Sunday, September 28, 2014

▶ EU Human Rights Committee hearing on Andargachew Tsege sep,24.2014

የአውሮፓ ህብረት የሰብአዊ መብት ኮሚቴ ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ናይን ብሎገሮች እንዲሁም በ2009 አ.ም
ወጣው አንቲ ቴሬሪስ ሎው ተገን በማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርሰውን  የሰብአዊ መብት እረገጣና
በኢንተር ኔት ላይ የሚደረገውን ጠላፋ፣የጋዜጠኞችን ማሳደድ ተቃዋሚዎችን በውሸት የተመሰረተ ክስ ማሰርና ማሳደድ
ተግባሩን  ሲሰማ ዋለ




Monday, September 22, 2014

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስራ አጦች በየቤታቸው ለማባበያ ካርድ እያደለ ነው


September 22,2014
• ‹‹ምርጫ ሲደርስ የሚደረግ ነው››
• ‹‹ለኢህአዴግ ጥላቻ አለሽ በሚል አንመዘግብም ብለውኛል››

ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሴክተር ለስራ አጦች ‹‹ስራ እንሰጣችኋለን›› በሚል በየቤታቸው የስራ ፈላጊዎች መለያ መታወቂያ ካርድ እያደለ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
የስራ ፈላጊዎች መለያ መታወቂያ ካርዱ የሚሰጠው የተማረም ሆነ ያልተማረ እስከ 60 አመት እድሜ ለሚገኝ ማንኛውም ስራ አጥ ነው እንደተባለ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ከዩኒቨርሲቲ የተመረቁት አዲስ ተማሪዎችና ከአሁን ቀደም ተመርቀው ስራ ያላገኙ ተማሪዎች ‹‹ቀበሌ መጥታችሁ ተመዝገቡ›› እንደተባለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ካርድ የተሰጣቸው ነዋሪዎች የመዘገቧቸው ሰዎች ‹‹ስራ እንሰጣችኋለን፤ ተከታታይ ስብሰባ ስላለ ስራ ለማግኘት ስብሰባውን መሳተፍ ይጠበቅባችኋል›› እንዳሏቸው ገልጸዋል፡፡ካርዱ ከተሰጣቸው መካከል ያልተማሩም የሚገኙበት ሲሆን በተለያየ መስክ በዲግሪ ተመርቀው ስራ ያጡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጨምሮ በርካታ ስራ አጦች እንዳሉ በመጠቆም ስራ የማግኘት ተስፋቸውን እንዲገልጹልን የጠየቅናቸው ነዋሪ ‹‹ስራ እንሰጣችኋለን ብለዋል፤ ከሰጡን ማየት ነው፡፡ ግን ለምርጫ ሳይሆን አይቀርም›› ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ከአሁን ቀደም በቤተሰብ ደረጃ 15 ተደራጁ ተብለው ሳይደራጁ የቀሩ የቤት እመቤት ‹‹ከአሁን ቀደምም በቤተሰብ ደረጃ 15 እንድንደራጅ ተጠይቀን ነበር፡፡ አልተደራጀንም፡፡ ምን አልባት አልሰራ ሲል ይሆናል፡፡ ያው ምርጫ ሲመጣ ብዙ ነገር ይመጣል›› ሲሉ የተሰጣቸው ካርድ የምርጫ ማባበያ ሊሆን እንደሚችል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡በሌላ በኩል ለገዥው ፓርቲ አሉታዊ አመለካከት አላቸው የሚባሉ ዜጎች እንዳይመዘገቡ የተደረገ ሲሆን እንድትመዘገብ በተጠየቀችበት ወቅት ‹‹ካርዱን ተቀብለን ስንሰበሰብ አባል እንድንሆን አትጠይቁንም?›› የሚል ጥያቄ በማንሳቷ ‹‹ለኢህአዴግ ጥላቻ አለሽ፡፡ አንመዘግብሽም›› እንደተባለች ገልጻለች፡፡
ምንም እንኳ መዝጋቢዎቹ ‹‹ሊስትሮም ቢሆን ስራ ካለው እንዳትመዘግቡ›› መባላቸውን የሚገልጹ ቢሆንም ሱቅና በመሳሰሉት የንግድ ስራዎች የተሰማሩ ዜጎች ‹‹ስራ አጥ›› ተብለው እየተመዘገቡ ይገኛሉ፡፡ ይህም ስራ ከመስጠት ይልቅ ለምርጫ ለማባበልና መረጃ ለመሰብሰብ ሊሆን እንደሚችል ካርድ የተሰጣቸው ነዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

 

Sunday, September 21, 2014

▶EthioSwedish Task Force Decorated woyane Ambassader with Rotten Fish eggs


EthioSwedish Task Force with coopration with Ogaden Association in Stockholm hade embarasd the Woyane Ambasader in Stockholm ,decorated with rotten fish and eggs over here car !! watch Video



Saturday, September 20, 2014

በሰሞኑ የኢህአዴግ ስልጠና ላይ የመምህራኑ ምላሽ

September 20,2014

ከመስከረም 5,2007 . ጀምሮ መንግስት የአቅም ግንባታ እያለ የጠራው ስልጠና እየተካሄደ ይገኛል:: ገዢው ፓርቲ ስልጣን ከያዘበት 1983 . ጀምሮ የተለያዩ ስልጠናዎችን ሲሰጥ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን የዘንድሮውም ከበፊቶቹ ምንም የተለየ ሀሳብ ያለተነሳበት እና ድግግሞሽ የበዛበት ብሎም ገዢው ፓርቲ ለኢትዮጵያዊነት እና ለመምህርነት ሙያ ያለውን አይን ያወጣ ጥላቻ ያሳየበት ነበር::

ስልጠናው እንደተጀመረ መምህራኑን የማሰልጠን ድፍረቱን እና እድሉን ያገኙት አቶ ኤፍሬም ግዛው የተሰኙ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ናቸው:: አቶ ኤፍሬም በንግግራቸው ወቅት በተደጋጋሚ ሀገሪቷ ከየትኛውም ዘመን በተለየ በኢኮኖሚያዊ እድገቱ እና ሰላም በማረጋገጡ ዘንድ ስኬታማ መሆን እንደቻለች ለማስረዳት ሞክረዋል::

እንደ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ እምነት ከሆነ የኢህአዴግ ትልቁ ችግር እራሱን ሞቶ ከተቀበረው የደርግ ስርአት ጋር እያነጻጸረ ህዝቡን ለመሸወድ የሚያደርገው ቀቢጸ ተስፋ ነው:: እድገት ውድድር መሆኑን እናምናለን ሆኖም ይህ ስርአት መወዳደር ካለበት ባላፉት 24 አመታት በእነጋና ቦትስዋና እና ደቡብ አፍሪካ ከታዩት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገቶች ጋር እንጂ ከሞተ ስርአት ጋር ሊሆን አይገባውም:: ሌላው የሰላም ጉዳይ ሰላም አንድ አይነት ትርጓሜ የለውም የጥይት ድምጽ ወይም የቦንብ ፍንዳታ አለመስማት ብቻውን ሰላም አለ ሊያስብል የሚችልበት ምንም አይነት መርህ አይኖርም::

ማሰብ ለቻለ እና ህሊና ላለው ሰው አዛውንቶች እና ህጻናት ጎዳና ወድቀው መመልከት ሰላምን ይነሳል, በሀገራቸው መኖር ስላልቻሉ በስደት አለም የበረሀው ሙቀት የባህር ራት የሆኑት ኢትዮጵያዊያንን ጉዳይ መስማትም ሰላምን ይነሳል, አንድ የሚበላው ያጣ ህጻን ከውሻ ጋር ተሻምቶ ሲመገብ መመልከትም ሰላምን ይነሳል:: በአጠቃላይ በግልጽ የጥይት ድምስ አለመስማት እንደስኬት ልንቆጥረው የሚገባ አይደለም ድምጽ ሳይሰማ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ጊዜ ይቁጠራቸው::  ግለሰብ ናቸው::

እኚህ ግለሰብ በተደጋጋሚ ነፍጠኛ, ጠባብ ትምክህተኛ እና ጨለምተኛ በማለት መምህራኑን ብሎም ሰፊውን የሀገራችንን ህዝብ ሲሳደቡ ውለው ከርመዋል ነገር ግን እንደ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ እምነት ከሆነ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ያለው ብቸኛው ነፍጠኛ, ጠባብ ትምክህተኛ እና ጨለምተኛ ለእኔ ብቻ ተዉት እያለ ያለው ኢህአዴግ ብቻ እና ብቻ ነው::
ከዚህ ስልጠና ለመታዘብ እንደቻልነው ገዢው ፓርቲ ትልቅ የተማሩ ሰዎች እጥረት አለበት ይህንንም እራሱ ኢህአዴግ ሆን ብሎ ያደረገው በመሆኑ እነደ መምህር የዚህችን ሀገር የነገ እጣ ፋንታ ስንመለከት ያስፈራል::

በመጨረሻ | መምህራን ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥል ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ጥሪውን እያስተላለፈ ሌሎች አካላትም ከመምህራኑ ጊዜያዊ ኮሚቴ ጋር ይቆሙ ዘንድ ጥሪውን ያቀርባል::
ድል ለመምህራን
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ
መስከረም 10,2007 .
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ



Thursday, September 18, 2014

መስከረም 7 ቀን 2007 ዓ.ም.                                                                                                                            

የአገራችን የኢትዮጵያን በትረ ሥልጣን በጠመንጃ ኃይል የተቆጣጠረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የሥልጣን እድሜውን ለማራዘም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየወሰደ ያለውን እሥራትና ግድያ አጠናክሮ መቀጠሉን የሚያጋልጡ ማስረጃዎች በየጊዜው ከራሱ ከአገዛዙ እየሾለኩ በመውጣት ላይ ናቸው።
መስከረም 5 ቀን 2007 ዓም በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን በምስል ተደግፎ የቀረበው በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ከነዚህ ማስረጃዎች አንዱ ነው ።
የወያኔን አገዛዝ ይቃወማሉ የተባሉና በኦጋዴን ክልል ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች ጋር ንኪኪ አላቸው የተባሉ እነዚያ የጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባ የሆኑ ምስኪን ዜጎች አስከሬን መሬት ለመሬት እየተጎተተ አንድ ቦታ እንዲከማች ሲደረግ፤ አስከሬኑን ለመሰብሰብ ከታዘዙት የአካባቢው ነዋሪዎች አንዱ የገዛ ወንድሙ አስከሬን ከሚጎተተው መሃል እንደነበረ መስማት ህሊናን የሚሰቀጥጥና የወያኔ የጭካኔ እርምጃ አቻ የሌለው ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው።

በደርግ ዘመን ቤተሰብ የተገደለበትን ሰው አስከሬን ለማግኘት የጥይት ዋጋ ለመክፈል ይገደድ ነበር በማለት ሥርዓቱን በነጋ በጠባ የሚወነጅል አገዛዝ ከሚወነጅላቸው ሥርዓት በባሰ በኦጋዴን የገደለውን ንጹህ ዜጋ አስከሬን የገዛ ወንድሙ መሬት ለመሬት እንዲጎትተው አድርጓል። በዚህም ህወሓት በሰብዓዊነት ላይ ከቀደምቶቹ ሁሉ የከፋ የሚሰቀጥጥ ወንጀል ፈጽሟል። ቀደም ሲል በበደኖ፤ በአርሲ፤ በአርባ ጉጉ፤ በሃዋሳ ፤ በጋምቤላ እና ድህረ ምርጫ 97 በአዲስ አበባና ሌሎች የአገሪቱ ከተሞች ነዋሪዎች ላይ በወያኔ ልዩ ትዕዛዝ ተመሳሳይ የጅምላ ጭፍጨፋዎች ተካሂደዋል። ይህ ሁሉ ወንጀል እየተፈጸመብን አስከዛሬ ወያኔን በጫንቃችን ተሸክመን ለመኖር የተገደድነው እነዚሁ ጥቂት ዘረኞች ሕዝባችንን በዘር፤ በቋንቋና በሃይማኖት በመከፋፈላቸው አንዱ የኅብረተሰብ ክፍል ሲጠቃ ሌላው በዝምታ የሚመለከትበት ሁኔታ በመፈጠሩ ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በኦጋዴን ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ይህንን አረመኔያዊ እርምጃ አጥብቆ ያወግዛል። ጊዜው ሲደርስ የዚህ ወንጀል ፈፃሚዎች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ብሎ ያምናል። ስለሆነም ወያኔ ሕዝባችንን አቅም ለማሳጣት ላለፉት 23 አመታት በኅብረተሰባችን መካከል የገነባውን የጥርጣሬና የጥላቻ ግንብ በመናድ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በኦጋዴንና በሌሎች የአገራችን ክፍሎች ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃና እልቂት ለማስቆም እንዲችሉ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል።
ኦጋዴን ውስጥ ለፈሰሰው የንጽሃን ደምና በሰብዓዊነት ላይ እየተፈጸመ ላለው ወንጀል ተጠያቂው ሥልጣንን በኃይል የሙጥኝ በማለት በአገርና በሕዝብ ሃብት ዘረፋ ላይ የተሰማራው ጥቂት የህወሃት አመራር መሆኑ አያጠያይቅም። ይህንን ወንጀለኛ ቡድን ለፍርድ ለማቅረብ ንቅናቄዓችን ግንቦት 7 የሚያደርገውን ሁለገብ ትግል ለፍትህ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ የቆመ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲቀላቀል በዚህ አጋጣሚ ጥሪ ቀርቦለታል።



ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Tuesday, September 16, 2014

የኢትዮጵያ ህዝብ ፍርድህ ምንድነው?

አኝዋክ የፍትሕ (ጀስቲስ) ም/ቤት ኦሞት ኦባንግን ለፍርድ ያቀርባል!!

Wanted omot obang olum
September 14,2014
ከአኝዋክ ጀስቲስ ካውንስል የተሰጠ መግለጫ  
Anuak-Justice-Council
የህወሃት ፍጹም ታማኝ ነበር። በተለያዩ ሃላፊነቶች በህጻናት፣ በወንድሞቹ፣ በእህቶቹ፣ በእናቶቹ፣ በአባቶቹ 
አጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በሰራው ወንጀል በህግ ይፈለጋል፣ በህግ የሚፈልጉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ 
ሳይሆኑ ዓለም አቀፍ የፍትህና የመብት ተሟጋቾች ናቸው። ህወሃትን ክዶ በስደት ከሚገኝበት አገር እጁን 
እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቦለታል። ይህ “ሰው” በጋምቤላ ክልል የፖሊስና የጸጥታ ሃላፊ የነበረ። የደህንነት አመራር ነበረ። 
ክልሉን በፕሬዚዳንትነት ለዓመታት የመራ፣ በጅምላ ለተጨፈጨፉት የአኝዋክ ንጹሃን ደም ቀዳሚ ተጠያቂ ነው – ኦሞት ኦባንግ !!
ኦሞት በዴሰምበር 13/2003 በጅምላ ጄኖሳይድ ለተፈጸመባቸው ከ424 በላይ የአኝዋክ ንጹሃን ዜጎች፣ በአስር ሺህ 
የሚቆጠሩ ዜጎች ስደት፣ መሬታቸው በግፍ ለተነጠቁና በጠመንጃ ለተፈናቀሉ ዜጎች ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆኑን ከአገራችን
 የቀበሌ ነዋሪ ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ ደረጃ በማስረጃ የሚታወቅ ነው። ኦሞት በጋምቤላ ለፈሰሰው የንጹሃን ደም “ነጻ” ሊሆን 
የሚችልበት አንድም አግባብ የለም። ድርጅታችን አኙዋክ ጀስቲስ ኦሞትን ፍትህ አደባባይ እንደሚያቆመው ቅንጣት ያክል 
የማይጠራጠረውም ለዚህ ነው። ከተሰወረበት ፊሊፒንስ አድኖ ለመያዝ አስፈላጊው ስራ እየተሰራ ነው።
ጄኖሳይድ ዎች፣ የሂውማን ራይትስ ዎችና ከአኝዋክ ጀስቲስ ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩት የአይሲሲ /የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት
 ጠበቆች/ በጋራ ኦሞት ኦባንግን ህግ ፊት ለማቅረብ እየሰሩ ነው። ኦሞት ከተሸሸገበት ፊሊፒንስ ወጥቶ ህግ ፊት እንዲቀርብ የሚደረገው ግፊት 
ባየለበት በአሁኑ ሰዓት የኦሞት አደባባይ ወጥቶ “ታግሎ አታጋይ” ለመሆን መወሰኑ ዜና የሆነበት ምክንያት አልገባንም።
omot wanted“የኢትዮጵያ ህዝብ ፍረድ፣ ፍርድህ ምንድን ነው?” ብለን ስንጠይቅ በህዝብ
 ዘንድ ያለውን የፍትህ ጥማት ዘንግተን አይደለም። እንደ ኦሞት አይነት በደምና 
በሙስና የተጨማለቀ ሰው ራሱን ነጻ ለማድረግ የሚናዘዘውን ኑዛዜ በጥንቃቄ 
እንድትመለከቱት ስለምንፈልግ ነው። ኦሞት ለኢሳት ከሰጠው መግለጫ ላይ ተቀንጭቦ 
“በሰበር ዜና” በተላለፈው መልዕክት “ኦሞት ወያኔን ለመታገል መወሰኑንና፣ በአኝዋክ 
ንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አስመልከቶ ወንጀሉን የፈጸሙትን ክፍሎች 
ዝርዝር ሰጥተዋል” መባሉን ሰምተናል።
ኦሞት ኦባንግ ከክልል ፕሬዚዳንትነቱ ተነስቶ ወደ ፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር 
ደዔታነት ከተዛወረ በኋላ አገር ጥሎ እንደኮበለለ አስቀድሞ ሊያነጋግረን ሞክሮ ነበር። 
ወያኔንን ለመታገል መወሰኑን ገልጾልን ነበር። አስፈላጊውን መረጃ ለመስጠት ተማጽኖንን
 ነበር። በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተመሰረተበትን ክስ እንድናጠራለት/ነጻ እንድናደርገው 
ሊማጸነን ሞክሮ ነበር። እኛ ግን እሱን ህግ ፊት ከማቅረብ የዘለለ ሃሳብና ፍላጎት 
ስላልነበረን “እጅህን ለፍትህ ስጥ” የሚል መልስ ነበር የመለስንለት። “የዓለም ዓቀፉ 
የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ቀርበህ ተናዘዝ” ነበር ያልነው።
ትናንት በወገኖቹ ደም አጥንት ላይ ቆሞ ሲደንስ፣ በኢህአዴግ መገናኛዎች ላይ የወገኖቹን
 ነፍስ ሲረግም የነበረ ወንጀለኛ በየትኛውም መስፈርት ለወገኖቹ ነጻ መሆን ይታገላል 
ብለን አናምንም። መታገልም ከፈለገ ራሱን ቅድሚያ ህግ ፊት አቅርቦ ነጻ ሊያደርግ ይገባል
 የሚል አቋም አለን። ትግል የሚመራው ስብዕና ባላቸውና በህዝብ ዘንድ ከበሬታ ባላቸው ወገኖች በመሆኑ አቶ ኦሞት ዲያስፖራውን ለመቀላቀል
 ያቀረበውን ምልጃ አበክረን እንቃወማለን። ዳግም ጄኖሳይድ አንለዋለን። በዚሁ መነሻ ጥንቃቄ ሊወሰድ እንደሚገባም እናሳስባለን። በቅርቡ 
ይፋ በሚሆነው የህግ አካሄድ ሁሉም ነገር ስለሚገለጥ ከሁሉም ወገን ማስተዋል ሊኖር እንደሚገባ ደግመን ደጋግመን ለመግለጽ እንወዳለን።
 እውነታው እየታወቀ እንደ ኦሞት ኦባንግ ካለ ወንጀለኛ ጋር ተባብሮ መሥራት የወንጀሉ ሰላባ የሆኑትን ንጹሃን የመካድ ያህል ሆኖ ይሰማናል። 
እንደ ኦሞት አይነት ወንጀለኞችን ወደ ትግል ማግበስበስ ኪሳራ ከመሆን እንደማያልፍ እናስገነዝባለን። ሳይውል ሳያድር እናየዋለን።
ኦሞት ኦባንግ በአኝዋክ ጭፍጨፋ ላይ እጃቸው አለበት የተባሉትን ሰዎች ሰም ዝርዝር መስጠቱ ተጠቁሟል። ድሮ ህግ ላይ ቀርቦ በማስረጃነት 
ሚዛን ደፍቶ መለስ ዜናዊ እንዲከሰስ ያስፈረደው ሰነድ ከመዘጋጀቱ በፊት ይህንን መሰሉ ትብብር ቢኖር በመጠኑም ቢሆን ባደነቅን ነበር። 
ዛሬ ሁሉም መረጃዎች ህዝብና ህግ ዘንድ ቀርበው ፍትህ በሚጠበቅበት ወቅት ላይ ጩኸትህ ከቶውንም አይገባንምና ኦሞት ኦባንግ መጀመሪያ 
ራስህን ነጻ እንድታደርግ እንመክርሃለን። ራስህን ሳትገደድ ለህግ አስረክብ!! ከዚህ ውጪ አሁን ማስተባበያ ማቅረቡ ጊዜው አይደለም። 
ለሂውማን ራይትስ ዎች የሰጠሃቸውን የጽሁፍ መልስ አንተነትህን ሊሸሽግ አይችልምና ካለህበት ታድነህ ህግ ፊት ከመቅረብህ በፊት ጊዜውን 
ተጠቀምበት።
ከአኙዋክ ጀስቲስ ካውንስል ጋር
መስከረም 13 ቀን 2014

የሽዋስ አሰፋ የርሃብ አድማ አደረገ


በማዕከላዊ ምርመራ ታስሮ የሚገኘውና የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሽዋስ አሰፋ የአራት ቀን የርሃብ አድማ አደረገ፡፡ የሸዋስ ማክሰኞ ጱግሜ 4 ጀምሮ አዲሱን አመት በርሃብ አድማ ያሳለፈ ሲሆን ቅዳሜ መስከረም 3/2007 ዓ.ም ምግብ እንደቀመሰ ባለቤቱ ወይዘሮ ሙሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡ አቶ የሽዋስ የርሃብ አድማ ያደረገው ከታሰረበት ሐምሌ 1/2006 ዓ.ም ጀምሮ ከጠበቃው ጋር ከአንድ ጊዜ በላይ መገናኘት ባለመቻሉና ዘመድ አዝናድ እንዲሁም የኃይማኖት አባት እንዳይጎበኘው በመከልከሉ ነው፡፡
የሽዋስ አሰፋ በባለቤቱ ብቻ ከሳምንት አንድ ቀን እንዲጎበኝ የተፈቀደለት ሲሆን የርሃብ አድማ ባደረገባቸው ቀናት ባለቤቱ ምግብ ስታስገባ ለየሸዋስ ምግቡ እንደደረሰው ተደርጎ ባዶ ሳህን ሲደርሳት ቆይቷል፡፡ ባለቤቱ የበዓል ቀን ልትጎበኘው በሄደችበት ወቅት ‹‹ወጥቷል›› ተብላ የተመለሰች ሲሆን በማግስቱ ልጆቹን ይዛ ልትጠይቅ ስትሄድም ‹‹ስብሰባ ላይ ናቸው!›› በሚል እንዳታገኘው በመደረጓ ለ15 ቀናት ሳትጠይቀው ቆይታለች፡፡

አቶ የሽዋስ ‹‹የርሃብ አድማውን ያደረኩት ቤተሰብና ጠበቃዬ እንዳይጠይቁኝ በመከልከላቸው ነው፡፡ ለምን እንዲጠይቁኝ አይደረግም? ብዬ ጥያቄ ሳቀርብ ማንም አልመጣም፡፡ ቢመጣ እንድትጠየቅ እናደርግ ነበር፡፡›› የሚል መልስ እንደሚሰጡት ገልጾአል፡፡ በሌላ በኩል ጠበቃው ተማም አባ ቡልጉ የሽዋስን ለማግኘት በተደጋጋሚ ወደ ማዕከላዊ አቅንቶ የተለያየ ምክንያትና መሰናክል እየፈጠሩ ሳያገናኙት እንደቀሩ ገልጾአል፡፡
ጠበቃ ተማም ‹‹ለበርካታ ቀናት አመላልሰውኛል፡፡ ለምሳሌ አንድ ቀን ረቡዕ ጠዋት ሄድኩኝ፡፡ መብትን መለመን ጥሩ ባይሆንም እንዲያገናኙኝ ብለምናቸውም ሊያገናኙኝ አልቻሉም፡፡ ከሰዓት እንድመለስ ነግረውኝ ከሰዓት ብሄድም አሁንም ሊያገናኙኝ አልቻሉም፡፡ ለቀጣይ ረቡዕ ቀጠሩኝ፡፡ አሁንም ረቡዕ ስሄድ የተለያየ ምክንያት እየፈጠሩ ሊያገናኙኝ አልቻሉም፡፡ እንዲያውም ‹‹ምን ታመጣለህ አናገናኝህም!›› አሉኝ፡፡ ብዙ ጥረት ባደርግም ሊያገናኙን አልቻሉም፡፡ የሚገርመው የዳንኤልና የሃብታሙ ጠበቃ የሆኑ ሌሎች ጓደኞች አሉኝ፡፡ አንድ ሰው ከአንድ ጠበቃ በላይ ሊኖረው እንደሚችል እየታወቀና እኔም ደንበኞቼን ማግኘት እንዳልችል ከልክለውኝ እነሱን ግን ‹‹እኛ የምናውቀው ተማምን ነው›› ይሏቸዋል፡፡ እኔ ስሄድ ደግሞ ደንበኞቼን እንዳላገኝ እደረጋለሁ፡፡›› ሲሉ ሁኔታውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
የሽዋስ ምግብ ሲገባለት ምግቡን የሚያደርሱለት አካላት መልሰው ለሚስቱ እንዲሰጧት ይነግራቸው እንደነበር የተናገረ ሲሆን የርሃብ አድማ ላይ እንደሆነ እንዳይታወቅ ምግቡን የበላ አስመስለው እቃውን ባዶ አድርገው መመለሳቸው አሳፋሪና ቅጥ ያጣ አፋኝነት መሆኑን መግለጹ ታውቋል፡፡ የሽዋስ አሰፋ በርሃብ አድማው ምክንያት ሰውነቱ እንደተዳከመ ባለቤቱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡
ምንጭ፡- ነገረ ኢትዮጵያ