሰኞ ምሽት እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ። ይህ የንቅናቄዉ አራተኛ መደበኛ ጉባኤ ንቅናቄዉ ባለፉት ሁለት አመታት የተጓዘባቸዉን መንገዶች፤ ያቀዳቸዉን ስራዎችና የዕቅዱን አፈጻጸም በጥልቀትና በስፋት በመዳሰስ መጪዉ የትግል ወቅት የሚጠይቀዉን የመስዋዕትነት ደረጃ ከወዲሁ ተመልክቶ ዘረኛዉን የወያኔ አገዘዝ በማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ የፍትህና የዲሞክራሲ ጥማት ሊያረኩ ይችላሉ ብሎ ያመነባቸዉን አበይት ዉሳኔዎች አሳልፏል።
የግንቦት ሰባት አራተኛ መደበኛ ጉባኤ የንቅናቄዉን የአለፉት አምስት አመታት ጉዞና በዚህ በአራተኛዉ ጉበኤ ላይ የስልጣን ዘመናቸዉን የጨረሱት የንቅናቄዉ ምክር ቤትና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስራ ዕቅድና የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጦ ሰፊና ጥልቅ ዉይይት ካካሄደ በኋላ በጉባኤዉ ላይ አዲስ ለተመረጡ የአመራር አባላት ንቅናቄዉ የታሰበበትን ግብ እንዳይመታ አንቀዉ የያዙትን እንቅፋቶች እንዲያስወግድና እንዲሁም የንቅነቁዉ ጥንካሬ በታየባቸዉ መስኮች አቅሙን አጣናክሮ በይበልጥ በመስራት የኢትዮጵያ ህዝብ ከንቅናቄዉ የሚጠብቀዉን የታሪክ አደራ እንዲወጣ አሳስቧል። በጉባኤዉ ወቅት አባላት ያደረጉት አመራሩን የመንቀፍ፤አቅጣጫ የማሳየት፤ ሀሳብ የማመንጨትና በአጠቃላይ በእያንዳንዱ የጉባአዉ ስብሰባ ላይ ባሳዩት ንቁ ተሳትፎ ንቅናቄዉ በህዝባዊ አመጽና እምቢተኝነት ዘርፎች ብቻ ሳይሆን በዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍም እያደገ መምጣቱን አሳይተዋል።
የግንቦት ሰባት አራተኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤትና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፤ ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ እንዲሁም የስነ ስርአትና የግልግል ኮሚቴ ሪፖርቶችን አዳምጦ ሰፊና ጥልቅ ዉይይት ካካሄደ በኋላ ሪፖርቶቹን አጽድቋል። ከዚህ በተጨማሪ የንቅናቄዉን እስትራቴጂና ይህንኑ እስትራቴጂ ተሸክሞ በተግባር የሚተረጉመዉን መዋቅር በአጽንኦት ከፈተሸ በኋላ በስትራቴጂዉ ላይ መጠነኛ ለዉጥ በማድረግ የእስትራቴጂዉንና የመዋቅር ለዉጡን ተቀብሎ አጽድቋል። ይህ የንቅናቁዉ አራተኛ ጉባዜ ንቅናቄዉን ላለፉት ሁለት አመታት የመሩትንና ያገለገሉትን የምክር ቤት፤ የኦዲትና ቁጥጥር፤ የስነ ስርአትና ግልግልና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግኖ በማሰናበት በምትካቸዉ ንቅናቄዉን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት የሚያገለግሉ የምክር ቤት አባላት፤ የኦዲትና ቁጥጥር፤ እንዲሁም የስነ ስርአትና ግልግል ኮሚቴ አባላትን መርጧል።
አራተኛዉ የግንቦት ሰባት መደበኛ ጉባኤ ኢትዮጵያ ዛሬ የምትገኝበትን ሁኔታ በዝርዝር ከቃኘ በኋላ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ዉጊያ የተያያዘዉ አገር ዉስጥና በዉጭ አገሮችም ስለሆነ ወያኔን በእነዚህ ሁለት የትግል መስኮች እንደአመጣጡ ከገጠምነዉ የሚሸነፍ ድርጅት መሆኑን ሙሉ በሙሉ በመቀበል አባላቱ ባሉበት ቦታ ሁሉ የሚሰሩት ስራ ወያኔን በማስወገድ ላይ እንዲያተኩር አሳስቧል። ከአለም ዙሪያ ከተለያዩ አገሮች የመጡ የግንቦት ሰባት አባላትን ያሰባሰበዉ አራተኛዉ የግንቦት ሰባት መደበኛ ጉባኤ የትግል ቃል ኪዳን የታደሰበት፤የመስዋዕትነት ዝግጅት የታየበትና አባላት የትግልና የስራ ልምድ የተላዋወጡበት ከምን ግዜዉም ባላይ የተሳካና የተዋጣለት ጉባኤ ነበር። በመጨረሻ ጉባኤዉ የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛ ጉባኤ ለአባላቱና በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ የትግል ጥሪ በማስተላለፍ ደማቅ በሆነ ስነሰርአት ተፍጽሟል።
የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ

የአሜሪካ የህግ ባለሙያዎችና አኢጋን (SMNE) በኅብረት ስራ ጀመሩ! ዓርብ የፖለቲካና የሙስሊም እስረኛ ጠበቆችን ያነጋግራሉ


ጎልጉል የድረ-ገጽ ጋዜጣ

በኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በተመለከተ የአሜሪካን የህግ ባለሙያዎች ማህበር (ABA – American Bar Association) ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስራ አርብ እንደሚጀምር ተገለጸ። አዲስ አበባ ካሉ የፖለቲካና የሙስሊም ወገን እስረኞች ጠበቆች ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ አርብ ግንቦት 23፤2005ዓም ያደርጋሉ። አቶ ኦባንግ ሜቶ የተረሱ እስረኞች ጉዳይም እንደሚካተት ጠቅሰው በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ለታሰሩ ዜጎች ጥብቅና የቆሙ ካሉ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ በቀጥታ እንዲገናኙ ጥሪ አቅርበዋል።
(ABA) በሚል ስያሜ የሚታወቀውና ከተቋቋመ 135ዓመታትን ያስቆጠረው የአሜሪካ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከ400 ሺህ በላይ የህግ ባለሙያ አባላት አሉት። ይህ በአሜሪካ ትልቅ የተባለ ማህበር በግፍ ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ድጋፍ ለማድረግ የወሰነው የአኢጋን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ በይፋ የድጋፍ ጥያቄ ባቀረቡ በቀናት ውስጥ ሲሆን፣ በጋራ በተከናወኑ ንግግሮችና የሰነድ ውይይቶች በወር ጊዜ ውስጥ ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት እንደተቻለ ለማወቅ ተችሏል።
ከወር በፊት በተካሄደ የማህበሩ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ንግግር እንዲያደርጉላቸው በተጋበዙት መሰረት አቶ ኦባንግ ህግን እየተንተራሰ ዜጎችን በቁም እስርና በወህኒ ቤት እያሰቃየ ስላለው የኢህአዴግ አገዛዝ በስፋት ባስረዱበት ወቅት ማህበሩ እሳቸው ከሚመሩት ድርጅት ጋር በትብብር ለመስራት ፈቃዱን አሳይቶ እንደ ነበር አቶ ኦባንግ ለጎልጉል ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ኢህአዴግ ህግን ከለላ በማድረግ በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ግፍና ወንጀል፣ ለአፈና ተግባሩ ማስፈጸሚያም የጸረ ሽብርተኝነትን፣ የመያዶችን፣ ወዘተ ህጎችን በማውጣት ዜጎችን ለወህኒ ቤትና ለቁም እስር፣ ለስደት፣ ለስቃይ መዳረጉን፣ የፍትህ አካላቱን ህግን በሚያከብሩና ፍትህ በሚያስፈጽሙ ገለልተኛ አካሎች ሳይሆን ራሱ በመሠረተው ተቋም እያመረተ የሚጠቀምባቸው የፖለቲካው መሳሪያዎቹ ስለመሆናቸው፣ በመዘርዘርና ማስረጃ በማጣቀስ አቶ ኦባንግ ለጉባኤው መናገራቸውን አመልክተዋል።
ቀደም ሲል ጀምሮ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚዎች የሚታወቁትም ሆነ ሚዲያው የዘነጋቸው ዜጎች ጉዳያቸው ዓለም ዓቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ በያቅጣጫው እየተደረገ ካለው የተለያየ ጥረት በተጨማሪ ሲመክርበት የነበረው ጉዳይ እንደሆነ በመግለጽ አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ኦባንግ “ተጽዕኖ ሊፈጥሩ የሚችሉት አካላት በራሳቸው ሰዎች በቂ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ ታላቅ ተግባር ነው። ድርጅታችን እንደ ስኬት ይቆጥረዋል። ዓርብ በዝርዝራችን ካገኘናቸው የታዋቂ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪ ጠበቆች ጋር የስካይፕ ስብሰባ ይካሄዳል። በቀጣይ አገር ቤት በመሄድ ባመቻቸው መንገድ ስራቸውን ያከናውናሉ” ብለዋል።
በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ጥያቄ በማንሳታቸው የታሰሩት ወገኖች፣ ወዘተ ጠበቆች ጋር በስካይፕ ንግግር እንደሚደረግ አቶ ኦባንግ አስታውቀዋል። እስከዛሬ ጆሮ ያልተሰጣቸው ወገኖች ጉዳይ አደባባይ ከማውጣት በተጨማሪ የጋራ ንቅናቄው ባቋቋማቸው ግብረኃይሎች አማካይነት ወደ ህግ የሚሄዱ፣ ሌሎች አብረው መስራት የሚፈልጉ አካላት የሚያቀርቧቸውን አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ጉዳዮች በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ክስ መስርቶ ለመሟገት ማህበሩ ዝግጁ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አስፈላጊውን የህግ ድጋፍ የሚፈልጉ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች ጥያቄያቸውን ለጋራ ንቅናቄው ማቅረብ ይችላሉ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ማህበሩ መንግስትን የሚያማክሩ፣ የሚመክሩ፣ ፖሊሲ በማርቀቅ ስራ ላይ የተሰማሩ ታዋቂ የህግ ባለሙያዎች፣ ለዓለም ዓቀፍ ሚዲያና ኔትወርኮች ቅርበት ያላቸውና ተሰሚነታቸው የጎላ በመሆኑ እንዲህ ካሉ አካላት ጋር በጨዋነት መስራት በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለማስተጋባት መልካም አጋጣሚ ማመቻቸት እንደሆነም አቶ ኦባንግ አመልክተዋል።
“… ኢህአዴግ በስደተኛነት ስም ደጋፊዎቹን በስርዓቱ የተገፉ በማስመሰል የሃሰት ማስረጃ እያስጨበጠ በአሜሪካ፣ በካናዳና በተለያዩ የምዕራብ አገራት ያሰማራቸውና በተቀነባበረላቸው መረጃ የስደት መኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ ስደተኛውን እንዲሰልሉና ለሥርዓቱ እንዲሰሩ እያደረገ መሆኑ፤ በተለያዩ አገራት በገቢር የተያዙ መረጃዎችና ዋቢ ክስተቶች መኖራቸውን የተረዳው የባለሙያዎቹ ማኅበር ጉዳዩን በጥልቀት እንደሚያየውና ያለውን ከፍተኛ የሰው ኃይል በመጠቀም ከአኢጋን ጋር እንደሚሰራ ከሌሎች ማኀበራት ጋር በመሆንም በተለይ በምዕራቡ ዓለም የተሰገሰጉትን አስመሳይ ስደተኞች ወደ ፍትህ የማምጣቱ ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ለድርጅታቸው አረጋግጠዋል” በማለት ከዚህ ቀደም ለጎልጉል ስለተናገሩት አስተያየት እንዲሰጡ አቶ ኦባንግ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።
“ኢህአዴግን የሚደግፉ ዜጎችም ቢሆኑ ለጋራ ንቅናቄያችን ልጆቹ ናቸው” በማለት አስተያየታቸውን የጀመሩት አቶ ኦባንግ “ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ላይ ምስጢረኛ ለመሆን እገደዳለሁ። አንድ ነገር ለማስታወስ ያህል ግን ምዕራባውያን አሠራራቸው መጭበርበሩን ካረጋገጡ ምህረት የላቸውም። ከሰብአዊነትም አንጻር ቢሆን አገሩ መኖር ያልቻለን ዜጋ ስደት አገር ድረስ እየተከታተሉ ማሳደድ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የለውም። በህግም አይፈቀድም። እንደዚህ ካሉት ጋር የሚተባበሩ አገሮችን ህግ ፊት በማቆም በህግ ስለፍትህ እንከራከራል” የሚል መልስ ሰጥተዋል።
ABA የሚባለው የህግ ባለሙያዎች ማህበር ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ከሁለት ሳምንት በፊት ሲያከብር ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት አቶ ኦባንግ ሜቶ በርካታ ጉዳዮችን በማንሳት ድጋፍ ጠይቀው አዎንታዊ ምላሽ እንዳገኙ፣ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። አቶ ኦባንግ እንደሚሉት አርብ የሚደረገው ንግግር የድጋፉና አብሮ የመስራቱ ሂደት መጀመሪያ ነው። ሥራው ጊዜ የሚወስድና እልህ የሚያስጨርስ መሆኑን ሁሉም እንዲያስተውለውና ፈጣን ውጤት በመጠበቅ ቶሎ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ሁሉም ዜጋ አለኝ የሚለውን መረጃ ለጋራ ንቅናቄው በመላክ ትብብሩን እንዲቀጥል ጨምረው ገልጸዋል፡፡

Monday, May 20, 2013

ህዝባዊ ውይይት በኖርዌይ


በኖርዌይ ኦስሎና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቅዳሜ በ18.05.13 ህዝባዊ ውይይት አደረጉ። ውይይቱ በሀገራችን በግፍ ለተገደሉ፤ በእስር ለሚንገላቱና ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ለሚሰቃዩና ለተሰደዱ ወገኖች የህሊና ፀሎት በማድረግ ተጀምሯል። በርካታ ታዳሚዎችም ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ በመደገፍ ጥቁር ልብስ ለብሰው ተገኝተዋል።

Ethiopians meeting in Norway
ውይይቱ የተጠራው በኖርዌይ ለወገን ደራሽ ግብረ ሀይል ሲሆን ያተኮረውም በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ነበር፤
ሀ. በውጪ ሀገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራ) በኢትዮጵያ  ፖለቲካ ውስጥ ስለሚጫወተው ሚናና በሀገር ቤት በሰማያዊ ፓርቲ ስለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ
ለ. ሰላማዊና ሌሎች የትግል ስልቶች በኢትዮጵያ እና ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ
ሐ. ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመገናኛ ብዙሀን፤ ከሰብአዊና ከዲሞክራሲ መብቶች አንጻር
መ. ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታና በሀገር ቤት ስለታቀደው የሰማያዊ ፓርቲ ተቃውሞ ሰልፍ
ሰ. የሀይማኖት ነጻነት በኢትዮጵያና ሰማያያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ  የሚሉት ይገኙበታል።
በነዚህ ወቅታዊና አንገብጋቢ ርዕሶች ላይ ለታዳሚዎች የመወያያ ሃሳቦችንና ገለጻዎችን ያቀረቡት በቅደም ተከተል አቶ አርጋው ያቆብ፤ አቶ ዳንኤል አበበ፤ አቶ ዳባ ጉተማ፤ አቶ ዳሂሎን ያሲን እንዲሁም አቶ ሙሀመድ ሲራጅ ሲሆኑ ዝግጅቱንና ውይይቱን የመሩት ደግሞ አቶ ዳዊት መኮንን ናቸው።
በውይይቱ ላይ በርካታና ዝርዝር ጉዳዮችና ሀሳቦች ተነስተዋል።
በውጪ ሀገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራው) በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና ሊጫወት እንደሚችል አቶ አርጋው በዝርዝ አቅርበዋል። በሚዲያና በቴክኖሎጂ በመደገፍ አገር ውስጥና ውጪ ካሉ ተቃዋሚ ሀይሎች ጋር የመረጃ ልውውጦችንና ቅስቀሳዎችን በማድረግ፤ ለአለም አቀፍ ድርጅቶች አቤቱታን በማቅረብ፤ ሰላማዊ ሰልፎችን በማድረግ፤ በመዋጮ በቁሳቁስና በሞራል ተቃዋሚ ሀይሎችን በመደገፍ፤ ገዢው አካል አለም አቀፋዊ ድጋፍ እንዳያገኝ በማድረግ፤ በሲቪክ ማህበራት በመደራጀት ወዘተ ዲያስፖራው በኢትዮጵያ ለሚደረገው የዲሞክራሲና የነፃነት ትግል ጉልህና ትልቅ ሚና ሊጫወት እንደሚችል አስረድተዋል። በአንፃሩ ደግሞ በሀገር ጉዳይ ላይ የተሳትፎ ማነስ፤ እኔ ምን አገባኝ የማለት፤ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አፍራሽ ዜናዎችን በማሰራጨትና የወያኔን ፖለቲካ በማራገብ፤ የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ ከትግሉ በማፈግፈግ፤ ለግል ጥቅም በመገዛት ከወያኔዎች ጋር በመተባበር ወዘተ ዲያስፖራው ትግሉን ሊያዳክመው እንደሚችል አስገንዝበው ይህን በተመለከታ ተቃዋሚ ሀይሎች ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
Ethiopian in the Diaspora, meeting in Norway
በሌላ በኩል ደግሞ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን በተመለከተ አቶ ዳንኤል እንዳብራሩት፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰላማዊ ትግል ማታገያ ስልቶች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም መካከል ዋና ዋና የሆኑት ከሶስት እስከ አምስት የሚጠጉ ስልቶችን ጠቅሰዋል። ከነዚህም መካከል ትብብር መንፈግና ተፅዕኖ መፍጠር ይገኙበታል። በዚህ አጋጣሚ አሁን ያለውን ስርዓት ለመለወጥ ሁለገብ የትግል እንቅስቃሴን መደገፍ ተገቢ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
አቶ ዳባ ጉተማ በበኩላቸው ስለዜጎች መፈናቀል፤ ገዢው ፓርቲ የሚቀሰቅሳቸው ፀብ አጫሪ ሁኔታዎች፤ ለፍትህና ለዲሞክራሲ በሰላማዊ መንገድ በሚታገሉ ንፁሀን ዜጎች ላይ ስለሚደርሰው ግድያ፤ አፈና፤ እስር፤ እንግልትና ወከባ፤ በኑሮ ውድነትና በመሳሰሉት በገጠርና በከተማ በህዝቡ ላይ ስለሚደርስ ስቃይ፤ በአሁኑ ወቅት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የሚሆኑት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን መስዋዕት ለማድረግ የቆረጡ መሆናቸው በአጠቃላይ የፖለቲካ መህዳሩ የሚመች እንዳልሆነ፤ እስከዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ገዢ እንጂ መሪ አግኝቶ እንደማያውቅና ያሁኑ ግን ሲኦል እንደሆነበት በዝርዝርና በተጨባጭ ምሳሌዎች በጣም በርካታ ጉዳዮችን አንስተው ለተወያይ ታዳሚዎች አቅርበዋል። በተጨማሪም ትላንት ካልነበረ ዛሬ እንደሌለ ዛሬ ከሌለ ደግሞ ነገ እንደማይኖር የታወቀ ስለሆነ ለዛሬ በጣም እንድናስብበት አሳስበዋል።
እንዲሁም አቶ ዳሂሎን ያሲን በተለይ በአሁኑ ወቅት ያለውን የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታና ሰማያዊ ፓርቲ ስለጠራው ሰላማዊ ሰልፍን አቶ ዳሂሎን እንደመነሻ የምርጫ 97 ሰላማዊ ሰልፍን ካነሱ በኋላ በአሁኑ ወቅት በይፋ ስለተጠራው ስለዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ሊኖሩት ስለሚችሉት አሉታዊና አዎንታዊ ገፅታዎች አብራርተዋል። በዋናነትም የሰላማዊ ሰልፉ መጠራት ቢሳካም ባይሳካም ያለውን ጠቀሜታና በንፅፅርም የሚታዩትን ስጋቶች ተንትነዋል።
Ethiopians gathered in Norway to discuss current Ethiopian politics
በወቅቱ በኢትዮጵያ ስላለው የሙስሊም ወገኖቻችንን ጥያቄዎችና በገዢ አካል ስለሚደረገው የሀይማኖት መብት ረገጣ በተጨማሪም አሁን ስላለው ችግር መንስኤ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ በአቶ ሙሀመድ ሲራጅ ቀርቧል።
ታዳሚዎችም በርካታ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን በማንሳት ከፍተኛ ተሳትፎ የተደረገበት ውይይት አድርገዋል።
በመጨረሻም የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ በጋዜጠኛ አበበ ገላው የተደረገበትን ተቃውሞ አንደኛ አመት በማስታወስ ነፃነት ነፃነት ነፃነት የሚለው መሪ ቃል በህብረት፣ በስብሰባው  መክፈጫ ላይ ተብሎ እንደተጀመረ ሁሉ የእለቱ ስብሰባ  ሲጠናቀቅም  በተመሳሳይ መልኩ ተሰብሳቢዉ  ከመቀመጫቸዉ ተነስተዉ በአንድ ድምፅ ነፃነት! ነፃነት! ነፃነት!  የሚለዉን ቃል አሰምተዋል።
በስብሰባዉ ማጠቃለያ  ተሰብሳቢዉ በጋራ የተስማሙባቸዉን  የሚከተሉትን ሦስት አበይት ሃሳቦች የስብሰባዉ የአቋም መግለጫ በማድረግ የእለቱን ስብሰባ አጠናቀዋል።
1ኛ.በኢትዮጵያ ዉስጥ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት፣የፖለቲካና ሃይማኖት ነፃነት፣ እንዲከበር በተጨማሪ የንፁሃን ወገኖቻችንን ከቤት ንብረታቸዉ አፈናቅለዉ ለሞት ያደረጓቸዉን ሰዋችና የመንግስት ባለስልጣናት፣የሃይማኖት መብት ጥያቄ ባቀረቡ ያሰሯቸዉና የገደሏቸዉን ባለሰልጣናት እነዲሁም በኢትዮጵያ በተለያየ ቦታ የፖለቲካ፣የሚዲያና ሲቪክ ማህበራት አባላትና መሪዋችን ያሰሩና ደም ያፈሰሱ የመንግስት ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።
2ኛ.በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰማያዊ ፓርቲ የጠራዉን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደግፉ በጋራ አቋም መግለጫቸዉ አረጋግጠዋል።በተጨማሪ ከአገር ዉጪና በአገር ቤት ያሉ የፖለቲካ፣የሲቪክ፣የሐይማኖት፣ የሴቶችና ወጣቶች መህበራት ሰማያዊ ፓርቲ ለጠራዉ ሰልፍ በተመሳሳይ መልኩ ድጋፍ እንዲያርጉላቸዉ ተሰብሳቢዉ አክለዉ በአቋም መግለጫቸዉ አሳዉቀዋል።
3ኛ.በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እያንዳንዳቸዉ የፌስቡካቸዉን ፕሮፋይል በማጥቆርና ቀስቃሽ ድጋፍ ሰጪ ፅሑፎችን ለሌለዉ በማሰራጨት፣እንዲሁም በፓልቶክና በሎሎች ብዙሃን ማሰራጫ ድጋፋቸዉን እንደሚሰጡና ሌላዉም ኢትዮጵያዊ በተመሳሳይ ሁኔታ ድጋፉን በመስጠት ሁሉም የዜግነቱን ግዳጅ እንዲወጣ አሳስበዋል።
አንድነት ሃይል ነዉ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
በኖርዌይ ለወገን ደራሽ ግብረ ሀይል