አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ታህሳሥ 19 እና 20 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተገኘው የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ለፓርቲው እጅግ ከበቂ በታች የሆነ ሽፋን በመስጠቱ የተነሳ ፓርቲው ቅሬታውን አሰምቷን፡፡ ሙሉ መግለጫው ተያይዞ ቀርቧል፡
ቁጥር አንድነት /801/2ዐዐ6 ቀን 28/ዐ4/2ዐዐ6 ዓም
ለኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅትለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
አዲስ አበባ
ጉዳየ፡- የዘገባ ሚዛናዊነትን ጥያቄ ይመለከታልአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ባሻሻለው በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2ዐዐዐ መሠረት የተመሰረተና እውቅና አግኝቶ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ህጋዊና ሠላማዊ ትግል የሚያካሂድ ፓርቲ ነው፡፡
ይሁን እንጂ ፓርቲያችን ታህሣሥ 19 እና 2ዐ ቀን 2ዐዐ6 ዓም በመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ የጡረተኞች መዝናኛ ክበብ ልዩ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጓል፡፡ ይህንን በሁለት ዓመት የተካሄደ ጉባኤ ለመዘገብ በስፍራው ተገኝታችሁ የተሰጠው ሽፋን በመጀሪያው ቀን ምንም ሲሆን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ የተሰጠው ሽፋን እጅግ አናሳና አሳዛኝ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ኢሕአዴግ በባህር ዳር ከተማ የአካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ ከቦታው ተገኝታችሁ በቀጥታና ተደጋጋሚ ሽፋን መስጠታችሁን ማስታወስ እንፈልጋለን፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ የሚተዳደሩ ሲሆን በሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች መሠረት የሁሉንም ፓርቲዎች የሥራ እንቅስቃሴ በእኩልነት ማስተናገድ እንዳለባቸው እናምናለን፡፡ በመሠረቱ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግም ሆነ እኛ በሚዲያ አጠቃቀም ጉዳይ በእኩልነት ሚዛን መታየት ሲገባ እንኳን ጠቅላላ ጉባኤ የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች የሥራ አስፈፃሚ ስብሰባ በጣም ሰፊ ሽፋን ሲያገኝ በኛ በኩል ለሚተላለፉ የጠቅላላ ጉባኤና ሌሎች ዘገባዎች ሚዛናዊነት የጎደለው መስተንግዶ እየተደረገ በመሆኑ ጉዳዩ ያሳሰበንና ያሳዛን መሆኑን መግለጽ እንወዳለን፡፡
ከሠላምታ ጋር
ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራውፕሬዚደንት
እንዲታወቅ ለሁሉም የመገናኛ ብዙሃን አካላት
No comments:
Post a Comment