Tuesday, July 2, 2013

የአሜሪካ አዲስ ፖሊሲ በአፍሪካ ላይ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በነደፉት የአሜሪካና የአፍሪካ ግንኙነቶች የሚመሠረቱበት አዲስ አቅጣጫና አካሄድ ከፍ ያሉ የምጣኔ ኃብት ዕድሎችን፣ ዴሞክራሲንና አፍሪካ መር የሆኑ የፀጥታ መፍትሔዎችን መደገፍና ማበረታታት እንደሚሆኑ አስታውቀዋል፡፡

በሦስት የአፍሪካ ሃገሮች ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኬፕ ታውን ላይ ትናንት ንግግር አድርገዋል፡፡

የሚስተር ኦባማ የኬፕ ታውን ንግግር የአሜሪካና የአፍሪካ መጭ ግንኙነቶች መሠረቶች ናቸው የተባሉ ግቦችን ያሣየ ስፋት ያለው ሥዕል ነው ተብሏል፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ በታንዛኒያፕሬዚዳንት ኦባማ በታንዛኒያ
ይህ የዩኤስ-አፍሪካ ፖሊሲ ድጋፍን ወይም እርዳታን፣ ንግድና መዋዕለ-ነዋይን፣ ጤናና የፀጥታ ትብብር አካባቢዎችን የሚሸፍን እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በፕሬዚዳንቱ አባባል የንግግራቸው ማዕቀፍ የተዋቀረው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ ለአህጉሪቱ ትሩፋት እንዲሆን ባኖሯቸው እሴቶች ላይ ነው፡፡ከመሬት ለመነሣት እየተንደረደረ ባሉት አህጉር ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ ከአዲስ የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማራጮች ጋር በመንቀሣቀስ የንግድ እገዳዎችና መሠናክሎችን በማስወገድ ተሣትፎዋን እንደምታሣድግ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

አፍሪካ ከድኅነት መካከለኛ ገቢ ወዳለው ሕዝብነት እየተሸጋገረች ብትሆንም፣ መከላከል በሚቻሉ በሽታዎች ምክንያት እየሞተ ያለው ሰው ቁጥር እየቀነሰ ቢሆንም “የሙስና ብስባሽ እና ግጭቶች” ሥጋቶችን እንዳጠሉባት መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ “ዩናይትድ ስቴትስ ኢንቨስት ማድረግ የምትፈልገው ጠንካራ በሚባሉ ሰዎች ወይም መሪዎች ላይ አይደለም፤ በጠንካራ ተቋማት ላይ እንጂ” ብለዋል ሚስተር ኦባማ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ቀጥለውም “ግልፅና ተጠያቂ መንግሥታትን፣ ነፃ የፍትሕና የፍርድ አካላትን፣ የሴቶችን የወሣኝነት አቅም የሚያበለፅጉና ውሣኔ ሰጭነትን የሚያጎናፅፉ ተቋማትን ትደግፋለች” ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማ በሮቢን ደሴት ኔልሰን ማንዴላ ለሃያ ዓመታት የታሠሩባትን ክፍል ሲጎበኙፕሬዚዳንት ኦባማ በሮቢን ደሴት ኔልሰን ማንዴላ ለሃያ ዓመታት የታሠሩባትን ክፍል ሲጎበኙ
ፕሬዚዳንቱ ከኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ ንግግራቸው በፊት ኔልሰን ማንዴላ ከሃያ ሰበት ዓመቱ የአፓርታይድ አገዛዝ ዘመን የወኅኒ ሕይወታቸው ሁለት አሠርት የሚሆኑትን ያሣለፉበትን አሥር ቤትና ክፍል ሮቢን ደሴት ላይ ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ፕሬዚዳንት ኦባማ ከትናንት በስተያ - ቅዳሜ ንግግር ባደረጉበት የሶዌቶ አዳራሽ ውጭ ተገኝተው የኢትዮጵያ መንግሥት ሰብዓዊ መብቶችን እንዲያከብር የአሜሪካ መንግሥት ጫና እንዲያሣድር ጠይቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትሱን ፕሬዚዳንት በአሁኑ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ የሚያደርጋቸው ምክንያት እንደሌለ አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምሕር ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማ የአፍሪካ ጉዟቸው የመጨረሻ ክፍል ለሆነው ጉብኝት ዛሬ - ሰኞ፣ ሰኔ 24/2013 ዓ.ም ታንዛኒያ ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳ መደብ ወደ ታንዛኒያ ሲነሱ

Saturday, June 29, 2013

የስምንት ሚኒስትሮች ሹመት ሰሞኑን ይፀድቃል


 የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ዛሬ ግምገማ ያካሂዳል
የኢህአዴግ 36 ከፍተኛ መሪዎችን ያካተተው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመታዊ ግምገማ ለማካሄድ ዛሬ የሚሰበሰብ ሲሆን የስምንት ሚኒስትሮች ሹም ሽርና ሽግሽግ በሚቀጥለው ሳምንት ለፓርላማ ቀርቦ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል፡፡ ለሹመት የሚቀርቡት ባለስልጣናት፤ የፍትህ ሚኒስትር፣ የከተማና ኮንስትራክሽን ልማት ሚኒስትር፣ የግብርና ሚኒስትር፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር፣ የገቢዎች ሚኒስትር የደህንነትና መረጃ ሚኒስትር፣ የደንና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር እንዲሁም በፓርላማ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ናቸው ተብሏል፡፡ አንዳንዶቹ ሹምሽር እርምጃዎች ሲሆኑ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ወደ አዲስ አበባ አስተዳደር እንዲዛወሩ በተደረጉ ባለስልጣናት ምትክ የሚካሄድ ሽግሽግ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የእጩ ተሿሚዎችን ማንነት ለማወቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡ ዛሬ የሚካሄደው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ከሹምሽሩ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ቢታሰብም፣ የሰብስባው ዋና ርዕሰ ጉዳይ አመታዊ ግምገማና አመታዊ እቅድ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት አስፈፃሚ አካል የመቆጣጠር ስልጣን ያለው የአገሪቱ ፓርላማ ጠንካራ የቁጥጥር ሃላፊነቱን በተግባር ማሳየት እንደጀመረ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጭምር ቢናገሩም፤ በሚኒስትሮች ሹመት ዙሪያ ግን የቀድሞው አሰራር አልተሻሻለም፡፡ በተለያዩ ዲሞክራሲያዊ አገራት ውስጥ የእጩ ሚኒስትሮች ማንነት በይፋ ታውቆ ለበርካታ ሳምንታት በፓርላማና በዜጐች ዘንድ ውይይት የሚካሄድበት ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ግን የተሿሚዎች ማንነት የሚገለፀው ሹመታቸው በሚፀድቅበት እለት ነው፡፡

የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ዛሬ ስብሰባ እንደሚያካሂድ የገለፁት የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን፤ የስብሰባው ዓላማ የዓመቱን የስራ አፈፃፀም በመገምገም ድርጅቱ በኪራይ ሰብሳቢነት ላይ የሚያካሂደውን ትግል አጠናክሮ ለመቀጠል በእቅዶች ላይ መወያየት ነው ብለዋል፡፡ የህዝቡን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ በማጐልበት የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትን፤ የህዝብ፣ የመንግስትና የድርጅት አቋሞች እንዲጠናከሩ፣ ችግሮች ያሉባቸውን ደግሞ አንጥሮ ለማውጣት ያለመ ስብሰባ ነው ብለዋል፡፡ በነባር ፖሊሲዎችና አሰራሮች ላይ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው መክሮባቸው አቋም ከወሰደባቸው በኋላ፤ የማስፋት፣ የማጠናከርና የማጐልበት እንዲሁም ተጨማሪና አዳዲስ ዝርዝር የአሰራር አቅጣጫዎችን በመተለም በመጪው አመት እቅድ ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ብለዋል - አቶ ሬድዋን፡፡

Friday, June 28, 2013

ስብሃት ነጋ “እውነት” ሲያዳልጣቸው

June 28, 2013
ከኢየሩሳሌም አርአያ
ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስበውት ይሁን ሳያስቡት “እውነት” አምልጧቸዋል። አጥብቀው ያነሷቸው የሙስና ጉዳዮች ራሱን የቻለ “አላማና ግብ” አላቸው። የመጀመሪያው በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው ክፍፍል (የጥቅም) እንደተዳፈነ እሳት ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ከተናገሩት የሚከተለውን እንመልከት፤ “በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፣ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፣ የመንግስት ሰዎች ነን የሚሉ የፀጥታና የስነ አእምሮ ሁከት ፈጥረዋል። መቶ ሚሊዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፣ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ያታያሉ።” ብለዋል። « እንቆርጣለን » ያሉት መለስ ዜናዊ ናቸው፤ መለስ በአደባባይ ይህን ከመናገር አልፈው ሲያስፈራሩም እንደነበር እናስታውሳለን። መለስ ያንን ያሉት በ10ሺዎች የሚገመት ቡና ከመጋዘን ጠፋ በተባለበት ወቅት ነው። ያንን ቡና የሰረቁትና ባህር ማዶ ሸጠው ገንዙቡን ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጭ ተጠቅሶ ይፋ ተደርጓል። እናም ስብሃት “መቶ ሚሊዮን የሰረቁ..» ያሉት አዜብ መስፍንን ሲሆን፣ « ያስዘረፉ» ያሉት ደግሞ ባለቤታቸው አቶ መለስን ነው። « 10ሺህ የሰረቁ..» የተባሉት በቅርቡ የታሰሩት የጉምሩክ ሰዎችን ሲሆን..እነዚህን በንፅፅር ያስቀመጡት የአዜብ (ተላላኪዎች) ስርቆት መጠነሰፊ መሆኑን ለማመላከት ነው። ስብሃት እስካሁን አድፍጠው ቆይተው በዚህ ሰሞን ይህን መናገራቸው ..« አዜብ የከተማዋ ም/ል ከንቲባ ይሆናሉ» የሚባለውን በመስማታቸው ሆን ብለው ያደረጉት ነው፥ ይላሉ ታዛቢዎች። በተለይ ሽማግሌውን በቅርብ የሚያውቋቸው የፓርቲው ሰዎች « ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በቀለኛ ነው። ጥርሱ ውስጥ የገባን ሰው ካላስወገደ እንቅልፍ አይወስደውም፤ ብዙ ሰው አጥፍቶዋል። አሁንም አዜብን እግር በእግር የሚከታተለው ለዚሁ ነው» ይላሉ። በማስከተልም ፥ « ሙስና ከተነሳ ስብሃትም እስከአንገቱ ተነክሮበታል። በገርጂና ሳር ቤት የሚገኘው <ሉሲ አካዳሚ > በአሜሪካ በሚኖሩ ስጋ ዘመዶቹ ስም እንዲሁም በቀድሞ የአየር ሃይል ጄ/ል ሰሎሞን ስም የሚንቀሳቀስ ግን የስብሃት የግል ንብረት መሆኑን የማይታወቅ መስሎት ነው?….ጎንደር -ሑመራ ያለው የሰሊጥ እርሻ የስብሃት አይደለም?…በ10ሚሊዮን ብር በሚገመት በመቀሌ (አፓርታይድ መንደር) ስብሃት ዘመናዊ ቪላ እንደሚገነባ አይታወቅም ብሎ ይሆን?…» ሲሉ እነዚህ ወገኖች የስብሃትን ሙስና በከፊል ይጠቅሳሉ።

sebehat nega one of the founders of TPLFስብሃት በዚህ አላበቁም፤ « ..እስካሁን ከፍተኛ ሙሰኞች ትንሹን ሙሰኛ ከሰው አሳስረው ያስፈርዱና ያሰቃዩ ነበር ይባላል። ከፍተኛ ሙሰኞች ከመርማሪው ጀምረው አቃቤ ሕጉም ዳኛው፣ ምስክሩም ይቆጣጠራሉ። ትንሽ የሰረቀም ምንም ያልሰረቀም ሲሰቃዩና ሲያደኸዩ የነበሩም፤ አሉም ይባላል። ስልክ እየደወሉም ይፈርዱ ነበር ይባላል።» ብለው አረፉት ስብሃት። ትክክል ናቸው!! ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ « ይህን ካልፈረድሽ በመኪና ገጭተን ነው የምንገድልሽ » ተብላለች። ያውም ከቤተ መንግስት ተደውሎ። አባተ ኪሾ ከደቡብ ባጀት ተመላሽ የሆነ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000) ለመንግስት ተመላሽ ሊያደርጉ ሲሉ …« ወዲህ በል..የምን መንግስት ነው?» በማለት ተቀብለው ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን አባተ ፍ/ቤት ጭምር ያጋለጡት ነው። ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ደግሞ ታምራት ላይኔ በውሸት እንዲመሰክር አምስት ጊዜ አግባብተውት እንቢ ሲል ከማስደብደባቸው በተጨማሪ ሌላ ክስ እንዲመሰረትበት አድርገዋል። አቃቤ ሕግ የነበረው ዮሃንስ ወ/ገብርኤል የነስብሃትን የውሸት ክስ ተቀብዬ ተግባራዊ አላደርግም፤ ህሊናዬ አይቀበለውም .. በማለቱ ብቻ ለአምስት አመት እንዲታሰር አላደረጋችሁም?…ብዙ ማስረጃና መረጃ መደርደር ይቻላል።..
አሁን ስብሃት ተናገሩት እንጂ…ህዝቡ ብሎ-ብሎ የታከተው ነገር ነው!! እነ እስክንድር፣መሃመድ አቡበከር፣ አንዷለም አራጌ፣ ርእዮት አለሙ….ወዘተ በርሶ ጓደኞች በስልክ ትእዛዝ የተፈረደባቸው ናቸው!!… «ፍትሃዊ ስርአትና መንግስት አለ..» እያሉ ህዝብን የሚያደነቁሩት እነበረከትና የጋሪ ፈረስ የሆኑት ሃ/ማሪያም እርቃናቸውን የሚያስቀር ነገር ነው በስብሃት የተቀመጠው።

የአብዬን ወደ እምዬ


ወያኔና ከወያኔ አፍ የሰሙትን ሁሉ እንደበቀቀን እየደጋገሙ የሚያነበንቡ ሎሌዎች የራሳቸውን መልክ የሚያዩበት መስታወት የተቸገሩ ይመስላል። ወየኔና ሎሌዎቹ እራሳቸውን ማየት ስለተሳናቸው ህዝብም ልክ እንደ እነሱ ኣራሱን የማያይና እነሱንና እኩይ ስራቸዉን የማያዉቅ እየመሰላቸው ሄዷል፡፡ ለዚህም ነዉ በግፈኛ አገዛዛቸው ተንገፍግፎ የሚቃወማቸውን ሁሉ ጥላሸት ለመቀባትና በራሳቸው ስም ለመጥራት ሲንጠራሩ የሚታዩት።

የወያኔ ዘረኞች የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ኃይሎች በሙሉ በፀረ-ኢትዮጵያዊነትና የአገርን ጥቅም ለባዕድ አሳልፎ በመሸጥ ሲከስሱ ስንሰማ አይናቸዉንና ፊታቸዉን ታጥበዉ አይነ ደረቅ ለመመሰል ስንት ኪሎ ጨው እንደፈጀባቸዉ መገመት ያዳግታል።
በአገራችን ታሪክ ውስጥ እንደወያኔ በኢትዮጵያ ህልውናና በወሳኝና ዘላቂ ጥቅሞቿ ላይ የዘመተ ኃይል ኖሮም ተፈጥሮም አያውቅም። ለመሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጀግኖች አባቶቻችን አጽም ያረፈበትን መሬት በስጦታ ለጎረቤት አገር እናካችሁ ብሎ የሰጠ ማነዉ? ማነው በሽፍትነት ዘመኑ ለተደረገለት ውለታና ተቀናቃኞቹን እንዲጠብቁለት በማሰብ የኢትዮጵያን ድንበር እንደ ዳቦ እየገመሰ ለባዕዳን የሸጠው?
ማነው የገዛ ወገኑን ከአያት ቅድመ አያት አጽመ ርስቱ ላይ እያፈናቀለ አንድ ሲኒ ቡና በማይገዛ ገንዛብ ለምለም መሬታችንን ለባእዳን የሚያቀራምተው? ማነው በህዝብ ስም በልመናና በችሮታ የተገኘን ገንዘብ እየዘረፈ ከአገርና ከህዝብ ደብቆ የባእድ አገር ባንኮችን የሚያደልበው? ኢትዮጵያ በሶማሊያ በተወረረችበት በ1970ዎቹ አመታት የሞቃዲሾን ፓስፖርት ተሸክመው ይንጎማለሉ የነበሩት የዛሬዎቹ የወያኔ አለቆች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ህዝብ ገና አልረሳዉምኮ!
የዛሬዎቹ የወያኔ መሪዎች ትናንት የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት ማየት ከማይፈልጉ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ጋር እጅና ጓንት ሆነዉ የኛን የጎሳ ድርጅት እስከረዳችሁ ድረስ ኢትዮጵያን እናደክምላችኋለን የሚሉ ጸረ አገርና ጸረ ህዝቦች ነበሩ።እነዚህ የለየላቸዉ ከሀዲዎች ዛሬ አይናቸዉን በጨው አጥበዉ እራሳቸዉን የኢትዮጵያ ጥቅም አስከባሪ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነትና ለአገር አንድነት መከበር የሚታገሉትን ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች የአገር ጠላት ብሎ ለመጥራት የሚያበቃ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያክል የሞራል ብቃት የላቸውም።
ወያኔዎች ስልጣን በያዙ ማግስት በጻፉትና እነሱን ሲጠቅም በሚጠቅሱት አገርንና ህዝብን ሲጠቅም ግን እየዳጡ በሚያልፉት ህገመንግስት ዉስጥ ደደቢት በረሃ የወሰዳቸዉን ዋነኛ አላማ መገነጣጠልን እንደ አገር ጥቅም በጹሁፍ ካልሰፈረ ብለው ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ የነበሩበትን ጊዜ እኛ የኢትዮጵያ ነገር የሚቆረቁረን ወገኖች አልረሳነውም። ለመሆኑ ሌሎችን በጸረ-ኢትዮጵያዊነት የሚከሰው ወያኔ እውነት ኢትዮጵያን ከወደደ መገነጣጠልን ለምን ተመኘላት? መገነጣጠልን የመሰለ አደጋ እንደ ብሔራዊ የአገር ጥቅም አይቶ የራሱን ምኞት በህግመንግስት ደረጃ ያጸደቀዉ ወያኔ እንዴት ሆኖ ነው ለኢትዮጵያ አንድነትና ክብር የሚጋደሉና የሚታገሉ ልጆቿን በሀገር ጠላትነት የሚከስሰው? የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ ጋር የሚደረገዉን ትግል ከመብትና ከነጻነት ትግል ባሻገር እንደ አገር አድን ትግል አድርጎ የሚመለከተዉ ይህንኑ ወያኔ በአገራችን ብሄራዊ ጥቅሞች ላይ በተደጋጋሚ ያሳየዉን ጠላትነት በመገንዘብ ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ተቃዋሚ ኃይሎችን በጅምላ የአገር ጠላት ለማስመሰል በሚቆጣጠራቸዉ የመገናኛ አዉታሮችና በታማኝ ሎሌዎቹ በኩል የጀመረዉን የስም ማጥፋት ዘመቻ ከወዲሁ ተረድቶ “የአብዬን ወደ እምዬ” ብሎ ትግሉን ከቀጠለ ዉሎ አድሯል። ወያኔና ለሆዳቸው ያደሩ ሎሌዎች ሁለመናቸውን የወረሰውን የፀረ-ህዝብና ጸረ ኢትዮጵያዊነት እከክ ማንም ላይ ማራገፍ አይችሉም። ድፍን ኢትዮጵያ ማንነታቸውን አሳምሮ ያውቃልና።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Biography: Nelson Mandela (video)


Biography: Nelson Mandela (video)

Nelson Rolihlahla Mandela (Xhosa pronunciation: [xoˈliːɬaɬa manˈdeːla]; born 18 July 1918) is a South African anti-apartheid activist, revolutionary and politician who served as President of South Africa from 1994 to 1999, the first to be elected in a fully representative, multiracial election. His administration focused on dismantling apartheid’s legacy, and cutting racism, poverty and inequality. Politically a democratic socialist, he served as president of the African National Congress (ANC) political party from 1990 to 1999.
A Xhosa born to the Thembu royal family, Mandela attended Fort Hare University and the University of Witwatersrand, studying law. Living in Johannesburg townships and becoming involved in anti-colonial politics, he joined the ANC, becoming a founding member of its Youth League. When the National Party government implemented apartheid in 1948, he rose to prominence in the ANC’s 1952 Defiance Campaign, being elected president of the Transvaal ANC branch and overseeing the 1955 Congress of the People. Working as a lawyer, he was repeatedly arrested for seditious activities and with the ANC leadership stood on the Treason Trial from 1956 to 1961. Although initially committed to non-violent protest, in association with the South African Communist Party he co-founded the militant Umkhonto we Sizwe (MK) in 1961, leading a bombing campaign against government targets. In 1962 he was arrested and convicted of sabotage and conspiracy to overthrow the government, being sentenced to life imprisonment.
Mandela served in Robben Island and then Pollsmoor Prison, while an international campaign lobbied for his release, which was granted after 27 years in 1990. Becoming ANC president, Mandela wrote his autobiography, and led negotiations with President F.W. de Klerk to abolish apartheid and establish multi-racial elections in 1994, in which he led the ANC to a landslide victory. As president, he created a new constitution and initiated the Truth and Reconciliation Commission to investigate past human rights abuses, while introducing policies aimed at land reform, combating poverty and expanding healthcare. Internationally, he acted as mediator between Libya and the United Kingdom in the Pan Am Flight 103 bombing trial, and oversaw a military intervention in Lesotho. Refusing to run for a second term and succeeded by his deputy Thabo Mbeki, Mandela became an elder statesman focusing on charitable work in combating poverty and HIV/AIDS.
Mandela has received international acclaim for his anti-colonial and anti-apartheid stance, having received over 250 awards, including the 1993 Nobel Peace Prize, the U.S. Presidential Medal of Freedom and the Soviet Order of Lenin. He is held in deep respect within South Africa as the “Father of the Nation”, where he is often known under his Xhosa clan name of Madiba. Controversial for much of his life, critics denounced him as a terrorist and communist sympathiser.

በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው


June 26 2013
Bereket Simon is the Ethiopian Communications Ministerዶር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበርንት ከሚመራው ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ በረከት ስምኦን የሚመሩት የመንግስት አካል በምስጢር እየዶለተ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ። በቅርቡ በአንድ ድረገፅ ላይ የወጣውን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር በማስረጃነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው በአገር ውስጥ እየተንቀሳቅሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ « ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው፤ ከግንቦት ሰባት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል» በሚል እነበረከት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የፓርቲውን አመራሮች «ከሽብረተኛ ቡድን ጋር በመገናኘት» ብለው ለመክሰስ ሴራ እያበጃጁ መሆኑን አስውታውቀዋል።

የፓርቲው አመራሮችን ከማሰር ባለፈ «ሰማያዊ ፓርቲ በሽብርተኛ ድርጅት የሚረዳ ነው» በሚል በአገር ውስጥ የሚኖረውን የፓርቲው ቀጣይ ህልውና ለማክሰም ጭምር እየዶለቱ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ከበረከት በተጨማሪ ደብረፂዮን ይህንን ሴራ በበላይነት እየመከሩበት እንደሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ ለሚገኝ አንድ ጋዜጠኛ ከገዢው ባለስልጣናት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደተላከለት የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። መጀመሪያ 250.000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ፣ በማስከተል 50.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሃዋላ እንደተደረገለትና ባጠቃላይ 300.000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በዶላር ተመንዝሮ በእጁ እንደደረሰው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ገንዘቡ ከነበረከት በኩል በምስጢር የተላከ መሆኑን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚሁ መሰረት ጋዜጠኛው ለሕወሐት/ኢህአዴግ ማገልገል መቀጠሉንና በተለይ አሁን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየተሸረበ ያለው ሴራ መነሻው ይህ ሰው እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል።
ከኢየሩሳሌም ኣርአያ

Monday, June 24, 2013

የኢትዮጵያ የአበባ ምርት በአፍጋኒስታን ገበያ አገኘ እንዴ?

June 24, 2013

ሐቅ! የአየር መንገዳችን የጭነት ጥያራዎች በግንቦት እና በያዝነው ሰኔ ወራት ወደ አፍጋኒስታን ደፋ ቀና ሲሉ ታይተዋል። (Flight Radar24.com ድረ-ገጽን ይመልከቱ)
ሐቅ! አየር መንገዱ ስድስት የጭነት ጥያራዎችን አሰማርቶ በቋሚ መልክ ወደ አውሮፓ፤ መካከለኛው ምሥራቅ እና እስያ ሸቀጣ ሸቀጥ ያመላልሳል። ኾኖም አፍጋኒስታን በቋሚነት ከሚበርባቸው አገሮች መኻል ያልተመዘገበች ከመሆኗም ባሻገር በጦርነት ከተዘፈቀች አገር ጋር ምን ዓይነት ንግድ ተጀመሮ ይሆን የሚያስብሉ ሰባት በረራዎች ቀልቤን ሊስቡት ችለዋል።
ሐቅ! አፍጋኖቹ ያለፉትን ሦስት-አሥርት ያህል ዓመታት ያሳለፉት እርስ በርስ በመፋጀት፤ በመፈራረቅ አገራቸውን የያዙባቸውን የሁለቱን ኃያላን መንግሥታት ወራሪ ሠራዊቶች በመከላከል እና በመኻሉም አክራሪ-ሃይማኖተኝነትን መርኅ በማድረግ ነው። የአገራቸው መልክዓ-ምድር እንደ ኢትዮጵያ ተራራማ ከመኾኑም ባሻገር የገጠሩ ዜጋ አኗኗር የኛውኑ ገጠሬ ጋር ይመሳሰላል። በጎቻቸው እንኳ በላት ምትክ ቂጣሞች ይሁኑ እንጂ የኛውኑ የአዳል ሙክት ነው የሚመስሉት። ግን ከኋላቸው ሲያስጠሉሉሉሉሉሉ!
afghanistan sheeps and Ethiopia
እንግዲህ ለዚህ መጣጥፍ መነሻ የሆነኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ የጭነት በረራዎች በግንቦት ወር አራት (የመጀመሪያው በረራ ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ/ም ነበር) ጊዜ
እና በያዝነው የሰኔ ወር ደግሞ ሦስት ተመሳሳይ በረራዎች (ወሩ ገና ስላላለቀ ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ!) የአሜሪካ ሠራዊት የሚጠቀምበትን የካንዳሃር ጥያራ ጣቢያ ሲጠቀሙ መገንዘቤ ነው። ለአሜሪካ ሠራዊት የቀንድ ከብት ጭነው ይኾን እንዴ? አይ ግዴላችሁም አበባ መሆን አለበት! ግን አንዱ በረራ ከሊዬዥ ቤልጂግ ተነስቶ ካንዳሃር ካረፈ በኋላ መልሱን በሆንግ ኮንግ በኩል ሲያደርግ ነዋ የታየው። ስለዚህ ጭነቱ አበባ ቢሆን ኖሮ ከአዲስ አበባ፣ ሊዬዥ፤ ከሊዬዥ ዱባይ፤ ከዱባይ ካንዳሃር እስከሚገባ አበባው የሚጠወልግ እና የኪሣራ ኪሣራ ነው የሚሆነው።

ወይ ከአፍጋኒስታን እነኛን የአዳል ሙክት የሚመስሉትን በጎች መንግሥታችን ሸምቶልን ይሆናላ! አይ፣ ወይ የሁዳዴ ወይ የረመዳን ጾም መፍቻ ወቅት ቢሆን ኖሮ በግ ተሸምቶልን ነው ለማለት ይቻል ይሆን ነበር። በግንቦትና በሰኔ ወራት ግን አይመስልም። እሺ! አየር መንገዳችን ሰራተኞቹን በጭነት አውሮፕላን እያጓጓዘ የዓመት እረፍታችውን በራሱ ወጭ አፍጋኒስታን ወስዶ ማዝናናት ጀመረ እንዴ ? እንደዚያ ከሆነ ጎረቤት አገር ኬንያ እየወሰደ ቢያዝናናቸው ወጭው አይቀልለትም ኖሯል ? ደግሞስ ጦርነት እሚካሄድበት አገር ወስዶ ለአደጋ ቢያጋልጣቸው የዋስትና ሽፋኑ አይከሽፍበትም ? አይ ምክንያቱ ይኼም ሊሆን አይችልም። በነገራችን ላይ ምንም ጭኖ ወይም ለመጫን ይሁን አፍጋኒስታን የሄደው በሽብር መኻል ጥያራው የተንኮል አደጋ ቢደርስበት የአየር መንገዱ ዋስትና ይሸፍነው ይኾን?
Ethiopian Airlines, cargo planes in Afghanistan
ታዲያ በስድስት ጠብድያ የጭነት ጥያራዎች የተጓጓዘው ምንድነው እንበል ? ምነው ዴሞክራሲ እና ግልጽነት በሰፈነበት አገር ተወልደን በሆነ ኖሮ? አየር መንገዳችን በየአንዳንዱ በረራው ከየት ተነስቶ ወዴት፤ ምን ጭኖ እንደሚንቀሳቀስ፤ በጥያራው ግዥ ያባከንነው ገንዘባችን ለኛው ትርፍ እየተሰራበት መሆን አለመሆኑን እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎቻችንን የመጠየቅ ብቻ ሳይሆን አጥጋቢ መልስ የማግኘት መብትም ይኖረን ነበር።

ቆይ ቆይ! የአሜሪካ ሠራዊት ከአፍጋኒስታን የመውጣት ዝግጅቱን እያጧጧፈ ነው የሚል ትንተና አንብቤ የለም እንዴ? አዎ! ሠራዊቱ ቁሳቁሱን አጠቃሎ እ.አ.አ. 1914 መጨረሻ በፊት እንዲወጣ በተወሰነው መሠረት የጊዜ ገደቡ ከመድረሱ በፊት ለማገባደድ ዝግጅቱን እያመቻቸ ይገኛል። የተከማቸውን የጦር መሣሪያ በያይነቱ፤ የመመላለሻ መኪናዎች፤ የተቀበረም ኾነ በሽምጥ የተነጣጠረ ፈንጂ መቋቋም የሚችሉ ተንቀሳቃሾችን (በእንግሊዝኛው Mine-Resistant Ambush Protected (MRAP) vehicles ይሏቸዋል) ማንሳት ይጠይቃል። ታዲያ ዕድሜ ለኅብረ-መረብ (ኢንተርኔት)፤ ሰሞኑን ያነበብኳቸው መጣጥፎች እንደሚገልጹት፣ ከአሜሪካው ዜጋና የሕዝብ ተወካዮች ሸንጎ የተደበቀ መፍትሄ ቢሆንም የሠራዊቱ ዓለቆች ከሃያ በመቶ (በግምት ሰባት ቢሊዮን ዶላር) የሚኾነውን የጦር መሣሪያና ተሽከርካሪዎች፤ የመገናኛ ቁሳ-ቁሶችና ንብረት — አላስፈላጊ ወይም ወደአሜሪካ የማጓጓዣው ወጭ ይከብዳል የሚል ውሳኔ ላይ ደርሰዋል — ከቻሉ ወዳጅ አገራት በራሳቸው ወጭ አስነስተው መውሰድ እንደሚችሉ፤ በዚህ ዓይነት ያልተነሳውን (ብልጫውን) ደግሞ እዚያው አፍጋኒስታን ውስጥ በመሰባበር ማውደም ላይ መኾናቸው ተዘግቧል።
ለምሣሌ የአሜሪካው ሠራዊት በአፍጋኒስታን ካሰማራቸው አሥራ-አንድ ሺ (አሥራ-አንድ ሺ) ኤም. አር. ኤ. ፒ. መኪናዎች (እያንዳንዳቸው አንድ ሚሊዮን ብር ነው ያወጡት!) ሁለት ሺዎቹን መልሶ እንደማይወስድ (ከነኚህም አብዛኛዎቹ ማጓጓዣቸውን አመቻችቶ የሚወስድ ወዳጅ አገር ስለሌለ እዚያው እንደሚሰባበሩ) ቀሪዎቹ ዘጠኝ ሺ መኪናዎች ደግሞ ወደአሜሪካ እና በየአገሩ ወደተሠማሩት የአሜሪካ ሠራዊት እዞች (ይሄም ኢትዮጵያን ሊመለከት ይችላል) እንደሚላኩ የፔንታጎን ቃል አቀባዮች መግለጻቸውን አንብቤያለሁ። ጉድ እኮ ነው!
ታዲያ ወያኔ ምኑ ሞኝ ነው! የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት ጥያራዎችን አሰማርቶ በነፃ የሚገኘውን መሣሪያ እና ኤም. አር. ኤ. ፒ. መኪናዎች ለማንሳት ነዋ ወደካንዳሃር ያዘዛቸው! በርሮበት ወደማያውቀው ጥያራ ጣቢያ፤ የኔ ብጤውን ተከታታይ ለማደናበር ሰባቱንም በረራዎች ከካንዳሃር በቀጥታ ወደሆንግ ኮንግ በማብረር (መሠረታዊ የጭነት በረራ መሥመር ባይሆንም እንኳ ሆንክ ኮንግ ከካንዳሃር የተሻለ ታማኝነት ይኖረዋል) ያለጥርጥር መሣሪያውን በምሥጢር እያጓጓዙ ነው ወደሚለው ድምዳሜ በበኩሌ የደረስኩ መሆኔ ይሰመርልኝ።
መችም “የስጦታ ፈረስ ጥርሱ አይገለጥም” የሚባለው የአባቶች ብሒል አይታዘበኝና፤ ገዢው የወያኔ ኃይል ዘጠና ዘጠኝ ነጥብ ስድስት ከመቶውን ወንበር በሚቆጣጠርበት “የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት” (ድንቄም የሕዝብ ውከላ እቴ!) ያሉት አንድዬው ተቃዋሚ አቶ ግርማ ሰይፉ እውነታውን ተገንዝበው ጥያቄ ቢያቀርቡም እንኳን ምናልባት ከአቶ መለስ የለመድነውን የትዕቢት ዘለፋ ከማትረፍ በቀር እውነት ያለበትን ጎራ እንኳ አቅጣጫ ይጠቆማሉ ብሎ ማሰብ ከንቱ ነው። እንኳን የአሜሪካኖቹ ትርፍራፊ በኛው ላይ ሊነጣጠር የታሰበ ሊሆን እንደሚችል ሊነገረን ቀርቶ ለምጽዋቱ እንኳን እንደባህላችን “እግዚአብሔር ይስጥልን” ለማለት አይፈቀድልንም። ታዲያ አቶ ኦባንግ ሐሙስ ዕለት በአሜሪካው ኮንግረስ ላይ “እራሳችንን እኛው ነፃ እናወጣለን። እናንተ ግን የመንገድ እንቅፋት አትሁኑብን!” ያሉዋቸውን በአንድ ፊት እናዳምጣለን የሚሉን አሜሪካኖች በጎን ወያኔን በምስጢር እስከቅንድቡ ድረስ እያስታጠቁት ነው።
እንግዲህ ለተጋለጡት በረራዎች የወያኔ አካላትም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው ምክንያት አድርገው ሊያቀርቡ የሚችሏቸውን መልሶች በመንደርደሪያዬ ላይ እንደሸፈንኳቸው ተስፋ እያደርግሁ ያልተለመደ፤ ያልተገለጸ፤ የንግድ ዓላማ ሊኖረው የማይችል እና ማደናበሪያ አቅጣጫዎችን ያካተተ ከካንዳሃር አፍጋኒስታን የሚነሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት ጥያራ በረራዎች የጦር መሣሪያዎችንና ወታደራዊ ቁሳ-ቁሶችን ለማንሳት ካልሆነ በቀር ሌላ ምክንያት አልታየኝም። ይልቁንስ ተቃዋሚ ቡድኖች ካሁኑ ማንሳት ያለባቸው 1ኛ) አሜሪካኖቹ በነፃ ውሰዱ ያሉትን ከፍ ያለ ዋጋ ከፈልንበት ብለው የለመዱትን ብዝበዛ እንዳያካሂዱ 2ኛ) ምስር ልትወጋን እየተነሳሳች ስለሆነ መከላከያ መሣሪያ ብለን ነው እንዳይሉ ከምስር ጋር እያካሄዱት ያለው የአፍ ጦርነት በሁለቱም በኩል የገዥ አካላቱን ዕድሜ ማራዘሚያ ስልት እንጂ ሌላ ምንም ትርጉም የሌለው መሆኑን 3ኛ) ምዕራባውያን በፊት ለፊት የዴሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብት፣ ወዘተ
ደጋፊናተቸውን በመለፈፍ እየሸነገሉ በኋላው በር ግን እኛኑ የሚያስቀጥቀጥ ግፊታቸውን እንደማያቆሙ እንደነቃንባቸው ማሳወቅ ነው።
ይመኩ ታምራት (ከሎንዶን)
ሰኞ ሰኔ 17 ቀን 2005 ዓ/ም
ምንጮች
* http://www.flightradar24.com
*Scrapping equipment key to Afghan drawdown By Ernesto Londoño,June 19, 2013
http://articles.washingtonpost.com/2013-06-19/world/40067061_1_afghanistan-war-mineresistant-