ወያኔ የኢኮኖሚ እድገቱ 11% አደገ እያለ በየጊዜው ዲስኩር ያሰማናል ሆኖም ግን ነገሩ ወዲህ ነው ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲ እንዲሉ በአዲስ አበባ 100,000 ሰዏች ከቆሻሻ ገንዳ ምግብ ይመገባሉ። ህፃናት እየራባቸው ትምህርት መከታተል እንደተሳናቸው ከህፃናቱ አንደበት አድምጠናል። የኢኮኖሚ ስሌቱ እንዴት እንደተሰላ እነርሱ ያውቃሉ እኔን ግን የገባኝ ሀገሪቷን እንደነቀዝ የሚመጠምጡ የወያኔ አሸርጋጆችና ሀገር ቆርሰው የሚሸጡ ባንዳ ሆዳሞች ሀብት ብቻ ተሰልቶ ኢኮኖሚው ማደጉ እየተነገረን ይገኛል።
ለማንኛውም ወያኔዎች ትንሽ በህኒናቸው ማሰብ ቢጀምሩ ጥሩ ይመስለኛል የእነርሱ ልጆች ጠግበው እና አማርጠው እየበሉ ደሃው የኢትዮጵያ ህዝብ እስከመቼ እየተራበና በገዛ ሀገሩ እንደባዳ እየተቆጠረ እንደሚኖር አነጋጋሪ ነው። በመሆኑም ስሜቱ እጅግ በጣም ከባድ ነው ይህንን ሰቆቃ በአፋጣኝ ለማቆም ሁላችንም በመተባበርና ያለንን አቅም ሁሉ በመጠቀም ህዝባችንን ነፃ ለማውጣት ትግሉን ወደፊት ማስኬድ አለብን እላለሁ። ቪድዮውን ይመልከቱ
No comments:
Post a Comment