Thursday, March 28, 2013

Azeb Mesfin is squandering millions of dollars – ABC


Azeb Mesfin, mother of corruption
A major newspaper based in Madrid, Spain, ABC Internacional, has reported that Azeb Mesfin, the wife of Ethiopia’s dictator Meles Zenawi is squandering the 1.2 billion euros her husband has stolen during the past two decades. (Read here)
 
The newspaper identifies Azeb Mesfin as one of the most wasteful wives of African leaders and accuses her of siphoning off millions of dollars.
 
Azeb is known among Ethiopians as the mother of corruption.
The other wives of African dictators the newspaper listed include Grace, the notorious wife of Zimbabwe’s dictator Robert Mugabe, and Leila Trabelsi, the wife of the recently deposted Tunisian dictator Ben Ali.

Monday, March 25, 2013

በጣም አስደንጋጭ ዜና ከአንድ መቶ ሺ ኢትዮጵያውያን ከቆሻሻ ገንዳ ውስጥ የሚመገቡ መሆኑ ተረጋገጠ


ወያኔ የኢኮኖሚ እድገቱ 11% አደገ እያለ በየጊዜው ዲስኩር ያሰማናል ሆኖም ግን ነገሩ ወዲህ ነው ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲ እንዲሉ በአዲስ አበባ 100,000 ሰዏች ከቆሻሻ ገንዳ ምግብ ይመገባሉ። ህፃናት እየራባቸው ትምህርት መከታተል እንደተሳናቸው ከህፃናቱ አንደበት አድምጠናል። የኢኮኖሚ ስሌቱ እንዴት እንደተሰላ እነርሱ ያውቃሉ እኔን ግን የገባኝ ሀገሪቷን እንደነቀዝ የሚመጠምጡ የወያኔ አሸርጋጆችና ሀገር ቆርሰው የሚሸጡ ባንዳ ሆዳሞች ሀብት ብቻ ተሰልቶ ኢኮኖሚው ማደጉ እየተነገረን ይገኛል።

ለማንኛውም ወያኔዎች ትንሽ በህኒናቸው ማሰብ ቢጀምሩ ጥሩ ይመስለኛል የእነርሱ ልጆች ጠግበው እና አማርጠው እየበሉ ደሃው የኢትዮጵያ ህዝብ እስከመቼ እየተራበና በገዛ ሀገሩ እንደባዳ እየተቆጠረ እንደሚኖር አነጋጋሪ ነው። በመሆኑም ስሜቱ እጅግ በጣም ከባድ ነው ይህንን ሰቆቃ በአፋጣኝ ለማቆም ሁላችንም በመተባበርና ያለንን አቅም ሁሉ በመጠቀም ህዝባችንን ነፃ ለማውጣት ትግሉን ወደፊት ማስኬድ አለብን እላለሁ። ቪድዮውን ይመልከቱ
 

Thursday, March 21, 2013

የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት የሆኑት አማረ ማሞና አሰፀያፊ ስራቸው


    • ታምራት ላይኔና አማረ (ክፍል-2)
                                                (ከኢየሩሳሌም አ.)
አማረ አረጋዊ በማስታወቂያ ሚ/ር የኢቲቪ ስራ አስኪያጅ ሃላፊ እያለ በጣም አፀያፊ ተግባራትን በየእለቱ ይፈፅም ነበር። እሱን ጨምሮ አራት የሕወሐት ሃላፊዎች ተመሳሳይ ወራዳ ተግባር ይፈፅሙ ነበር፤ አንዱ ዋሽንግተን የሚገኝና የፓርቲው ሰላይ ሲሆን አንዱ የሻዕቢያ ተላላኪ ሆኖዋል፤ ሌላው ሹም በርካታ ሴቶችን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታ ሆን ብሎ በማስያዝ አገር ቤት እንዳለ (እስከ 2000ዓ.ም) አውቃለሁ፤ አሁን ግን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ መረጃው የለኝም።…
       በወቅቱ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ጉዳዩን ሰምተው አማረን ግምገማ ይጠራሉ፤ ቃል በቃል እገልፀዋለሁ፥ « አማረ ቢሮ ውስጥ (office sex) ትፈፅማለህ፤ ..» በማለት በማስረጃ አስደግፈው ሲነግሩት፣ የሰጠው መልስ ፥ « በረሃ አይደለም ያለሁት፤ ስራዬን እስካልበደልኩ ድረስ የፈለኩትን ማድረግ እችላለሁ፤ መብቴ ነው..» የሚል ነበር። በዚህም ምክንያት በታምራት ትእዛዝ አማረ ከሃላፊነት እንዲነሳ ተደረገ።.. በእርግጥ አማረ ኢቲቪ እያለ ለጋዜጠኞችና ለፕሮግራም አዘጋጆች ሙያዊ ነፃነት በመስጠት በኩል ስሙ በበጎ የመነሳቱን ያክል፣ በአንፃሩ ለዜና አንባቢነት..ወዘተ ለመቀጠር የምትመጣ ሴት እንደግዴታ የሚቀርብላት ገላዋን ለአማረ <ማቅረብ> ነበር። በሕዝብ የሚታወቁና የተጎበኙ በዝርዝር ማንነታቸውን መግለፅ ቢቻልም ለዛሬው ማለፍን መረጥኩ። በነገራችን ላይ አንድ ሴት በግሩፕ ጭምር ቢሮ ውስጥ ያማግጡ እንደነበር ሳልጠቁም አላልፍም።…በተጨማሪ በወቅቱ የማ/ሚ/ር የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ « ዳንዲ» በሚለው መፅሃፍ እንደገለፁት « በስነምግባር ጉድለት የተገመገሙና እርምጃ የተወሰደባቸው እንዳሉ..» ጠቁመው ነበር። ያውም በጨዋ አገላለፅ!! ስም ግን አልጠቀሱም። አንዱ ግን አማረ ነበር።….
     አማረ በአቶ ታምራት ውሳኔ በተላለፈበት ሰሞን እንዳጋጣሚ አቶ መለስ ለጉብኝት አውሮፓ ነበሩ። ሲመለሱ የጠየቁት « አማረ የታለ?» ብለው ነበር። የተፈጠረው ሁኔታ ተነገራቸው። አማረን አስጠርተው አነጋገሩት። ከዛም አማረ ጋዜጣ መጀመር እንደሚፈልግ ገለፀ። በሃሳቡ ተስማሙ። ጋዜጣው «እንደ መነፅር ሆኖ መንግስትን፣ፓርቲውን..» ማገልገል እንዳለበት ተስማሙ። በአቶ መለስ ቀጭን ትእዛዝ ለ<ሪፖርተር> ወይም « ኤም.ሲ.ሲ» ማስጀመሪያ አንድ ሚሊዮን ብር (በወቅቱ ምንዛሬ ከሁለት መቶ ሺህ የሚበልጥ ዶላር) እንዲፈቀድለት አደረጉ። ለገንዘቡ መፈቀድ የተሰጠው ሽፋን ወይም ምክንያት < የግልጋሎት ዘመን > የሚል ነበር። በአንፃሩ የእርሱን ሁለት ወንድሞች ጨምሮ 36ሺህ የፓርቲው ታጋዮች በመለስ ዜናዊ « ጓሓፍ » ወይም <ቁሻሻ> ተብለው ጎዳና በጅምላ የተጣሉት አንዳች ሳንቲም ሳይሰጣቸው ነበር። የትና ለማን ነው አማረ ያገለገለው?..ስንት አመት?..ሴቶች እህቶቻችን <ገላ> ላይ እንዳሻው <ስለተገለገለ> ?...የሚሉ አስገራሚ ጥያቄዎች መነሳታቸው ግድ ነው። 
ያም ሆነ ይህ አማረ ከመለስ በተበጀለት የህዝብ ገንዘብ ..በግል ፕሬስ ሽፋን የሚነግድበትን <ጋዜጣ> ጀመረ። እንደተባለው <መነፅር> ሆኖ ቀጠለ። የአየር መንገድ ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ አህመድ ቀሎ ከሃላፊነት ሲነሱ በ<ጦቢያ> ጋዜጣ ላይ በወቅቱ በሰጡት መግለጫ « እኔን ያባረረኝ መንግስት ሳይሆን..ለመንግስት መስተዋት ሆኖ በሚያገለግለው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው» ብለው ነበር።…አማረ ሲበዛ ቂመኛ ሰው ነው፤ ታምራት ላይኔን እስኪበቃው በጋዜጣው ተበቅሏቸዋል። ከታሰሩ በኋላ ፥ < ከመኖሪያ ቤታቸው ቁምሳጥን ውስጥ የተገኘ የፍቅር ደብዳቤ…» እያለ በየሳምንቱ ዘምቶባቸዋል። 
                                                                                              (ይቀጥላል)
    • ታምራት ላይኔና አማረ (ክፍል-2)
      (ከኢየሩሳሌም አ.)

      አማረ አረጋዊ በማስታወቂያ ሚ/ር የኢቲቪ ስራ አስኪያጅ ሃላፊ እያለ በጣም አፀያፊ ተግባራትን በየእለቱ ይፈፅም ነበር። እሱ...ን ጨምሮ አራት የሕወሐት ሃላፊዎች ተመሳሳይ ወራዳ ተግባር ይፈፅሙ ነበር፤ አንዱ ዋሽንግተን የሚገኝና የፓርቲው ሰላይ ሲሆን አንዱ የሻዕቢያ ተላላኪ ሆኖዋል፤ ሌላው ሹም በርካታ ሴቶችን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታ ሆን ብሎ በማስያዝ አገር ቤት እንዳለ (እስከ 2000ዓ.ም) አውቃለሁ፤ አሁን ግን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ መረጃው የለኝም።

      በወቅቱ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ጉዳዩን ሰምተው አማረን ግምገማ ይጠራሉ፤ ቃል በቃል እገልፀዋለሁ፥ « አማረ ቢሮ ውስጥ (office sex) ትፈፅማለህ፤ ..» በማለት በማስረጃ አስደግፈው ሲነግሩት፣ የሰጠው መልስ ፥ « በረሃ አይደለም ያለሁት፤ ስራዬን እስካልበደልኩ ድረስ የፈለኩትን ማድረግ እችላለሁ፤ መብቴ ነው..» የሚል ነበር። በዚህም ምክንያት በታምራት ትእዛዝ አማረ ከሃላፊነት እንዲነሳ ተደረገ።.

      በእርግጥ አማረ ኢቲቪ እያለ ለጋዜጠኞችና ለፕሮግራም አዘጋጆች ሙያዊ ነፃነት በመስጠት በኩል ስሙ በበጎ የመነሳቱን ያክል፣ በአንፃሩ ለዜና አንባቢነት..ወዘተ ለመቀጠር የምትመጣ ሴት እንደግዴታ የሚቀርብላት ገላዋን ለአማረ <ማቅረብ> ነበር። በሕዝብ የሚታወቁና የተጎበኙ በዝርዝር ማንነታቸውን መግለፅ ቢቻልም ለዛሬው ማለፍን መረጥኩ። በነገራችን ላይ አንድ ሴት በግሩፕ ጭምር ቢሮ ውስጥ ያማግጡ እንደነበር ሳልጠቁም አላልፍም።…በተጨማሪ በወቅቱ የማ/ሚ/ር የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ « ዳንዲ» በሚለው መፅሃፍ እንደገለፁት « በስነምግባር ጉድለት የተገመገሙና እርምጃ የተወሰደባቸው እንዳሉ..» ጠቁመው ነበር። ያውም በጨዋ አገላለፅ!! ስም ግን አልጠቀሱም። አንዱ ግን አማረ ነበር።

      አማረ በአቶ ታምራት ውሳኔ በተላለፈበት ሰሞን እንዳጋጣሚ አቶ መለስ ለጉብኝት አውሮፓ ነበሩ። ሲመለሱ የጠየቁት « አማረ የታለ?» ብለው ነበር። የተፈጠረው ሁኔታ ተነገራቸው። አማረን አስጠርተው አነጋገሩት። ከዛም አማረ ጋዜጣ መጀመር እንደሚፈልግ ገለፀ። በሃሳቡ ተስማሙ። ጋዜጣው «እንደ መነፅር ሆኖ መንግስትን፣ፓርቲውን..» ማገልገል እንዳለበት ተስማሙ። በአቶ መለስ ቀጭን ትእዛዝ ለ<ሪፖርተር> ወይም « ኤም.ሲ.ሲ» ማስጀመሪያ አንድ ሚሊዮን ብር (በወቅቱ ምንዛሬ ከሁለት መቶ ሺህ የሚበልጥ ዶላር) እንዲፈቀድለት አደረጉ። ለገንዘቡ መፈቀድ የተሰጠው ሽፋን ወይም ምክንያት < የግልጋሎት ዘመን > የሚል ነበር። በአንፃሩ የእርሱን ሁለት ወንድሞች ጨምሮ 36ሺህ የፓርቲው ታጋዮች በመለስ ዜናዊ « ጓሓፍ » ወይም <ቁሻሻ> ተብለው ጎዳና በጅምላ የተጣሉት አንዳች ሳንቲም ሳይሰጣቸው ነበር። የትና ለማን ነው አማረ ያገለገለው?..ስንት አመት?..ሴቶች እህቶቻችን <ገላ> ላይ እንዳሻው <ስለተገለገለ> ?...የሚሉ አስገራሚ ጥያቄዎች መነሳታቸው ግድ ነው። 

      ያም ሆነ ይህ አማረ ከመለስ በተበጀለት የህዝብ ገንዘብ ..በግል ፕሬስ ሽፋን የሚነግድበትን <ጋዜጣ> ጀመረ። እንደተባለው <መነፅር> ሆኖ ቀጠለ። የአየር መንገድ ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ አህመድ ቀሎ ከሃላፊነት ሲነሱ በ<ጦቢያ> ጋዜጣ ላይ በወቅቱ በሰጡት መግለጫ « እኔን ያባረረኝ መንግስት ሳይሆን..ለመንግስት መስተዋት ሆኖ በሚያገለግለው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው» ብለው ነበር።…አማረ ሲበዛ ቂመኛ ሰው ነው፤ ታምራት ላይኔን እስኪበቃው በጋዜጣው ተበቅሏቸዋል። ከታሰሩ በኋላ ፥ < ከመኖሪያ ቤታቸው ቁምሳጥን ውስጥ የተገኘ የፍቅር ደብዳቤ…» እያለ በየሳምንቱ ዘምቶባቸዋል። 
      (ይቀጥላል)

Wednesday, March 20, 2013

Ethiopians in Frankfurt call for release of all political prisoners





FRANKFURT, Germany - Ethiopian protesters in the Germany city of Frankfurt condemned the dictatorial regime in Addis Ababa and called for greater freedom in the country. The activists called for the release of all political prisoners. Religious leaders also took part in the rally organized by EPPF-Guard (March 1, 2013)

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት International Ethiopian Women's Organization

   
 
ከዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት የተሰጠ የድጋፍ ጥሪ ! 


ውድ አገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ግዜ የምትገኝበት ነባራዊ ሁኔታ፣ ለብሔራዊ የጋራ ሕልውናዋ ሆነ የሕዝቧ ደህንነት ከመቼውም ግዜ በበለጠ ፣ በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢና አስጊ ወቅት ላይ ደርሷል ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከመንጋቱ በፊት ይጨልማል ነውና ፣ለጨለማ ግዜ የዳረገን ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን። ሆኖም ከጨለማ ወደ ብረሃን መሸጋገር አይቀርም እና ከተሸጋገርን በዃላ ግን ይዘን መገኘት ያለብንን ብሔራዊ እሴቶች እንዳናጣ ከወዲሁ በሁሉም ረገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል። ከታሪክ እንደምንረዳው ሕዝብንና  የራስን ማንነት ማጣት ይኖራልና ። የወያኔ ዘረኛ የጎሳ አገዛዝ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በሴቶች ፣በክርስትናና በእስልምና ሐይማኖት ተቋሞች በተለይም ደግሞ በቅርቡ በዐማራው ማህበረሰብ ላይ የሚፈጽመውን በግፍ የማፈናቀልና የዘር ማጽዳት  ዘመቻ ባስቸኳይ  ካልተገታ ለትውልድ የሚተላለፍ ቀውስና ጥፍት ከፊታችን ተደቅኖ የሚጠብቀን መራራ ሃቅ ነው።

እንደሚታወቀው ወያኔ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት ለማፍረስና አገራችንን ለመበተን ከነደፋቸው እቅዶች ውስጥ ቀዳሚ ቦታ ከያዙት አንዱና ዋነኛው የዐማራውን ማህበረሰብ በጠላትነት ፈርጆ ማጥቃት ፣ማዳከምና ማጥፋት የሚለው ዓላማ ነው። በዓላማቸውም መሠረት ላለፉት ሃያ አንድ ዓመታት በዐማራው ማህበረሰብ ላይ ይነጣጠር የነበረው ጥቃት ዛሬ በስፋትና በጥልቀት ተፋፍሞ አሳሳቢና አደገኛ በሆነ ደረጃ በመካሄድ ላይ ነው። ላለፉት ጥቂት ወራት  በተለያዩ የአገራችን ግዛት ውስጥ የሚኖሩትን የዐማራው ማህበረሰብ ኢትዮጵያውያን  ከኑሮዋቸውና ከቤታቸው በማፈናቀል የህልውና መብታቸው ተገፎ ኢሰብአዊ የሆነ ጥቃት እየተካሄደባቸው ነው። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህጻናትና ሴቶች የመከራው ገፈት ቀማሽ እንደመሆናቸው ሁሉ ለአሰቃቂ ችግርና እንግልት ተዳርገዋል። በአንጻሩ ግን የኢትዮጵያ መሬት ለባእዳን አገሮች በገፍ እየተቸረቸረ ኢትዮጵያውያን ግን ዐማራ  ስለሆኑ ብቻ ከመሪታቸው ተፈናቅለው ለዱርና ለመንገድ አዳሪነት ተዳርገዋል፣መሠረታዊ የመኖር መብታቸውን ተቀምተዋል።

ዛሬ የዐማራው ማህበረሰብ ለወያኔ ዘረኛ የጎሳ አገዛዝ የተቀነባበረ ኢትዮጵያዊነትን የመበተን እቅድ  ውስጥ ዋናውን ቦታ የያዘ ኢላማ ይሁን እንጂ ነገ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የሚከሰት መሆኑ የወያኔ ተግባራዊ ባህሪ ያረጋገጠው ሃቅ ነው። ይህን አገር የማፍረስና ሕዝብን የማፈናቀል ሂደት ባስቸኳይ ማስቆም ፣ለዚህም ችግርና መከራ የዳረገንን የወያኔ ዘረኛ ሥርዓትን ከመሠረቱ መንቅሎ ማስወገድ አማራጭ የሌለው የወቅቱ የኢትዮጵያውያን ተግባር ሊሆን ይገባል። ስለዚህም ይህን ተግባር ከግቡ ለማድረስ ኢትዮጵያዊነትን ማዕከል ያደረጉ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ ንቅናቄዎች ፣የብዙሃንና የሞያ ማህበርት ሁሉ በሓይማኖት፣ በቋንቋ ፣በጎሳ፣ ሳንለያይ በዐማራው ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰውን ኢሰብአዊ ድርጊት በማውገዝ ችግሩ የጋራ መሆኑን በመገንዘብ ሙሉ ድጋፋቸውንና ትብብራቸውን  መግለጽ ተገቢ ይሆናል። እንደሌሎች ኢትዮጵያዊ ጥያቄዎች የዐማራው ማህበረሰብ ችግርና ጥያቄ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይና ጥያቄ ነው። 

በዐማራው ማህበረሰብ ላይ የሚካሄደው የመበተንና ዘር  የማጥፋት ጥቃት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት መሆኑን በመገንዘብ ፣ በአንድ ድምጽ ድርጊቱን ማውገዝና ማስቆም የትግላችን አንደኛው ገጽታና አጣዳፊ የጋራ ተግባር ነው። ጥቃቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያስከትለው አደጋ በዐማራው ማህበረሰብ ላይ ብቻ ሳይወሰን በጋራ ህልውናችንና ደህንነታችን ላይ ጭምር ነው። 

ባጠቃላይ በአገራችን ላይ በተለይም ሰሞኑን በሓይማኖት ተቋሞችና  በዐማራው ማህበረሰብ ላይ የሚፈጸመውን ግፍና ወንጀል ለማስቆም በሚደረገው ትግል የሴቶች በሙሉ ወሳኝነት መሳተፍ አማራጭ የሌለው ታሪካዊ ግዴታ ነው። የሴቶች መብት ያለ አገር ህልውና ሊከበር ስለማይችል አገርን ለማዳንም የሴቶች ሚና ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ በዚህ አሳሳቢ ወቅት በድጋሚ ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት ለኢትዮጵያውያን ሁሉ  የተግባራዊ ትብብርና የድጋፍ ጥሪ እናስተላልፋለን።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ !
ድል የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ! 
ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት
መጋቢት, 2005 (March, 2013)           

Sunday, March 17, 2013

FinFisher spyware seen targeting victims in Vietnam, Ethiopia


By Jeremy Kirk
March 13, 2013 — IDG News Service — New research suggests a controversial spyware suite called FinFisher is being used to track activists in more countries than previously thought, including Vietnam and Ethiopia.
FinFisher, made by a subsidiary of U.K-based Gamma Group, is a set of remote intrusion and interception tools intended for use by law enforcement and intelligence agencies. But critics say the software is also used by repressive regimes to target activists, and they consider it malicious software.
Despite being known for several years, researchers say FinFisher's use is widening and that technical modifications are being made to help it evade detection.
The latest research was published Wednesday by the Munk School of Global Affairs, part of the University of Toronto. Researchers there found more command-and-control servers used by FinFisher to control the software and collect captured information.
One sample of FinFisher, which the researchers dubbed FinSpy, appears to have been used to target an opposition group in Ethiopia called Ginbot 7, which was designated as a terrorist group by the country in 2011, wrote Morgan Marquis-Boire, a security researcher and technical advisor at the Munk School and a security engineer at Google.
FinSpy presented itself as an image file of Ginbot 7 in an attempt to get victims to open it, he wrote. It communicates with a command-and-control server, which is still operational, hosted on an IP address belonging to Ethiopia's state-owned telecommunications company, Ethio Telecom. The sample is similar to one that was sent to Bahraini activists in 2012.
"The existence of a FinSpy sample that contains Ethiopia-specific imagery and that communicates with a still-active command and control server in Ethiopia strongly suggests that the Ethiopian Government is using FinSpy," Marquis-Boire wrote.
A FinFisher product for Android mobile devices was also analyzed that communicated with a command-and-control server in Vietnam.
The software, called FinSpy Mobile for Android, sends a person's text messages to a Vietnamese phone number, Marquis-Boire wrote. The FinFisher suite of products includes similar software designed for iOS, Android, Windows Mobile and BlackBerry, including functions such as the ability to send GPS coordinates and snoop on conversations near where a phone is used.
"Both the command and control server IP and the phone number used for text-message exfiltration are in Vietnam, which indicates a domestic campaign," Marquis-Boire wrote. "This apparent FinSpy deployment in Vietnam is troubling in the context of recent threats against online free expression and activism."
A scan of the Internet also found 30 new command-and-control servers used to control FinFisher products in some 19 countries. Seven of the countries had not been known to host FinFisher servers before; they are Canada, Bangladesh, India, Malaysia, Serbia, Vietnam and Mexico. The report notes that those countries may not be involved in the actual surveillance, but networks located in those countries are being used to store information.

Monday, March 11, 2013

እኛም እንድገመዋ… ርዕዮትን እያሰሩ … ቐሽ ገብሩን ቢዘክሩ… “ሼም” የለም በአገሩ





ተዓምረኛው ኢቲቪ ለማርች ስምንት የሴቶች ቀን መታሰቢያ አንድ ዶክመንተሪ ፊልም አሳይቶናል። ፊልሙ የዛሬ አመት ተላልፎ እኛም የአቅማችንን አስተያየት ሰጥተንበት ነበር። ታድያ ዛሬም ኢቲቪዬ ፊልሙን ደግሞ አሳይቶናል። ታድያ መድገም ብርቅ ነው እንዴ… እኛም አስተያየታችንን እንድገመዋ!



በመጀመሪያ አበሻ እንደመሆኔ መጠን ጭቆናን “እምቢ” ብለው ፋኖን ለዘመሩ ታጋዮች ትልቅ አክብሮት እንዳለኝ ያለ ሽሙጥ እገልፃለሁ።
ተስፋዬ ገብረ አብ ከተረካቸው ትረካዎች በሙሉ “የቁንድዶ ፈረስ” ትረካ በጣም የመሰጠችኝ  ናት። እስቲ ለማስታወስ ልሞክር…
ሐረር አካባቢ፤ የጋሪ ፈረሶች የሚደርስባቸው የስራ ጫና እጅግ በጣም ከባድ ነበር። ከስራ ጫናው እኩል ደግሞ ዱላም አለው። ልክ አሁን አሁን ደሞዛችን አነሰ ብለን “ኡኡ” ስንል “ለአባይ እና ለሌሎች ልማቶች ደግሞ መዋጮ አዋጡ” ተብለን መከራችንን እንደምናየው ማለት ነው። በዚህ ላይ እነዚህ የጋሪ ፈረሶች ስራውና ዱላ የሚደራረብባቸው አንሶ ጌታቸው (አባ ፈርዳው) ቀለባቸውንም በአግባቡ አይሰፍርላቸውም ነበርና ከሰውነት ጎዳና ወጥተው ክስት ጉስቁል አሉ።
ይሄን ግዜ “እምቢኝ” አሉና “ቁንድዶ” ወደተባለ ጫካ ገቡ። ከዛም ባህሪያቸው ተለውጦ እንደፈረስ ሳይሆን እንደ እንደ አውሬ ሆኑ። ማን ወንድ መጥቶ ዳግም ወደዛ የጋሪ ባርነት ይመልሳቸው? ማንም።
ታድያ ፈረሶቹ እዛው ጫካ ውስጥ መሽገው እንዳሻቸው እየበሉ እንዳሻቸው እየቦረቁ አማረባቸው። ወዘናቸውም “ጢም” አለ።
“በአሁኑ ግዜ የሀረር አካባቢ ነዋሪዎች የኦህዴድ አባላትን እስከ መቼ የጋሪ ፈረስ ትሆናላችሁ? አንዳንዴ እንኳን የቁንድዶ ፈረስ ሁኑ እንጂ…! እያሉ ያሽሟጥጧቸዋል።” ብሎናል ተስፋዬ። (ልክ ነኝ አይደል ተስፋዬ…? “ይሄንን እኔ አላልኩም” ካልክ እኔ ለማለት እገደዳለሁ…!(ፈገግታ))
እናም እኔ በበኩሌ የቁንድዶ ፈረስነትን አደንቃለሁ። አላማው ልክ ነው አይደለም የሚለው ጥያቄ በይደር ይቆይ። ነገር ግን በደል ሲበዛ “እምቢ” ማለት ከአባት የወረስነው ነው። ዛሬ የሽብረተኝነት አዋጅ ወጥቶ ሳይከለከል አይቀርም እንጂ አንድ ዘፈን ትዝ ይለኛል…
“ደብቆታል መሰል ሶማ በረሃው
“እምቢ” ያለው ጎበዝ የታል ሽፈራው” የሚል ዘፈን።
በአሁኑ ወቅት፤ ይህንን ዘፈን በይፋ መዝፈን የሚቻል አይመስለኝም። ምክንያቱም በሽብርተኝነት አዋጁ አንድ ግለሰብ፤ በዘፈን በፅሁፍ እና በተለያዩ መንገዶች “ሽብርተኛን” እንኳንስ ሲያበረታታ ተገኝቶ ይቅርና፤ “አበረታቷል” ተብሎ ሲታሰብም “ጉዱ ይፈላል” ይላል። በተጨባጭ እንደምናየው ደግሞ እንኳንስ እምቢ ብለው ሶማ ጫካ ገብተው ይቅርና በከተማው ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ራሳቸው “አሸባሪ” ስለመሆናቸው መረጃው አለ። ማስረጃው ጠፍቶ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩም እኛም የጨነቀን…! ስለዚህ “ደብቆታል መሰል ሶማ በረሃው እምቢ ያለው ጎበዝ የታል ሽፈራው…” ብሎ ማዜም አይቻልም ማለት ነው።
ለማንኛውም፤ ዘፈኑ ግን “እምቢ” ባይነትን እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙሃን የሀገሬ ሰው እንደሚያደንቅ ያስረዳልኛል። አዎ አንዳንዴም እምቢ ማለት ጥሩ ነው። “እምቢ… እምቢ ለሀገሬ! እምቢ… እምቢ ለክብሪ! እምቢ… ታታታታ” ፉከራው ራሱ ማማሩ።
ስለዚህ ቐሽ ገብሩ፤ አሞራውና ሌሎችም “እምቢ” ባይ ታጋዮች “እምቢ” በማለታቸው አደንቃቸዋለሁ። እንኳንም እምቢ አላችሁ!
ወደ ቐሽ ገብሩ ስንመጣ የዶክመንተሪው አዘጋጆች ልብ ያላሉት ወይም ደግሞ “ምን ታመጣላችሁ” ብለው ችላ ያሉት አንድ ስህተት የፌስ ቡክ ወዳጆቼ አግኝተው  ነበር።  ልብ በሉልኝ ህውሃት ሆዬ ቐሽ ገብሩን መትረየስ ሲያሸክማት ገና የአስራ ሶስት አመት ልጅ ነበረች። ከፈለጋችሁ አስሉት በአስራ ዘጠኝ ስድሳ አንድ ተወለደች። በአስራ ዘጠኝ ሰባ አራት ወደ ትግል ገባች። ማነው ሂሳብ የሚችል…? በሉ እስቲ አስሉልኝ። ሰባ አራት ሲቀነስ ስድሳ አንድ እኩል ይሆናል፤ አስራ ሶስት። ዘጋቢው ፊልም ሲቀጥልም “…ትግሉን በተቀላቀለች በጥቂት ወራት ውስጥ እጇን ተመታች። እንደዛም ሆና መትረየስ ትሸከም ነበር።” ይላል። ጉድ በል ህውሃት…! አይሉኝም?
በዛ ሰሞን አለም ሲነጋገርበት ከሰነበተባቸው ነገሮች ውስጥ በኡጋንዳ የሚገኘው የሎርድ ሬዚስታንት አርሚ መሪ፤ ጆሴፍ ኮኒ ህፃናትን ጦርነት ውስጥ እየማገደ ነው በሚል ታድኖ ይከሰስ ዘንድ የተጀመረው “ኮኒ ሁለት ሺህ አስራ ሁለት” የሚል እንቅስቃሴ ነው። በአለም አቀፍ ህግ፣ አረ በኢትዮጵያ ህገ መንግስትም ቢሆን ህፃናትን ለጦርነት ማሳተፍ የለየለት ወንጀል ነው። በእግዜሩ ዘንድም ያስጠይቃል።
እና ህውሃት የአስራ ሶስት አመቷን ህፃን ሙሉ “ቐሽ ገብሩ” ን በጦርነት ማሳተፉ ሳያንስ የግፉ ግፍ ደግሞ ለማርች ስምንት የሴቶች መብት ክብረ በዓል ላይ ታሪኳን እንደ ጥሩ ነገር ዘገበልን። እውነቱን ለመናገር ይሄ ትልቅ የወንጀል መረጃ ነው። እንደኔ እምነት ይህንን መረጃ ያጠናከሩ ሰዎች የውስጥ አርበኝነት ስራ እየሰሩ ነው። ይሄ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ገና በርካታ መረጃዎችን ያወጣል። እዝችው ላይ ሙሉ ወይም ቐሽ ገብሩ ገና አስራ ስምንት አመት እንኳ ሳይሞላት አንድ ጎረምሳ በፍቅር ስም አስረግዞ እስከማስወረድ እንድትደርስ እንዳደረጋትም ዶክመንተሪው ይዘግባል። ሰውየው ከሷ ጋር ያሳለፈውን ፍቅርም ሲናገርም በኩራት ነው። እንዴት ነው ነገሩ… እኛ መሀሙድ አህመድ በአንድ ዘፈኑ ላይ “ሸግየዋ ጉብሊቷ… የአስራ አምስት አመቷ እንዴት ነሽ በሉልኝ የምታውቁ ቤቷን” ብሎ ስለዘፈነ አይደል እንዴ ከህፃናት መብት አንፃር ወንጀል ነውና ይቅርታ መጠየቅ አለበት እያልን የምንሟገተው? እንዲህ የባሰውን ነውር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አየነው። ለዚህ ነው አይናችን የተርገበገው…?
ወዳጄ እንዴት ሰነበቱ አይገርምዎትም ይሄ ሁሉ መንደርርደሪያ መሆኑ… ይበሉ ወደ ዋናው ጉዳይ ተያይዘን እናምራ
እናልዎ… ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተለያየ ግዜ የተለያየ ዘጋቢም አወዛጋቢም ፊልሞችን ያቀርብልናል።
በዛ ሳምትን ያየነውም የቐሽ ገብሩ ዶክመንተሪም የዚሁ አካል ነው። እንግዲህ ከላይ ያነሳነውን በቐሽ ገብሩ የተጋለጠውን ህፃናትን ወደ ጦርነት የማሰማራት እና ለአቅመ ህይዋን ያልደረሱ ሴቶችን የማማገጥ ወንጀል እንዲህ ያለውን ጉዳይ ለሚከታተሉ አካሎች እንተወው እና የፈረደባትን ይቺን ህፃን “እምቢ” እንዳለች ጀግና እንቁጠራት። ቆጠርናት…!
ኢህአዴግ ደርግን ብዙ ግዜ ደርግ በጦርነት የማረካቸውን ታጋዮቼን የማያምኑበትን እንዲናገሩ ያሰቃያቸው ነበር፤ ከዛም እምቢ ሲሉት ያስራቸዋል፤ ይገድላቸዋል። ብሎ ይወቅሳል። ይቀጥልናም ቢሆንም ግን፤ “እንደ አሞራው ሁኑ እንደ ቐሽ ገብሩ ሁኑ ብሎ ይመክረናል። እኛም ምክር የምንሰማ ልባሞች ነንና እሺ ብለን እንደ አሞራው፤ እንደ ቐሽ ገብሩም ለመሆን እንታትራለን ከዛ ውጤቱ ምን ይሆናል አይሉኝም…? ለምን እጠይቅሀለው እያወቅሁት…? አሉኝ እንዴ!?
ሰሞኑን አቶ አንዷለም አራጌ ላይ የሆነውን ነገር ሰምተዋል። አንዷለም አራጌ እንደ አሞራው ሁኑ ከመባሉ በፊትም እንደ አሞራው “እምቢ” ባይ ነበር። ለዛውም ጫካ ሳይገባ ፊት ለፊት እምቢ ብሎ የተጋፈጠ ደፋር የተቃማዊ ፓርቲ አመራር ነው። ምን ዋጋ አለው አንዷለም እንደ አሞራው “እምቢ” ቢልም ኢህአዴግ ደግሞ እንደ ደርግ “እምቢ” ማለት አይቻልም ብሎ አሰረው። ማሰር ብቻ ቢሆን በስንት ጣዕሙ ጎረምሳ አስገብቶ አስደበደበው እንጂ!
ማርች ስምንት የአለም ሴቶች ቀን ነው። በአለም ላይ ያሉ ሴቶች ቀደም ሲል ሲደርስባቸው የነበረ ጭቆና ይብቃ የተባለበት ቀን። ይህ ቀን፤ የህውሃት ሴቶች ቀንም የአንድነት ሴቶች ቀንም፤ የጋዜጠኛ ሴቶች ቀንም፣ የሁሉም ሴቶች ቀን ነው።
ርዕዮት አለሙ አሳሪዎቿ የጠላነውን አብረሽን ከጠላሽ ትለቀቂያለሽ ብለዋት ነበር። ቃል በቃል ሲነገር “ኤልያስ ክፍሌ የተባለው ጋዜጠኛን አሸባሪ ነው መሰስክሪበት እና ትለቀቂያለሽ” ተባለች። እርሷም እኔ “በወንጀለኝነት አላውቀውም” ብላ ድርቅ አለች። እንግዲያስ ብሎ ኢህአዴግም አስራ አራት አመት ፈረደባት። ቐሽ ገብሩን ደርግ የያዛት ግዜ “የህውሃት ሰዎችን ወንጀለኛ ናቸው ብለሽ መስክሪባቸው” አላት እምቢኝ ብላ ድርቅ አለች ሞት ፈረደባት። እንግዲህ ቐሽ ገብሩ እና ርዮት አለሙ አንድ ናቸው “እምቢኝ” ብለዋልና። ደርግ እና ኢህአዴግስ…? የመጣው ይምጣ ደፍሬ ልናገር ነው..! አዎ ደርግ እና ኢህአዴግም አንድ ናቸው። እምቢ ያላቸው ላይ ሁሉ ይፈርዳሉና። በነገራችን ላይ የደርግ ፕሮፖጋንዳ ሰራተኞች ቐሽ ገብሩን ለማናገር መከራቸውን ሲያዩ የነበረውን ያህል የኢህአዴግ ጋዜጠኞችም በተደበቀ ካሜራ ሳይቀር ርዮትን ለማናገር አበሳቸውን ሲያዩ ነበር። ነገር ግን ቐሽ ገብሩም ርዮትም አለሙም ፍንክች የአባ ቢላው ልጅ ብለዋል። ወይ መገጣጠም…! አይሉልኝም?
እና ታድያ የሴቶች ቀን ክብረ በዓል ሲዘከር መንግስት ርዕዮትን አስሮ ስለ ቐሽ ገብሩ ሲተርክ የአራዳ ልጆች ሰሙ። ሰምተውም ጠየቁ “ሼም የለም እንዴ በአገሩ!?” አሉ ዝርዝር ያለው የስራ ሂደት ካለ መልስ ያምጣ…!
በጥቅሉ መንግስት እነ ርዕዮትን፣ እነ እስክንድርን፣ እነ ውብሸትን፣ እነ ሂሩትን፣ እነ አንዷለምን እነ ናትናኤልን፤ ስንቱን ጠርቼ እዘልቀዋለሁ? በጅምላው እምቢ ያሉትን ሁሉ እያሰረ እና እየገረፈ “ደርግ ታጋዮቼን አሰረ፣ ገረፈ፣ ገደለ” ብሎ ዋይ ዋይ ማለት ውሃ የማያነሳ ወቀሳ ነው። መፅሐፉም ይላል “የሌሎችን ጉድፍ ከማየትህ በፊት በአንተ አይን ውስጥ ያለውን ቆሻሻ ተመልከት…”
በመጨረሻም
ያወጋነውን ለፍሬ ይበልልን
አማን ያሰንብተን!  ከአቤ ቶክቻው ብሎግ የተወሰደ

Saturday, March 9, 2013

አለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ በኦስሎ ኖርዌይ ንግስት ሶኒያ በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት ተከብሮ ዋለ


በኦስሎfolketeateret በተባለው አዳራሽ በኖርዌጅያን የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 12.00 በዓሉ የተጀመረ ሲሆን በዓሉንም አስመልክቶ የኖርዌይ ንግስት የሆኑት ሶንያ ሃራልሰን የእንኳን አደረሳችሁ የደስታ መግለጫ በማስተላለፍ በአሉን የከፈቱ ሲሆን በመቀጠልም የተለያዩ የሴቶች ማህበራትን ወክለው የመጡ እንግዶች እንዲሁም ትውልደ ፓኪስታኒ የሆነችው  የባህል ሚንስትርዋ ሃዲያ ታጂክ ጨምሮ በየተራ ድርጅታቸውን በማስተዋወቅ ንግግር አድርገዋል። በየመሃሉም አስተማሪና አዝናኝ የሆኑ የሙዚቃና የዳንስ ዝግጅቶች ተካሂደዋል። በመጨረሻም የምሳ ግብዣ ተደርጎ የጠዋቱ ፕሮግራም በ14፡00 ሰዓት የተጠናቀቀ ሲሆን።

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሴቶች ክፍልም በበአሉ ላይ የተሳተፉ ሲሆን በአዳራሹ ውስጥ ለታደመው ታዳሚ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሴቶች የሰብአዊ መብት እረገጣና ጭቆናን የሚገልጹ የተለያዩ በራሪ ወረቀቶችን በመበተንና መፈክሮችን በመያዝ በሀገራችን ውስጥ ባለው የመንግስት ብልሹ አስተዳደር ምክንያት ሴቶች ለከፍተኛ ችግር እየተዳረጉ መሆኑንም አሳይተዋል።


በተጨማሪም ምሽት 18፡00 ላይ በነበረው የሰላማዊ ሰልፍ ላይ ቀደም ብሎ በመገኘት የሻማ ማብራት ስነስርዓት የተደረገ ሲሆን በስነስርዓቱም ላይ በድርጅቱ የሴቶች ክፍል ሊቀመንበር ወ/ዘሮ ገነት የእንኳን አደረሳችሁ የመክፈቻ ንግግር ካሰሙ በኋላ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ ዳዊት መኮንን አጭር ንግግር አድርገዋል።

በመቀጠልም በወ/ሪት ሔለን ንጉሴ በዓሉን አስመልክቶ አለም አቀፍ ይዘቱንና ጠቀሜታውን በመግለጽ እንዲሁም በአገራችን በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ከፍተኛ ችግር አንስተው ይህንን ችግር ለመፍታት በሀገራችን ውስጥ ያለውን ብልሹ አስተዳደር በማስወገድ ለዲሞክራሲና ለፍትህ እንዲሁም ለሴቶች እኩልነት ከሚታገሉ ድርጅቶች ጋር በመወገን መታገል እንዳለብን የገለፁ ሲሆን ወ/ሮ ሥርጉት ሰው መሳይ አራዊት የተሰኘ ሴቶች እህቶቻችን በአረብ ሀገር የሚደርስባቸውን ግፍ የሚገልጽ ግጥም አቅርብዋል።

 በአጠቃላይ ፕሮግራሙ በተሳካ ሁኔታ የተፈፀመ መሆኑን በመግለጽ በፕሮግራሙ ላይ ከጎናችን ተገኝተው ድጋፋቸውን ለሰጡን ወንድሞቻችን ሁሉ ምስጋና አቀርባለሁ።

 ድል ለኢትዩጵያ ሴቶች
 ብርሃን ለኢትዮጵያ
 መሰደድ ይብቃ
                                                                                  ሄለን ንጉሴ ከኖርዌይ
                                                                                     ማርች 8 2013