በመ/ር ታደሰ ቢተውልኝ፣ መ/ር ገብሩ ሳሙኤል ፣ ሽሻይ አዘናው እና አስገደ ገ/ስላሴ በዓረና ትግራይ ለ4 አመታት የቆዩ የተለያዩ ዝንባሌዎችና ባህሪ በመከሰታቸው ወደ አባላትና ህዝብ ያልወጣ ውስጣዊ ትግል ሲካሄድ ቆይቷል። እነዚህ ይታዩ የነበሩ ግልጽነት አለመኖር ፤ የዲሞክራሲ ጥበትና አሳታፊ አለመሆን ፤አባታዊነትና አምባገነንነት፤ ድርጅታዊ አሰራር አለመኖር ወዘተ ነግሰው እንደቆዩ እንዲሁም እንደ ብርሃኑ በርሀ የድሮ ም/ሊቀ መንበር ያሁኑ ሊቀ መንበር በፈጠሩት ኢ-ዲሞክራሲያዊ አሰራር ምክንያት ከተራ አባላት እስከ ከፍተኛ የፓርቲው አመራር ከፓርቲው ራሳቸው ተገልለዋል(ራሳቸው አግለዋል) :: የአባላቱ መፍለስ ችግር ምንድነው ? ብለን እንዲፈታ ጥያቄ ብናነሳ ሰሚ ጀሮ ኣላገኘንም:: ይቅርና ተራ አባላት በማ/ኮሚቴና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባዎች ተነስተው በዲሞክራሲያዊና በመግባባት ተወያይተን እንድንፈታው በወቅቱ ሊቀ መንበር የነበሩ አቶ ገብሩ አስራት፤ ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ፤ የዛን ጊዜ ም/ሊቀመንበር ያሁኑ ሊቀ መንበር ብርሃኑ በርሄ ጠይቀን የሰማን አካል አልተገኘም :: እነዚህ ሰዎችና ሌሎች የነሱ ጥቂት አጃቢዎቻቸው ልክ በህወሓት አመራር ሁነው “እኛ ያልናችሁ አድርጉ” እያሉ ብዙ የትግራይ ወጣት እያከሰሙ እንደመጡ በኛ ላይም ለመፈፀም ሞክረው በትግላችን ያ የአባታዊነት ባህሪያቸው ግቡን ሳይመታ ቆይቷል :: ከጳጉሜ 2 እስከ 3/13/2005 3ኛ ጉባኤ ሲደረግ ብዙ አጀንዳዎች ተነስተው ፈጥረውት በቆዩት ቡድናዊነት ምክንያት በፓርቲው የነበሩ ፖሊሲዎች ፤አቋሞች ህገ ደንብና ፕሮግራም እንዲሁም ስለ የህወሓት ሰርጎ ገብ ባንዳዎች አደገኝነት ፤ ስለ ሃገራዊ አንድነት፤ ውህደት በሚመለከቱ በጥልቀት ተወያይተንበት ሳንተማመን በድፈንፍን ታልፏል :: በዛን ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎች በድፈንፍን እንዲታለፍ ያደረጉ
አቶ ገብሩ አስራት፣ ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ፣ ብርሃኑ በርሀና ሌሎች አጃቢዎች ነበሩ ::
ሁኔታው ጥራት ይኑረው አይኑረው የነበረው ጉባኤተኛ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ጥራት የሌለው አመራር መርጦ መጣ :: በኛ
በኩልም ሁኔታው በሂደት ይጠራል ብለን ለጉባኤ ክብር በመስጠት በነአቶ ገብሩ አስራትና ብርሃኑ በርሄ ቡድን ተሸነፍን ብለን ስሜት ሳንይዝ በሁሉም አቅጣጫ ፓርቲው የሰጠን የስራ ምድብ ከመስራት አልፈን በግላችንም በአደረጃጀት፣ በፕሮፖጋንዳና ፋይናንስ እየሰራን ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ በፓርቲው ያሉት ለአላማችን እንቅፋት የሆኑ አመለካከቶችና ባህርያት የህወሓት ሰርጎ ገብነትና የህወሓት ፋሽሽታዊ አፈና ሳይበግረን ፊትለፊት እየተጋፈጥን ደማችን በጎዳና እየፈሰሰ እንደ አቅማዳ እየታሰርን እየተፈታን እስካሁን ቆይተናል :: ልብ በሉ! ይህ ሁሉ የምናደርገው በውስጠ ፓርቲ ያሉ ችግሮች ይፈቱ ? ችግር አለ እያልን እያመለከትን ልዩነት ሳይገድበን ነበር እየታገልን የቆየን። በዘንድሮ የትግል ጊዚያችን ጎን ለጎን ግን
1. መምህር ገብሩ ሳሙኤል፣ የአረና ቁጥጥር ኮሚሽን አባል ብዙ ጊዜ በቃልና በፅሁፍ
2. መምህር ታደሰ ቢተውልኝ፣ የአረና ማእከላዊ ኮሚቴ 14 ገፅ ያለው ፅሁፍ 2 ጊዜ
3. ሽሻይ አዘናው፣ የአረና ማእከላዊ ኮሚቴ አባል 4 ጊዜ በፅሁፍ
4. አሰገደ ገ/ስላሴ አረና ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ እስከ 2005 መጨረሻ የአረና ስራ አስፈፃሚ የነበረ፣ አሁን ተራ አባል 7 ጊዜ
በጽሁፍ ፤ በፓርቲው ውስጥ ያሉ ችግሮች እንዲፈቱ ስናመለክት ቆይተን መልስ ለመስጠት ወይም በግለ ሰብ ወይም በቡድን ወይም
በአስቸኳይ የማ/ኮሚቴ ስብሰባ ከመፍታት ይልቅ እጅግ ጠንካራ ታጋዮች በ20/11/2006 ለመ/ር ገብሩ ሳሙኤል በሌለበት ለጠየቀው ጥያቄ ምክንያት የሆነው ሳይጠየቅ በድብቅ ስብሰባ በማካሄድ እስከ መጪው ጉባኤ ማለት ለ2 አመት ከቁጥጥር ኮሚሽን እንዲታገድ ተወሰነበት::
ሽሻይ አዘናው በጋዜጣ ለሰጠው መግለጫ በ14 ቀናት ውስጥ ማስተባበያ እንዲሰጥ ካልሰጠ ግን ከአመራርነቱም ሆነ ከአባልነቱ
እንዲባረር ፤ መ/ር ታደሰ ቢተውልኝ ለጻፈው የአስቸኳይ ግምገማ ጥሪ ጥፋት ተቆጥሮ የህወሓት ባንዳዎች እንዲባረር የውሳኔ ሃሳብ ሲያቀርቡ በአብላጫ ድምፅ በማስጠንቀቅያ እንዲታለፍ ከተወሰነባቸው በኋላ የፓርቲው ማስታወቂያቸው ትተውላቸው ከፓርቲው ሁለቱም የማ/ኮሚቴ አባላት ፓርቲውን ለቀው ወጥተዋል። አስገደ ገ/ስላሴ ካሁን በፊት ያልነበረ ብርሃኑ በርሄ የመቀሌ ከተማ የአባላት መሰረታዊ ድርጅት የሚባሉ እንዲወስኑ በተሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት አቶ አስገደ ከፓርቲው እንዲባረር ተወስኗል ::
ይህ የተደረገው በዓረና አመራር ውስጥ ስልጣን ያላቸው የህወሃት ባንዳዎች ስላሉ ሆን ተብሎ አስገደ ከተመታ ዓረና ይፈርሳል ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ ነው :: እጅጉን የገረመን ግን እኛ የምናከብራቸው የነበርን፤ ከዛ ወንጀለኛ ህወሓት ጋር ሁነው የሰሩት ወንጀል ምንም ሳይሸማቀቁ በትግሉ ወቅት የሰሩት አገርና ዜጎችን የሚጎዳ የሰሩት ወንጀል ህዝብ ይፍረድ ብለው ለህወሓት ፋሽሽታዊ ስርአት በመቃወም ከ21ኛ ክ/ዘመን ወጣት አስተሳሰብ ጎን በመሰለፋቸው እንወዳቸውና እናከብራቸው ፤ እንዲመሩን፣ ተሞክሮ እንዲያካፍሉን፣ ከነሱ የሚጠበቅ ሙያ እንዲያስተላልፉልን ነበር ምኞታችን :: ግን አልሆነም ::
አቶ ገብሩ አስራትና ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ በህወሓት ዳስ እስክስታ እየመቱ አገኘናቸው :: ይኸውም ብርሃኑ በርሄ ለህወሓት መሪዎች
ለማጋለጥ፤ በመድረክ ወጥተው ለመሞገት ፍቃደኛ ካለመሆን አልፈው የህወሓት ባለስልጣናትና ካድሬዎች የሚያናድድ ፅሁፍ
እንዳትፅፋ፣ እንዳትናገሩ፣ ተናደው በኛ ላይ እርምጃ እንዳይወስዱ እያለ ኦረነቴሽን የሚሰጥ ፤ አደገኛ በሚባሉ ቦታዎች በሚደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ተደብቆ እየቀረ፤ በተገኘባቸው ስብሰባዎችም አባሎቻችን እንዳይናገሩ በመከልከል ቅሬታ እየፈጠረ ራሱ የሚያስተላልፋቸው መልእክቶችም ከህወሓት እንዳይጋጭ በፍርሃትና ስግአት ንግግር ሲያደርግ እየታየ ባለበት ሁኔታ በሄድንባቸው ስብሰባዎች ህዝባችን ራሳችሁ ፈትሹ እያለ ምክሩን እየለገሰልን ባለበት ሁኔታ እሱና አጃቢዎቹ ተንደላቅቆ ከነነፍጡ ሲኖር በአንፃሩ እነ አስገደ ፤መ/ር ታደሰ ፤ ገብሩ ሳሙኤልና ሽሻይ አዘናውና ሌሎች አባሎቻችን ለ6 አመታት ጉልበታቸው፤ አእምሯቸው ገንዘባቸው ኢንቨስት ሲያደርጉና ዘርመንዘራቸው ጭምር በአፋኝ ኢ-ፍትሐዊ የህወሓት ስርአት ሲሰቃዩ ቆይተው አሁን ደግሞ አረና ውስጥ ባሉ የህወሓት ባንዳዎች ሲመቱ እነ አቶ ገብሩ አስራት ዋና መቺ ሃይል ሁነው መገኘታቸው ምን ያህል ክዳት መሆኑ አለማወቃቸው ነው ችግሩ ::
በኛ እምነት ግን እነ አቶ ገብሩ እስራት ከህወሓት መሪዎች ልዩነት ነበራቸው ወይ? የሚል ጥያቄ ልናነሳ አድርጎናል :: ምክንያቱም
ብርሃኑ በርሄ ጭምር የክልል ትግራይ ባለስልጣናት ሁኖው ብዙ ምሁራን ከዚህ ክልል በማባረር በተለይ ለአስተማሪዎች ሞራላቸው
በመንካት በክልላችን ፍፁም አምባገነን የሆነ አሰራር ያራምዱ እንደነበረ ከትግራይ ህዝብ ጭንቅላት አልተፋቀም :: እንደውም በህዝብ ወርደን ስንቀሰቅስና ስብሰባ ስናደርግ እነ ገብሩ እኮ ትናንት አፋኞች ነበሩ በማለት ተቀውሟቸው ይገልፃሉ :: እኛም እነሱን ወክለን ህዝብን ለማሳመን ብዙ ጥረት አድርገናል :: አሁን ግን ፍፁም አባታዊና አምባገነን እርምጃ በላያችን ላይ ተወሰደብን :: በ2 ቀናት ስብሰባ የነ አቶ ገብሩ አስራት አነጋገር ልክ የህወሓት መሪዎች በትጥቅ ትግል ጊዜ በጫካ ሽፋን አድርገው ቢፈልጉ ያስራሉ ሲፈልጉ በነፍጥ ደብዛቸው ሲያጠፉ የጠሉት ሰው ሲያባርሩ እንደነበረ ሁሉ አሁንም እነ ገብሩ አረጋሽና ብርሃኑ የሚሸፍናቸው ጫካ ቢኖርና ነፍጥ ቢኖራቸው(ለነገሩ ያሁኑ ሊቀ መንበር አሁንም ነፍጥ እንደታጠቀ ነው ) ልክ እንደ ህወሓት መሪዎች እርምጃ ለመውሰድ የሚያግዳቸው አልነበረም ::
እስቲ ልብ በሉ! አንድ የግለሰብ መብት አከብራለሁ የሚል አምናለሁ የሚል የፓርቲ ማ/ኮሚቴ ሃሳባችሁ በፅሁፍ ለመሪዎች
አቀረባችሁ: በሚዲያ ተናገራችሁ ብሎ ጠንካራ ታጋዮችን ማባረር እጅጉን የህዝብ ትግልን በሚያጨልም ማባረርና ሞራል በሚነካ ስም ማጥፋት ለነአቶ ገብሩና አረጋሽ ማንነታቸውን ያጋለጠ እርምጃ ከመሆኑ በላይ ህወሓትን ታግሎ ለመጣል ተነሳስቶ የነበረ ህዝብ እጅጉን ሞራል የሚነካ እርምጃ ነው :: እኛ ብንሆን ዛሬ ይሁን ነገ የህወሓት ኢህአደግ ስርአት እስካልተወገደ ድረስ ወይ እስከ ህልፈተ ህይወታችን ቆርጠን ከመታገል ውጪ ምንም ፍንክች አንልም :: ለህወሓትም ለአረና አባታዊና አምባገነናዊ አገዛዝ አንምበረከክም ።
የሰላማዊ ትግልአቅጣጫ አስፈላጊውን መስዋእትነት እየከፈልን እንታገላለን ::
በዚሁ ሓምሌ 19ና 20/2006 የአረና ማ/ኮሚቴ ስብሰባ እነ አቶ ገብሩ አስራት አነጋገር በውህደት ጉዳይ አንስተው ሲነጋገሩ ያ
ስንቃወመው የነበርን ፀረ ውህደት አቋም በመጠናከር የህወሓት መሪዎች እነ ገብሩ: አረጋሽና አውዓሎም የነበሩበት ጨምሮ
ከትምክህተኛው የአማራ ድርጅት ኢ.ህ.አ.ፓ አብረን አንታገልም ብለው በኢ.ህ.አ.ፓ ና ህወሓት መሪዎች የግል ፍላጎት ብዙ ወጣት
ምሁራን የቀጠፈው ጦርነት ተመልሰው አሁን ደግሞ ሲተነትኑት ሰንብተዋል ::
“ከጎሳ ፓርቲ ውህደት አናደርግም ከሚለው መኢአድ ውህደት አይቻልም፤ በውጭና በሃገር ውስጥ አንድነትና መኢአድ ለማዋሃድ
የሚጥር ሃይል አለ እነዚህ ተዋህደው ጠንካራ ፓርቲዎች ሁነው በመውጣት የአማራን የበላይነት የሚፈልጉ ናቸው ከዛ በኋላ ትግራይ ለመቆጣጠር ከተቻለ አረና በራሱ ካልተቻለ አባላቱ በመውሰድ ትግራይን መቆጣጠር የሚሉ ናቸው :: በአሁኑ ጊዜ በ3ት መንገድ ጦርነት ተከፍቶብናል 1. በህወሓት 2. በውስጣችን 3. በተቀዋሚዎችተቃማዊዎች ህወሓትን ለማሸነፍ ትግራይን መቆጣጠር አለበት። ለዚህም ከአረና አባላት በመውሰድ እንደ መሳርያ በመጠቀም ትግራይን መቆጣጠር አለብን የሚሉ ናቸው:: ” የነአቶ ገብሩ አስራት አነጋገር ምን ያመለክታል? በኛ እምነት አቶ ገብሩ የኢትዮጵያ አንድነትና እኩልነት የማይቀበሉ ሁነው ተገኝቷል። አንድነት ሊውጠን ነው ማለት ምን እርባና አለው ከመጠራጠር አልፎ? በኛ እምነት እነ አቶ ገብሩ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለማምጣት ሳይሆን ወደ ፓርላማ ሸልኮው ለመግባት ወይም የፓርቲ መሪዎች ነን እያሉ በየኤምባሲው በር፤በፕሬስ ኮንፈረንስ አንድ ቃል እየተናገሩ ፓርቲው እንደ መደበቂያ ዋሻ ለመጠቀም ነው:: አዲስ አበባ ተወሽቀው ቆይተው በአመት አንድ ጊዜ የማ/ኮሚቴ ስብሰባ ብቅ እያሉ የተቀነባበረ አስተያየት መስጠት ለታጋዮች ሞራል መጉዳት አይደለምን?
ታጋዮች ከሆኑ በየከተማውና ገጠር ከባንዳዎች እየተጋፈጡ ለምን ህዝብን አያስተምሩም? እኛ 4ታችን የተባረርን አባላት 6 አመታት ሙሉ ከባንዳወችና ከሃዲዎች ጋር እየተላተምን ተታግለናል፤በጽሁፍ ለህወሓት ኢህአደግ አጋልጠናል (በተለይ አስገደ) በሃገር ውስጥም በውጭም ያሉ ኢትዮጵያዊያን ይመሰክራሉ ::
አሁንም ምንም እንኳን አባታዊ አመራራቸሁና የብርሃኑ ቡድን (የህወሓት ባንዳዎች) ወንጀሉን ለመሸፈን ቢመታን ትግላችን ግን
አሁንም ይቀጥላል :: የ90 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ መዋኛ ባህር አለን :: ከወንድሞቻችንና እህቶቻችን ኦሮሞ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣
ሶማል፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ሃዲያ፣ ከምባታ፣ ጉራጌ ከሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ሁነን እንታገላለን :: ወየውላችሁ እነ አቶ ገብሩ አስራት
ለውርደት የታደላችሁ እንጂ አሁንም ልናረጋግጥላችሁ በህወሓት ዳስ እስክስታ አንመታም ::
በመጨረሻም ለመላው የአረና አባላትና ደጋፊዎች በሃገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ ፤ በኢትዮጵያ የምትገኙ እውነተኛ ተቃዋሚ ፣
ፓርቲዎች አሁንም የአረና ማ/ኮሚቴ መጥፎ ውሳኔ ቢወስንም እኛ ልናረጋግጥላችሁ ምንፈልገው አሁንም ታጋዮች ነን :: ሰፊ የትግል ሜዳ አለን :: የአረና አባላት ከእንግዲህ ወዲህ በህወሓት ዳስ እስክስታ መምታት ይቁም :: የብርሃኑ በርሄና አንጃዎቹ መጫወቻ መሆን የለባችሁም :: በአረና ማ/ኮሚቴ ያላችሁ ንፁሃን ወጣት ሙሁራንና ታጋዮች ነገሩ በሙሁራዊ አይን እየተነተናችሁ ለዚህ ህዝብ የሚጠቅም ስራ በቅንነትና በንጽህና በመስራት ህዝባችን ከህወሓት የጨለማ ንሮ አድኑት :: እኛም በሆነ መንገድ ከጎናችሁ ነን
በሃገራችን ያላችሁ ዲሞክራትና ሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች - አረና ትግራይ ለቅን አላማ ተነስቶ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት መንጋጋ
ያላቅቀኝ ይሆን ?ብሎ ተስፋ አድርጎ ነበር :: አሁን ግን እነ አቶ ገብሩ አስራት ለባንዳዎች ግንባር ቀደም በማሰለፍ ለህወሓት አሳልፈው በመስጠት ተስፋውን አጨልመውታል :: በመሆኑም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግዳጃችሁን ተወጡ ::
በዲያስፖራ የምትገኙ የአረና ትግራይ ደጋፊዎች ከአሁን በፊት የአንድወገን ሰምታችሁ ምንም ሳታጣሩ የፃፋችሁት ትክክል አልነበረም፤ አሁንም ይህንን ድርጊታችሁ ሳትደግሙ ዳግም የህወሓት ባንዳዎች ውሸት ሳትሰሙ በአንድ እጃችሁ ማንጨብጨብ ትታችሁ በአረና ትግራይ ደርሶ ያለው የመፍረስ አደጋ አጥንታችሁ ተፈጥሮ ያለው የህወሓት ባንዳዎች ሰርጎ ገብነት እንዲወገድ የድርጅት ውስጣዊ ግጭቶችን የመፍታት ልምድና ተሞኩሮ ትለግሱ ዘንድ ጥሪያችን እናቀርባለን ::
ፀሃፊዎች፦
1.መምህር ታደሰ ቢተውልኝ ማ/ኮሚቴ
2.ሽሻይ አዘናው ማ/ኮሚቴ
3.መምህር ገብሩ ሳሙኤል ቁ/ኮሚሽን
4.አስገደ ገ/ስላሴ ተራ አባል
ከሰላምታ ጋር
ይቀጥላል
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
July 29, 2014
No comments:
Post a Comment