Tuesday, October 28, 2014

ሚሊዮኖች ድምጽ -ሃብታሙ አያሌው ቶርቸር እየተደረገ ነው !


October 28,2014

ክስ ሳይመሰረትበት ለአራት ወራት በማእከላዊ እስር ቤት የሚገኘው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ ከፍተኛ ኢሰብአዊ ግፍ እየተፈጸመበት እንደሆነ ታወቀ።

ወደ ፖለቲካው የማትመለስ ከሆነ ትወጣለህ። አለበለዚያ እዚሁ ነው የምትሞተውበማለት አማራጭ ቢያቀርቡለትም፣ ሃብታሙ መሞትን እመርጣለሁ የሚል መልስ የሰጣቸው ሲሆን፣ እየደረሰበት ባለው ስቃይ በጣም እየታመመ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።እስኪ ትግሉን እናስቀጥላለን የሚሉ ሰዎች ያድኑህ ? “ ሲሉ አሳሪዎቹ በስቃዩ የሚደሰቱ ሲሆን፣ ከባለቤቱ በስትቀር ጠበቃዉም ሁሉ ሳይቀር እንዳያየው ተደርጓል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ /ሃላፊ በታፈነና አየር በማያስወጣ ክፍል ዉስጥ እንዲታሰር በመደረጉ በተደጋጋሚ ለተቅማጥና ተያያዥ በሽታ መጋለጡን፣ እንዲሁም የመተንፈስ ችግር እንዳለበት ለማወቅ ችለናል።የፓርቲያችሁ የገንዘብ ምንጭ ምንድን ነው ? አንድነት ዉስጥ ያሉ ጠንካራ አባላት እነማን ናቸው ? “ በሚል ጥያቄ የቀረበለት ዳንኤል ሺበሺ፣ ክብሩን በሚነካ መልኩ እንደሚሰደብም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ሃብታሙ አያሌው በእርሱ ላይ እይደረሰ ያለው ግፍ በማንም ዜጋ ላይ መድረስ እንደሌለበት በመግልጽየግፈኛው አገዛዝ እንዲያበቃ የኢትዮጵያ ሕዝብ መነሳት አለበትሲልም ለህዝቡ የትግል ጥሪ አስተላልፏል።
የአንድነት ራዲዮ የዘገበዉን እንደሚከተለው ያድምጡ !


Monday, October 27, 2014

የ “ካዛንችሱ መንግስት በአዲሰ አበባ ማዘጋጃ ቤት” –

ከግርማ ሰይፉ ማሩ
October 27.2014
ዛሬ ጥቅምት 17/ 2007 እግር ጥሎኝ አዲሰ አበባ ማዘጋጃ ቤት ጎራ ብዬ ነበር፡፡ የታዘብኩት ነገር ያስታወኝ ኤርሚያስ ለገስ “የመለስ ትሩፋቶች” በሚል ባወጣው መፅሃፍ ውስጥ “የካዛንችስ መንግሰት” ብሎ ያስነበበንን በገሃድ ከካዛንችስ ቦታ ቀይሮ አዲስ አበባ መስተዳደር ግቢ ውስጥ መኖሩን ነው፡፡ የካዛንችሱ መንግሰት ምን እንደሚሰራ እዚህ መዘርዘር አይጠበቅብኝም፤ በጥቅሉ ግን የአዲስ አበባ ህዝብ “መርጦ” ወይም ቀጥሮ ያስቀመጣቸው ሰዎች ሳይሆን ውሳኔ የሚስጡት ሌሎች በስውር በደህንነት ስም በኢህአዴግ የተቀመጡ ሰውር እጆች መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

እነዚህ ሰውር እጆች ለእኛ ለተቃዋሚዎች አዲስ አይደሉም ለምሳሌ፤
· በሆቴሎች አዳራሽ ለማከራየት አንችልም ምንም ጠቃሚ ገንዘብ ቢሆን ሆቴሎች ፈቃደኞች አይደለም፤
· ማተሚያ ቤቶች የተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም እነርሱን ይደግፋሉ የሚባሉ የግል ጋዜጦችና መፅሄቶች አያትሙም
· መብራት ኃይል ለአንድነት የማተሚያ ማሽን ሊያንቀሳቅስ የሚችል የኤሌትሪክ ሀይል (ሰሪ ፌዝ የሚባል ሀይል) ለፓርቲ ለማስገባት ፈቃደኛ አይደለም፤
· ቤት አከራዮች ቤታቸውን ለማከራየት ይፈራሉ፤
· በቅስቀሳ ጊዜ መኪና እና የድምፅ መሳሪያዎች ማግኘት ፈተና ነው፤
· ለቅስቀሳ የወጡ ሰዎች እንደ በግ በየጣቢያው ሲታሰሩ የሚያስሩት ሰዎች በግልፅ ዩኒፎርም የለበሱት ፖሊሶች ሳይሆኑ በሬዲዮ የሚያዙ ማን እንደሆኑ የማይታወቁ ናቸው፤ ወዘተ ይህ ሁሉ የሚሆነው በህግ አግባብ ሳይሆን በሰውር መንግስት ውስጥ ያሉ ሰውር እጆች የሚሰሩት ነው፡፡

ለዛሬ ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ ግን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የህዝባዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ኦፌሰር የሆኑት አቶ ማርቆስ ብዙነህ የሰጡን ምላሽ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ በቀጣይ ፓርቲው በሚያደርገው እንቅስቃሴዎች የፓርቲ አባላትን በስነ ምግባር የታነፁ እና ሰላማዊ ትግል በሰለጠነ መንገድ የሚደረግና በግብግብ ሳይሆን በሃሳብ የበላይነት የተመሰረተ እንዲሆን ለማድረግ ለሚያካሂደው ስልጠና ለማካሄድ አዳራሽ ለመከራየት ባቀረብነው ጥያቄ በጎ ምላሽ እንደሌለ ከውስጥ ሰምተን ምክንያቱን በግንባር ለማወቅ ሄጄ የሰማሁት ምላሽ በአንድ መንግሰታዊ ተቋም ውስጥ ተቀጥሮ ደሞዝ ከሚበላ ሲቪል ሰራተኛ የሚጠበቅ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡ የሰጡን ምላሽ “አራት ሰዎች መጥተው ፍቃዱ እንዳይስጥ ጠይቀው አለቃይ እንዳትሰጥ ስለአለኝ ነው የሚል ነው፡፡” በቃ ይህ ነው ምክንያቱ፡፡ አንድነት ፓርቲ ይህን ፈቃዳ ላለማግኘት አንድም ያጎደለው መስፈርት የለም፡፡ አቶ ማርቆስ አለቃቸው ይህን መልስ ሲሰጣቸው ለምን? እንዴት ብዬ? ከመመሪያ አንጻር ልክ አይደለም ብለው አይጠይቁም፡፡ አለቃቸውንም አይሞግቱም፡፡ እርሳቸውም የሚያውቁት አለቃቸውም ቢሆን እራሳቸው እንደማይወስኑ፡፡ የሚወስነው ይህ ስውር እጅ ያለው ካዛንችስ የነበረው አሁን በመስተዳድር ቅፅር ግቢ የሚገኘው መንግሰት እንደሆነ፡፡

አንድ መስሪያ ቤት ሰራውን የሚሰራው በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን በደንብ እና መመሪያ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ኦፊሰሮች ተግባራቸውን ሲያከናውኑ ደግሞ እነዚህ የህግ ማዕቀፎች መሰረት አድረገው ነው ብለን እንጠብቃለን፡፡ በዚህች ምስኪን ሀገር ግን ይህ ምፀት ነው፡፡ በህግ ማዕቀፍ የሚሰራ ኦፊስር ማግኘት ዘበት እየሆነ መጥቶዋል፡፡ አለቃው በቃል አድርግ ያለውን የሚያደርግ የማርቆስ ዓይነት ኦፊሰር ሞልቶ ተርፎዋል፡፡ በጣም የሚገርመኝ የዚህ ዓይነት ኦፊሰሮች ለልጆቻቸው ሰራ ሄጃላሁ የሚሉ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ባይሉዋቸው ደግ ነው፡፡ ይህን ሊያደርጉ መሄዳቸውን ሲያውቁ ያፍሩባቸዋል ብዬ ስለማስብ ነው፡፡ ለምን ለልጆቻችን ማፈሪያ እንደምንሆን አይገባኝም፡፡

መልካም አስተዳደር አስፍናለሁ የሚል መንግሰት መልካም አሰተዳደር የሚሰፍነው በአዳራሽ ኮፍያና ቲ ሸርት ለብሶ በሚደረግ ዲስኩር እንዳልሆነ የገባው አይመስለም፡፡ መልካም አስተዳደር የሚሰፍነው በህግ ማዕቀፍ አገልግሎት የሚሰጥ ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛ አገልግሎት ሲሰጥ እንጂ በስውር በቃል በሚሰጥ ትዕዛዝ እንዳለሆነ መረዳት ይኖርብናል፡፡ ማርቆስ በሚሰጠው መልስ እየተበሳጨ፣ እያዘነ ሲከፋውም እየተሳደበ የሚሄድ ተገልጋይ መዘዝ እንደሚያመጠ ግን የገባቸው አይመስለኝም፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ደግሞ በስውር መንግሰት በዚህ መንገድ እንዲሆን ስለሚፈልግ ነው፡፡

ዛሬ በግልፅ የተረዳሁት በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ብሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ መልካም አስተዳደር የማሰፈን ችግር ምንጭ በደህንነት ስም በስውር ያለው መንግሰት የሚሰጠው ትዕዛዝ ሲሆን፣ ሲቀጥልም አድርግ ያሉትን ለማድረግ በተጠንቀቅ ዝግጁ የሆነው የማርቆስ ዓይነት ደሞዝ እየበሉ ያሉ ሲቪል ሰራተኞች ናቸው፡፡ አለቃዬ እንዲህ አድርግ ብሎኝ ነው በሚል መመሪያን መሰረት ያላደረግ ትዕዛዝ የሚሰፈፅሙ የማርቆስ ዓይነት ኦፊሰሮች የዚህች ሀገር መከራ እንዲረዝም፣ ህዝቡ የመልካም አስተዳደር ትሩፋት እንዳያገኝ ተባባሪ እንደሆኑ አበክረን መንገር ይኖርብናል፡፡ ይህንን አሜን ብሎ የተቀበለ ህዝብ መከራውና ግፉ ተስማምቶኛል እንዳለ ይቆጠራል፡፡ የዚህ ዓይነት ህዝብ ደግሞ ምንም ዓይነት አንባገነን መንግስት ቢመጣ የሚገባው ነው ማለት ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ኢህአዴግ አይመጥነንም ያለ ህዝብ በቃ!!!! ሊለው ይገባል፡፡ ኢህአዴግ በቃ ሊባል ይገባል!!!!

ቸር ይግጠምን



Saturday, October 25, 2014

በአዲስ አበባ በሚካሄደው የፖለቲካ ስልጠና ላይ ሰልጣኞች ለምናነሳቸው ጥያቄዎች መልስ አላገኘንም አሉ

ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የፖለቲካ ስልጠና መድረክ ከወረዳ ጽ/ቤት እስከ ማዕከል ቢሮዎች የሚገኙ ሰራተኞች እና የፌደራል መ/ቤት ሰራተኞች ከማክሰኞ ጥቅምት 3 ቀን እስከ ቅዳሜ ጥቅምት 14/2007 ዓ.ም ለተከታታይ 11 ቀን የፖለቲካ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፣  በዚህ መድረክ እስካሁን ከታዩት በላይ በሰልጣኖችና በኢህአዴግ አመራሮች መካከል ፍጥጫ ታይቷል። ጠንካራ ጥያቄ በማቅረብ ሰልጣኙን አነሳስቷል የተባለ አንድ ሰልጣኝ ከስራው እንዲባረር መደረጉን ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ብሎ በነበሩት የስልጠና መድረኮች የነበሩ ሰልጣኞች በተለይ የድርጅት አባሎቹ በስልጠና ላይ ሳሉ ከአበል በተጨማሪ በእረፍት ሰዓት እሽግ ውሃ፣ ሻይ ቡና እና በቂ የእረፍት ጊዜ እንዲሁም የፌደራል መ/ቤት ሰራተኞች ደግሞ በአዲስ አበባ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ገብተው የተሟላ  የምግብና መኝታ አገልግሎት በማግኘት ሰልጥነው ሲወጡ በአንፃሩ ደግሞ የ2ኛና 3ኛ ዙር ሰልጣኞች ለእኛ ለምን የተሟላ አገልግሎት አይሰጠንም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል።
ሰልጣኞቹ ከመንግስት የስራ ሰዓት ውጪ በእረፍት ቀን ቅዳሜ ጭምር በጫና ተገደን ለምን እንድንሰለጥን ይደረጋል ሲሉም ተደምጠዋል።
ሰልጣኞቹ ላነሱዋቸው ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ሳይሰጥ ወደ ስልጠና እንዲገቡ የታዘዙ ሲሆን በዚህም ሁኔታ ላይ እንዳሉ በከተማው ሁሉም የስልጠና ቦታዎች በአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ ለመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች የተከፋፈለው ተመሳሳይ ቪዲዮ  በድጋሚ በፕሮጀክተር ስክሪን በመታገዝ በተመሳሳይ የጊዜ ሰሌዳ በከተማው በተዘጋጁ ሁሉም የስልጠና አዳራሾች አንድ ጊዜ ገለጻ አንድ ጊዜ የጥያቄና መልስ ውይይት እየተደረገ ሰልጣኝ ሰራተኞችም በ1ለ5 በቡድን እንዲከፋፈሉ ተደርጎ በገለጻው ላይ ውይይት እንዲያደርጉ ተደርጓል።
ሰልጣኝ የመንግስት ሰራተኞች ጥያቄ ማንሳት ሲጀምሩ በአንዳንድ መድረክ የሚገኙ አወያዮች የተሳታፊ ጠያቂዎችን ስምና የመጡበትን መ/ቤት በመጠየቅ ማስታወሻ ሲይዙ ተስተውሏል።  ይህንንም ተከትሎ ሰራተኛው ለምን ትጠይቁናላችሁ በማለት ተቃውሞ ሲያነሱ አወያዮች ደግሞ ለመግባባትና ለመተዋወቅ ያክል ነው በማለት ሲመልሱ በተቃራኒው ሰራተኛው እናንተ የምታመጡት አይታወቅም! አናምናችሁም! በማለት ተቃውሞ አሰምቷል።
በተከታታይ በተደረጉት የስልጠና ቀናት የአዲስ አበባ መስተዳድር የተለያዩ የካቢኔ አባላት ቅሰቀሳ አድርገዋል። አቶ ተወልደ ገ/ፃድቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አህአዴግ ጽ/ቤት ኃላፊና የከንቲባው ዋና አማካሪ “የኢትዮጵያ ህዝቦች ትግልና አገራዊ ህዳሴያችን” የሚል ሰነድ፤ አቶ አባተ ስጦታው /የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ “የተሃድሶው መስመርና የኢትዮጵያ ህዳሴ” የሚል ሰነድ፤ አቶ ይስሐቅ ግርማይ /የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቅም ግንባታ ዋና ቢሮ ኃላፊ “የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ትግላችንና ፈተናዎቹ” የሚል ሰነድ፤ ዶ/ር ታቦር ገ/መድህን /የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ “የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ህገ መንግስትና የፌደራል ሥርዓቱ ዓላማዎች፣ መርሆዎች፣ዕሴቶች፣ባህሪያትና ውጤቶች” የሚል ሰነድ፤ እንዲሁም ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ /የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቅም ግንባታ ም/ቢሮ ኃላፊ “ልማታዊ ሲቪል ሰርቪስ የመገንባት ፋይዳና አገራዊ ሕዳሴውን በማሣካት ሂደት የሲቪል ሰርቪሱ ሚና” በሚሉ ሰነዶች ላይ በንባብ ብቻ የተመሰረተ አሰልቺ የቪዲዮ ገለጻ እስከ ስልጠናው መጨረሻ በቅደም ተከተል ሰጥተዋል፡፡
ሆኖም ሁሉም የካቢኔ አባላት በተቀረጹት ቪዲዮ ላይ ከሰነዱ ወጪ በራሳቸው ሃሳብ የታቃኘ ገለጻ ሲያደርጉ ወይም ከሰነዱ ወጪ አንድም ሃሳብ ሲያብራሩ አልታዩም።
ከዚህ በተመሳሳይ ደግሞ ቀድሞ ብሎ ነሐሴ ወር አጋማሽ ላይ ስልጠና ገብተው ለነበረው የድርጅት አባላት ሰልጣኞች በየመድረኩ አንስተውት በነበረው ጥያቄ ላይ የተመለሰውን በቪዲዮ የተቀረጸ የቪሲዲ መልስ በተመሳሳይ ሁኔታ ለአሁኖቹ ሰልጣኞች ሲከፍትላቸው እንደነበር ሰልጣኞች ገልጸዋል።
“የተሃድሶው መስመርና የኢትዮጵያ ህዳሴ” የሚለው ሰነድ በ2003 ዓ.ም የታተመ ሲሆን የተቀሩት ሁሉም ሰነዶች ግን ነሐሴ 2006 ዓ.ም የታተሙ ናቸው፡፡
በሰነዶቹ ላይ ኢህአዴግ ለሃገራችን ኢትዮጵያ ፍጹም ትክክለኛ ተመራጭ ፓርቲ፣ የህዝብ ሁለንተናዊ ጥያቄ መፍትሔ አምጪ ፤በኢትዮጵያ ከነበሩ ነገስታት ሁሉ በማንኛውም ሁኔታ የተለየ  መንግስት ተደርጎ ተወድሷል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሰልጣኞች ሰነዶቹ የሃገሪቱን ብሎም የዓለምን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያላስገቡ፤ ኢትዮጵያ በታሪክ የነበሯትን የስልጣኔ በር የከፈቱና ለአፍሪካ ነፃነትን አስተምረው ያለፉ መንግስታትን ታሪክ በቁንጽል አቅርባችሁ፣እንዲሁም አዛብታችሁ የቀድሞ ስርዓቶችን በጅምላ አጣጥላችሁና ኮንናችሁ በተፃፃራሪው ደግሞ የራሳችሁን ብቻ ያሞካሻችሁበት ነው በማለት ሲሞግታቸው ሰንብተዋል፡፡
በተለይም ባለፉት 12 ዓመታት አገራችን በዓለም ፈጣን እድገት አላቸው ከሚባሉት አገሮች ቀዳሚነት ተጠቃሽ መሆኑዋ፣ በዚህም በ1994/95 ከ83 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ያላመረተችው አገራችን በአሁኑ ጊዜ 254 ሚሊዮን ኩንታል የሰብል ምርት ያመረተችበት ደረጃ ላይ እንድንደርስ አስችሏል ተብሎ ሲገለጽ እንዲሁም “በአለም ባንክ ጥናት መሰረት የኢትዮጵያዊያን የነፍስ ወከፍ አማካይ የህይወት ዘመን (life expectancy) ከ23 ዓመታት በፊት ከነበረበት 49 ዓመት ወደ 64 ዓመት ከፍ ብሏል ተብሎ ሲነገር ተሳታፊዎች አዳራሾችን በሳቅ ሞልተዋቸው እንደነበር ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
እስካሁን በሰልጣኝ የመንግስት ሰራተኞች ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል፣  የትምህርት ጥራት ችግርና የፕሬስ አፈና ይገኙበታል።
ኢህአዴግ ለውጥ አላመጣም በሚል ትችት ሲቀርብበት ራሱን ከነበሩት መንግስታት ማነፃጸሩ ተገቢ ነወይ?  በሲቪል ሰርቪሱ ውስጥ የተሰገሰጉት 1ለ5፣ የልማት ቡድን፣ የለውጥ ቡድን፤ ህዋስ፣ ብሄራዊ ድርጅት ወ.ዘ.ተ የሚባሉት  አደረጃጀቶች ከብዛታቸው አንፃር ለሁሉም ጊዜ ሲመደብላቸው ለስራ ማነቆ አይሆኑሞይ? በአለም ገበያ ብዙ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ የንግድ ድርጅቶች እያሉ መንግስት ለሚገነባቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች የግባአት አቅርቦት ለመከላከያ ኢንጅነሪንግ ያለጨረታ መስጠቱ ተገቢ ነወይ? ፓርቲዎቸን ኪራይ ሰብሳቢ፣የድሮ ስርዓት ናፋቂ፣የኋልዮሽ ጉዞ፣ብጥብጥ ናፋቂ ብሎ በማጣጣል የዳበረ ዴሞክራሲ ማምጣት ይቻላል? የልማታዊ ዴሞክራሲ አማራጪን ተግባራዊ የምናደርገው ለስንት አመት ነው? በተቃራኒው ደግሞ የኒዮሊበራሊዝም አስተሳሰብን ለአገራችን ጭራሽ አይጠቅምም ትላላችሁ? በቻይና ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ሰብዓዊ መብታቸው ሲጣስ ይታያል፤ በአገራችን ሁለተኛ ዜጋ ልንሆን ነወይ? የክህሎትና የአመለካከት ለውጥ ተቀራራቢነት በሌለበት ሁኔታ ልማታዊ ሲቪል ሰርቪሱ እንዴት ሊሳካ ይችላል? የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተዋል።
እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት ከድርጅት ወገንተኝነት ነፃ ነው ብሎ መናገር ይቻላል? ብዙህነትን የማስተናገድ ችግር ጎልቶ የወጣው በኢህአዴግ ወይስ በድሮ የአገራችን ገዥዎች ነው በግልጽ ብታብራሩት? በአዲስ አበባ የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና አፈጻጸም መመሪያ መሰረት ቦታ ተረክበው ከ6 ወር በላይ የግንባታ እንቅስቃሴ ካልተደረገ አስፈላጊው ርምጃ እንደሚወሰድ ቢታወቅም የመንግስት የቅርብ ወዳጆች የሆኑት ግን ለረጅም ዓመት ሰፊ ሄክታር መሬት አጥረው ሲቀመጡ ጠያቂ የለም ይሄን እንዴት ታዩታላችሁ? ህገ መንግስቱ በተለያዩ አዋጆች የሚሸራረፍ ከሆነ የዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብቶች እንዴት ማስጠበቅ ይቻላል? ይህን ስልጠና በዚህ ወቅት ለመንግስት ሰራተኛው ለምን መስጠት አስፈለገ? ዓላማውስ ምንድን ነው? በዴሞክራሲ ስርዓት ትግበራ ትችት ሲቀርብባችሁ ዴሞክራሲያችን ገና በጅምር ላይ ነው ትላላችሁ፤ መቼ ነው በተግባር ሲውል የሚታየው? በኢህአዴግ ውስጥ የተማሩ ሰዎች የሉበትም ብሎ ለመናገር ባያሰደፍርም በፖለቲካ ታማኝነታቸው ብቻ አቅም የሌላቸው ሰዎች አይሾሙም ወይ፤ ይህ ከሆነ ቀጣይነት ያለው ለውጥ እንዴት ሊመጣ ይችላል? ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነት አለ እየተባለ፤ፓርቲዎች ሰልፍ ሲያዘጋጁ በመርፌ ቀዳዳ የማለፍ ያክል ምክንያትና ሰበብ በመደርደር በግልጽ ታደናቅፋላችሁ ለምን የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተዋል።
ሰልጣኞች ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ ካነሱዋቸው ጥያቄዎች መካከል ደግሞ በድሮ መንግስታት የኢትዮጵያ የብር ምንዛሬ ከሌሎች አገራት ገንዘብ ጋር ሲነፃጸር ተቀራራቢ ነበር፣ የአሁንስ ምንዛሬ እንዴት ትገመግሙታላችሁ? በሲቪል ሰርቪሱ ውስጥ በሚገኙ ሠራተኞች የድርጅት አባል ባልሆኑት ላይ በደረጃ እድገትና በሌሎች ጥቅማጥቅሞች ላይ ግልጽ አድሎ ታደርጋላችሁ፤ አሁን አሁን ደግሞ እየባሰ መጥቷል እንዴት ታዩታላችሁ? የአጼ ሚኒሊክ ወታደር ነፍጠኛ ከተባለ የኢህአዴግ ወታደርስ ምን ይባላል? ጋዜጠኛችና ጦማሪዎችን በዘመቻ ታስራላችሁ፤ራሳችሁ ቪዛና ፓስፖርት አዘጋጅታችሁ ከአገር እንዲሰደዱ ምቹ ሁኔታ እየፈጠራችሁ አይደለሞይ? በአሸባሪነት ሰበብ ህዝብ ከአደጋ ለማዳን ነው ይሄን ያደረግነው እያላችሁ ከፍ/ቤት የመያዣና የብርበራ ትዕዛዝ ሳይወጣ ዜጎችን በድንገት ታፍናላችሁ፤ ይሄ ድርጊት ህገ መንግስቱን መጣስ አይሆንሞይ? በኢህአዴግ የመተካካት መርህን ተግባራዊ እያደረገ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል ወይ? የመድብለ ፓርቲ ስርዓት በአውራ ፓርቲ ሲመራ አምባገነንነትን አያመጣም ወይ? የኢትዮጵያና የኤርትራ ወቅታዊ ግንኙነት ሰላምም ጦርነትም የለም ሆኖ እስከመቼ ይቀጥላል? በህግ መንግስቱ ችግሮች ላይ ሃገራዊ መግባባት ያልተቻለው ለምንድን ነው? የትምህርት ጥራት የሚመጣው በሂደት ነው እየተባለ ነው ታዲያ ለየትኛው ትውልድ ይደርሳል? አንድ ሰው በቁጥጥር ስር ውሎ ከታሰረ በኋላ በ48 ሰዓት ፍ/ቤት መቅረብ እንዳለበት ህጉ ያስቀምጣል፤ ነገር ግን ተግባራዊ ሲደረግ አይታይም፤ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህጉ ሲከበር አይታይም፣ ጠባብነትና ብሔርተኝነት ከእናንተ ወጪ በማን ይገለጻል? የአገራችንን ፖሊስና ስትራቴጅ የፃፈው መለስ ነው ብላችሁ ነበር መለስ ከሞተ ወዲህ አዲስ አስተሳሰብ ማውጣት አልቻላችሁም ወይ? መንግስት በየአቅጣጫው የአፈጻጸም ችግር አሉብን ይላል ነገር ግን ችግሮች ከታወቁ መፍትሔ ሲወሰድና ለውጥ ሲመጣ አይታይም፤ በየዓመቱ የሚታዩ ያልተፈቱ ችግሮች ማለቂያቸው መቼ ነው? የሚሉት ይጠቀሳሉ።
በአንደኛው ስልጠና ላይ ያወያዩት አቶ ይስሃቅ ግርማይ በሲቪል ስርአቱ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ የትምክት ሃይሎች አሁንም በህዝብና በመንግስት መካከል ልዩነት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል። ይህ ሃይል ለማጥፋት እንዳልተቻለም ገልጸዋል
መንግስት ስልጠናው ያስፈልገበት ምክንያት ከዜጎች ጋር አገራዊ መግባባት ለመፍጠርና ህዝቡ ስለሚካሄደው ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዲያውቅ ነው ይላል። ሌሎች ወገኖች በበኩላቸው ስልጠናውን የምርጫ ቅስቀሳ አንዱ አካል አድርገው ይመለከቱታል።

Tuesday, October 21, 2014

‹‹ሰላማዊ ትግል የሚባል ነገር አይሰራም፤ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን፡፡››

በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ጫናው በርትቷል
• ‹‹ሰላማዊ ትግል የሚባል ነገር አይሰራም፤ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን፡፡›› 
የብአዴን አመራሮች


በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት የሚደርስባቸው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ጸሃፊ የሆነው ጠበቃ ሳሙኤል አወቀ በእሱና በሌሎች የፓርቲው አመራሮችና አባላት ላይ ዛቻ እንደሚፈጸምባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ ቢሮ በ2006 ዓ.ም የእቅድ ግምገማ እና የ2007 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም እቅድ በተወያየበት እና የሁሉም ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የስራ ሂደት ባለቤቶች በተገኙበት፣ ‹‹ሳሙኤል አወቀ የሚባል በጥብቅና ሽፋን የመሬት ፖሊሲውን የሚታገል፣ ለተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊ አርሶ አደሮች ጥብቅና የሚቆም፣ ከአሸባሪ ጋር ግንኙነት ባለው ድርጅት አመራር የሆነን ግለሰብ በህግ ሽፋን እስር ቤት እንዲወርድ ያላደረገ አቃቤ ህግ አቃቤ ህግ አይደለም›› ተብሎ በህግ ስም እርምጃ እንዲወሰድበት ትዕዛዝ መተላለፉን ጠበቃው ገልጾአል፡፡
በተለይ የደብረማርቆስ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አቃቤ ህጎች ዋነኛ ችግራቸው ጠበቃ ሳሙኤልን በህግ ስም ማስቀጣት አለመቻላቸው እንደሆነ ተገምግመዋል ተብሏል፡፡ ጠበቃው ወዲያውኑ የፈጠራ ክስ እንደተመሰረተበት፣ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ‹‹ለፍትህ ስርዓቱ አጋዥ ባለመሆኑ›› በሚል መከሰሱንና ባልተከራከረበት ፍርድ ሂደትም 8000 ብር ቅጣት እንዲከፍል እንደተወሰነበት ገልጾአል፡፡
ጠበቃው በ28/1 እናርጅ እናውጋ ለቀጠሮ ባቀናበት ወቅትም የእናርጅ እናውጋ አስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊ አቶ ስራው በረኩ እና የብአዴን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ መኳንንት አበበ እና ሌሎችም ከፖሊስና ከጸጥታ የመጡ አመራሮች ‹‹ምን ልታደርግ ነው? ልትቀሰቅስ ነው?›› በሚል እንዳዋከቡትና አቶ ስራው በረኩ ‹‹አንጠልጥዬ ነው እስር ቤት የማስገባህ፡፡ ማንም ሊያድንህ አይችልም›› ብለው እንደዛቱበት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
‹‹የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሆነህ በፍትህ ስርዓቱ መገልገል አትችልም፣ ጥብቅናህን መልቀቅ አለብህ፣ ነገረ ኢትዮጵያ ላይ ትጽፋለህ፣ የፍትህ መምሪያ ሃላፊውን (ጸጋየ መንግስቴ) ችግር እንደሚፈጽምብህ በነገረ ኢትዮጵያና በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ጽፈህበታል፣ እንዲህ እያደረክ መኖር አትችልም፣ አንተን ገሎ መጣል ቀላል ነው፣ ለነፍስህ የምታዝን ከሆነ አገር ልቅቅ›› ብለው እንደዛቱበት ገልጾአል፡፡
ሌሎች ጠበቃ ጓደኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሄዱ ‹‹እሱ ማለት ሰማያዊ ነው፡፡ ሰማያዊ ደግሞ የአክራሪ ሙስሊም ፓርቲ ነው፡፡ እናንተ ለምን ከእሱ ጋር ትሄዳላችሁ?›› ብለው እንደሚያስፈራሯቸውና ደንበኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሰሩ ማስጠንቀቂያ እንደሚደርሳቸው ጠበቃው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
ጠበቃውን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባል ሆነው ማደራጀት መብታቸው መሆኑን ሲገልጹ የብአዴን አመራሮች ‹‹እናንተ እኛን ስለማትረዱን ነው፡፡ እኛ ጋር ሰላማዊ ትግል የሚባል አይሰራም፡፡ ወንድ ከሆናችሁ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን›› በሚል ለህግ የማይገዙና ለሰላማዊ ትግል ቁርጠኝነት እንደሌላቸው አሳይተውናል ብለዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የሰማያዊ ፓርቲና አመራር የሆኑ ነጋዴዎች ከፓርቲው እንዲለቁ ለማድረግ የንግድ ድርጅታቸውን እንደሚዘጉ እያስፈራሩ እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ለአብነት ያህልም አቶ ይኸይስ ቀጸላ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ‹‹ሻይ ቤት ከፍተው እያደራጁ ነው፡፡ የንግድ ድርጅቱን እንደ ጽ/ቤት ይጠቀሙበታል፡፡ በመሆኑም ካላረፉ ሻይ ቤቱን እንዘጋዋለን›› እያሉ እንደሚያስፈራሩ ታውቋል፡፡
የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የገዥው ፓርቲ ዛቻና ማስፈራሪያ እንዲሁም እርምጃዎች እየተጠናከሩ ቢሆንም እርምጃው እነሱ ተጽዕኖ በመፍጠራቸው የመጣ በመሆኑ ይበልጡን እንደሚያበረታታቸውና የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
አቶ መኳንንት አበበን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችን የእጅ ስልካቸው ላይ በመወደል ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡

Monday, October 13, 2014

አክብሩ የተባለነው የተኛውን ሰንደቅ ነው፤ የተዘቀዘቀወን፣ የተረገጠውን ወይስ የተቀበረወን…?

ባንዲራ2
”ሰንደቅ አላማውን በማያከብሩት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ” (አዲስ አድማስ)
የትኛውን ሰንደቅ አላማ፤ የተዘቀዘቀወን፣ የተረገጠውን ወይስ የተቀበረወን…? (እኔ)
እንደ አቶ መለስ እና እንደ ኢሃዴግ ባንዲራውን ጠምዶ የያዘ ማንም አልነበረም። ምክንያቱ ግልጽ ነው፤ ኢህ አዴግ ያኔ ”ወንበዴ” የነበረች ጊዜ ያኔ መንግስት የነበረው ደርግ አይቀጡ ቅጣትም ይሁን ይቀጡ ቅጥጣት ”ወንበዴውን” በሚቀጣው ጊዜ በድል ቦታ ላይ የሚያውለበልበው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን ነበረ። እና በወቅቱ ወንበዴ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ነጋዴ የሆኑ መሪዎቻⶭን ባንዲራን ጠምደው ቢይዟት ምንም አይደንቅም። (በቅንፍም፤ መሪዎቻችንን ነጋዴ ያልኩት ከወንበዴ ጋር እንዲገጥም ብዬ እንጂ ለክፋት አለመሆኑን እገልጻለሁ።)
በነገራችን ላይ ኢህ አህአዴግን ኢሃዴግ ያደረጉት አራቱም ድርጅቶች ለየከልላቱ የመረጡት ባንዲራ /አርማ/ ከኢትዮጵያ ባንዲራ መልክ ራቅ ያለ እንዲሆን የተደረገውም የባንዲራውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ላይ ቂም ከመቋጠር የተነሳ ሊሆን እንደሚችል እንጠረጥራለን።
መጠርጠራችን ካልቀረም የኦነግን አርማ ራሱ ኢህአዴግ ጠምዳ የያዘችው ከዋናው ሰንደቅ አላማ ቀለማት የተቀዳ በመሆኑ ነው። ከዚህ በፊት እንዳወጋነው ኦነግ ሲመሰረት የነበሩ ታጋዮች የትግሉ ማዕከል ”ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ” (የተጨቆኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች) የሚል መሆን አለበት የሚሉ እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር የሚሉ ሁለት ሃሳቦች ይንሸራሸሩ ነበር። የኦነግን አርማ ልብ ብለን ስናይ ሁለቱም አይነት የግንባሩ ታጋዮች ጸባቸው ከኢትዮጵያ ሰንደቅ እና የሰንደቁ ቀለማት ሳይሆን ጨቋኞች ከሚሏቸው አመራሮች ጋር መሆኑን መረዳት ቀላል ነው።
የኢህአዴግ ቂም ግን ስር ነቀል አቄቂያም ነው። ”ፀቤ ከጨቋኙ ደርግ አምባገነናዊ ስራአት ጋር ነው” ሲለን የነበረው ኢህ አዴግ ”ባንዲራን ጨርቅ ነው” ከማለት ጀምሮ በአፋር ግመሎቹ ሁሉ ያውቁታል የሚባለውን፣ በኦሮሞ የተቃዋሚው አርማ ቀለም ሁሉ የተደረገውን፣ በደቡብ ከትንሽ እስከ ትልቅ በዓላት ማድመቂያ የተደረገውን፣ በትግራይ እና በአማራው ዘንድም የማንነት መገለጫ ሆኖ የነበረውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም በሌሎች ክልላዊ ባንዲራ ተካው። ሳስበው ኢህ አዴግ ጠቅላላ የሀሪቱን ሰንደቅ አላማ ራሱ ሌላ አይነት ቀለማት ቢሰጠው ደስታው ይመስለኛል። ነገር ግን ሰንደቁን እንደ ደሙ ለሚያየው መላ ኢትዮጵያዊ ይሄ ከባድ ነበር።
ባንዲራ
የሆነው ሆኖ ”የብሄር ብሄረስቦች ህዝቦች እና ሀይማኖቶች በእኩልነትና በአንደነት አብረው ለመኖር ያላቸውን ተስፋ” ያሳያል የተባለው ኮከብ የባንዲራው አውራ ሆኖ ተቀመጠ። (ውይ ትርጉሙ እንዴት ደስ ይላል።… ችግሩ የብሄር ብሄረስቦች እና ሃይማኖቶች እኩለነት እኩለ የገዢው ፓርቲ ግዝገዛ እና ብዝበዛ ሰለባ መሆናቸው ነው) ይሄ ሁሉም ሆኖም የመንግስታችን ዋና ሴራ ሂደት ባለቤቶች (ይቅርታ ሴራ ሂደት ያልኩት ስራ ሂደት ለማለት ፈልጌ ነው) እና የመንግስታችን ዋና ሰዎች ለሰንደቅ አላማው ቁብ ሲሰጡ አልታዩም። ከአምስት ይሁን ከስድስት አመት በፊት በባንዲራ ጉዳይ ልብ ገዝተናል ያለው መንግስታችን አሁን ደግሞ የባንዲራ ቀን ካላከበራችሁ ወዮላችሁ እያለን ነው።
እኛም እንጠይቃለን፤
የቱን ባንዲራ…
አቶ መለስ ጨርቅ ነው ያሉትን ነው፣ ወይስ በአደባባይ ዘቅዝቀው የያዙትን፣ ወይስ በቀብራቸው ጊዜ ሳይሞት አብሯቸው አፈር የገባውን፣ ወይስ መቼለታ ዶክተር ቴውድሮስ ያስረገጡትን ባንዲራ ነው ካላከበራችሁ ወዮላችሁ የምትሉን… !?

Wednesday, October 1, 2014

Statement from Ginbot 7 Regarding the Horrific Video of Murdered Civilians in the Ogaden Region

Ginbot 7, Movement for Justice, Freedom and Democracy is deeply saddened and outraged by the recent leaked video of barbaric killings of civilians suspected of supporting the Ogaden National Liberation Front (ONLF). Anyone with a conscience should be disturbed by the brutal scenes and sounds of hundreds of civilians whom the regime’s security forces have raped, tortured and killed.
Once again this video is a stark reminder to all Ethiopians, irrespective of their ethnic background and religious affiliation, that Ethiopia is ruled by a savage, blood-thirsty regime carrying out a reign of terror in all parts of Ethiopia.
There are no words of condolence that can adequately convey our sorrow, our sympathy for the victims and their families. The unfathomable brutality of the Tigrai People’s Liberation Front (TPLF) security forces dragging the dead corpses of alleged ONLF supporters in an act of coward savagery is an insult to the moral values of the Ethiopian people, and humanity in general
We affirm our just revulsion over these heinous crimes and call on those responsible for such a heinous crime to be held accountable.
There is no question that in the last 23 years the brutal TPLF regime has committed thousands of grave human rights violations against civilians in the Ogaden region and other parts of Ethiopia. Many of its most gruesome acts constitute war crimes and crimes against humanity.
The TPLF brutal and merciless regime has stubbornly continued its unabated threats to annihilate any group that does not embrace its bankrupt ideology of ethnic politics which it zealously promotes to stay in power.
The people of Ethiopia want to live together in peace with their rights, dignity and freedom protected and respected like the rest of humanity. More than ever, it is high time and in their long term interest in the region for Western democratic nations that support the TPLF by financing, arming and training its security forces to take a very hard look at the moral and political hazards of forming an alliance with a barbaric regime that engages in wanton violence (mass executions, torture, war crimes, ethnic cleansing) against its perceived political enemies.
Donor countries need to stop burying their head in the sand and acknowledge the basic fact that the TPLF regime is a threat to the people of Ethiopia and the stability of the Horn of Africa. Where there is no justice, there will never be peace.
Let it be clear to all concerned that the status quo in Ethiopia is not sustainable. The Ethiopian people will prevail over the inhumane and brutal dictatorship of the fascist minority dictatorship of the TPLF.
Freedom and Justice for the People of Ethiopia!