28 አፕሪል 2013
ሄለን ንጉሴ
ለአባይ ግድብ በሚል በተለያዩ ሃገራት በሚገኙ የወያኔ ጀሌዎች እየተደረገ ያለው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በተለያዩ ሃገራት በሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ከአባይ ግድብ በፊት በሃገራችን ውስጥ የሚፈፀመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዲገደብና ከግድቡ በፊት ቀዳሚ የሆኑ ነገሮች ትኩረት እንዲሰጣቸው በማለት በሚያቀርቧቸው ጥያቄዎችና የተቃውሞ ሰልፎች የገንዘብ ማሰባሰቢያው መክሸፉ ይታወሳል።
በቅርቡ በ20 አፕሪል 2013 በኖርዌ ስታቫንገር እየተባለ በሚጠራው ከተማ በስቶኮልም ስዊድን አምባሳደር የሆኑት ወሮ መብራትና አንድ የዲያስፖራ ተወካይ ነኝ ባይ ባልደረባቸውን አስከትለው ገንዘብ ሊሰበስቡ መጥተው ቁጥሩ በርከት ያለና ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ ለተቃውሞ በመጣው ኢትዮጵያዊ ክፉኛ ተዋርደው የነሱን ባንዲራ አይናቸው እያየ በመሸፈን በትክክለኛው የኢትዮጵያ ባንዲራ በመተካትና በማሸማቀቅ አንዲት ሳንቲም ሳይሰበስቡ ስብሰባው በፖሊስ ሃይል መሰረዙ ይታወሳል።
የድፍረታቸው ድፍረት እንደገና በኖርዌ ኦስሎ ከተማ በዛሬው እለት 28 አፕሪል 2013 ገንዘብ ሊሰበስቡ መጡና ከስታቫንገር እጅጉን በበለጠ ሁኔታ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸው እንደለመዱት ውርደታቸውን ተከናንበው ሌባ ሌባ በሚል የህዝብ አጀብ ስብሰባቸው ከፍተኛ ቁጥር ባለው የፖሊስ ሃይል ተበትንዋል።
No comments:
Post a Comment