Tuesday, January 21, 2014

የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለአገር ወይስ ለፖለቲካ ስርአቱ ነው የሚል ጥያቄ አነሱ


መንግስት በመረጃዎች አያያዝ ዝርክርክነት ፣ በሳይበር በሚደረጉ ስለላዎች እና ከውስጥ ባሉ የመንግስት አካላት እየሾለኩ በሚወጡ መረጃዎች ህልውናየ አደጋ ላይ ወድቋል በማለት ግመገማ ማድረጉን ተከትሎ  ”የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለማን ነው?” የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን  ከደህንነት መስሪያ ቤት ለኢሳት የደረሰው በድምጽ የተደገፈ መረጃ አመለከተ። በስብሰባው ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የመንግስት ሹሞችም ተገኝተው ነበር።

ጥያቄውን ያነሱት በፌደራል ስር የሚገኙ የደህንነት ስራተኞች እና ቀደም ብሎ በአቶ መለስ ዜናዊ ዘመን በትግራይ ውስጥ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ሽፋን የተቋቋመው ኤም አይ ቲ እየተባለ በሚጠራው ከመቀሌ ከተማ 9 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በተገነባው ተቋም ውስጥ ተመርቀው የወጡት የደህንነት ሰራተኞች ናቸው።
የደህንነት ሰራተኞቹ “የእኛ ሃለፊነት የአገር ደህንነትን ማስጠበቅ ነው የፖለቲካ ስርአቱን ?” በሚል  ጥያቄ ያነሱ ሲሆን፣ አንድ  የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን  ” የፖለቲካ ስራ የማይሰራ ደህንነት የለም፣ የደህንነት ስራ ሲጀመር ስርአት የማቆየት ስራ ነው፤ ስርአቱን የምናቆይበት ደግሞ ፕሮፌሽናል ነው፣ በስርአቱ ላይ እምነት ማሳደር የሚጠይቅ ተግባር ነው፣ የግንቦት7ትን አስተሳሰብ የሚያቀነቅንና ስርአቱ በጉልበት መፍረስ አለበት ብሎ የሚያስብ ሰው፣ የተስፋየ ወልደ ስላሴ አይነት የደህንነት ብቃት አለው ቢባል፣ ሞሳድ 20 አመታት አሰልጥኖታል ቢባል ስርአቱን ከማፍረስ ውጭ ደህንነቱን ሊያስጠብቅ አይችልም” ፣ ስለዚህ የደህንነት ስራ ለሚሰሩ ወገኖች የፖለቲካ ወገንተኝነታቸው ወሳኝ ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል ።
“የደህንነት ተቋሙ ፣ ሰራዊቱና ሚዲያው በተቃዋሚዎች ዘንድ መቼውንም ቢሆን ገለልተኛ ተደርጎ አይቆጠርም” ያሉት እኝህ ከፍተኛ ባለስልጣን ፣ ገለልተኛ ማድረግ የሚባል አስተሳሰብ ያለው ካለ እንደዛ ሊሆን አይችልም፣ ሊሆን የሚችለው የተቃዋሚዎችን ሰዎች ደህንነት ውስጥ ማስገባት ነው ብለዋል። ” በተለይም በተቋም ደረጃ ፤በምህጻረ ቃል ኢንሳ እየተባለ የሚጠራው የመረጃ ደህንነት መስሪያ ቤት፤ የዜግነት እና ኤምግሬሺን ፤የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤በጀኔራል ሳሞራ የኑስ የሚመራው የመከላከያ ደህንነት ፤የአስተዳደር እና ፀጥታ ፤ የፌደራል ፖሊስ ፤ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል በእዝ ሰንሰለት በሚፈጠር ልዩነት እርስ በርስ እየተወዛገቡ ሲሆን፣ ተቋሞቹን በትክክል የሚመሩትን አካላት  ለመለየት አስቸጋሪ ሆኖ መገኘቱና እርስ በርስ በሚፈጥሩት  እሰጥ አገባ  አንዱ አንዱ የሚሰራውን የማጠፋፋት እርምጃ እየወሰዱ መሆኑ በግምገማው ላይ ተነስቷል፡፡
የመንግስት ሚስጥሮች ለሶስተኛ ወገኖች ተላልፈው እየተሰጡ በመሆኑ ሚስጢሮችን  መደበቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል ሲሉ አንዳንድ ባለስልጣኖች አስተያየቶችን ሰጥተዋል።
ለተነሱት አስተያየቶች መልስ የሰጡት ባለስልጣኑ፣ ኢንሳ የተቋቋመውም ይህን ለመስራት መሆኑን  ገልጸው፣ “አገሮች ሙሉ በሙሉ ከሳይበር ስለላ ነጻ ባለመሆናቸው አቶ ሃይለማርያምም ነጻ ናቸው ብየ አላስብም” ብለዋል። “አሜሪካኖች የምንናገረውን ሁሉ ከፈለጉ ይሰሙታል” የሚሉት እኝሁ ባለስልጣን፣ “እኛም የአቅማችንን ያክል አሜሪካኖች የሚናገሩትን ለማዳመጥ እንሞክራለን” ብለዋል። የሳይበር ስለላ ለማካሄድ ጥሩ ጅምሮች ቢኖሩም፣ ያን ያክል የምንኩራራበት ግን አይደለም በማለት ኢነሳ ያለበትን ደረጃ አመላክተዋል
ከኦሮሚያና ከደቡብ የመጡ የደህንነት ሹሞች ደግሞ “በመከላከያ የደህንነት ተቋሞች ውስጥ የአንድ ብሄር የበላይነት ጎልቶ ይታያል” በሚል ቅሬታ ያነሱ ሲሆን ፣ ባለስልጣኑም “የሰራዊት ማመጣጠን ስራ በረጅም ጊዜ የሚሰራ ስራ  ነው ” በማለት ለመመለስ ሞክረዋል።
” ትግሉን መርተው እዚህ ድረስ የመጡ ሰዎችና በመከላከያ ውስጥ ያለውን የመኮንኖች ቦታ የያዙት ከአንድ አካባቢ የመጡ መሆናቸው ግልጽ ነው የሚሉት ባለስልጣኑ፣ ያም ሆኖ ከትግራይ የመጡ በርካታ ጄኔራሎች ጡረታ እንዲወጡ ቢደረግም ሂደቱ ግን ረጅም ጊዜ የሚወሰድ ነው ሲሉ አክለዋል።
“የብሄር ተዋጽኦ ብቻ የአንድን ሰራዊት ጠንካራና ደካማ ጎን መገለጫ ተደርጎ መወሰድ ካለበት አደጋ አለው ” ያሉት ባለስልጣኑ፣ የአንድ ብሄር የበላይነት አለ ተብሎ በአጭር ጊዜ ለማመጣጠን ብቻ በአንድ አዳር ሁሉንም ነገር መቀየር እንደማይቻል መንግስት ያምናል ሲሉ ተናግረዋል
አቶ መለስ ዜናዊ በውጭ ሃይሎች ተገድለዋል ይባላልና በምን እንደሞቱ በትክክል ይነገረን በሚል ባለስልጣናት ላነሱት ጥያቄም የደህንነት ባለስልጣኑ፣ “አቶ መለስ በውጭ ሃይሎች ተገድለዋል የሚል ትክክለኛ ማስረጃ የለም በማለት መመለስ የጀመሩት ባለስልጣኑ፣ እርሳቸው የሞቱት በስራ ብዛት ተዳክመው እና ህክምናውን መቋቋም ባለመቻላቸው ነው ሲሉ ደምድመዋል።
በተያያዘ ዜናም የሃገሪቱን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ከኢሳት ጋር በመሆን እየሰራችሁ ነው፣ ለኢሳትም መረጃ ታቀብላላችሁ  ተብለው የተጠረጠሩ  5 የደህንነት አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል።  ወጣት መብራቴ ታምራት ፤ወጣት ጀማል አወል ፤ወጣት ደጀኔ አድማስ ፤ ወጣት ሃይሉ ጨርቆስ ፤መቶ አለቃ አሰፋ አብርሃ ሰሞኑን በደህንነቶች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢሳት የደህንነት ምንጮች ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ዜናም በሃገሪቱ በ28ቱ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ የህወሃት አባላት ተማሪዎች እና የደህንነቶች ሃለፊዎች ግምገማ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
በግምገማው ወቅት የኦህዴድ እና የብአዴን መሪዎች የተማሪዎችን እንቅስቃሴ በመከታተል ባሰዩት ውጤት የተገመገሙ ሲሆን፣ ባለፉት ስድስት ወራት የአክሱም ፤ ደብረ ታቦር እና ደብረ ብርሃን የኒቨርስቲዎች ከፍተኛ የአመጽ እንቅስቃሴ የታየባቸው በመሆኑ ልዩ የደህንነት ክትትል እንደሚያስፈልጋቸው ተወስቷል።
ምንጭ፦ ኢሳት

Monday, January 20, 2014

ሴት የቢሮ ሠራተኞች እና ተማሪዎች በወሲብ ንግድ ኑሮአቸውን ይደጉማሉ


“የአዲስ አበባ ተማሪዎች ለከፍተኛ የስነ ምግባር ጉድለት ተጋልጠዋል”
ተማሪዎች ያለዕድሜያቸው ጫት፣ ሲጋራና ልቅ ወሲብ ይጀምራሉ ሴት የቢሮ ሠራተኞች እና ተማሪዎች በወሲብ ንግድ ኑሮአቸውን ይደጉማሉ
በአዲስ አበባ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች፤ ለከፍተኛ የስነ ምግባር ጉድለቶች እንደተጋለጡ ጥናቶች አመለከቱ፡፡ ሰሞኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር “ስነምግባር ለእድገት ሁሉ መሠረት ነው” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በቀረቡት ጥናቶች በተለይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፤ በየትምህርት ቤቶቹ አካባቢ ባሉ ህገወጥ የአልኮል፣ የአደንዛዥ እጽ መጠቀሚያ እና የወሲብ ፊልሞች ማሣያ ቤቶች መበራከት የተነሣ ለችግሩ ተጋላጭነታቸው በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ተጠቁሟል፡፡ አብዛኞቹ ተማሪዎች ወሲብ መፈፀም የሚጀምሩት በዚሁ የትምህርት ደረጃ ላይ እያሉ ነው ተብሏል፡፡ ከጥናት አቅራቢዎቹ አንዷ የሆኑት ወ/ሮ ጽዮን አክሊሉ በጥናታቸው እንዳመለከቱት፤ ተማሪዎች ሲጋራ፣ የአልኮል መጠጥ፣ ጫት እና ልቅ ወሲብ የሚጀምሩት በአብዛኛው ሁለተኛ ደረጃ ከገቡ በኋላ ሲሆን 41.5 በመቶ የሚሆኑት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ ሲጋራ ማጨስ እንደሚጀምሩ ጠቅሰው፤ 67.1 በመቶ ያህሉ ደግሞ በዚህ የትምህርት ደረጃ ወሲብ መፈፀም ይጀምራሉ ብለዋል፡፡
18.1 በመቶ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎችም ያለ እድሜያቸው በሲጋራ ሱስ የሚጠመዱ ሲሆን 20.6 በመቶዎቹም በዚህ የእድሜ እርከን ውስጥ ወሲብ መፈፀም እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል፡፡ የአልኮል መጠጥ እና የጫት ተጠቃሚነትን መጠን በተመለከተ ከሌሎች የትምህርት ደረጃዎች ይልቅ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በከፍተኛ ደረጃ የድርጊቱ ጀማሪዎችና አዘውታሪዎች እንደሆኑ ጥናቱ ይገልፃል፡፡ በጥናቱ ከተካተቱ ተማሪዎች መካከል 51.4 በመቶዎቹ የአልኮል ተጠቃሚነትን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ የጀመሩ ሲሆን፤ 27.2 በመቶዎቹ ደግሞ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ ጀምረዋል፡፡ 44.6 በመቶ የሚሆኑት ጫት የጀመሩት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ ሲሆን፤ 15.1 በመቶዎቹ ደግሞ የ1ኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ መጀመራቸው ታውቋል፡፡ በተለይ የአንደኛ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በከፍተኛ መጠን ያለእድሜያቸው ለአጓጉል ድርጊቶች መጋለጣቸው፣ በስነምግባር የታነፁ ዜጐችን በማፍራት ረገድ አገሪቱ ፈታኝ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ አመላካች ነው ብለዋል - ጥናት አቅራቢዋ፡፡ እጽና አልኮል መጠቀም፣ ልቅ ወሲብ ከመፈፀም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ያመላከቱት አጥኚዋ፤ በተለይ ለችግሩ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑት የከተማ ልጆች ሲሆኑ ወላጆቻቸው የተማሩ የሚባሉና ከፍ ያለ የገንዘብ አቅም ያላቸው እንደሆኑ ጠቅሰዋል። ከገጠር አካባቢ የሚመጡ ተማሪዎች በአንፃሩ የገንዘብ አቅማቸው አነስተኛ በመሆኑ፣ አልኮልና እፆችን እንዲሁም የወሲብ ተግባራትን እንደልባቸው ለመፈፀም እንደሚቸገሩ ተጠቁሟል፡፡
በእነዚህ የትምህርት ደረጃዎች ያሉና የአቻ ግፊት ሳይበግራቸው ከእነዚህ ሁሉ ሱሶች ነፃ ሆነው የተገኙት ለስነ ምግባራቸው መታነጽ ምክንያቱ፣ በወላጅ ምክር ያደጉና የሃይማኖት ጥንካሬ ያላቸው መሆኑን ያመለከቱት ጥናት አቅራቢዋ፤ የሃይማኖት ተቋማት በዚህ ረገድ ጠንካራ ስራ ለመስራት ቢሞክሩ የበለጠ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡ በእኚሁ ጥናት አቅራቢ የቀረበው ሌላው ርዕሰ ጉዳይ በጐልማሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን በሀገራችን ከ150ሺህ በላይ ሴተኛ አዳሪዎች እንዳሉ ቢገመትም በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ሴት የቢሮ ሠራተኞች እና ተማሪዎች በወሲብ ንግድ ተሰማርተው በአቋራጭ ተጨማሪ ገቢ እያገኙ ኑሮአቸውን እየደጐሙ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ለዚህ ልማድ መስፋፋት ደግሞ ባለሃብቶችና በእድሜ የገፉ ሰዎች አማጋጭ እየሆኑ መምት፣ የመዲናዋ የቱሪስቶችና ዓለማቀፍ ክንውኖች ማዕከልነቷ ማደጉና የጥበብ ውጤቶች ስለ ወሲብ የተዛባ አመለካከት ይዘው ብቅ ማለታቸው በምክንያትነት ተቀምጧል፡፡ ማሣጅ ቤቶችና ራቁት የዳንስ ቤቶች ወሲብ ንግድ መስፋፋቱ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውም በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡
ለእነዚህ ሁሉ የስነምግባር ጉድለቶችና ማህበረሰባዊ እሴቶች ውድቀት የህግ ክፍተት መኖሩ ትልቅ ሚና እንዳለው ባይካድም፣ በመንግስት ሚዲያዎች ሳይቀር የሚተላለፉ የማስታወቂያ መልዕክቶች፣ የቃላት አመራረጥና የፕሮግራም አቅራቢዎቹ አለባበስ፣ የመረጃዎች ፍሬ ሃሳብ እና ስነ ምግባር የጐደላቸው ጽሑፎች በስፋት መስተናገድ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ተብሏል፡፡ ሌላው ጥናት አቅራቢ አባ በአማን ግሩም የተባሉ የሃይማኖት አባት በበኩላቸው፤ ከቤተሰብ እስከ አገር አቀፍ ደረጃ የመከባበር እሴት መጥፋት፣ ማታለልና ሙስና መስፋፋት ለትውልዱ በስነምግባር አለመታነጽ እንደምክንያት ካቀረቧቸው መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ ይሄን ለመቀየር ከሃይማኖት መሪዎችም ሆነ ከመንግስት የስራ ሃላፊዎች የአርአያነት ተግባር እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት አባ በአማን፤ እነዚህ አካላት የትውልዱን ስነምግባር በማነጽ ረገድ ያላቸው ሚና እንዲጐላ ቢደረግ መልካም ነው ብለዋል፡፡ ምቀኝነት፣ ውሸት፣ ሃሜት፣ ስርቆት፣ ሙስና፣ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ አስገድዶ መድፈር፣ የአደንዛዥ እፅ ዝውውርና ተጠቃሚነት እንዲሁም ሽብርና ጦርነት በዓለም ላይ መበራከታቸው ለስነምግባር እሴቶች መጓደል ምክንያት መሆኑን የዘረዘሩት ሌላው ጥናት አቅራቢ ሐጂ አብዱልሃማድ አቡበከር፤ መንግስት እና የሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም ማህበረሰቡ በጋራ ኢትዮጵያውያን ወጣት ተማሪዎች ከእነዚህ የስነምግባር ጉድለቶች የሚርቁበትን አቅጣጫ ማሳየት እንደሚገባቸው አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ የከተማው የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዲሳሞ ኦቶሬ በበኩላቸው፤ ተማሪዎችን ከአልኮል፣ አደገኛ እጽ፣ ጫት እና ከወሲብ ሱስ ተጋላጭነት የራቁ ለማድረግ ቢሮአቸው የተለያዩ የድርጊት መርሃ ግብሮችን ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆንም፣ ለእነዚህ መጤ ልማዶች መስፋፋት ምክንያት የሆኑ የንግድ ቤቶች ከትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚርቁበትን የወሰን መጠን የሚያስቀምጥና ህጋዊ ክልከላ የሚያደርግ ህግ እየተረቀቀ እንደሆነ በቢሮው ሃላፊዎች ተገልጿል፡፡
AddisAdmassNews.com

“ነፃነታችንን መልሱልን!?”



ከተመስገን ደሳለኝ

የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ‹መዝገበ ቃላት› ለነፃነት የሚሰጠው ትርጓሜ ‹አራምደዋለሁ› ከሚለው ግራ-ዘመሙ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ብያኔ አንፃር የሚተነተን በመሆኑ፣ የየትኛውም ተቋም ነፃ ሆኖ የመንቀሳቀስ መብት ላይ ረዣዥም እጆቹን ደጋግሞ እየጫነ ሲጨፈልቅና ሲያስጨፈልቅ ለመኖሩ በርካታ ማሳዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ይሁንና ከብዙዎቹ መሀል ለጊዜው የእምነት ተቋማት የነፃነት ወሰን እስከ ምን ድረስ ነው? የሚለውን ተጠየቅ በተለይም ከሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች (ክርስትና እና እስልምና) አንፃር ተራ በተራ ከፈተሽን በኋላ ተቋማቱን ከእንዲህ አይነቱ ወደ ቅርቃር ከሚገፋ ፈተና የሚታደጋቸውን ብቸኛ የመውጫ መንገድ ለማስታወስ እሞክራለሁ፡፡

‹‹እስልምናን መቆጣጠር››

ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ገዥው ፓርቲ እስልምናን ሙሉ ለሙሉ የመቆጣጠር እቅዱን ዳር ለማድረስ ያልፈነቀለው ድንጋይ፣ የአልማሰው ሥር እንዳልነበር ጥቂት የማይባሉ ምልክቶችን አይተናል፡፡ ለምሳሌነትም የቅርቡ በተለምዶ ‹‹የአወሊያ ንቅናቄ›› ተብሎ የሚጠቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ በቂ ይመስለኛል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ (ንቅናቄ) ለመጀመሪያ ጊዜ አደባባይ የወጣው፣ መንግስት የእምነት ተቋሙን በማያፈናፍን መልኩ ለመቆጣጠር በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ፊት-አውራሪነት ያለአንዳች ይሉኝታ (የብዙሃኑን የእምነቱ ተከታዮች ይሁንታ ሳያገኝ) ‹‹አህባሽ›› የተሰኘ አስተምህሮ በድፍረት ለመጫን ከሞከረባቸው ጊዜያት አንስቶ ባደረጋቸው ተከታታይ ጣልቃ-ገብነቶች ሳቢያ ነው ወደሚል ድምዳሜ ከሚያደርሱን ምክንያቶች ዋነኛው ሆኖ ይነሳል፡፡ ለመንደርደሪያነት ያህልም የተቃውሞውን ጅማሮ በአዲስ መስመር በጨረፍታ እንዳስሰው፡፡
…ለንቅናቄው መነሾ የሆነው በወቅቱ የመጅሊሱ የአመራር አባል የነበሩት ጀማል መሀመድ፣ ለእምነቱ ብቸኛ የሆነውን ሚሲዮናዊ አወሊያ ትምህርት ቤትን በተመለከተ ታሕሳስ 21 ቀን 2004 ዓ.ም ላይ የላኩት ደብዳቤ ነው፤ የደብዳቤው ጭብጥም በርካታ የመስጂድ ኢማሞች፣ መምህራን እና የአረብኛ ተማሪዎች መባረራቸውን የሚያረዳ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡

የመጅሊስ አመራርን ‹ፖለቲካዊ ክንድ› ፈርጣማነት በሚያሳብቅ መልኩ የተሰናዳው ይህ ደብዳቤ የቀሰቀሰው ቁጣ፣ ሕዝበ-ሙስሊሙ ለዓመታት አምቆት የነበረውን ብሶት ሊያፈነዳና በርካታ የመብት ጥያቄዎቹን እንዲያነሳ መግፍኤ ይሆናል ብሎ አስቀድሞ የገመተ ያለ አይመስለኝም፤ የሆነው ግን ይህ ነበር፡፡ የእምነት ነፃነት እንዲከበር ሶስት መሰረታዊ ጭብጦችን የያዙት ጥያቄዎችም፡- ‹‹የመጅሊስ አመራሮች አይወክሉንምና ወርደው አዲስ ምርጫ ይካሄድ››፣ ‹‹አህባሽን በምእመኑ ጫንቃ ላይ በግዴታ ለመጫን የሚደረገው ሙኩራ ይቁም›› እና ‹‹አወሊያ ከመጅሊስ ወጥቶ በገለልተኛ ቦርድ ይተዳደር›› በሚል ስር የሚጠቃለሉ ናቸው፡፡ የኋላ ኋላም በአገዛዙ ‹‹እስላማዊ መንግስት በሽብር ተግባር ለመመስረት›› ወደሚል ተምኔታዊ ውንጀላ የተቀየሩት እነዚሁ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡

በርግጥ ‹‹አህባሽ››ን ተከልሎ የመጣው መንግስታዊ ጫና ዋነኛ ዓላማው (ከአንዳንድ የምዕራብ ሀገራት ፍላጎት ባሻገር) አስተምህሮውን ተገን አድርጎ ምእመኑን እርስ በርስ በመከፋፈል፣ የተቋሙን ነፃነት በቀላሉ ለመጋፋት የሚያስችለውን መደላድል መፍጠር ነው፡፡ ይሁንና ስልቱ ምንም እንኳ ከሃሳቡ ተጋፊዎች አንጻር አነስተኛ ቢሆንም፣ መንገድ ጠራጊ ደጋፊዎች ሊያስገኝለት መቻሉን መካድ ግን መሬት ካለው እውነታ ጋር እንደ መላተም ይቆጠራል፤ ምክንያቱም የመጅሊሱ አመራር ሙሉ በሙሉ ከአገዛዙ ጎን በመቆም አጀንዳው ቅቡል እንደሆነ ለማስመሰል የማይናቅ አስተዋጽኦ አድርጓልና፡፡

ይህም ሆኖ አብዛኛው የእምነቱ ተከታይ በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ ተቃውሞ በተነሳበት እዛው አወሊያ ግቢ ተሰባስቦ፣ ከሰባት መቶ ሺህ በላይ የውክልና ፊርማ በማሰባሰብ፣ አስራ ሰባት አባላት ያሉት አንድ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አዋቅሮ ሲያበቃ ከላይ የተጠቀሰውን ሕገ-መንግስታዊ የመብት መከበር ጥያቄውን መልክ አስይዞ መታገሉ ብዙም አላዳገተውም፡፡ እነሆም በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች ሕዝበ-ሙስሊሙን ከጎኑ በማሰለፍ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ እስከተከበረው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ድረስ በየመስጊዶቹ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለጥያቄዎቹ ሁነኛ መልስ ይሰጠው ዘንድ ከፍተኛ የተቃውሞ ትግል አድርጓል፤ በተጨማሪም የኮሚቴው አባላት ከተመረጡ ከስምንት ወራት በኋላ (ሐምሌ 10/2004 ዓ.ም) በግፍ መታሰራቸው ሳያንበረክከውና ሳይከፋፍለው፤ ይከተለው ከነበረው ሰላማዊ መንገድ ውልፍት ሳይል ለተራዘመ ጊዜያት መቀጠሉ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የታሪክ ገፅ ላይ አዲስ አሻራውን ለማሳረፈ ያስቻለው ይመስለኛል፡፡


አህአዴግአዊ ‹ህቡዕ መዳፍ›…

አገዛዙ በግልፅ የሚታየውን መጅሊስ፣ በማይታይ ስውር ‹መዳፉ› ልጓም ጨብጦ እየጋለበ በኃይማኖታዊ ተቋሙ ላይ በስፋት ጣልቃ መግባቱን የምንረዳው ‹‹መፍትሄ አፈላላጊ›› ተብለው የተመረጡትን የኮሚቴውን አባላት አንድ በአንድ ለቅሞ ወህኒ ቤት ከወረወረ በኋላ፣ የከሰሰበትን የመወንጀያ ጭብጥ እና እንዲከላከሉ የወሰነበትን የማስረጃዎች ይዘት ስንመረምር ነው፡፡
በርግጥ ሁሉም የተከሰሱት በፀረ-ሽብር ሕጉ ሲሆን፣ ከውሳኔው በኋላም አንዳንድ አንቀጾች ከመሻሻላቸው በቀር ምንም የረባ ለውጥ አልታየም፡፡ ይሁንና መንግስት ገና ከመነሻው (ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ) በኮሚቴው አባላት ላይ የተለያዩ ‹ዶክመንተሪ ፊልሞች›ን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በማስተላለፍ የወንጀለኛነት ብያኔ እና የማጠልሸት ቅስቀሳ አድርጎባቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላም (ጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም) ‹‹ጥፋቶች›› ያላቸውን አራት ጭብጦች በመዘርዘር መደበኛ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡ የክሱ ይዘትም ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው ተጠቃሎ ሊቀርብ ይችላል፡-

‹‹…‹መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ› በሚል እርስ በእርስ ተመራርጠው ሲያበቁ ከጥር 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ሁሌ በየሳምንቱ አርብ ለፀሎት አወሊያ መስጊድ ለሚሰበሰበው ሕዝብ የሽብር ዓላማቸውን ለማራመድ በአዲስ አበባ እና በክልሎች ባዘጋጁት የሰደቃ እና የአንድነት ዝግጅቶች ለሚጠሩት ሕዝብ፣ በማሕበራዊ ድህረ-ገፆች፣ ለዚሁ ትግበራ በተቋቋሙት የተለያዩ ኃይማኖታዊ መገናኛ ብዙሀን፣ በመፃህፍት፣ በበራሪ ፅሁፎችና ዘጋቢ ፊልሞች አማካኝነት… የመጨረሻ ግባቸው የሆነውን እስላማዊ መንግስት ለመመስረት የሙስሊሙ ሕዝብ ቁጥር ከ80 በመቶ በላይ ነው በማለት ለሽብር ተግባር ቀስቅሰዋል፤ አነሳስተዋል፡፡››

ጉዳዩንም በዝግ ችሎት ሲመለከት የነበረው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከአንድ ወር በፊት (ታሕሳስ 3 ቀን 2006 ዓ.ም) የሰጠው ውሳኔ በሶስት የተከፈለ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የመጀመሪያው አቡበከር መሀመድ፣ አህመዲ ጀበል፣ ያሲን ኑር እና ካሚል ሸምሱን ጨምሮ አስራ አራት ሰዎች ያሉበት ሲሆን፣ ከተከሰሱበት የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ አንቀጽ 32(1)(ሀ)(ለ) እና 38(1) መካከል፣ በአንቀጽ 32(1)(ሀ) እንዲከላከሉ ተወስኗል፤ በተጨማሪም ‹‹በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3(1)(2)(4)(6) እና አንቀጽ 4 ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ›› ከሚለው ደግሞ አንቀጽ 3 ቀርቶ በአንቀጽ 4 ተመሳሳይ የተከላከሉ ብይን ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ሁለተኛው ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸውን ጨምሮ አራት ሰዎችን የሚመለከት ሲሆን፤ እነርሱም ከእነ አቡበክር ክስ ጋር የተጠቀሰባቸው የወንጀለኛ መቅጫ አንቀጾች ሁሉም ውድቅ ሆነው በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀፅ 7(1) ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡ ሶስተኛው የአቶ ጁነዲን ሳዶን ባለቤት ወ/ሮ ሀቢብ መሀመድ እና ሁለት የበጎ አድራጎት ድርጅትን ጨምሮ አስራ ሁለት ተከሳሾች ያሉበት ሲሆን፣ የተላለፈው ውሳኔም በነፃ መሰናበታቸውን የሚገልፅ ነው፡፡

‹‹ማስረጃ›› ፍለጋ…

ከክሱ ጀርባ ረጅሙ የመንግስት እጅ መኖሩን የሚያመላክተው ‹‹ጥፋተኛ›› በተባሉት ተከሳሾች ላይ የቀረበው ‹‹ማስረጃ›› ነው፡፡ እንዲያ ስርዓቱን በኃይል አፈራርሰውና ሌሎች ኃይማኖታዊ ተቋማትን ጨፍልቀው ‹‹እስላማዊ መንግስት›› ሊመሰርቱ ወጥነው ሲንቀሳቀሱ እጅ ከፈንጅ ለመያዛቸው በበቂ ሁኔታ ያስረዱልናል ብለው የጠቀሷቸው ‹‹ማስረጃዎች›› በጠቅላላ የሚከተሉት ናቸው፡- ‹ሁሉም ታሳሪዎች ለፖሊስ ሰጡ የተባለው የእምነት-ክህደት ቃል፣ ዓቃቢ-ሕግ ሰብስቦ ያቀረባቸው የሰው ምስክሮች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ላፕቶፖች፣ ሲዲዎች፣ በራሪ ወረቀቶች፣ ጭልፋና የወጥ-ድስቶች…›፤ በቃ! በአናቱም ‹‹የሙስሊሙ ቁጥር ከሀገሪቱ ሕዝብ ሰማኒያ በመቶውን ይይዛል ብለዋል›› የሚለው ክስ ተራ አሉባልታ መሆኑን ለማስረገጥ፣ ራሳቸው የኮሚቴው አባላት መጋቢት 2004 ዓ.ም ለቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ከፃፉት ደብዳቤ ውስጥ የሚከተለውን አንቀጽ ብቻ መጥቀሱ በቂ ነው፡-
‹‹…እንደሚታወቀው የሃገሪቱን ሰላሳ ሶስት በመቶ የሚሆነውን የሕብረተሰብ ክፍል የሚወክለው የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ም/ቤት (መጅሊስ) ተገቢው ሕጋዊ ሰውነት የለውም…››

እናሳ! ዓቃቢ-ሕግጋኑ 80 በመቶን ከየት አምጥተው ይሆን? …በርግጥ አቶ መለስ ዜናዊ ‹‹መረጃ እንጂ ማስረጃ የለንም›› እንዲል ገዥው ፓርቲ በእነዚህ የ‹‹ሽብር›› ማስፈፀሚያ ቁሳቁሶች ነው መንበረ-መንግስቱን ከመገልበጥም ሆነ ሀገሪቱን ከኃይማኖታዊ ስርዓት ለጥቂት ታድጌያታለሁና ወንዶች በጭብጨባ፣ ሴቶች በእልልታ አመስግኑኝ የሚለው፡፡
የክሱን ልብ-ወለድነት በአመክንዮ ለማስረዳት ከ‹‹ማስረጃዎቹ›› ውስጥ ሁለት ጉዳዮችን ብቻ መምዘዙ ይበቃናል፡፡ ተከሳሾቹ ለፖሊስ በምን ሁኔታ ቃላቸውን እንደሰጡ እና የአንድ ምስክር እማኝነትን (ምንም እንኳ ችሎቱ በዝግ የተካሄደ በመሆኑ የሁሉንም የሀሰት መስካሪነት ሙሉ ለሙሉ ማጋለጥ ባይቻልም፣ ዳኞቹ ራሳቸው ባሳለፉት ውሳኔ ላይ የተጠቀሰው የአንድ የምስክር ቃል ይህንን መከራከሪያ ያስረግጥልናል)

የመርማሪዎቹ ‹‹ችሎታ››…

የጥፋተኝነታቸው ማሳያ የሆነው የኮሚቴው አባላት ለፖሊስ የሰጡት ቃል ተብሎ በሰነድነት የቀረበው በድምሩ 413 ገፅ ሲሆን፤ ይህ ምርመራም በምን መልኩ እንደተካሄደ በቅርቡ ታሳሪዎቹ በተለያዩ ሚዲያዎች ባሰራጩት ደብዳቤ ላይ የፍትሕ ስርዓቱን ገመና እና በዚች አገር ሰብዓዊ መብቶች ምን ያህል ዋጋ እንዳጡ ልብ የሚሰብሩና በድንጋጤ ዓቅል የሚያስቱ መከራዎቻቸውን ጭምር በመዘርዘር ነግረውናል፡፡ በደብዳቤው ላይ ዓቃቢ-ሕግ ክስ መመስረቻ ያደረገውን ቃላቸውን ፖሊሶቹ ፈልፍለው የደረሱበት የመርማሪነት ‹‹ጥበብ››ን እንዲህ በማለት ነበር የገለፁት፡-

‹‹…በማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊ እና አካላዊ ስቃይ ደርሶብናል፡፡ ከአስራ አራት ሰዓታት በላይ ያለ እረፍት ቀጥ ብለን እንድንቆም በማድረግ፣ ጀርባችን እስኪላጥ ራቁታችንን በሽቦ በመግረፍ፣ በሰንሰለት በማሰር እና አይናችንን በጨርቅ በመሸፈን የውስጥ እግራችን እስከሚላጥ ገልብጦ በመግረፍ፣ ቀንና ማታ አሰቃቂ በሆነ ምርመራ እና በድብደባ ብዛት እንቅልፍ በመንሳት፣ ፂማችንን በመንጨትና እንድንላጭ በማስገደድ፣ ከአቅም በላይ የሆነ ስፖርት በግድ በማሰራት፣ ብልት በመግረፍ፣ ‹ልጅህን እንገድለዋለን! ሚስትህን አስረን በፊትህ ቶርች እናደርጋታለን! ብልትህ ላይ የውሃ ሃይላንድ በማንጠልጠል መሀን እናደርግሀለን!› እያሉ በማስፈራራት ከፍተኛ የሆነ እንግልትና ስቃይ አድርሰውብናል፡፡ …በክረምት ቀርቶ በበጋ እንኳ ቅዝቃዜው በማይቻለው ‹ሳይቤሪያ› ተብሎ በሚጠራው ጨለማ ክፍል አጉረውናል፡፡ መቋቋም የሚያዳግተውን የማሳቃያ ስሌታቸውን በመጠቀም ያላሰብነውንና ያልሰራነውን ‹እመኑ! ተናገሩ! ፈርሙ!› ብለው አስገድደውናል፡፡››

ወደድንም ጠላንም የሀገራችን እውነተኛ ገፅታ ይሄ ነው፡፡ በአናቱም ታሳሪዎቹ የደረሰባቸውን ግፍና መከራ የሚያረጋግጡልን ገፊ-ምክንያቶች፣ የመጀመሪያው ከዚህ ቀደም የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት እና የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ድርጅቶች ማዕከላዊን በተመለከተ ያወጧቸው ሪፖርቶች ሲሆን፤ ሁለተኛው ታሳሪዎቹ ራሳቸው ይህንኑ የጭካኔ ተግባር በዝርዝር ጠቅሰው በመርማሪ ፖሊሶቹ ላይ በፍርድ ቤት ክስ መስርተው የነበረ መሆኑ ነው፤ ሶስተኛው ደግሞ መንግስት ‹ጅሃዳዊ ሀረካት› በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ‹ዶክመንተሪ ፊልም› በድጋሚ እኩለ ሌሊት ላይ በተላለፈበት ወቅት የማዕከላዊ መርማሪዎች የኮሚቴው ሰብሳቢ የሆነውን አቡበከር መሀመድን እጁን በሰንሰለት የፊጥኝ አስረው ሰብዓዊነቱን በሚያንቋሽሽና መንፈሱን በሚያሸማቅቅ ሁናቴ ቃሉን ሲቀበሉ በቴሌቪዥን መስኮት መመልከታችን ነው፡፡

የዓቃቢ-ሕግ ምስክር ሲባል…

ለዚህ ሙግት ማሳያ የማደርገው ከዓቃቢ-ሕግ ምስክሮች መሀል አንዱ የሰጠውን የምስክርነት ቃል ነው፤ ይህ ግለሰብ በ21ኛ ተከሳሽ ሼኽ ጣሂር አብዱልቃዲር መኖሪያ ቤት ሽጉጥ ከነጥይቱን ጨምሮ የተለያዩ ማስረጃዎች በብርበራ ሲገኝ መመልከቱን በችሎቱ ፊት በፈጣሪው ስም ምሎ ተናግሯል፤ የሚገርመው ነገር ግን ይህ አይደለም፤ ዳኞቹ በሰጡት ውሳኔ ላይ እንደሚከተለው ማለታቸውን መስማታችን እንጂ፡-

‹‹እነዚህ ማስረጃዎች (ሽጉጡም ጨምር) አልቀረቡም፤ ዓ/ሕግም በማስረጃ ዝርዝርና በሰነድነት አልጠቀሳቸውም፤ ሌላ ማስረጃም አልቀረበም፡፡››

እንግዲህ በዝምታ ተገርሞ ከማለፍ በቀር ‹ታዲያ ምስክሩ ከየት አምጥቶ ነው ስለመሳሪያው የዘባረቀው?› የሚል ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም፤ ቢቀርብም አጥጋቢ መልስ አይገኝለትም፤ ለምን ቢሉ ሀገሪቱ ኢትዮጵያ ነቻ!! ያውም ኢህአዴግ በብረት መዳፉ ጨፍልቆ የሚገዛት ምስኪን ሀገር፡፡ ...መቼም ይህ ተጨባጭ እውነታ እንዲህ ገሀድ መውጣቱ በዚህ ፀያፍ ተግባር ውስጥ የቀጥታ ተሳትፎ ያልነበራቸውን የገዥው ፓርቲ አመራርንም ሆነ አባላትን ጭምር የአትንኩኝ ባይነት ንዴት ይቀሰቅስ እንደሆነ እንጂ፣ ስለሕገ-መንግስት፣ ሕሊና፣ ሕዝብና አገር በድፍረት መናገር (ጥብቅና መቆም) የሚችሉበት ሞራል ይኖራቸዋል ብሎ ማሰብ ተላላነት ነው (በነገራችን ላይ የሀገሬ የፍትሕ ደጆች እንዲህ የዘቀጡ መሆናቸው ሲጋለጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በድህረ-ምርጫ 97ም የፈጠራ ማስረጃዎች እና ሓሳዊ ምስክሮች ምን ያህል ነግሰውበት እንደነበረ ታይቷል፡፡ የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ‹‹የቃሊቲው መንግስት›› እና የአንተነህ ሙሉጌታ ‹‹የተዋረደው ፍርድ ቤት›› መፃህፍት ሂደቱን በቦታው የነበርን እስኪመስለን ድረስ በውብ ቋንቋ ከሽነው በዝርዝር ተርከውልናል)

ከቤተ-ክህነት ጀርባ…

በርግጥ ከቤተ-ክህነት ‹የእምነት ነፃነት ይከበር!› ጥያቄ ጋር በቀጥታ ተያይዞ ለአስከፊው የቃሊቲ ማጎሪያ የተዳረጉ መንፈሳውያን መሪዎች እስካሁን የሉም፡፡ ይህ ግን የአገዛዙ ‹እርኩስ መንፈስ› በደጆቿ ዙሪያ አልረበበም እንደማለት አይደለም፡፡ ፓትሪያርክን አባርሮ ሌላ መሾም፣ እነአቦይ ስብሃትን የመሳሰሉ የፓርቲው አንጋፋ መሪዎች በአደባባይ ‹‹አንድም ከመንግስት ነፃ የሆነ ጳጳስ የለም!›› ከማለት አልፈው፣ ‹‹ነፃ የሆነ ጳጳስ ካለ እሸልመዋለሁ›› እስከሚለው ተሳልቋቸው ድረስ ያሉ ማረጋገጫዎች የሚያሳዩት የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ነውና፡፡ በተለይም በያዝነው ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ወራት ውስጥ ብቻ በቤተ-ክህነቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የገባውን ስውር እጅ እና የእምነቱን የአስተምህሮ መንገድ፣ ከኑፋቄው በመለየትም ሆነ በተለያዩ መንፈሳዊ ተግባሮቹ ስመ-ገናና የሆነውን ‹‹ማህበረ ቅዱሳን›› ላይ የተሸረበውን መንግስታዊ ተንኮል ‹‹ቀጣዩ የኢህአዴግ ዒላማ ማህበረ ቅዱስን ይሆን?›› እና ‹‹ኢህአዴግና የኃይማኖት ነፃነት›› በሚሉ ፅሁፎች እዚሁ መፅሄት ላይ ቀደም ሲል በስፋት ስላወሳናቸው ዛሬ መድገሙ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ ይሁንና ጣልቃ ገብነቱን የሚያመላክቱ ሁለት አዳዲስ ማሳያዎችን የአጀንዳውን ተጠይቅ ለማጠናከር እጠቅሳቸዋለሁ፡፡

ወረራ-ሲኖዶስ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢህአዴግ ለ‹‹አውራ ፓርቲ››ነቱ ዋስትና የእምነት ተቋማትንም በ‹መንፈሳዊ ክንፍ›ነት ከጎኑ የማሰለፍ ግዴታ ውስጥ የከተተው ይመስል፣ ከፍተኛ ባጀት መድቦና ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት እንደሆነ መታዘብ ይቻላል፡፡ ባሳለፍነው ወርሃ ጥቅምት መደበኛው የሲኖዶሱ ጉባኤ በተደረገበት ወቅት፣ ለመጪው ግንቦት አጠናቅቀው እንዲያዘጋጁ ኃላፊነት ለሰጣቸው አራት አባላቱ ያስተላለፈው ውሳኔ፡- ‹‹ዘጠኝ እጩ ጳጳሳትን መልምላችሁ አቅርቡ!›› የሚል ነበር፡፡ ሆኖም ከቤተ-ክህነት ምንጮቼ ባገኘሁት መረጃ፣ መንግስት የፊታችን ግንቦት ወር በሚደረገው ጉባኤ ላይ ሹመታቸው ፀድቆ በቀጥታ የሲኖዶሱ አባል መሆን በሚችሉት ዘጠኙ ጳጳሳት ምልመላ ላይ ረዥም እጁን እየከተተ መሆኑን ነው፡፡

እንደሚታወሰው ነባሩ የቤተ-ክህነት የጳጳሳት የአመራረጥ መስፈርት የሚከተሉት ናቸው፡- ‹‹በምንኩስና የኖረ (ትዳርም ልጅም ያሌለው)፣ መንፈሳዊውንም ሆነ ዓለማዊው ትምህርቱን በሚገባ ያጠናቀቀ፣ ከአንድ በላይ ቋንቋ መናገር የሚችል፣ እውነትና ሀሰትን የማይናገር፣ አስካሪ መጠጥ የማይጠጣ፣ እድሜው ሃምሳ ዓመት የደረሰ፣ በሚያገለግለበት ቦታ ምስጉን መሆኑ የተረጋገጠ…፡፡›› ይሁንና ጀግናው ኢህአዴግ ደግሞ የፖለቲካ ታማኝነትን በተጨማሪነት ለመክተት ‹አክራሪ ያልሆነ› እና ‹ልማታዊ የሆነ› በሚሉ ሁለት መስፈርቶች ሸፋፍኖ በለመደው ስውር እጁ ተፅእኖ በማድረግ በሲኖዶሱ ውስጥ ያለውን ጉልበት ለማጠናከር እየሞከረ እንደሆነ ማረጋገጤ ለተጠየቁ እንደ አንድ ማሳያ ሊወሰድ ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡

የለውጡ አንድምታ…

ከወራት በፊት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ሆነው በሲኖዶሱ የተሾሙት አቡነ እስጢፋኖስ፣ በአቡነ ቴውፍሎስ ዘመን ፀድቆ ይሰራበት የነበረውን ‹ቃለ-አዋዲ› ለማሻሻል ይሁን ለመሻር ባይታወቅም አዲስ ጥናት አጥንቶ እንዲያቀርብላቸው ኃላፊነቱን ለማህበረ ቅዱሳን ይሰጣሉ፡፡ ማህበሩም በአጭር ጊዜ ውስጥ ‹‹የአዲስ አበባ የሀገረ-ስብከት የአደረጃጀትና አሰራር ለውጥ ጥናት›› በሚል ርዕስ የቤት ስራውን አጠናቅቆ ያቀርባል፡፡

ነገር ግን የመዋቅርንና የአሰራር ለውጥን ጨምሮ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለበት ዘመናዊ የፋይናንስ ስርዓት እንደተካተተበት የተነገረው የጥናቱ ረቂቅ መሰናዳቱን ተከትሎ ገና ከአሁኑ ከአንዳንድ የደብር አስተዳዳሪዎች ዘንድ ከባድ ተቃውሞ እየደረሰበት ነው፡፡ እንደ ምንጮቼ መረጃ ሁናቴው በጊዜ መፍትሄ ካልተበጀለት ሀገረ-ስብከቱንም ሆነ የደብር አስተዳዳሪዎችን መከፋፈሉ አይቀሬ ነው፡፡

ይህንን ጉዳይ እዚህ ጋ ያነሳሁት የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ያሳያል በሚል ነው፡፡ ይኸውም የጥናቱ ይዘት በወሬ ደረጃ በመናፈሱ ብቻ ‹‹መተግበር የለበትም!›› የሚል ተቃውሞ እያሰሙ ያሉ አንዳንድ ጳጳሳት እና የደብር አስተዳዳሪዎች ‹‹መንግስት ከጎናችን ስለሆነ፣ ከእርሱ ጋር እንነጋገርበታለን››፣ ‹‹ይህ ህግ መፅደቅ የለበትም፣ አለበለዚያ ሪፖርት ለምናቀርብለት አካል ሪፖርት እናደርጋለን››፣ ‹‹አርፋችሁ ብትቀመጡ ይሻላችኋል››፣ ‹‹እርሶንም (አቡነ እስጢፋኖስን) ከሥልጣንዎት እናወርዶታለን››… እና መሰል ማስፈራሪያዎችን አቡኑ ቢሮ ድረስ በመሄድ መናገራቸው ነው፡፡ በጥቅሉ እነዚህ ሁነቶች ስርዓቱ በቤተ-ክህነት የውስጥ አስተዳደር ምን ያህል ጠልቆ እጁን እንደሰደደ ያስረግጡልኛል ብዬ አምናለሁ፡፡

‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ወዴት ተሰወረ?

ባሳለፍነው ሳምንት ሁለተኛ ዓመቱን የደፈነው የሕዝበ-ሙስሊሙ ‹‹የእምነት ነፃነት ይከበር!›› ጥያቄ፣ በተለይም ‹‹መፍትሄ አፈላላጊ›› ተብለው የተመረጡት የኮሚቴ አባላት ለእስር ከተዳረጉ በኋላ የተቃውሞ ንቅናቄው ሲመራ የቆየው ‹‹ድምፃችን ይሰማ!›› የሚል መርህ ባነገቡ አስተባባሪዎች እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ፍፁም ሰላማዊውን እና ሕጋዊውን መንገድ በመከተል የጁምዐን ሶላት እየጠበቁ የኮሚቴው አባላት በአስቸኳይ ከተጣሉበት የስቃይ ጎረኖ እንዲወጡና ያነሷቸው የመብት ጥያቄዎችም ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲመለሱ አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎችም የሀገሪቱ ከተሞች ያስተባበረው የተቃውሞ ድምፅ ዛሬ በቦታው የለም፡፡ በግልባጩ መስጊዶቹ በከባድ ፀጥታ የተመቱ መስለዋል፡፡

ከማሕበራዊ ሚዲያዎች እስከ የእጅ ስልክ መልዕክት መለዋወጫዎች፤ ከበራሪ ወረቀቶች እስከ ፍትህ ሬዲዮ ድረስ ያሉ የመረጃ ማስተላለፊያ ዘዴዎችን እጅግ በሰለጠነ መንገድ ይጠቀም የነበረው የ‹‹ድምፃችን ይሰማ!›› ተቃውሞ፣ በዘንድሮው የዒድ በዓል ወቅት በእምነቱ ተከታዮች ላይ መንግስት ከወሰደው መጠን የለሽ የጭካኔ እርምጃ በኋላ ዳግም አልተከሰተም፡፡ ይሁንና ምንም እንኳ በበዓሉ ዋዜማ አስተባባሪዎቹ የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ለጊዜው ለማቋረጥ መወሰናቸውን ቢያሳውቁም፣ በስርዓቱ የአመራር አባላት ዘንድ ያለው አተያይ ግን ተቃውሞውን በኃይል መቆጣጠር እንደተቻለ ነው፡፡ በርግጥም ይህ አይነቱ የተሳሳተ መደምደሚያ ይመስለኛል የኮሚቴው አባላትን ውሃ በማይቋጥር ክስ ‹‹ጥፋተኛ›› ብሎ እንዲከላከሉ እስከመወሰን ድረስ የልብ-ልብ የሰጠው፡፡

የሆነው ሆኖ አገዛዙ የእስልምና እምነት ተከታዮችን በአህባሽ እና ሓሳዊ ሰባኪያን ከፋፍሎ ለማዳከም ያደረገው ሙከራ ቢከሽፍም፣ ዛሬም የተነሱት ሕጋዊ የመብት ጥያቄዎች መልስ ካለማግኘታቸውም በላይ፣ በእነዛ ፈታኝ ጊዜያት ሚሊዮኖችን ወክለው በድፍረት ከፊት መስመር የተሰለፉት ንፅሃን የኮሚቴው አባላት በእስር እየማቀቁና ለተለመደው የፖለቲካ ፍርደ-ገምድል ውሳኔ እያመቻቿቸው ስለመሆኑ የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› አስተባባሪዎች ይዘነጉታል ተብሎ አይገመትም፡፡ በአናቱም ይህ ሁናቴ እንደ ልጅነት ዘመን፣ የሚታሰረው ታስሮ፣ የሚገደለው ተገድሎ፣ የሚሰደደው ተሰዶ… ሲያበቃ ‹ዳቦ ተቆረሰ፣ ዕቃቃው ፈረሰ› ተብሎ በየፊናችን የምንበታተንበት አይነት ጨዋታ አለመሆኑን ማስታወሱ አግባብ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
የመውጫው መንገድ ኢህአዴግ ያለፉትን ሃያ ሁለት የሰቆቃ ዓመታት በስሁቱ የ‹አብዮታዊ ዲሞክራሲ› ርዕዮተ-ዓለም ብያኔ ሀገሪቱንና ሕዝቧን ለአስከፊ ድህነት፣ ለመራራ ጭቆና ዳርጓል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ባነበረው መከፋፈልና አለመተማመን የሥልጣን ዕድሜውን ያለስጋት ማራዘሙ ተሳክቶለታል፡፡ ጥያቄውም ከዚህ የሚነሳ ቢሆንም፣ ምላሹ በቅርቦቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ከታየው የሙስሊሙ ሰላማዊ የትግል ስልት ጋር የሚተሳሰር ይመስለኛል፤ ምክንያቱም ማንኛውም የመብት ጥሰት የሚያሳስበው ዜጋ ይህን ክቡድ መንፈስ ከመቀላቀል የተሻለ አመራጭ የለውምና (በነገራችን ላይ የኮሚቴው አባላት በቀጠሮ ከሚቀርቡበት የፊታችን ጥር 22 ቀን ጀምሮ ችሎቱ ለታዳሚ ክፍት በመሆኑ ያለአንዳች የኃይማኖት ልዩነት ወደ ፍርድ ቤት በመትመም ከጎናቸው ታላቅ የሕዝብ ደጀን መኖሩን ማሳየቱ መንፈሳቸውን ለማበርታት መልካም አጋጣሚ ነው)

በጥቅሉ ሰማያዊ ነፃነታቸው በፖለቲካ ጉልበት እየተናደ የመጣው የሁለቱ ኃይማኖት ልሂቃንና ተከታዮች ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ የጎንዮሽ መተያየታቸውን ገርቶ፣ የብሔር ልዩነትን አዘልሎ በአንድ አውድ ሊያሰባስባቸው የሚችል ገፊ-ምክንያት አላቸው፡፡ እናም ስርዓቱ እርስ በእርስ በጥርጣሬና በስጋት እንዲተያዩ ለማድረግ በተንሸዋረረ የ‹‹መቻቻል›› ፕሮፓጋንዳ ስም እየዘረጋው ያለውን የረቀቀ ወጥመድ በመሻገር፣ የአደባባይ ተቃውሞዎችን በጋራ በማስተባበር የማያቋርጥ ጫና ፈጥረው ለቤተ-አምልኮዎቻቸው ‹‹ነፃነታችንን መልሱልን!?›› አንገብጋቢ ጥያቄ መፍትሄ ማስገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን የተቀደሰ ዓላማ ከግብ ለማድረስ በተለይም ከ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ውጤታም እንቅስቃሴ ጥቂት ገፆችን በመገንጠል ሰፊ መዋቅር ያለው ‹‹ማሕበረ ቅዱሳን›› ደጋግሞ ቢከልሰው ካለፈ ቁጭት ራሱን መታደግ የሚችልበትን የመውጫ ቀዳዳ ማግኘቱ ብዙ አያለፋውም፡፡
በመጨረሻም ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ከታሳሪዎቹ የኮሚቴው አባላት መካከል አንዱ የሆነው ካሚል ሸምሱ ሐምሌ 8 ቀን 2004 ዓ.ም እንደ ተናገረው ጠቅሶ በማሕበራዊ ድህረ-ገፆች ያሰራጨውን መልዕክት የርዕሰ-ጉዳያችን መደምደሚ ይሆን ዘንድ ወደደሁ፡-
‹‹የዚህች ሀገር ሰላም ፀጥታ ነው፤ ዲሞክራሲን ማስፈን የሚቻለው፤ የሕግ የበላይነትን ማስከበር የሚቻለው በጋራ ነው፤ እኛም የእዛው አካል ስንሆን ነው፤ የአንዱ መብት ተከብሮ የሌላው ተጥሶ ሊሆን አይችልም! አንደኛው የሕገ-መንግስት ክፍል ተከብሮ ሌላኛው ተደፍጥጦ ሊሆን አይችልም! ሰላምን ነው የምንዘምረው! ለሰላም ነው የምንታገለው! ጥያቄያችንን በሰላማዊ መንገድ እንሄድበታለን!››
ኢትዮሚድያ -- Ethiomedia.com
January 19, 2014

Saturday, January 18, 2014

ዛሬ የሚያስፈሯሯችሁን እስከ ዘላለሙ የማትሰሙበት ግዜ ይመጣልና አትፍሩ



ህወሃት የሚያራምደው የዘረኝነት ፖለቲካና፤ የተዘፈቀበት የሙስና አዘቀት ሊወጣ ከማይችልበት አዙሪት ውስት ከተውታል።ከእንግዲህ ወዲህ ለህወሃቶች የቀራቸው አንድ አማራጭ ብቻ ነው። ሁሉንም ዜጎች በዘረኝነት ሰንሰለት አስሮ ቀጥቅጦ እና አፍኖ መግዛት ቀጣዩ ቅዥታቸው ነው።

የዚህ አፍኖ የመግዛት ቅዥታቸው መገለጫም ዜጎች ህወሃት ስለሚፈፅመው ወንጀል ምንም ዓይነት መረጃ እንዳያገኙ ማድረግ አንዱ ነው።ህወሃት የሚፈፅመው ወንጀል ከህዝብ ዓይንና ጆሮ ተሠውሮ እንዲረሳ ይመኛል። ይሄን ምኞቱን እውን ለማድረግም ሌሎች ነፃ ሚዲያዎችን አሸባሪ ማለት ወይም ደግሞ ሌላ የተሰወረ አጀንዳ ያላቸው እያለ ማላዘንን ሥራየ ብሎ ተያይዘውታል። ከሰሞኑ አዲስ አበባ ውስጥ የሚታተሙ ስምንት የግል ህትመቶችን አሸባሪዎች በማለት ክስ መስርተዋል። አስቀድመው ፈርደው ከጨረሱ በኋላ ክስ መመሥረት የህወሃቶች የተለመደ የፍትህ ሥርዓት ነው። በአገሪቷ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ሁኖ የተቋቋመውን ኢሳትንም አሸባሪ እያሉ ሰሚ አልባ ጩኸት እየጮኹ ነው። የኢሳት ቴሌቭዥንና ሬዲዮንን የሚሰማም በአሸባሪነት ይከሰሳል እያሉ በየዜጎች ደጅ እየተንከላወሱ ለማስፈራራት እየሞከሩ ነው።
እኛ ግን እንዲህ እንላለን !!! አትፍሩ ! አትፍሩ ! አትፍሩ ! ኢሳትን ሰምታችኋል ብሎ የሚያስፈራሯችሁን ለዘላለሙ የማትሰሟቸው ግዜ እየመጣ ነው። የነፃነት ጎህ ቀዶ ሁላችን የፈለግነውን ሰምተን፤ ያልፈለግነውንም የምንተውበት ዘመን እሩቅ አይደለም። ግንቦት ሰባት የፍትህ የነፃነት እና የእኩልነት ንቅናቄም የተቋቋመው ዜጎች ያለማንም ጣልቃ ገብነት የወደዱትን ወስደው፤ የጠሉትን መተው የሚችሉበትን መንገድ ለማመቻቸት ነው። ዘረኞቹ በደምና አጥንት ታውረው ጭካኔን ከጀግንነት ቀላቅለው እኛ ብቻ ወንድ ባሉበት መንደር ሌላ ጀግና ኢትዮጵያዊ ወንድ ገስግሶ የሚመጣበት ዕለት እየደረሰ ነውና እንዳትፈሩ እንመክራችኋለን። ህወሃቶች ዜጎችን ከሰው በታች አድርገው ለመግዛት እንዲመኙ ያደረጋቸው እብሪት የሚተነፍስበት ዘመን እሩቅ አይሆንምና አሁንም አትፍሩ።
ህወሃቶች ከእነርሱ ቁጥጥር ውጪ ያሉ ነፃ ሚዲያዎችን እንደማይታገሱ የታወቀ ነው። ለምን ቢሉ የወንጀላቸው ብዛት፤ የክፋታቸው ጥልቀት ሳይነገር ተሠውሮ እንዲቀር ስለሚመኙ ነው። ይህን ምኞታቸውን እውን ለማድረግም ራሳቸው የሠረቱን ህግ ውልቅልቁን አውጥተው ያፈራርሱታል። ዜጎች መረጃ የማግኘት መብት አላቸው ተብሎ እነርሱ “ህገ-መንግስታችን” እያሉ በሚጠሩት ላይ በማያሻማ ሁኔታ የተቀመጠ ቢሆንም እነርሱ ግን ለራሳቸው ህግ መታመንን አልመረጡም። እንዲያውም እነርሱ ሞተንለታል የሚሉትን ህግ አፈር አስገብተው ራሳቸው ህግ ሆነው ተፈጥረዋል። እነርሱ ህግ ሁነው በመፈጠራቸውም በየዜጎች ደጅ እየተንከላወሱ ኢሳትን ብትሰሙ ወዮላችሁ እያሉ ያስፈራራሉ። ዜጎች ግን የሞኝ ዘፈናቸውን መልሰው መልሰው ለሚያላዝኑ ኢሕአዴጋዊያን ዛቻ የሚንበረከኩ አይሆኑም። አገራቸውን በተመለከተ ማንኛውንም መረጃ ለመስማት ያላቸውን ነፃነትም ለምናምንቴዎች አሳልፈው የሚሰጡ አይሆኑም።
ጎሬቤታችን ኬኒያ ከአስር በላይ የግል ቴሌቭዥን ጣቢያዎች አሏት።በርካታ በአጭር ሞገድና በኤፊኤም ሞገዶች የሚተላለፉ ሬዲዮኖችም አሏት። የኬኒያ መንግስት ለዜጎቹ ክብርና ፍቅር ስላለው የተቻለውን ያክል ነፃ ሚዲያ እንዲኖር ይጥራል። ለህዝቡ ክብርና ፍቅር የሌለው ህወሃት ግን በወረቀት ላይ በፃፈው ህግ ዜጎች መረጃ የማግኘት መብታቸው ያልተገደበ ነው ቢልም በተግባር ግን የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት ያፍናል። ነፃ ሚዲያ እንዳይፈጠር ለማድረግ፤ የተፈጠሩትንም ለማጥፋት ግዜውንና የአገሪቷን ሃብት በከንቱ ያባክናል። ህወሃት ከድሃ ጉሮሮ እየነጠቀ ኢሳትን ለማፈን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አባክኗል። የአገሪቷ የህግ ተቋማትም ሌቦችንና ነፍሰ ገዳዮችን መከታተል ትተው በነፃነት እንፃፍ ብለው የተነሱ ጋዜጠኞችን በማሳደድ የአገሪቷን የሥራ ሠዓትና ሃብት በከንቱ ያባክናሉ። ህወሃቶች ይሄው ናቸው። አገር፤ ወገን፤ ህዝብ የሚባል ነገር በሂሊናቸው ያልተፈጠረ፤ እነርሱ ብቻቸውን ሌላውን ተጭነው መኖር የሚፈልጉ፤ የጨካኞችና የእብሪተኞች ስብስብ መሆኑን መዘንጋት አያስፈልግም።
የተከበራችሁ ያገራችን ዜጎች !
አገራችሁን በተመለከተ መረጃ ማግኘት የዜግነት መብታችሁ መሆኑን እንዳትረሱ። ይሄም እነርሱ “ህገ-መንግስት” ብለው በሚጠሩት ላይም በግልፅ ተቀምጧል። ይሄን በህግ ደንግጎ ሲያበቃ ኢሳትንና ሌሎችን ነፃ ሚዲያዎችን መስማት አትችሉም ሲል የማውቅላችሁ እኔ ነኝና የምትሰሙትንና የምታዩትን የምመርጥላችሁ እኔ ነኝ እያለ መሆኑን አስታወሱ። ይሄ ማለት አዋቂው እኔ እንጂ እናንተማ ክፉን ከደጉ ለመለየት ገና አልደረሳችሁም ማለት መሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል።መንግስት ነኝ ብሎ በአገሪቷ ጫንቃ ላይ የተቀመጠው ህወሃት-ኢሕአዴግ ህዝቡን የማያከብር ብቻ ሳይሆን ለህዝብ ያለው ንቀትም ወሰን የሌለው ሁኗል። ይሄ ዘረኛና ዘራፊ ቡድን ክብራችንን አዋርዶና አንገታችንን አስደፍቶ ሊገዛን አይገባውም። ፍርሃት ይብቃ። ህወሃት እየፈጠረ ያለው ፍራቻን መሸሸ አይገባም፤ ይሄን ፍርሃት መጋፈጥ የጀግና ተግባር ነውና ለክብራችሁና ለነፃነታችሁ ስትሉ ፍርሃቱን ተጋፈጡት እንጂ አትሽሹት።
በዚያ በጨካኞች መንደር ሁናችሁ በሠላማዊ ትግል ብቻ ለውጥ እናመጣለን ብላችሁ የተደራጃችሁ የፖለቲካ ድርጅቶችም መረጃ የማግኘት፤ መረጃ የመሰብሰብ እና የማሰራጨት መብታችሁ ነው ብለን ልንነግራችሁ አንዳዳም። በነፃ ሚዲያ መናገርም ሆነ ለማንኛውም ሚዲያ መረጃ የመስጠት ማንም የሚሰጣችሁ መብት እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። እኛ እንደምንገምተው ኢሳትም ሆነ ሌሎች ነፃ ሚዲያዎች የእናንተም ሃብት ናቸው። ህወሃት-ኢሕአዴግ አትስሙ ወይም ደግሞ አትናገሩ ሲላችሁ ያንን የእብሪተኛ ትዕዛዝ አለመቀበላችሁን ለነፃ ሚዲያዎች መረጃ በመስጠትና ሃሳባችሁን በነፃው ሚዲያ በመግለፅ እምቢተኝነታችሁን በማሳየት ለምትመሩት ህዝብ አርአያ እንድትሆኑ ብናሳስባችሁ ደፈሩን እንደማትሉ ተስፋ እናደርጋለን። ከዚህ አንፃር ሰማያዊ ፓሪትና አንድነት ያወጡትን መግለጫ በአድናቆት የምንመለከተው መሆኑን ለማስታወቅ እንወደላን።
ለህወሃት-ኢሕአዴጎች !
ራሳችሁን ከአሸባሪ ምግባርና መዝገብ ማስፋቅ ሳትችሉ የነፃነት ፍላጎት ያላቸውን ሁሉ አሸባሪ እያላችሁ ማላዘናችሁን የምታቆሙበት ግዜ እየመጣላችሁ ነው። እናንተ ከላይ ሁናችሁ ህዝቡ ከሥር ሁኖ እናንተን ተሸክሞ ለዘላለም እንደማይኖር አበክረን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።በየሰው ደጅ ካድሬዎቻችሁን ልካችሁ ኢሳትን አትስሙ እያላችሁ የማስፈራራት እብሪታችሁ ረገብ የሚልበት ግዜ እየመጣላችሁ ነው። ዛሬ ህዝባችንን የእኛን ብቻ ስሙ፤ የእነርሱን አትስሙ ማለታችሁ ለህዝባችን ያላችሁን ንቀት የሚያመላክት ነው።ህዝባችንን እንደናቃችሁና እንዳዋረዳችሁ አትቀጥሉም። የነፃነትን ፍላጎት አፍናችሁ አታቆሙትም። የፍትህ ጥማታችንን በአፈሙዝ ልትገቱት አትችሉም። የእኩልነትን ጥያቄ በውሸትና በዛቻ አታዳፍኑትም። እውነት እውነት እንላችኋለን ወንጀላችሁ ሳይነገር፤ በስውር የዘረፋችሁት በአደባባይ ሳይገለጥ አይቀርም። እኛም ቀንና ማታ ለዚያ ግብ ሳናገራግር እየሰራን ነው። በአገራችን የነፃነት ጎህ ሳይቀድ ለሽፋሽፎቶቻችን እንቅልፍ፤ ለስጋችንም ዕርፍት አይሆንም። የዘረኞችና የዘራፊዎች ጀንበር ሳትጠልቅ፤ የእኩልነት ናፋቂዎች ጎህ ሳትቀድ አናርፍም። ያነገታችሁት መሣሪያ የሸንበቆ ምርኩዝ እስከ ሚሆን የጀመርነውን ትግል ዕለት ዕለት እያጎለበትነው እንቀጥላለን።
ህወሃት-ኢሕአዴጎች ሆይ ስሙ! ይሄን ህዝብ ከሚችለዉ በላይ ገፍታችኋታል። ህዝቡም ሊሸከማችሁ ከሚገባ በላይ ተሸክሟችኋል።እንዲህ ህዝባችንን መፈናፈኛ አሳጥታችሁ እና እስከ ልጅ ልጆቻችሁ ረግጣችሁ ለመግዛት ያለማችሁት ህልም በህልምነቱ ብቻ እንደሚቀር ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አይግባችሁ። ትግላችን ጥሩ መሠረት ይዟል። ከዚህ በኋላ ወደ ኋላ የሚመልሰን ምድራዊ ኃይል የለም።እውነት እውነት እንላችኋለን ለዘላለም ኢትዮጵያዊያንን አዋርዳችሁ የመግዛት ህልማችሁ ቅዥት መሆኑን ደግመን ልንነግራችሁ እንወዳለን።
በህወሃት-ኢሕአዴግ ውስጥ ሁናችሁ የነፃነት፤ የፍትህ እና የእኩልነት ጥያቄያችንን የምትጋሩን ወገኖቻችን እሰክ አሁን የምታደርጉት የውስጥ ትግል ፍሬ እያፈራ ነው። ፍሬውን በራሪ ወፍ እንዳይለቅመው የተለመደው ጥንቃቄ እንዳይለያችሁ ይሁን። አሁን ህዝቡ መረጃ እንዳያገኝና፤ መረጃ እንዳይሰጥ የሚሞከረው ሙከራ ህገ-መንግስት ተብየውን የሚጥስ መሆኑን ታውቃላችሁ። ይሄን ካድሬው ሁሉ እንዲገነዘበው የውስጥ ትግሉ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። ራሱ ያወጣውን ህገ መንግስት አፈራርሶ ከትቢያ የሚቀላቅል ቡድን በምን ሞራል ብቃት ነው ሌላውን ህገ-መንግስቱን ሊንዱ ነበር እያለ የሚከሰው ? በኢትዮጵያዊያን ላይ የተጫነው ህገ-መንግስት በህወቶች ሲፈርስ ትክክል ፤በሌላው በተግባር እንዲውል ሲጠየቅ ደግሞ ስህተት ሁኖ በአሸባሪነት የሚያስከሥሥ መሆኑን ግንዛቤ መጨበጥ ይጠቅማል።
በመጨረሻም በህወሃት-ኢሕአዴግ የጭቆና ቀንበር ሥር ለምትንገላቱ ወገኖቻችን ሆይ ! አትፍሩ። ይህን የሚያስፈራራችሁን አካል እስከ መጨረሻው የማትሰሙበት ዘመን እየመጣ ነው። አሁን ፍርሃታችሁን ግደሉት።የምትሰሙትንና የምታዩትን እኔ ነኝ የምመርጥላችሁ ከሚል እብረተኛ እጅ ራሳችሁን ለማላቀቅ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ እያደረገ ያለውን የነፃነት፤ የፍትህና የእኩልነት ትግል ተቀላቀሉ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Terror Plot to Turn Ethiopian Epiphany Celebration into an Inferno Uncovered

January 17, 2014
The Horn Times Breaking news
Report compiled by Getahune Bekele-South Africa
Christians and Muslim communities urged to be vigilant against the government’s plot.
According to our well-placed sources in the inner circle of the ruling minority junta’s powerful and complex security apparatus, the regime has already assigned several well-trained and craven secret service agents dressed as Muslims to carry out massive bombing campaign during the Ethiopian Orthodox Tewahido Church’s Epiphany commemoration feast (Timket) on the 19th  and 20 January 2014.
The distinctly unpopular and even more feared government of Ethiopia, the godfather of terror and wanton destruction, impervious to its own People’s opinion, is now ready to use the TPLF homicide machine to inflict damage that would surpass the 2005 similar attack, which subdued the Ethiopians into modern day slavery for 22 years.
“The crazed junta, a third world political grouping obsessed with eternal power, has been planning this ferocious and terrifying attack for more than three months.” the whistle blower told the Horn Times in shocking details including names and locations of high value targets, Orthodox churches and Mosques that are marked to be reduced to smoldering rubble in a flood of fire.
The unique Ethiopian Epiphany, the ritual reenactment of the baptism of Jesus in the Jordan River as well as a symbolic renewal of the faithful’s baptismal vows; the divine liturgy is celebrated near a stream or pool at 2 am before dawn, an opportune time for federal security agents to launch Al-Qaeda style bombing rampage.
“Once the blasts turn the colorful Timket procession into an inferno, causing considerable harm and panic, security agents in Muslim clothing will follow that up by slipshod gun attacks on the devotees.” The whistle blower added.
Furthermore, the TPLF homicide agents already poisoned in the Southern Ethiopian town of Alaba Kulito since Monday 13 January 2014, to launch the terror attacks are ordered to burn down two mosques immediately after the blasts to make it look like a retaliatory attack by the Christians, the security agent who is working in the chief tug, TPLF intelligence top dog Getachew Assefa’s office further divulged.
According to the leaked critical terror master plan designed to consolidate Tigre People Liberation Front/TPLF’s power base a head of the crucial 2015 elections, the two Amhara kilel towns of Woldia and Haike in the historic Wello province are also targets.
The two towns are believed to be the strong hold of major opposition party UDJ and the shining symbols of interfaith harmony where Christian and Muslim Amharas are living side by side since time immemorial. The unabashed mission of the regime’s agents who are already in the area is to cause a sectarian strife and put the blame on peaceable and benevolent Wollo Muslims whom the junta regarded as rebels.
In Oromia Kilel, TPLF homicide squads are positioned in majority Muslim areas of Bale and Arsi provinces to attack the Epiphany festival with terrifying force similar to the Totolamo massacre of August 3, 2013, where TPLF terror squad mowed down more than 20 Muslims.
The other major principal target for the state sponsored terror to shock and awe Ethiopians is the coffee rich city of Jimma where TPLF inspired sectarian violence often simmers to the boil in the past 22 years of minority rule in the Horn of Africa nation.
Nonetheless, the top security agent warned that an attack equivalent to the Nazi blitzkrieg is going to engulf the Eastern town of Jijiga, the town that sits on major ethnic and religious fault line created by the ruling minority junta.
Ignoramus agents stationed in Jijiga dressed in ethnic Somali Muslim attire are ready to attack the January 19 and 20th Orthodox Christian church Epiphany procession, and the same agents in Christian attire and even priestly robs would then attack Mosques, an attack expected to ignite a flood of fire in the already volatile town and its environ.
Quizzed by the Horn Times over what the government is stand to gain from the blood bath, the agent alleged that  corrupt and genocidal TPLF warlords are deeply concerned about being driven out of power in the upcoming elections unless they find ways of breaking apart the unity and the strong bond that exists between Ethiopian Christians and Muslims.
“I don’t know whether the planned horrendous attack would prove a political disaster for the junta; but what I can tell you is that hardcore TPLF intelligence operatives led by Getachew Assefa started pulling together capable agents 3 months ago for the major assault on the defenseless people. The aim is to inflict enormous damage on the nation’s psyche.
“Then so called Muslim extremists, Ginbot-7, Oromo People Liberation Front, UDJP and Semayawi/blue party will be blamed for the attacks. After unhinged diatribe by TPLF propagandists, what is to follow is what we used to for the past 22 years. Wave of arrests targeting Muslim and opposition party leaders, planting and fabrication of evidences, killing innocent people depicting them as terrorists…all these to totally subdue the people and go to the 2015 elections with no opposition at all. That is it.”
Another source familiar with TPLF intelligence operation said the TPLF junta’s past nauseating claims that it had foiled terror attacks were all pure fabrications used to instill fear and impose martial law. A cowardly act that exposes the moral makeup of TPLF warlords who, after 22 years in power still prefer to use terror rather than dialogue to remain supreme rulers of the impoverished nation.
To balance our story we called the office of the feared top spy Getachew Assefa, but the Horn Times was issued with another landline number to call his deputy Ato Esayeyas whom we are told is the alleged coordinator of the bloody attack. Nevertheless, a female officer at the intelligence headquarters in Addis Ababa screamed several epithets and slammed the phone shut when we asked her about the alleged terror plot by the ruling minority junta against the people.
infohorntimes@gmail.com

ክህደት ከአናት ሲጀምር፣ በቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ


January 18, 2014

ከቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት
እውነት ቤት ሥትሰራ …
ውሸት ላግዝ ካለችሚስማር ካቀበለችጭቃ ካራገጠችቤቱም አልተሰራ … እውነትም አልኖረች ።
… እንደዚያ ነው በባቢሎን ዘመን ።
የአንዱ ቋንቋ ከአንደኛው ይዘበራረቃል ….. መግባባትና መረዳዳት ብርቅ ይሆናል ። በጠራ አማርኛ የተጣፈውን በጉግማንጉግኛ በመተርጐም ከውስጡ የሚፈልጉትን ብቻ አለፍ አለፍ እያሉ ያነቡታል ። እናም የራሳቸውን ትርጉም ይሰጡታል ። ፍየል ወድያ ….. ቅዝምዝምም ወዲህ ይሆናል ።
ከቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት መካከል ጥቂት አዛውንቶች ታሪክን ደልዘው በወያኒኛ አዲስ ታሪክ ስለ አየር ኃይሉ እንዲፅፉ በህውሃት እየተጠየቁ ነው ። እነዚህ ባለ ብዙ አኩሪ ታሪክ ባለቤት አዛውንቶች መንታ መንገድ ላይ ቆመዋል ። በዓለም ዙርያ ተበትነው ያሉት የቀድሞው አየር ኃይል አባላት ሃሳባቸውን እንዲደግፉና የእርዳታ እጃቸውንም እንዲዘረጉ ለማግባባት እየሞከሩ ነው ። እኛም የቀድሞው የአየር ኃይል አባላት እንዲህ አልን ……….

“ የአየር ኃይልን ታሪክ ለትውልድ ለማስቀረት የምታደርጉት ጥረት በጐና የሚደገፍ ምግባር ነው በርቱ ፤ ነገር ግን የገዢው ፓርቲ ሞግዚትነት አያስፈልጋችሁም ። በተጨማሪም በተፅዕኖ ስር ሆናችሁ ሚዛናዊነት የሚጐድለውና የተደለዘ ታሪክ ለትውልድ እንዳታቆዩ ሥጋት ቢጤ አለችን ። (ያም ቢሆን መፅሃፉን ካነበብን በኋላ የምንታዘበው ይሆናል … አያጣላም ።)
የአየር ኃይል ቬተራን አሶሴሽንን እናቋቁማለን የምትሉትን በተመለከተ ግን ወራጅ አለ ። እጅግ ከስጋት በላይ የሆኑ ጥያቄዎች አሉን ። “ የቀድሞው አየር ኃይል ቬተራን አሶሴሽን ” እያላችሁን ከሆነ ግን እንግባባለን ።
የሚለውን ጥቅል ሃሳብ በመልዕክታችን ብንሰድላቸው በጉግማንጉግኛ በመተርጐም እኛ ፖለቲካ አንነካካም …. ፖለቲካንና ኰረንቲን በሩቁ ነው ብለናል ይሉናል ከአዲስ አባ ደብዳቤ እየፃፉ ። እነሱ ለካ የአሁኑን የህውሃትን መንደርተኛ አየር ኃይል ነው ቬተራን እያሉ የሚያንቆለጳጵሱት ። በህውሃት ሰማይ ስር ጉድ ሳይሰማ አያድርም አይደል !
እኛ ድፍን የአየር ኃይል ተቋም ላይ ስለተፈፀመ ክህደት ስናወራ …. እነሱ አንድ ግለሰብ አገርንና ህዝብን ለከዳ ስርዓት ስለሚመሰርተው ዕድርና የተዝካር ግርግር ሊያስረዱን ይሞክራሉ ። እኛ እኰ የቆማችሁበት አፈር ሥር ነፍሱ ያልወጣች የምታጣጥር የገዛ ጓደኛችሁ ነፍስ አለች ነው የምንላቸው ። መጀመሪያ ባለንጀራችሁን ነፃ አውጡት ፤ እናንተም በጐን በሾርኔ ሳይሆን በአደባባይ በህግ ነፃ ውጡ ምክንያቱም እንደ ዶሮዋ ገመዳችሁ ረዘመላችሁ እንጂ ፈፅሞ አልተለቀቃችሁም እያልን ነው ።
ህውሃት እንደሆነ በሰው ተጠቅሞና አዋርዶ እንደሚያባርር የአደባባይ ሚስጢር ነው ። ደግሞም ይህ ይጠፋችኋል ብለን አንሞግትም ፤ ….. የመሰንበት ጉጉት ህሊናን ፈፅሞ ካልተቆጣጠረ በቀር ።
አየር ኃይል ለአገር አንድነት የተፋለመ ጀግና እንጂ ጨፍጫፊ ያለመሆኑን በአደባባይ ስትመሰክሩና በህግ ስታስነግሩ ….. የአየር ኃይል ተቋም እንደ ተቋም ነፃ ሲወጣ …. እርቅ ሲወርድ ፣ አገርን ከጠላት በመከላከላቸው ብቻ የሞትና የእድሜ ልክ ፍርደኞች በአደባባይ ነፃ ሲወጡ …. ያን ጊዜ ሁላችንም በአንድነት ነፃ እንወጣለን ። ያለበለዚያ ግን ትውልድም አገርም ላይ ይቅር የማይባል ክህደት ትፈፅማላችሁ እያልን ነው ያለነው ፤ በጠራ አገርኛ ቋንቋ ።
የቬተራን አሶሴሽንን በመወከል ያገባኛል ብለው ከአዲስ አበባ መልዕክት የሰደዱልን ሰው በፍፁም ሃሳባችንና ሥጋታችንን በትክክል የተገነዘቡ አይመስሉም ወይንም ዛሬ ኢትዮጵያ በምትባለው አገር ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የሚከታተሉም መሆናቸውን እንድንጠራጠር እያደረገን ነው ። ድንገት ዘንድሮ ጆሮዋቸውም ዓይናቸውም የተከፈተላቸው ይመስል በቃል ያጠኑትንና ስለ አየር ኃይሉ የሚገምቱትን በጐ ፍላጐት ለመተግበር የተነሱ ይመስላል ።
የህውሃት አስተዳደር አዛውንት የአየር ኃይሉን አባላት በማምሻ እድሜያቸው ታሪክን ደልዘው የእራሱን የተንጋደደና የተንሸዋረረ ታሪክ እንዲፅፉለት እየተጠቀመባቸውና ከጠራ ታሪካቸው አንስቶ ከራሱ ቆሻሻና ስውር ፍላጐት ሥር እያንደባልላቸው ያለ ይመስላል ።
አየር ኃይሉ በአዋጅ ሙሉ ለሙሉ ከስራ ውጪ በተደረገበት ዘመን ላይ ፤ ጨፍጫፊ ተብሎም ቅፅል ስም ወጥቶለት ወደ ከርቸሌ መጋዙንና በመንደርተኛ ፓይለቶች እየተተካ መሆነኑን ትንፍሽ እንዳይሉ በዚሁ በምሽት እድሜያቸው እየተደለሉ ናቸው ።
እንዲያውም ሙዝየም እስከ መክፈት የዘለቀ ህልምም እንዳላቸው እየጠቀሱ ነው ። አገር ቢኖረንማ ኖሮ ለትውልድ የሚቀር ፣ ታሪክን የሚዘክር ሙዝየም ማቆም እንዴት የተባረከ ህልም ነበር ? ነገር ግን አገርም ዜግነትም በተዋረዱበትና እድሜያቸውን ሙሉ ለአገር አገልግሎት ያበረከቱ አንጋፎች እንደ አሮጌ ቁና በውርደት እንዲኖሩ በአደባባይና በአዋጅ ባይበየን ኖሮ ፣ ትውልድም በበጐ መሰረት ላይ ቀጥሎ ቢሆን ኖሮ …. ሁሉም አላማ በጐና ለአገርም ሆነ ለትውልድ የሚጠቅሙ ይሆኑ ነበር ።
እንግዲያውስ እነዚህ በህውሃት እየተደለሉ ያሉት የአየር ኃይሉ ነባር አዛውንቶች እርማቸውን ያውጡ ። ህውሃት አገሪቷን ከተቆጣጠረ ወዲህ ያለውን አየር ኃይል ተብዬ እንጂ የቀድሞውን ታሪክ ምናምኒት አሻራ እንኳ አያገኙም። አጠቃላይ ሰፈሩና ቢሮዎቹም ጭምር በአይጥ መንጋ እንደተመታ ባድማ ዶክመንቶች ተፈርፍረው ድምጥማጣቸው መጥፋቱን አይጠራጠሩ ። የአየር ኃይሉን የታሪክ አሻራ ሊያስረዱ የሚችሉ የተለያዩ አውሮፕላኖችን ማናምኒት ሳያስቀር አቧራቸውን እያራገፈ የህውሃቱ አበበ ተ/ኃይማኖት (ጆቤ) እዚህ ግባ በማይባል ዋጋ መቸብቸቡን እንዴት ሳይነግራቸው እንደቀረ ይገርመናል ? ይህ ቀበኛ ሽፍታ ለጌጥና ለታሪክ በአየር
ኃይሉ ጠ/መምሪያ ፊት ለፊት እንኳ ተቀምጣ የነበረችውን ገብሬ ቦላሌን ሳይቀር አንጠፍጥፎ መሸጡን ለምን ደበቃቸው ? ታሪክ በመስራት አገራችንን ያስከበረችውን ኤፍ-5 አውሮፕላንንስ አንዲት ሳያስቀር መቸብቸቡንስ ? በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር የሚመራውን የአሁኑን ሥርዓት አያውቁትም እንበል ወይስ የክፋትና የብቀላ ምግባሩን ሁሉ ትተው በጐ ተክለ ሰውነት ሊገነቡለት እየሞከሩ ይሆን ? ታዲያ ይህንን እየሰሩ እንዴት ፖለቲካ አንነካካም ይሉናል ?

በእነርሱው አመራር ስር የተገነባው የአየር ኃይል ሰራዊት እኰ በጅምላ ጨፍጫፊና ወንጀለኛ ተብሎ እድሜውን ሙሉ ከአቀናው መስሪያ ቤት በውርደት ተባሮ ቤተሰቡ ተበትኖ በረሃብና በችጋር እንዲያልቅ ተፈርዶበታል !
እውነተኛዎቹ የአየር ኃይሉ አርበኞች ድፍን 22 ዓመታት ሙሉ ተሸማቀውና አንገታቸውን ደፍተው መሃል ደ/ዘ ውስጥ (በቀለ ሞላ ሆቴል ፊት ለፊት) በጠጠርና በቆርኪ ዳማና ቼዝ ሲጫወቱ የአዛውንቶቻችን መንግስት የት ነበር ? ለዚህ ሁሉ ግፍና በደል ተጠያቂው ማነው ? እነዚህንና ሌሎች በደሎችን እንዴት ነው የሚያስታርቁት ? በምንስ መመዘኛ ቀበኛ ሽፍታ የመሰረት ድንጋይ እንዲያነጥፍላቸው ያደርጋሉ …. ! ከረገጡት ምድር ስር የባልንጀሮቻቸው የምትቃትት ነፍስ ምን ትላቸው ይሆን ?
ፖለቲካ … ፖለቲካ …. ለምን እንደሚሉን አልገባንም ። ፖለቲካ ምንድነው ?
ለዘመነኖቹ የመንግስት ባለስልጣናት ማደር ? ለስብሰባ ሲጠሩ ፈጥኖ ሸገር ላይ መከሰት ? ወይስ ሲመሩት የነበረውን ሰራዊት አስማርኰና ክዶ ለትግራዩ የነፃነት (ተገንጣይ) ግንባር በፈቃደኝነት መገበር ?
እኛ ፖለቲከኞች እያሉን የሚያበሻቅጡን ከአገር በግፍ ተገፍታሪ ስደተኞች በሰላም ተከባብረንና ተዛዝነን ድፍን 20 ዓመታትን እንዳሳለፍን በአለፈው የበጋ ወቅት በዋሽንግተን ከተማ ተገኝተው መታዘባቸውን እናውቃለን ።
አየር ኃይል ማለት ለኛ መታወቂያችን ፣ ማንነታችንና ዜግነታችንም ጭምር ነው ። በህብረት ተደጋግፈን እንኖራለን፤ የተቸገረን እንረዳለን ፣ የታመመን እናስታምማለን … እንጠይቃለን ፣ እስከወዲያኛው የሚሰናበተንንም በኃዘን እንሸኛለን ።
ጀግኖቻችንን ከተጣሉበት እያስታወስንና እያነሳን እናከብራቹኋለን እንላለን ። በየዓመቱም የአየር ኃይል ቀን በማለት በህብረት ዩኒፎርማችንን ለብሰን ባንዲራችንን ከፍ አድርገን እያውለበለብን ኢትዮጵያ ሃገሬን እንዘምራለን….. ።
ይህንን ባንዲራና ዝማሬ የአሁኑ መንግስት አይወደውም ። በዘር ከፋፍሎ እኛ እና እነርሱ ፣ የቀድሞውና የአሁኑ ፣ ጨፍጫፊና ዲሞክራቲክ በማለት እየለያየ አጥፍቶናል። አሁን ደግሞ እዚሁ ያለንበት አገር ድረስ ክንዱን እያረዘመ መካከላችን ሊገባ እየተቅበዘበዘ እንደሆነ ይገባናል ። እባካችሁን አዛውንቶቻችን ለዚህ መንደርተኛ ስርዓት ክርንና ጅማት እየሆናችሁ ህውሃት ጣቱን እቤታችን ድረስ እንዲያረዝም እየረዳችሁ መካከላችን እንዲገባ አታድርጉ ፤ በማህበራችንም በኩል አትምጡ ።
በግል እኰ መፅሃፍ አይደለም ኤግዚቢሽንም መክፈት ትችላላችሁ ። አሁን እየመጣችሁበት ያለው መንገድ ግን የሁሉንም ምክር ፣ የብዙሃንን ይሁኝታ ይጠይቃል ። እናንተ ደግሞ እዚያው አገር ቤት ያሉትን እውነተኞቹን አርበኞች አንድ በአንድ ሲያልቁ ጠብቃችሁ ፣ በህይወት የተረፉትንም ንቃችሁና ገፍትራችሁ ቀበኛ የሃገር ጠላት
የሆኑትን ቱባ የህውሃት ባለስልጣናትን በጀርባችሁ አዝለችሁ አትላንቲክን በማቆራረጥ ልታነታርኩን ትሞክራላችሁ።

ለምን ድምፃችሁን አጥፍታችሁ ታሪክ መፃፍም ሆነ ዕድር ማቋቋም አልመረጣችሁም ? በማህበራችን በኩል ለመምጣት ለምን መረጣችሁ …. ? በብዙሃን ስደተኛና በውርደት ተባራሪ ስም በየሸራተኑ ከበሮ መደለቁንስ ምን አመጣው ?
እንግዲያውስ ለሁለተኛ ጊዜ ምክር እንለግስ ……….
ሰው ባለቀ እድሜው ላይ ለኑዛዜ ይመቻቻል ….. እውነትን ተናግሬ ካልሞትኩ ብሎ ከህሊናው ጋር ትንቅንቅና እልክ ይጋባል ….. እውነቱን አፍርጦ በመሸበት ያድራል … እንጂ ለዳግም ምርኰ እራሱን አሳልፎ አይሰጥም ።
በዚህ እድሜ እኰ ግጥም ብሎ ከሞላ የውስኪ ባንኰኒ ላይ የምንጭ ውሃ ካልሆነ ንክች አላደርግም .. ፣ ከተትረፈረፈ ጮማና ቁርጥ መሃል ቲማቲምና ቅጠላ ቅጠል ካልሆነ ምናምኒት አልቀምስም እየተባለ የሚኖርበት እድሜ ነው ፣ ብዙ የሚያጓጓ ህይወት የለም ። ታዲያ ምንድነው በዚህ በኪኒኒ ተደግፎ በሚኬድበት የምሽት እድሜ ላይ ሆኖ ውሃና ዘይትን ለመቀላቀል መሞከር ? በዚህ ምግባር ትውልድ አይደለም ከአብራክህ የወጣ ልጅ ይጠየፍሃል ።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
ታዛቢዎች በህብረት !
ከቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በያሉበት ።