በፌብርዋሪ 27, 2014 የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማህበር በኖርዌ የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የአኗኗር ሁኔታ በተመለከተ የውይይት መድረክ በማዘጋጀት ስደተኞችን አወያየ። በዝግጅቱ ላይ በተለያዩ የኖዌ ከተሞች ነዋሪ የሆኑ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉ ሲሆን ስደተኞቹ ሐገራቸውን ጥለው የወጡበትን ምክንያት ሲናገሩ በሐገራቸው ባለው ጨቋኝ መንግስት በደረሰባቸው የተለያየ በደል መሆኑን ጠቁመው ወደ ኖርዌ ከመጡ በኋላ የኖርዌ መንግስት የጥገኝነት ጥያቄያቸውን በአግባቡ እንደማይመለከት እና በርካታ ኢትዮጵያውያን የስደት ጥያቄያቸው ውድቅ እንደሚሆን ተናግረዋል።
ይህ ሊሆን የቻለበትንም ምክንያት ሲያብራሩ የወያኔ መንግስት ለኖርዌ በሚሰጠው የተሳሳተ መረጃ በሃገራቸው ዲሞክራሲ እና ሰላም አለ ምንም የፖለቲካ ችግር እንደሌለ አድርጎ መረጃ ስለሚያቀርብላቸው ስደተኞቹ እዚህም እየተበደሉ መሆኑን ገልፀዋል በአንፃሩ ደግሞ የወያኔ መንግስት እዚህ ስደት ጠይቀው በሚኖሩበት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሰላይ መድቦ ስደተኞችን እንደሚያሰልል የራሳቸው የኖርዌጅያን PST የተባለው የፖሊስ የስለላ ድርጅት ማጋለጡንም አስረድተዋል።
በዚህ ውይይት ላይ ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ እና ጋዜጠኛ ደረጀ ሐ/ወልድ በእንግድነት የተገኙ ሲሆን ስደተኞቹ ከሁሉ በላይ በሰው ሃገር መጥቶ ስደት ከመጠየቅ ይልቅ ያሰደዳቸውን መንግስት ከስልጣን በማውረድ በኢትዮጵያ ሃገራችን ዲሞክራሲያዊ መንግስት ተመስርቶ በሐገራቸው ለመኖር ከመቼውም ጊዜ በላይ ለሐገራቸው ለመታገል ቆርጠው መነሳታቸውንና ሰደትን ከስር መሰረቱ ለማድረቅ በእልህ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
በመጨረሻም የሰው ሃገር የሰው መሆኑን አውቃለሁ በተስፋ እንጀራ እድሜዬን እገፋለሁ ነውና ነገሩ ሁላችንም በውጭ ተሰደን የምንኖር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ስደትን ከስሩ ነቅለን ለመጣል መፍትሄው አንድና አንድ መሆኑን እንወቅ እሱም ጠላታችን ወያኔ ብቻ ነውና የእኛን መበታተን የሚወድ ስለዚህ በርትተን ከታገልን የማናሸንፍበት ምንም ምክንያት የለምና በጋራ ጠላታችን ላይ እንዝመት ወያኔን አባረን ማንም ከሚወደው ሃገሩ ሳይሰደድ በሰላም ለመኖር እንተባበር።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
ሄለን/ከኖርዌ/
No comments:
Post a Comment