Saturday, August 16, 2014

በሕወሓትና ሻዕቢያ ዙሪያ ያለው ቤተሰባዊ ስብስብ


ከአርአያ ተስፋማሪያም

የሻዕቢያ ከፍተኛ የጦር አዛዥ / ስብሃት ኤፍሬም ባለቤት ታጋይ ሩት ሃይሌ ትባላለች። ሩት ሃይሌ እና የሕወሓቱ ሽማግሌ ስብሃት ነጋ የቅርብ ስጋ ዝምድና እንዳላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል። 

ሌላው / ሰለሞን እንቑይ ይጠቀሳሉ፤ ፓርቲውን የተቀላቀሉት 1983. ሲሆን ቀደም ሲል በለንደን ይኖሩ ነበር።በወቅቱ «..» ሃላፊነት ቦታ ተቆናጠጡ። 1993. የትግራይ አፈ-ጉባኤ ተደርገው ተሾሙ፤ የድርጅቱ /ኰሚቴ አባልነትን ጨምሮ 5 ቁልፍ ሃላፊነቶችን እንዲጨብጡ ተደረገ። 1994. መጋቢት ወር ከፓርቲው ልሳን ጋር በትግርኛ ቁዋንቑ ባደረጉት ቃለምልልስ አስመራ ተወልደው እንዳደጉ የገለጹት / ሰለሞን የሻዕብያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ የአጎት ልጅ መሆናቸው ምንጮች አረጋግጠዋል።

1995. በመቀሌ በተነሳ ተቃውሞ፡ አምስት ሰላማዊ ነዋሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ በሺህ የሚቆጠር ህዝብ የዶ/ ሰለሞንን መኖሪያ ቤት ከማውደሙም በተጨማሪ « የሻዕብያ ወኪል እኛን አይመራንም» በሚል የተቃውሞ ድምጹን አሰምቶዋል። ( በነገራችን ላይ ይህ ጉዳይ « በኢትኦጵ» ጋዜጣ በወቅቱ በዝርዝር መረጃው ቀርቦ ነበር።)

ሌላው የሻዕቢያ አባል የነበረው ኤርትራዊው ሳሙኤል /ማሪያም ሲጠቀስ፤ // አማካሪ ሆኖ የተመደበው 1993. ነበር። ከሁለት አመት ቆይታ በሁዋላ የአድዋ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ ተደርጎ ተዛወረ። 1996. ወደ ኢሮብ ወረዳ ያቀናው ሳሙኤል የአካባቢውን ሕዝብ ሰብስቦበአቶ መለስ በወቅቱ የረቀቀውን ባለ 5 ነጥብ አጀንዳ ተብዬ ለነዋሪው ለማስረዳት ይሞክራል።

በፅኑ ኢትዮጲያዊነቱና በጀግንነቱ የሚታወቀው የኢሮብና አካባቢዋ ነዋሪ የሳሙኤልን ማንነት አብጠርጥሮ በመናገርና አጀንዳውን በማብጠልጠል ተቃውሞ ያሰማል። ሳሙኤል /ማሪያም ስብሰባውን በማቑዋረጥ በመጣበት ኮብራ መኪና ተሳፍሮ ጥቂት እንደተጉዋዘ.. በአካባቢው ነዋሪ 12 ጥይት ተደብድቦ ተገደለ።

በአሁኑ ወቅት የትግራይ ክልል /ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው የሚመሩት / ሒሩት ናቸው። ኤርትራዊ የሆኑት ሒሩት የአባዲ ዘሞ ባለቤት ሲሆኑ፤ የሂሩት ወንድም እያብ (የቀድሞ መጠሪያ ስሙ ሱራፌል) ከአራት አመት በፊት /ሚንስትርና የጠ// አማካሪ ተደርጎ በመለስ መሾሙን ምንጮች ጠቁመዋል። ኤርትራዊው እያብ ትምህርት የሌለው፤ ምንም አይነት ችሎታና ብቃት እንደሌለው እየታወቀ ሃላፊነት በሚጠይቅ ትልቅ ቦታ መመደቡ አስገራሚ ነው ያሉት ምንጮች አሁንም በጠ// /ማሪያም ካቢኔ መቀጠሉን አክለው ገልጸዋል።

በማስከተል በሕወሓት /ኰሚቴ ያለውን ቤተሰባዊ ግሩፕ ምንጮቹ እንደሚከተለው አስቀምጠዋል፤

ቅዱሳን ነጋ፡ ፀጋዬ በርሄ፡ ፈትለወርቅ /እግዚያብሄር ከማ/ኰሚቴ አባላት ቅድሚያ ይጠቀሳሉ። ቅዱሳን የሽማግሌው ስብሃት ነጋ እህት ስትሆን የጸጋዬ ባለቤት ናት። ፈትለወርቅ ደግሞ የስብሃት ወንድም ልጅ ናት። ፈትለወርቅ የአባይ ፀሓዬ ባለቤት ነበረች። አንድ ልጅ አፍርተዋል፤ ከተለያዩ ቆይቶዋል። አባይ ፀሃዬ ወጣት ኮረዳ ተሞሽረው በሙስና የደለበ ኑሮ ይገፋሉ ብለዋል ምንጮች። በአደገኛ ሰላይነታቸው የሚታወቁት ብርሃነ /ማርያም (በቅፅል ስማቸው ብርሃነ ማረት) ከስብሃት ነጋ ጋር የጋብቻ ዝምድና ያላቸው ሌላው የማ/ኰሚቴ አባል ናቸው።

የአዲስአለም ባሌማ ባለቤት ፀሓይ እቁባይ ትባላለች፤ የአርከበ እቁባይ እሕት ናት። የአርከበ ባለቤት ደግሞ ንግስቲ /ክርስቶስ ስትሆን፡ የብርሃነ /ክርስቶስ እሕት ናት።


''አማራጭ የሌለው ምርጫ''

ሄለን ንጉሤ
ከኖርዌ

አንድ ሀገር እንደ ሀገር ለመቀጠል የሚያስችላትን ትልቁን ድርሻ የመወጣት ኃላፊነት ያለበት በስልጣን ላይ ያለው ስርአት ነው። ሥርዓቱ የሐገሪቱን ህገ መንግስት በመፈፀምና በማስፈፀም ህገ መንግስቱ ሳይሸራረፍና ሳይጣስ እንዲሁም ዜጎች ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸውን ያለ አንዳች መድልኦ በመጠቀም በፍርድ ቤት የመከሰስና የመክሰስ፣ የመርታትና ያለመርታት መብታቸው ተከብሮ በሐገሪቱ የህግ የበላይነት ተረጋግጦ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ለማድረግ በስልጣን ላይ ያለው ስርአት ወሳኝነት አለው።  በአንፃሩ ደግሞ በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት ይህንን ማስፈፀም ካልቻለና ሆን ብሎ የሐገሪቱን ልዑአላዊነት ላለማስጠበቅ የሚሰራ ከሆነ ዜጎች እንደዜጋ የራሳቸውን መብት ማስጠበቅና በሐገራቸው መልካም አስተዳደር የማስፈን ግዴታ ያለባቸው ለመሆኑ ምንም አይነት ጥያቄ የማያስፈልገው የዜግነት ግዴታ መሆኑ በግልፅ ሊታወቅ ይገባል።

ኢትዮጵያ ሀገራችን አሁን ያለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ እንደሚያሳየው በሀገሪቱ ላይ ያለው ባንዳ አምባገነን ቡድን ሀገሪቱን የሚጠቅም አንዳች ስራ ባለመስራቱ ሀገሪቱ በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። እንደአለመታደል ሆኖ ሳይሆን ሆን ተብሎ በወያኔ ዘረኛ አምባገነን ሥርዓት በተያዘ ሀገር የማፈራረስ ሴራ ሀገራችን አሁን ላለችበት ደረጃ ተዳርጋለች። እንደ ሀገር እንኳን መቀጠል ከማይችሉ ሀገራት ተርታ አንዷ ሆና መገኘቷንም የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ያሳያሉ። ዜጎቿን አፍና የምትበላ ሰው መሳይ አውሬዎች የሚያስተዳድሯት ሀገር ሆናለች።

በሀገሪቱ መንግስትን መተቸት በፍፁም የማይታሰብ ሲሆን ጋዜጠኞች ነፃ ሐሳባቸውን ማንሸራሸርና ትክክለኛ መረጃን ለህዝብ ማቅረብ ተስኗቸዋል። ያለው የአፈና ሥርዓት በግል የሚሰሩ ጋዜጠኞችን እና ፀሐፊዎችን እያደነ ለእስርና ለግርፋት፣ ለመከራ የሚዳርግ በመሆኑ ጋዜጠኞች እና ፀሐፊዎች ይሄ እጣ ፈንታቸው መሆኑን አውቀው መከራውን እየተቀበሉ ይገኛሉ። እስርና እንግልቱን መሸከም ያቃታቸው ደግሞ የሚወዷትን ሀገራቸውንና  የሚወዱትን ሞያቸውን ትተው ነፍሳቸውን ለማትረፍ እየተሰደዱ ይገኛሉ።

አምባገነኑ ወያኔ ህገ መንግቱን ወደ ህገ አራዊት ቀይሮ ዜጎችን ለማሰቃያ እየተጠቀመበት ይገኛል። ለዚህም ማሳያ በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያሰጉኛል ብሎ ያሰባቸውን በሙሉ በፀረ-ሽብር ህግ እየከሰሰ ያለምንም ማስረጃና መረጃ ለእስርና ለስቃይ ዳርጓል። ሌሎችም የተቃዋሚ ድርጅት አባላት በሰው በላ ደህንነቶቻቸው በየመንገዱ ተገድለዋል። የእስልምና ሐይማኖት ተከታዮች ተደብድበዋል ተገለዋል ሴቶች እህቶቻችንን ሂጃባቸውን አስወልቀው በመግረፍ ለዜጎች ያላቸውን ንቀት በአደባባይ አሳይተዋል። ህዝቡን በዘር በማጋጨትና በመከፋፈል ጥላቻን በህዝቡ መሃል ለመዝራት ከፍተኛ የካድሬ ስራ ሰርተዋል። የአንድ ዘር የበላይነት አስጠብቀው ሌላው በሃገሩ እንደሌላ ዜጋ አንገቱን ደፍቶ እንዲሄድ በዘሩ እየተንቋሸሸ እየተሰደበ፣ ከቀዬው እየተፈናቀለ ይገኛል። በሀገር ውስጥ የሚደርሰውን በደል መዘርዘር ጊዜ አይበቃም ሁሉም የሚያውቀው ነው ግን ይሄ እስከ መቼ ይቀጥላል መቼ ነው የሚያቆመው ብለን ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል።

ወያኔ በሀገር ውስጥ የሚያደርሰው በደል አልበቃ ብሎት በውጪ ተሰዶ የሚኖረውን ስደተኛ የሀገሪቷን ከፍተኛ ገንዘብ ለስለላ በማዋል ከተለያዩ የጎረቤት ሀገሮች ጋር ተባብሮ የዱርዬ ስራ በመስራት ስደተኞችን እያፈኑ መውሰድ የተለመደ ስራቸው ሆኗል። በቅርቡ ደግሞ እጃቸውን ትንሽ ረዘም አድርገው አለም አቀፍ ህግን በሚፃረር መልኩ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራስ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከየመን ታፍነው ተወስደው ሰው ባልሆኑ አውሬ የደህንነት ሰዎች ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑ ይታወቃል። አቶ አንዳርጋቸው የታላቋ ብሪታኒያ ዜግነት ያላቸው ቢሆንም እስከአሁን ድረስ ማንም እንዲጎበኛቸውም ሆነ የህግ አማካሪ እንዳያገኛቸው ተደርገው በአስቸጋሪና ከባድ በተባለ የማሰቃያ ዘዴዎች በመጠቀም እያሰቃዩአቸው ይገኛሉ።

ወያኔ በ23 አመታት የአገዛዝ ዘመኑ ሲገዛን የኖረው በራሳቸው መተማመን በማይችሉ ባልተማሩና ሀገር ቀርቶ  መንደር ማስተዳደር የማይችሉ አናሳ አስተሳሰብ ባላቸው የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆን እነኚህ የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ሰላማዊ ትግል የሚባል ነገር ስለማይገባቸው የተደረጉትን የሰላማዊ ትግሎች በሙሉ በማጨናገፍ የትግሉን አቅጣጫ እራሳቸው ወደ ለመዱት ሜዳ ቀይረውታል።  በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እናመጣለን ብለው በየዋህነት በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችን በሙሉ በአሸባሪነት እየከሰሱ ወደ ማእከላዊና ቃሊቲ እያጎሩ ይገኛሉ። ወያኔ በሰላማዊ መንገድ ስልጣን ያሰረክባል ብሎ ማሰብ የዋህነት መሆኑን እራሳቸው በስራቸው እየመሰከሩልን ነው።

እንግዲህ በሰላማዊ ትግል ለውጥ ይመጣል ብለን ሌላ 23 አመት የምንጠብቅ ከሆን የዋሃን ብቻ ሳንሆን ጅሎች መሆናችንን ማወቅ አለብን። ወያኔ የትግሉን አቅጣጫ እንድንቀይር የሚያስገድደንን እጅግ በርካታ በደሎችና  ግፎች አድርሶብናል። ትከሻን መሸከም ከሚችለው በላይ ተሸክመን ጎብጠናል ቀና ብለን መሄድ ያስፈልገናል። ቀና ብለን ደረታችንን ነፍተን ለመሄድ ደግሞ ትከሻችንን የተጫነንን ነገር ከላያችን አውርደን መጣል ይኖርብና።  በደል በቃኝ፣ እስር በቃኝ፣ ግርፋት በቃኝ፣ እንግልት በቃኝ፣ ስደት በቃኝ፣ ዘረኝነት በቃኝ፣ እምቢኝ ማለት ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል። ይህንን ከልባችን ተሰምቶን ካልንና የሰላማዊ በሮች መዘጋታቸውን ካወቅን አማራጭ ያጣንለትን ምርጫ መውሰዳችን ግድ ይሆናል።

ማንም ሰው የሰላም አማራጮችን አጥብቆ የሚፈልግ ቢሆንም ወያኔ በሰላም ስልጣን እንደማያስረክብ ደጋግሞ ነግሮናል እንደውም ይሞክሩኝ አይነት ንግግሮችንም በተደጋጋሚ አሰምተውናል ስለሆነም እነሱ በመረጡት መንገድ ሀገራችንን ከወያኔ የውስጥ ወራሪ ነፃ ለማውጣት የትጥቅ ትግሉ የግድ መሆኑ የማይቀር አማራጭ የሌለው ምርጫ በመሆኑ የትጥቅ ትግሉን መደገፍ ያስፈልገናል። የትጥቅ ትግሉን ውድ ህይወታችንን ገብረን፣ አጥንታችንን ከስክሰን፣ ደማችንን አፍስሰን፣ ሀገራችንን ከወያኔ ስርአት ነፃ እናወጣለን የህዝባችን ራእይ እውን እንዲሆን እንታገላለን ብለው ጫካ ገብተው መሬት ላይ የወረደ ስራ እየሰሩ ያሉ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የትግሉን መስመር ጀምረውልናል። እኛ ሁላችንም ሀገራችን በህዝቦችዋ በተመረጡ መሪዎች የምትተዳደር እንድትሆን፣ የህግ የበላይነት የሚከበርባት ሀገር እንድትሆን፣ የዜጎች የሰብአዊ መብት የሚከበርባት፣ ዜጎች ያለ አንዳች መድልኦ በእኩል የሚተዳደሩባት፣ በጥቅሉ የመልካም አስተዳደር ባለቤት የምትሆንባት ዜጎቿ የማያፍሩባትን ሀገር ለመመስረት ሁላችንም አስተዋፅኦ ማበርከት ይኖርብናል። ትግሉን ወደፊት ለማራመድ ብቻ ሳይሆን ትግሉን ጫፍ ለማድረስ ጭምር ለራሳችን ቃል ገብተን ትግሉን መቀላቀል የምንችል ትግሉን በመቀላቀል የማንችል ደግሞ ትግሉን በምንችለው ሁሉ በማገዝ ሀገራችንን ከአምባገነንኖች ነፃ ማውጣትና አዲሲቷን ኢትዮጵያ መመስረት መቻል አለብን።

የትጥቅ ትግል ዋናው አስፈላጊነቱ እነኚህ ባንዳ የባንዳ ልጆች ከስልጣን በጠመንጃ እንጂ በሰላማዊ መንገድ አንለቅም በማለታቸውና ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደሀገር መቀጠል ስላለባት ሳትፈራርስ በፊት የግድ የስርአት ለውጥ  አስፈላጊ በመሆኑ አማራጭ የሌለው ምርጫ የትጥቅ ትግሉ ግድ ይላል!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

Friday, August 15, 2014

“አሸባሪነት” በወያኔ አገዛዝ ሥር ባለችው ኢትዮጵያ

በአገራችን፣ በወያኔ አገዛዝ መደበኛ ትርጉማቸውን ከሳቱ በርካታ ቃላት መካከል “የሽብር ድርጊት“ እና ”አሸባሪ“ የሚሉት ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። ሰፊ ተቀባይነት ያለው የአሸባሪ ትርጉም “የሽብር ድርጊቶችን የሚፈጽም ሰው ወይም ድርጅት” ማለት ነው። “የሽብር ድርጊቶች” የሚባሉት ደግሞ የተለመዱ ጥቃቶችን ሳይሆን የሀይማኖት፣ የፓለቲካ ወይም የርዕዮተዓለም ግብ ለማሳካት ሲባል በሰዎች ላይ ፍርሀትን ለማንገስ፤ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሱ አስከፊ ጥቃቶችን ነው። የሽብር ድርጊቶችን ሰላማዊውን ሕዝብ ጭዳ የሚያደርጉ በመሆኑ በጥብቅ ሊወገዙ ይገባል። ዓላማን በሽብር ድርጊቶች ማስፈፀም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

በወያኔ መዝገበ ቃላት ግን “ሽብርተኛ” እና “የሽብር ድርጊቶች” በዘፈቀደ የሚነገሩ ተራ ቃላት ሆነዋል። ስለአገራቸው እና ስለትውልድ የሚጨነቁ፤ ሀሳባቸው በነፃነት የሚያራምዱ፤ የወያኔን ፕሮፖጋንዳ እንደ በቀቀን የማይደግሙ ዜጎች “አሸባሪዎች” እየተባሉ ወደ እስር ቤቶች እየተወረወሩ ነው። ጋዜጠኞች፣ ጦማርተኞች፣ ፍጹም ሰላምተኛ አማኞች እና ሰላማዊ ፓለቲከኞች በሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚውን ሥፍራ የያዙ ናቸው።
በአንፃሩ ደግሞ እውነተኛው አሸባሪ ህወሓት፣ የመንግሥትን ሥልጣን ይዞ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማሸበሩን በስፋት ተያይዞታል። ህወሓት ዘረኛ ርዕዮተ ዓለሙን ለማስፈፀም ሲል ባለፉት ሠላሳ አምስት ዓመታት ውስጥ የፈፀማቸው የሽብር ድርጊቶች ተዘርዝረው አያልቁም። የህወሓት የሽብር ድርጊቶች ዓላማ የኢትዮጵያን ሕዝብ በፍርሀት አደንዝዞ መግዛት ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ “አሸባሪ” የሚለውን ቃል ራሱ በማሸበሪያ መሣሪያነት እያዋለው ነው። ይህ የውስጥም የውጭም ታዛቢዎችን የሚያሳስት በመሆኑ ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ነው።
“የፀረ-ሽብር አዋጅ” የሚባለው ህገ-አልባነትን ህጋዊ ያደረገው ሰነድ የመንደር ካድሬዎች ሳይቀሩ አንድን ሰው በሽብርተኝነት “ጠርጥረው” ማሳሰርና ማስደብደብ አስችሏቸዋል። የአስተሳሰብ ድህነት ያጠቃቸው የህወሓት ካድሬዎች ብቻ ሳይሆኑ ኃላፊነት የጎደላቸው ፓሊሶችም የፀረ-ሽብር ህጉን ጉልበታቸውን ማሳያ እና ተፎካካሪዎቻቸውን ማጥቂያ አድርገውታል። በፀረ-ሽብር ህጉ ተከስሰው ወህኒ የወረዱ ዜጎችን ያጤነ ማንኛውም ሰው ኢትዮጵያ አገራችን በዚህ ህግ ሰበብ ምርጥ ዜጎቿን እያጣች እንደሆነ ይገነዘባል።
በሽብርተኝነት ለመጠርጠር የሚያበቁ ምክንያቶች እጅግ አሳዛኝ ናቸው። ለካድሬ ሰበካ እውነተኛነት ጥርጣሬውን የገለፀ አስተዋይ ሰው መሆን ብቻውን እንኳን በሽብርተነት ያስጠረጥራል። በዚህም ምክንያት ነው በእውቀትም በአስተሳሰብም የበሰሉ ዜጎቻን በአሸባሪነት የመፈረጅ እድላቸው ከፍተኛ የሆነው። የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በርካታ የሀገራችን ምርጥ ዜጎች የዚህ የተዛነፈ ትርጓሜ ሰለባ ሆነዋል። ተስፋ የሚጣልባቸው በርካታ ወጣቶች በዚህ ህገ-ወጥ ህግ እና የተሳሳተ ትርጓሜ ምክንያት የወጣትነት እድሜዓቸውን በእስር ቤት እንዲያሳፉ ተገደዋል። ከዚያ የበዙት ደግሞ በቃሉ ተሸማቀው፤ በሚያስከፍለው ዋጋ ተሸብረው ራሳቸውን እንዲደብቁ ተደርገዋል።
ለመሆኑ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ምርጥ ዜጓቿ በአሸባሪነት ስም ወህኒ እየተወረወሩ ሲሰቃዩ ምላሻችን ምን ሊሆን ይገባል? እስከመቼ አስተዋይ፣ አርቆ አሳቢና አመዛዛኝ የሆኑ መሪዎቻችንን ለወያኔ ፋሽቶች እየገበርን እንኖራለን? ሀገራችን ይህን ኪሳራ የመሸከም አቅም አላት?
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔን ለማስወገድ የተሻለ ነው ብሎ ያመነበት የትግል ስልት – ሁለገብ የትግል ስልት ነው። በዚህ የትግል ስልት መሠረት ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት እና ሕዝባዊ አመጽ ተደጋግፈውና ተናበው መሄድ አለባቸው ብሎ ያምናል። ስለሆነም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በአመቸውና በሚያምንበት መንገድ ለትግሉ አስተዋጽኦ የማበርከት እድል አለው።
በዚህም መሠረት ለሀገር፣ ለትውልድ ድህንነት ዋጋ ለመክፈል እና ለገዛ ራሳችን ህሊና ታማኝ ለመሆን በወያኔ “አሸባሪ” ለመባል መድፈር የትግላችን አንዱ አካል አድርገን መቁጠር ይኖርብናል። በወያኔ “አሸባሪ” መባል የሚያሸማቅቅ ሳይሆን የሚያኮራ፤ ለታላቅ ኃላፊነት እና ሕዝባዊ አደራ በእጩነት የሚያቀርብ መሆኑን በራሳችንም በማኅበረሰባችንም ውስጥ ማስረጽ ይኖርብናል። “አሸባሪ” የሚለው ቃል በወያኔ ተግባር መሠረት ሲተረጎም “ለሀገርና ለትውልድ ደህነት የሚጨነቅ ምርጥ ዜጋ“ ማለት እንደሆነ ማስተማር ይገባናል።
ወያኔ ወደ ሕዝብ የሚወረውረውን ጦር መልሰን ወደ ራሱ መወርወር ይኖርብናል። ወያኔ አሸባሪነት ዜጎችን ለማጥቂያ እያዋለው መሆኑ ተረድተን እኛ በዚህ ስያሜ መሸማቀቅ ሳይሆን፣ መኩራትና መልሰን ወያኔን ማሸማቀቅ ይኖርብናል። በውጭ አገራት እየተስፋፋ የመጣው የወያኔ ሹማምንትን የማሸማቀቅ ዘመቻ በኢትዮጵያ ውስጥም መጀመር ይኖርበታል።
ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽ ሲቀናጁ ድላችንን ያፈጥናሉ። በወያኔ “አሸባሪ” መባል የመልካም ዜግነት ምስክርነት እንደሆነ በሙሉ ልባችን እንቀበል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Wednesday, August 13, 2014

በምእራብ ኢትዮጵያ ለኩምሩክ ድንበር አቅራቢያ ጦርነት ተካሄደ


ከወያኔያዊ ምርጫ በፊት የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ሊያሰጋ ይችላል ሲሉ ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።


ያኔ ራሱን ለማንገስ ከሚጠራው ምርጫ በፊት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር አከባቢዎች ጦርነት ሊካሄድ ይችላል ሲሉ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።በተለያዩ አጋጣሚዎች የተነሱ የሳተላይት ፍቶዎች በማስረጃነት በመጥቀስ ይህን ሰሞን በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከአፍሪካ ህብረት ሰዎች እና ከአከባቢው የፖለቲካ አዋቂዎች ጋር የተለያዩ ስብሰባዎችን የሚያካሂዱት ዋናው የዚሁ ጦርነት ስጋትና አከባቢው ላይ ብሄራዊ ጥቅማቸው ላይ ምን ሊከሰት ይችላል የሚለውን በመገምገም ላይ መሆናቸው ታውቋል።

ዲፕሎማቶቹ የአሜሪካ መንግስት የሲአይኤን ሪፖርት ተከትሎ በትራንስፖርት ቢሮአቸው አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ የአየር በረራ የሚከለክል ደንብ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፤ የዚህ ጉዳይ ዋነኛ ምክንያት ደሞ አከባቢው ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መሆኑና በጦርነት ቀጠና የተመዘግበ ድንገት ጦርነት ይነሳል የሚል ግምት የተወሰደበት መሆኑ በአከባቢው ከፍተኛ የሆነ ከባድ መሳሪያዎች ታንኮች እና ብረት ለበስ አውዳሚ የጦር መሳሪያዎች የተከማቹ በመሆኑ ጦርነት አይቀሬ ስለሆነ በቋፍ ላይ ባለ የጦርነት ቀጠና ላይ አየር ማብረሩ ስጋት እንደሆነ ይናገራሉ፡፤ስለዚህ እንደ ዲፕሎማቶቹ እምነት ከወያኔያዊው ምርጫ በፊት የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ያስጋል።

በምእራብ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ጉምዝ ወደ ድንበር ከተማው ኩምሩክ አክባቢ በግምት 50 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የወያኔው መከላከያ ሰራዊት ካምፕ አቅራቢያ በሰራዊቱ እና ከደቡብ ሱዳን ሰርገው ገብተዋል በሚባሉ ሃይሎች መካከል 3 ሰአታት ጦርነት መካሄዱን አንድ የምእራብ እዝ መኮንን በላኩልኝ መረጃ ገልጸዋል።

ወታደሮቹ በክምፑ አከባቢ ቅኝት በሚያደርጉበት ጊዜ ድንገት የመጡ ሰርጎቦች የተባሉ ሃይሎች አከባቢውን በመውረር ከባድ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን 26 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲግደሉ በርካቶች ቆስለዋል። በዚህ የሰአታት ጦርነት እንደ መኮንኑ አባባል ከተዋጊዎቹ ወገን ጥልው የሸሹት ሁለት ሬሳ ብቻ ነው ብለዋል።



ምንሊክ ሳልሳዊ