
የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ብ/ጄነራል ክንፈ ዳኘው ላለፉት ሶስት ወራት ገደማ ከስልጣናቸው ታግደው ከቆዩ በኋላ በዚህ ሳምንት ወደ ሃላፊነት መመለሳቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ…. በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ታግደው ከቆዩት ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል አንዱ ጄ/ል ክንፈ እንደሚገኙበት የጠቆሙት ምንጮቹ ስልካቸውን በመጥለፍ በእንቅስቃሴያቸው ዙሪያ ክትትል ይደረግባቸው እንደነበር አስታውቀዋል። ጄ/ል ክንፈ በሳሞራ ታግደው የቆዩት የነአዜብ/በረከትን ቡድን በመቃወም ከነስብሃት ቡድን ጋር በመሰለፋቸው እንደሆነ ምንጮቹ አመልክተዋል። የጠ/ሚ/ር መለስን ሕልፈት ተከትሎ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት ስር እየሰደደ መሄዱንና የልዩነቱ መንስኤም በሕወሐት የተፈጠረው ቀውስ – ጄነራሎቹ ጎራ እንዲለዩ ጫና ማሳደሩን ያመለከቱት ምንጮች፣ አክለውም ልዩነቱ በአገር ጉዳይ ዙሪያ ሳይሆን አንዱ ሌላኛውን በማስወገድ የራስን ጥቅም አስጠብቆ በስልጣን ለመቆየት የሚደረግ የሙስና መጠላለፍ ነው ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ- ጄ/ል ሳሞራ የሚመሩት ስብሰባ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች ተሳታፊነት በዚህ ሳምንት ሲካሄድ መሰንበቱን ምንጮች ጠቆሙ። ውጥረትና ያለመረጋጋት በተስተዋለበት የሳሞራ ንግግር በዋና አጀንዳነት የቀረበው የግንቦት ሰባት ጉዳይ ሲሆን በዚህም ፥ « ግንቦት ሰባት በመንግስትና በሕገ-መንግስቱ ዙሪያ መጠነሰፊ አደጋ ጋርጦብናል፤ በግንቦት ሰባት የሚደገፉ በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ልንወስድ ይገባል፤» ማለታቸውን የገለፁት ምንጮቹ፣ ሳሞራ «ለምሳሌ.» ሲሉ ሰማያዊ ፓርቲን እንዲሁም « አንዳንድ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች» በማለት መፈረጃቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እያነሳ ያለውን ፍትሃዊ የመብት ጥያቄ፣ ሳሞራ ከግንቦት ሰባት ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
ከኢየሩሳሌም አርአያ
No comments:
Post a Comment