Monday, September 30, 2013

ግንቦት7 በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ መስመሩን እየዘረጋ መሆኑን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ


መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው ይህንን የተናገሩት በኖርዌይ ከተካሄደው ደማቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሁዋላ ነው

የግንቦት7 ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው  የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ በአንድ በኩል በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል አባላት ላይ ከፍተኛ መነቃቃት የሚፈጥር በሌላ በኩል ደግሞ የተጣለብን ህዝባዊ አደራ ከፍተኛ መሆኑን የሚያስታውሰን ነው ብለዋል።
በቅርቡ ከኢትዮጵያ አየር ሀይል ከድተው የሄዱት ሰዎች በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ የገለጹት አቶ አንዳርጋቸው ፣ በመከላከያ ሰራዊት በእግረና፣ በአየር ሃይልና በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ሊደርሱበት በማይችሉበት መንገድ መስመር እየዘረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
በውጭ አገራት ተመሳሳይ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ለማድረግ እቅድ አላችሁ ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ አንዳርጋቸው፣ ህዝባዊ ሀይሉ ከተግባር ጋር በተዛመደ መልኩ የገቢ መሰባሰብ ዝግጅት መርሀ ግብሩን ይፋ እስከሚያደርግ ድረስ በህዝባዊ ሀይሉ ወይም በግለሰቦች ስም ምንም አይነት የገቢ መሰባሰቢያ ዝግጅት መደረግ እንደሌለበት ገልጸዋል
በሌላ ዜና ደግሞ በርካታ ቁጥር ያላቸው በስቶክሆልም እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ውይይት አድርገዋል።  አቶ አንዳርጋቸው የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይልን ዓላማዎች፡ተልዕኮዎች እና ራዕይ በማስተዋወቅ ህዝባዊ ሃይሉ ከምስረታ ጀምሮ አሁን ያለበትን ደረጃ  በምስልና በጽሁፍ የተደገፈ ገለጻ ለተሰብሳቢው አቅርበዋል።
እሳቸው እና ሌሎች የአመራር አካላት እንዲሁም አባላት የተገኙበት የውትድርና ስልጠና አንዱ የበታች አንዱ የበላይ እንዳልሆነ በማስገንዘብ ይህ ህዝባዊ ሃይል  ቤተሰባቸውን፡ስራቸውን፡ ገንዘባቸውን፡ እና የተደላደለ ኑሯቸውን በመተው ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን የተዋቀረ እንደሆነ ገልጸዋል።
የግንቦት ሰባት ዓላማ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ማስፈን ብቻ ሳይሆን ባለፉት 22 ዓመታት ኢትዮጵያውያን የተገፈፉትን ክብራቸውን ማስመለስ ጭምር መሆኑን አቶ አንዳርጋቸው አስምረውበታል ሲል ቴዎድሮስ አረጋ ከስዊድን ዘግቧል።

Sunday, September 29, 2013

በአንድነት ፓርቲ መሰከረም 19 የተጠራው ሰልፍ አጀማመር ፎቶና መፈክሮች በከፊሉ


September 29, 2013

አንድነት ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በጥሩ ሁኔታ የተጀመረ ሲሆን ከጅምሩ የአዲስ አበባ አሰተዳደር ፕሊስ እጅ ለ እጅ በመያያዝ ሕዝቡን እንዳይንቀሳቀስ እየሞከረ ቢሆንም ሕዝቡ ግን ወደፊት ለመሄድ ዝግጁ እንደሆነና ወደፊት የመገሰገሱ ሰሜቱ እየጨመረ ነው::ዶ/ር ነጋሶና የ33 አመራሮች ወደፊት በመሄድ ሕዝቡን ለመምራት እየሞከሩ ይገኛሉ ::በዚህ አጋጣሚ ሕዝቡ በፕሊሶችና በአድማ በታኝ ወደፊት እንዳይሄድ እየተሞከረ ነው !!
ሙሰና የስራቱ መገለጫ ነው!!
ፍትህ ናፈቃን !!!
ፍትህ እያሉ ቃሊቲ ገቡ !!
መብትን መጣየቅ አሽባሪነት አይደለም !!!
ወኔ የሌለው ያገር ሽክም ነው !!
ርዮት አለሙ !! እሰክንድር ነጋ !!አንዷለም አራጌ!! እነ አቡበከር አሽባሪ አይደሉም !!
አምባገነኖች ያሉበት የሁሉም ቤት እሰር ቤት ነው !!
ሕገመንግስታዊ መብት መጠየቅ አሽባሪነት አይደለም !!
በመሳሪያ ሕዝብ ማንበርከክ አይቻልም !!
አንበረከክም !!
Andenat party
Andenat party
Andenat Party
Andenat Party
Andenat party
Andenat Party
Andenat party
Andenat Party
Andenat party
Andent Party

Addis Ababa rocked by protest rally Sunday, September 29, 2013



The protest rally organized by the Unity for Democracy and Justice Party and Medrek has drawn hundreds of thousands of people. But the government has blocked the protesters from marching to Meskel Square and other venues requested by the organizers. The protesters have condemned political oppression and human rights violations. They demanded for the unconditional release of jailed journalists and activists.

Saturday, September 28, 2013

ታላቅ ሰበር ዜና፤ በኖርዌ ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ በስኬት ተከናወነ!!!!!!!!!!

ዛሬ ሴፕቴምበር 28, 2013 በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልን ለመርዳት በኖርዌ ኦስሎ ከተማ የተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የህዝባዊ ሃይሉ ከፍተኛ አመራር ኮማንደር አሰፋ እና የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲሁም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳዊት መኮንንና ጥሪ የተደረገላቸ እንግዶችና ከተለያየ የአውሮፓና ስካንዴኔቪያን ሃገሮች መጡና በጣም በርካታ የሆኑ በኖርዌ በሚኖሩ ከተለያየ ከተማ የመጡ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በታላቅ ወኔና የሃገር ፍቅር ስሜት በስኬት ተከናወኖ አመሸ።

በዝግጅቱ ላይ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይሉ አመራር ስለድርጅታቸው በሰፊው ህዝቡን ያስደሰተ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከታዳሚው የቀረባላቸውንም ጥያቄዎች በስፋት በማብራራት ለታዳሚው ከፍተኛ ግንዛቤ አስጨብጠዋል። በተመሳሳይ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በምስል የተደገፈ ከፍተኛ ማብራሪያ ሰጥተው ከህዝብ የቀረበላቸውን ጥያቄዎች ሰፋ አድርገው አስረድተዋል።

በአንፃሩ እጃችን እረጅም ነው ብለው የሚያስቡ ጠባብ አስተሳሰብ ያላቸው የወያኔ ተላላኪ ቡድኖች ዲሞክራሲ ባለበት በኖርዌ ምድር መጥተ እንኳን የማይቀየሩ አምባገነኖች እዚህም ዝግጅታችን እንዳይሳካ ለማበላሸት እንቅልፍ ሳይተኙ የሃሰት ፕሮፓጋንዳቸውን እየነፉ ህዝብ ለማደናገር የአሸባሪ ድርጅት ለመርዳት የገቢ ማሰባሰቢያ ሊያደርጉ ነበር ነገር ግን ፕሮግራሙ ተሰረዘ በማለት ዜና ቢያሰራጩም እኛ ግን እየረዳን ያለነው የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል በየትኛውም አለም  በአሸባሪነት መዝገብ ውስጥ ያልተመዘገበ ድርጅት መሆኑን የኖርዌ ፕሮፌሰር በሃገሪቱ ውስጥ ለሚታተም አንድ  ጋዜጣ አስተያየታቸውን የገለፁ ሲሆን በእለቱም ዝገጅቱ በደማቅ ሁኔታ ተከናውኖ ከዚህ ቀደም በየተኛውም የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮገራም ያልታየ ከፍተኛ የገንዘብ ገቢም ተደርጓል።

በአጠቃላይ በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ጨረታዎች፤ ቀስቃሽ ሙዚቃ፤ ባህላዊ ምግብና መጠጥ እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶች ለሽያጭ ቀርበው የነበረ ሲሆን በተጨማሪም የትጥቅ ትግል ለምን አስፈለገ በሚል አጭር ገላጭ ድራማ ቀርቦ ህዝቡን በጣም አስደስቷል። በዝግጅቱ መክፈቻና መዝጊያ ላይም የህዝባዊ ሃይሉ መዝሙር ላንቺ ነው ሃገሬ ላንቺ ነው የሚለው በህዝቡ ተዘምሮ ዝገጅቱም እኩለ  ለሊት በድምቅት ተጠናቋል፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ሞት ለወያኔ
ሄለን ንጉሴ/ኖርዌ






Thursday, September 26, 2013

ከለውጡ በኋላስ? (ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ )


September 24, 2013

ኢህአዴግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ (በውስጥም በውጪም ተግዳሮቶች) መገፋቱን በሚያመላክቱ የፖለቲካ አጀንዳዎች ላይ የሚያጠነጥን አንድ ፅሁፍ (‹የአብዮቱ የምፅዓት ቀን ምልክቶች›› በሚል ርዕስ) አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል፤ ይዘቱም በመጪዎቹ ወራት ወይም ዓመት ስርዓቱ ‹ምርጫ› አሊያም ‹ህዝባዊ› እምቢተኝነት ከሚያመጣው ‹ማዕበል› (እንደበረከት ስምዖን አገላለፅ ‹ናዳን በሚገታ ሩጫ›) የማምለጥ ዕድሉ የጠበበ መሆኑን የሚያመላክት ነው፤ ይሁንና አንድ አብዮት ታላቅ (ውጤታማ) ሊባል የሚችለው አምባገነን ስርዓትን በመቀየሩ ብቻ ስላልሆነ (ሥር-ነቀል ለውጥ የሚፈጥር አብዮት ዋጋ የሚኖረው የዲሞክራሲ ተቋማትን መሰረት መጣል ሲችል ነውና) በቀጣይ መፃኢ ዕድሉ ላይ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

Journalist Temasegan Dasaleg
በዚህ ፅሁፍህ ተጠየቅም ‹ከስርዓቱ ለውጥ በኋላ፣ ማን ነው አማራጩ?› የሚለው ጥያቄ ትኩረት ይደረግበት ዘንድ አመላክታለሁ፡፡
ምክንያቱም በጠለፉ መንገድ ከቀሩ አብዮቶች ታሪክ ተምረን፣ ‹መጥነን ካልደቆስን› የሚከፈለውን ዋጋ በብላሽ የሚያስቀር አሳዛኝ ሁናቴ ሊፈጠር ይችላልና (ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን ‹‹አብዮት፣ ለአብዮት ብቻ ሲባል መካሄድ የለበትም›› እንዲል፣ ከኢህአዴግ መገላገሉ መልካም ቢሆንም፣ የአገላጋዩን ማቀፊያ ከወዲሁ መምረጡ ወይም የምንጠይቀውን ማወቁ ብልህነት ነው)

አማራጩ ተወልዷልን?
ከኢህአዴግ በኋላ የሚተካው አማራጭ ተዘጋጅቷል? …ይህንን ቀዳዳ አስቀድሞ መድፈኑን አስቸኳይ ያደረገው፣ ለውጡ የሚመጣበት መንገድ ‹ከህዝባዊ እምቢተኝነት› ይሆናል የሚለው ቅደመ-ግምት ነው፡፡ ከታዓማኒና በዕኩል አሳታፊ ምርጫ የሚነሳ ሽግግር (‹ሕዝብ የሚፈልገውን ያውቃልና ውሳኔው መከበር አለበት› ከሚለው የዲሞክራሲ ፅንሰ-ሃሳብ በመነሳት) አሳሳቢነቱ ከአደባባይ ተቃውሞ የሚመነጨውን ያህል አይደለም፤ ስለዚህም ከስጋት ነፃ መሆን የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መሰረታቸውን ሀገር ቤት አድርገው በህግ የተመዘገቡ የፖለቲካ ድርጅቶች የቤት ስራቸውን ሰርተው ዝግጁ ሆነው ሲጠብቁ ብቻ ነው፡፡ ይህ ግን የድርጅቶቹን ቁጥር ከሰማኒያ በላይ ከማሻቀብ ያለፈ አስተዋፅኦ የሌላቸውን አሰስ-ገሰስ ‹ፓርቲ›ዎች በሙሉ እንደሚመለከት ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡

ነፍስ ይማርና በ‹‹ልዕልና ጋዜጣ›› እልፍ አእላፍ ችግሮቹን ማረም ከቻለ መድረክ ተስፋ ሊጣልበት ይችላል ብዬ እንደማስብ መፃፌን አስታውሳለሁ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመድረክ አሰላለፍ ሊቀየር በማጋደሉ (ከአንድነት ጋ አብሮ መቀጠሉ ማጠራጠሩ) እና ሰማያዊ ፓርቲ አዎንታዊ እንቅስቃሴ ከማድረጉ አኳያ ተፎካካሪ ሊሆን የሚችልበት ዕድል በመፍጠሩ፣ በአጀንዳው ላይ ማካትቱን ተገቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ይሁንና ሌሎች ፓርቲዎችን እዚህ ጋ ያላነሳሁበት፣ ከላይ ከጠቀስኩት በተጨማሪ ሶስት ምክንያቶች አሉኝ፤ ቅቡልነትን ማጣት፣ እንቅስቃሴ አልባ መሆን እና በገዥው ፓርቲ ስፖንሰርነት መተንፈስ የሚሉ፡፡

መድረክ
የስድስት ፓርቲዎች ስብስብ ነው፤ በምርጫ ሁለት ሺህ ሁለት (ምንም እንኳ ከአንድ የምክር ቤት ወንበር በላይ ባይሳካለትም) ከሁሉም
ተቀናቃኞች በላይ ጐልቶ መውጣት ችሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የአምስተኛውን ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫም ተስፋ አድርጎ ለመጠበቁ

ማሳያዎቹ፡- አንድም ስብስቡ ዛሬም ህላዊ መሆኑ፣ ሁለትም ለበርካታ አባላቱና ደጋፊዎቹ ወደ ‹ግንባር ተሻጋገሩ› ግፊት ምላሽ መስጠት
መቻሉ ነው፡፡

በምስረታው ዋዜማና ማግስት ብዙ የተነገረለት መድረክ እርስ በእርሱ (በአንድ ጠርዝ-የአንድነት አመራሮች፤ በሌላኛው-ኦፌኮ እና ኢሶዴፓ) የፈጠረው ውዝግብ በዙሪያው ለተሰለፉ አባላትና ደጋፊዎች ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡ ለግንባሩ ቅርብ የሆነ ወዳጄ የችግሩን መጦዝ የገለፀው ‹‹ሁለቱ ጎራዎች በስብሰባ ወቅት ‹በውሃ ቀጠነ› ለፀብ ሲገባበዙ የሚያይ እና ለስድብ የሚጠቀሙባቸውን ቃላት የሚሰማ በአንድ ግንባር የተሰለፉ ናቸው ብሎ ከሚያምን ‹ግመል በመርፌ ቀዳዳ መሽሎኩን› ቢቀበል ይቀለዋል›› በሚል ምፀት ነው፡፡ አደጋውን የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ኩነቶቹ ከመለዘብ ይልቅ መባባሳቸው ይመስለኛል፡፡

በመሬት ያለው እውነታ ይህ ቢሆንም፣ ፓርቲው በ2005 ዓ.ም ወርሃ መጋቢት ወደ ‹ግንባር› መሻገሩን ከማብሰሩም በላይ፣
‹‹የኢትዮጵያን ወቅታዊና መሰረታዊ ችግሮች የመፍቻ አጋጣሚዎች›› በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገው ባለአራት ገፅ ‹ማኔፌስቶ›፣ የሀገሪቱን ችግር በሙሉ በአራት ክፍል ቀንብቦ ካስቀመጠ በኋላ፣ ጉዳዩን ፈረንጅኛው ‹የሲኒ ማዕበል› እንደሚለው አድርጎ በማለፍ የ‹ደግፉኝ› ጥሪውን እንዲህ ሲል አስተላልፏል፡-‹‹ይህንን ፀረ-ህዝብና ፀረ-ሀገር የሆነውን ኢህአዴጋዊ ስርዓት በሰላማዊ አግባብ በምታደርገው ብርቱ ትግልህ መለወጥ እንደምትችል ካለፈው የትግል ተሞክሮህ ሆነ የአለም ህዝቦች ለነፃነት፣ ለዕኩልነትና ለፍትህ ብሎም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን መሆን ከሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎችና ከሚያስመዘግቧቸውም ድሎች ትገነዘባለህ፡፡ ስለሆነም መድረክ ይህንን ክቡር ትግልህን በመምራት ባለቤትነት እንድትበቃ በፅናትህ ከጎንህ ሆኖ ለመታገለ መወሰኑን ተገንዝበህ ከምንጊዜም በላይ ሁለንተናዊ ድጋፍህን እንድትሰጥ ጥሪያችንን በከፍተኛ አክብሮትና በአንተም ላይ ባለን ሙሉ እምነት እናስተላልፋለን፡፡››በግሌ መድረክ ራሱ በሁለት ምክንያቶች እምነት ሊጣልበት የሚችል አልመስለኝም፡፡

የመጀመሪያው ከአንድነት ጋር የገባበት ድምፅ የለሽ ውዝግብ ከዕለት ወደ እለት እያደገ መሄዱ ነው፤ አዲሱ የዶክተር መረራ ጉዲና መጽሐፍም ቅራኔውን ቢያሳፋው አይገርምም፤ ዶ/ሩ ስለ2002ቱ ምርጫ ባወሳበት ምዕራፍ ‹‹የ1997ቱ የቅንጅት ወራሽ ነው ብለን የተማመንበት አንድነት እውነተኛ ወራሽ ለመሆን በጣም ብዙ እንደሚቀረው ተረዳው›› ያለበት ግምገማ እና ‹‹ያልገባኝና የሚከነክነኝ አንድነት ኦሮሚያ ላይ በብዛት ያወዳደራቸው ኦህዴድ ያሰማራቸው ወሮበሎች ነበሩ›› ፍረጃው ‹ትችት›ን በቅንነት ለመቀበል ልምድ ከሌለው የሀገሪቱ ፖለቲካ አንጻር አቧራ ማስነሳቱ አይቀሬ ለመሆኑ መገመቱ አይከብድም፡፡ ይህ እንግዲህ አንድነትን የአማራ (የከተማ ልሂቃን) ተወካይ የሚያደረገውን ወቀሳ ሳይጨመር ነው (እዚህ ጋ የሚነሳው አስቂኙ ጉዳይ ወቀሳውን የሚሰነዝሩት አባል ፓርቲዎች አንድነት የብሔር ድርጅት ቢሆን ይበልጥ ተጠቃሚ ከመሆናቸው በተጨማሪ ለአብዛኛው ችግሮቻቸው በቀላሉ መፍትሄ የመስጠቱ ጉዳይ ሲታሰብ ነው) ሁለተኛው መድረኩ ከለውጡ በኋላ ሀገር ለመምራት የሚያስችል የጠራ የፖለቲካ አመለካከት አለመከተሉ ነው፤ በውስጡ ያሉ ፓርቲዎች ቢያንስ ሁለት የተለያዩ ፕሮግራም የሚያራምዱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
የአንድነትን እና የኦፌኮን ፕሮግራም ብንወስድ
የችግሩን ግዝፈት ያሳየናል፤ አንድነት መልካ ምድር ላይ ስለተመሰረተ ፌደራሊዝም አስተዳደር ጠቀሜታ ሲያብራራ፤ የኦፌኮ ባለስድስት ገፅ ፕሮግራም ደግሞ በማንነት ላይ ስለተመሰረተ ፌደራሊዝም ይሰብካል፡፡ በግልባጩ ውድሀት ይፈፅሙ እንዳይባል ደግሞ የእነ ዶ/ር መረራ ‹ከተዋህድን ኦሮሞ ተውጦ ይጠፋል› ስጋት ጋሬጣ ነው፡፡ አንዳንድ የአመራር አባላቱ ‹‹ዓላማችን ቅድሚያ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን መገንባት ነው›› የሚል መከራከሪያ ሲያቀርቡ ቢደመጡም፣ ከዚህ በኩል ከሚነሳው ተግዳሮት በቀላሉ የሚመለጥ አይመስለኝም (በነገራችን ላይ መድረኩ በወቅታዊው ቁመና ‹ግንባር› ለመመስረት የሚያስችለውን መስፈርት ሟሟላቱ ራሱ አጠራጣሪ ነው)

አንድነት
የአንድነት ተግዳሮት ወደ መድረክ ከመግባት ጋ ተያይዞ የመጣ ነው (ከጠዋቱ ሰማያዊ ፓርቲን የመሰረቱት ወጣቶች ከድርጅቱ ለመውጣት አንዱ ምክንያታቸው ይህ እንደሆነ ይታወሳል)፤ ትብብሩን ‹ያልተባረከ ጋብቻ› የሚያስብለው ደግሞ የዛሬ አራት ዓመት ‹ወደ መድረክ ካልገባን ትግሉን እናደናቅፋለን› ሲሉ የነበሩ አንዳንድ የአንድነት አመራሮች የውዝግቡ ተሳፊ መሆናቸውን ስንመለከት ነው፤ መተነኳኮሱ በ2002ቱ ምርጫ ማግስት የተጀመረ ቢሆንም፣ ባለፈው ዓመት ወደ መጦዝ ተሸጋግሯል፡፡ በተለይም አንድነት ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ንቅናቄ›› በሚል መርህ ያካሄደው የሶስት ወር ዘመቻ መድረክን አለማካተቱ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልፅ ነው፡፡ በ‹‹ፀረ-ሽብር›› አዋጁ ላይ (ኢህአዴግንና ኢዴፓን ጨምሮ) በተደረገው ክርክርም አንድነት እና መድረክ በተለያዩ ሰዎች ተወክለው መቅረባቸው ግንኙነቱን እንደ ቀድሞ ለማየት አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡

ይህም ሆኖ አንድነት በራሱ የተሻለ ፓርቲ ሆኖ ሊወጣ የሚችልበት ዕድል አለው፡፡ ምሁራዊ ስብስቡም ሆነ የኢኮኖሚ አቅሙ (የዲያስፖራ ድጋፉ) አንፃራዊ ጥንካሬ እንዲያገኝ ረድቶታል፤ ርዕዮተ-ዓለሙንም ከተቀናቃኝ ፓርቲዎች በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀቱ ለቅቡልነቱ አስተዋፅኦ ሊያደርግለት ይችላል፤ ከመኢአድ ጋር የጀመረውን ውህደት (‹የአማራ ተወካይ› የሚለውን ፍረጃ ቢያጠናክረውም) ከዳር ካደረሰ ደግሞ ከአቻዎቹ ጋ ያለው ልዩነት በእጅጉ መስፋቱ አይቀሬ ነው (መኢአድ የፈራረሰው ከአናት ነውና ግዙፍ መዋቅሩ ‹እረኛ አልባ› በመሆኑ፣ አንድነት በውህደት ስም ቢሰበስበው በከፍተኛ ደረጃ ይጠቅመዋል)

የወል-መንገድ
በቀጣይ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ለመገኘት መድረክና አንድነት መቻቻላቸው ወሳኝ ነው፡፡ ይሁንና ኩነቱን በታዛቢነት መመልከት የመረጡት የአረና ሰዎቸ በግንባሩ ቢሮ ሰላም ለማውረድ የአስታራቂነት ሚና ቢጫወቱ ጠቃሚነቱ ለእነርሱም ነው፡፡ አንድነቶችም፣ በመድረክ ስም እዚህ ድረስ ለመጓዝ የከፈሉት ዋጋ ብላሽ ከሆነ ማንንም አያተርፍም፡፡ በአናቱም ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አስገዳጅ መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ ምክንያቱም አንድነት የሰበሰባቸው ልሂቃኖችም ሆኑ በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ያነበረው መዋቅር (ጥንካሬው ላይ ያለኝ ጥርጣሬ እንደተጠበቀ ሆኖ) ቅድሚያ ለብሔር ፖለቲካ ከሚሰጡ አካባቢዎች በ‹መድረክ ባርኔጣ› በሚገኝ ድጋፍ (ድምፅ) ካልታገዘ በቀር አየር ላይ ተንጠልጥሎ ከመቅረት አይታደገውም፡፡

የመድረክ ተግዳሮትም ተመሳሳይ ነው፤ በፖለቲካው ላይ ውጤት የሚያዛባ ተፅዕኖ ማሳረፍ የሚቻላቸውንና አንድነት የራሱ ያደረጋቸውን ከተሜዎች ‹ቡራኬ› ሳይቀበል ወደ ውድድር መግባቱ ‹ውሃ በወንፊት…› አይነት ሊሆንበት ይችላል፡፡ የመድረክንና የአንድነትን የወል ቀዳዳ መዘርዘሩን እዚሁ ገትቼ፣ የተሻለ ጥንካሬና የመግባባት መንፈስ ለማስረፅ በቅድሚያ የችግሮቻቸውን መንስኤ ለይተው ማወቅ አለባቸው ብዬ ስለማስብ፣ በግሌ ‹ያለመግባባቱ መነሻ› ከምላቸው ዋና ጉዳዮች ሶስቱን በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡፡

፩- የፕሮግራም መጋጨት ያመጣው ጣጣ አንዱ ነው፤ ይኸውም የፀቡ የቡድን አባቶች የ‹ሕብረ ብሔር› እና የ‹ክልል› ፖለቲካ አቀንቃኝነት፣ ሁሉም አባል ፓርቲዎች መድረኩን ሲፈጥሩ የየራሳቸውን ፕሮግራም እንደያዙ መሆኑ፣ ጥቂት የማይባሉ ልዩነታቸውን ሳይፈቱ ‹በይደር› ማስቀመጣቸው… እንደ ማሳያ ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ ሁኔታም የእርስ በእርስ መተማማን እንዳይኖራቸው ያደረገ ይመስለኛል(ከዚህ አኳያም ለመፍትሄው ቅድሚያ ከልሰጡ በመድረክ በኩል ‹መጪው ጊዜ ብሩህ ይሆናል› ብሎ መጠበቅ ‹የዋህ› ሊያስብል ይችላል) የጫናው ተፅእኖ ደግሞ በሁለቱም በኩል (በአንድነትና በብሄር ድርጅቶቹ) ከሚከተሉት የፖለቲካ አመለካከት አንፃር ወደ ስልጣን የመምጣቱ አጋጣሚ ቢፈጠር፣ የታገሉለትን ስርዓት ማንበሩ ፍፁም አዳጋች መሆኑን በማስታወስ ነው፤ አንድነቶች ፓርቲያቸው ከመድረክ እንዲወጣ ይጎተጉታሉ፤ ብሔር ተኮሮቹ ደግሞ ‹አንድነት የነፍጠኛውን ስርዓት የሚመለስ በመሆኑ፣ ወይ ወደ ብሄር ድርጅት ራሱን ይቀየር፣ አሊያም ፕሮግራሙን ይከልስ› የሚለው ሙግታቸው በአሳማኝ ሁኔታ መፍትሄ አለማግኘቱ ራሱን የቻለ ሌላ ትግል ከሚፈልግ አጀንዳ ጋ አላትሟቸዋል፡፡
፪-አንድነት በሚያራምደው የሊብራል ዲሞክራሲ እና አብዛኛው የመድረክ አባል ድርጅቶች በሚከተሉት የሶሻል ዲሞክራሲ መካከል ያለውን ልዩነት የማሰታረቅ ስራ አለመሰራቱ ነው፡፡ ‹‹የአንድነት ፓርቲ ስትራቴጂና የአምስት ዓመት ዕቅድ›› በሚል ርዕስ 246 ገፅ ይዞ በታተመው መፅሀፍ ላይ ‹‹አንድነት የሚመሰረትበት ርዕዮተ-ዓለም ሊበራሊዝም ሆኖ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች የሶሻል ዲሞክራሲን ጠቃሚ ገፅታዎች ይወስዳል›› የሚለው አንቀፅ ቢጤን ለመልካም ግንኙነት መደላድል መሆን ይችላል (በነገራችን ላይ‹እንዲህ የችግር ቋት ተሸክመው ስለምን በጋራ ለመስራት ተስማሙ?› የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርምና ግምቴን ላስቀምጥ፤ የብሔር ድርጅቶቹን እስትንፋስ የሚቆጣጠሩት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ እና ዶ/ር መረራ ጉዲና ምርጫ 97ን ከሁለት አቅጣጫ ገምግመው ከደረሱበት ድምዳሜ ጋ የሚያያዝ ይመስለኛል፤ ይኸውም ‹አንድነት፣ የቅንጅት ወራሽ ነው› የሚለው የተሳሳተው ትንተና አንዱ ሲሆን፣ ሁለተኛው በዛው ምርጫ ተቀማጭነታቸው አውሮፓና አሜሪካ ከሆኑ አስራ ሁለት ፓርቲዎች ጋር መስርተውት የነበረው ‹‹ህብረት››፣ ፓርላማ በመግባታቸው፣ ከውግዘት ጋር እንዲባረሩ በማድረጉ ያሳደረባቸው መገለል ሊሆን ይችላል፤ በአንድነት በኩል ደግሞ ‹የመድረኩ መሀንዲስ› ተደርገው የተወሰዱት ዶ/ር ነጋሶና አቶ ስዬ አብርሃ አንድነትን ለመቀላቀል ወደ መድረክ መግባትን እንደ መደራደሪያ በማቅረባቸው ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ዛሬም ያልተሸነፈው የ‹ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ› ግልብ ግፊት ነው ብዬ አስባለሁ፤ የዚህ ድምር ውጤትም ከነርዕዮተ-ዓለም እና የፕሮግራም ልዩነት ወደ መድረኩ አምጥቷቸው አይን የሚገባ ሥራ እንዳይሰሩ አግዷቸዋል)
፫-የመድረክ አባል ድርጅቶች መተዳደሪያ ደንብን አለማክበር ‹የፖለቲካ ብልጠት› በማድረጋቸው፣ ለራሳቸው ተጨማሪ የመናተረኪያአጀንዳ ፈጥረዋል፡፡ ይህ አይነቱ ስርዓት አልበኝነት በጋራም በተናጥልም ተፈፅሟል፡፡ አንድነትን ጨምሮ የመድረኩ ስራ አስፈፃሚ ደጋግሞከመርሁ ሲያፈነግጥ ታይቷል፤ ለምሳሌ በደንቡ ላይ መሻሻል ያለበትን አንቀፅ የሚወስነውም ሆነ ከፍተኛው ስልጣን የጠቅላላ ጉባዔውመሆኑ በግልፅ ተቀምጦ ሳለ፣ ጉባዔው ከተሰበሰበባቸው በአንዱ ዕለት ‹የመድረኩ ሊቀ-መንበረ በዙር ከሚሆን፣ በብቃት ይሁን›፤እንዲሁም ‹አዲስ ፓርቲ በአባልነት የምንቀበልበት መንገድ መሻሻል አለበት› የሚሉ አቋሞች ላይ ቢደርስም፣ ስራ አስፈፃሚው ቃል በቃል‹ይህንን አሰራር ጉባኤው ሊቀይረው አይችልም› ሲል ውድቅ ያደረገበትን አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡
በተናጥል አንድነት፣ ኦፌኮ እና ኢሶዴፓ በአንቀፅ 21 ‹የአባል ድርጅቶች ግዴታ› በሚል ርዕስ ስር የተቀመጡትን፡- ‹ከአፍራሽና ተቃራኒ ከሆኑ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ›፣ ‹በአባላት መካከል አለመተማመን ከሚፈጥሩ ማናቸውም ተግባር መቆጠብ›፣ ‹የግንባሩን አቋም የሚፃረር አቋም ያለማራመድ› እና መሰል ደንቦችን ደጋግመው በአደባባይ ሲጥሱ ታይተዋል፤ ይህ አይነቱ ስርዓተ-አልበኝነት መፍትሄ ሳያገኝ የተሻለና ጠንካራ ሆኖ መውጣቱ አዳጋች ይመስለኛል፡፡

ሰማያዊ
ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ በመሆኑ ለወቀሳ መቸኮሉ አግባብ እንዳልሆነ ቢሰማኝም፣ ፓርቲው እያሳየ ካለው ፈጣን እንቅስቃሴ አኳያ፣ በፍጥነቶቹ መካከል የሚፈጥራቸውን ድክመቶቹን ቢያሻሽል ጠቀሜታው ለሀገር ስለሆነ የግል አስታየየት መስጠቱን አስፈላጊ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የሰማያዊ ዋናው ድክመት ከ‹ግንፍሌ ፓርቲ›ነት አልፎ የመሄድ ፍላጎት ያለው አለመምሰሉ ነው (ጽ/ቤቱ አራት ኪሎ /ግንፍሌ/ አካባቢ ይገኛል)፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ለመንቀሳቀስ ሲሞክር አይታይም፤ በሌሎቸ የሀገሪቱ ከተሞች የተከፈተ ተጨማሪ ቢሮ ካለ፣ ከምስረታው በኋላ የአባላቱ ቁጥር ምን ያህል እንደደረሰ፣ እና መሰል መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ሄዶ የነበረው የመፅሄቱ ሪፖርተር ‹እንዴት እንደምትጠቀሙበት ስለማናውቅ አንናገርም› በሚል ክልከላ በመመለሱ ስለወቅታዊው ቁመና እዚህ ጋ መጥቀስ አልተቻለም (ከዚህ ውጪ ሊቀ-መንበሩ ይልቃል ጌትነት ከ‹ሰንደቅ› ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ-መጠይቅ ‹‹ባለፉት 40 ዓመታት ከመጣው የፓርቲዎች ጥንካሬ ይልቅ፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲ ብቻውን አምጥጦታል›› ያለው ሀረግ ስህተት ቢሆንም፣ አንድም በሂደት የሚታረም፣ሁለትም የአፍ ወለምታ፣ ሶስትም ከልምድ ማነስ የሚያጋጥም በመሆኑ ‹ፀጉር መንጨቱ› ፓርቲው ፍርሃትን ለመስበር ከሚያደርገው እንቅስቃሴ አኳያ ገንቢ አይደለምና አልፈዋለሁ፡፡)

‹እምነት ጨምሩልን›
‹ለውጥ! ለውጥ!› የሚል ድምፅ በመላ ሀገሪቱ የበረከተው የ‹ቡርዣ› ወይም ‹አድሀሪ› አብዮትን በመናፈቅ አይደለም፤ እንዲህ አይነት አብዮት፣ ከሰው ለውጥ በቀር ሕዝባዊ ጠቀሜታ የለውማና፡፡ የደርግም ሆነ የኢህአዴግ ‹አብዮት› የዚህ አምሳያ በመሆኑ ነው፣ ዛሬም ዘመን ተጋሪዎቼ ‹ፋኖ ተሰማራ!› ከማለት ነፃ ያልወጡት፡፡ ‹ሶስተኛው አብዮት› የማይሸነፍ እና የማይንበረከክ እንዲሆንልን ከምንመኘው በላይ ወደ ‹መፈንቅለ-መንግስት›ነት እንዳይቀየር መጠንቀቁንም ግዴታ ያደረገው ጠንካራ ፓርቲና የነቃ ማህበረሰብ ያለመኖሩ ስጋት ነው፡ ይህ ደግሞ ከወዲሁ ከአማራጩ ኃይል ጎን መቆም ይቻል ዘንድ ‹እምነት ጨምሩልን!› (ሀገር የመረከብ አቅማቸውን አሳዩን?) እንድንል አስገድዷል (‹ጀግናው› ኢህአዴግ ወደ ማይቀረው ሽንፈት መንገዱን ከጀመረ ጥቂት ክረምቶች በማለፋቸው፣ ከለውጡ በኋላ የሚመጣው ኃይል ሁለንታው የተቃና መሆኑን ማስመስከር አለበት)መድረክ፣ አንድነት እና ሰማያዊ ወደራሳቸው ይመለከቱ ዘንድ ከሞላ ጎደል የወል ‹ክፍተቶች› ወይም ‹ድክመቶች› የምላቸውን ሶስት ጉዳዮች ከዚህ ቀጥሎ እጠቅሳለሁ፡፡

ሃሳብ-አልባ
ፓርቲዎቹ በምስረታቸው ዘመን ቅድሚያ የሚሰጡት ለምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፍኬት እና ‹ተቃዋሚ ድርጅት› ተብለው ለመጠራት በመሆኑ አንድም የሀገሪቱን አንኳር ችግሮች አጥንተው መፍትሄ በመያዝ አልተዘጋጁም፤ ሁለትም ከነባር ድርጅቶች ድክመትና ጥንካሬ ተምረው አልመጡም፤ በዚህም የሚፈልጉትን ሳያወቁ እና የተለየ አማራጭ ሳይይዙ ወደ ፖለቲካው ገብተዋል ወደሚል ጠርዝ እየገፋን ነው፤ ጠንካራና የተፍታታ የፖለቲካ ፕሮግራም የላቸውም፤ በንፅፅር ‹‹አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ›› የተሻለ ፕሮግራም ለመቅረፅ ከመሞከሩ ውጪ፣ የመንግስቱ ስልጣን ‹ገጭ-ቋ› ቢል ‹አማራጭ ሊሆኑ ይችላሉ› የሚባሉት ፓርቲዎች ‹እያሾፉ ነው› በሚል ችላ ካልተባሉ በቀር ‹ፕሮግራሜ› ብለው ያቀረቡትን ለተመለከተ ምን ያህል ሃሳብ አልባ እንደሆኑ ለመረዳት አይቸገርም፡፡

የሆነው ሆኖ ይህንን ፅሁፍ ሳዘጋጅ የነበረኝ አመለካከት ስለመድረክና አንድነት የፖለቲካ ፕሮግራም ደካማነት ከዚህ ቀደም ስለጠቀስኩ፣ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲን ብቻ አንስተን ብንነጋገር ይሻላል የሚል ነበር፤ ይሁንና የድርጅቱን ፕሮግራም ካነበብኩ በኋላ ግን ምንም ማውራት እንደማይቻል ተረዳው (ያውም ያየሁት ወረቀት ‹ፕሮግራም› ተብሎ ሊጠራ ከቻለ ማለት ነው)፡፡ ፓርቲው ለስልጣን የመብቃት ዕድል ካገኘ፣ ለዘመናት ሲንከባለልና ሲደራረብ የመጣውን ዘርፈ ብዙ የሀገሪቷን ችግር የሚፈታው ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራም›› በማለት ርዕስ ባዘጋጀው ባለአስራ አምስት ገፅ ወረቀት ነው፡፡ መቼም በዚህ ፕሮግራም ‹ከሌሎች የተሻልኩ ነኝ-ምረጡኝ› የማለቱ ድፍረት ግራ አጋቢ ይመስለኛል፤ ምናልባት ‹የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና ካዘጋጀው አራት ገፅ ፕሮግራም፣ የእኛ የበለጠ ነው› የሚል መከራከሪያ ካልቀረበ፡፡

ስለርዕዮተ-ዓለሙም ቢሆን ‹ለዘብተኛ ሌብራሊዝም› ከማለት ያለፈ ያብራራልን ጉዳይ የለም (በዚህ በኩል ኢዴፓ ከሁሉም በተሻለ የተብራራና የጠበቀ ፕሮግራም አለው፤ ግና! ለአንድ ፓርቲ ከምንም በላይ አስፈላጊ የሆነውን ‹ታአማኒነት› አፍርሷልና ፕሮግራሙ ጠቀመ አልጠቀመ ፋይዳ አለው ማለት አይቻልም) በተቀረ ያለ ርዕዮተ-ዓለም ፓርቲ መስርቶ፣ ‹ሀገሬን፣ ሀገሬን…› ማለቱን ከቀረርቶ ለይቶ መረዳት ይቸግራል፡፡ መድረክ፣ አንድነት እና ሰማያዊ አሁንም ጊዜውም ዕድሉም አላቸውና ስልጣን ቢይዙ በዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች፣ በፖሊሲዎች፣ በማህበራዊ ፍትህ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ያላችውን የመፍትሄ ሃሳብ እና የተሻለ አማራጭ በትክክል ተንትነው ማዘጋጀቱን ቢያስቀድሙ መልካም ይመስለኛል፡፡

ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ በ1997 ዓ.ም ‹‹የምርጫ ማኒፌስቶ›› ብሎ ያዘጋጀው ሰነድ እንኳ ከ130 ገፅ በላይ የፈጀ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ እናም ፓርቲዎቹ ‹ፕሮግራሜ› የሚሉትንም ሆነ፣ ከተራራ የገዘፈ ችግሮቻችንን በደቃቃ ግምገማ ለማብራራት መዳከሩን አርቀው በመስቀል ወደ ቁም-ነገሩ ቢያዘንብሉ ጠቀሜታው ለራሳቸው ነው፤ ‹የትም ፍጪው…› መረሳት አለበት፤ ለፖለቲካ ፓርቲ ሃሳብ ከምንም በላይ ወሳኝ ነው፡፡ ዳሩስ! በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተዘጋጀ ፓርቲ፣ የሚሸጥ ርዕዮተ-ዓለም ካላዘጋጀ በቀር ወታደራዊ ድርጅት አይደለምና ‹በኃይል ተጠቅሜ ፍላጎቴን አሳካለሁ› ሊል አይችልም፡፡ እውነት እውነት እላችኋለውም በዚህ በኩል ቀድሞ የነቃ፣ እርሱ አትራፊ ነው፤ ረቢው እንዳለውም ‹ላለው ይጨመርለታል›ና፡፡
ምሁር አልባ
የተፎካካሪ ድርጅቶች ሌላኛው ክፍተት ምሁራንን /ሙያተኞችን/ አለማቀፍ እንደሆነ ተደጋግሞ ቢነገርም፣ ዛሬም በዚህ በኩል የተሰራ ሥራ የለም፡፡ ይህንን ቀዳዳ ለመድፈን አመራሩና አባለቱ ከጽ/ቤት በመውጣት መቀስቀስ፣ ማሳመን፣ ማግባባት… አለባቸው ብዬ አስባለሁ፤ መቼም በሁሉም ዘርፍ ‹እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው› ግብዝነትን የወረሱት ነፍሱን ይማረውና ከአቶ መለስ ይመስለኛል፤ ይህ አይነቱ አመለካከት ግን ወንዝ አያሻግርም፡፡ በርግጥ ‹ፖለቲካና ኮረንቲ…› በሚባልበት አገር፣ በደፍረት፣ ድርጅት እስከመመስረት መድረስ ትልቅ ታሪክ ቢሆንም፣ ጠንካራ መሆን ካልተቻለ ዞሮ ዞሮ ያው ክሽፈት ነው፡፡ አደባባዩም እንደቀድሞ ‹ድንጋይ ዳቦ ነው› ብለው ለሚከራከሩ አፈ-ጮማ ፖለቲከኞች ቦታ የሌለው መሆኑ ግልፅ ይመስለኛል፡፡ በተለያየ ሙያ የሰለጠኑ ምሁራኖችን ወደ ፓርቲያችሁ ለመሳብ መደላደሉን አመቻቹ፤ ፍርሃት መሰበር እንዳለበት አሳምኗቸው፤ አንኳኩ፤ ከልከፈቱም ደጋግሙት፡፡

የሴራ ፖለቲካ
ሌላው ድርጅቶቹ የሚጠነክሩት፡- ከሴራ፣ ከስርቻ ስር ፖለቲካ፣ ከጠልፎ መጣል ጨዋታ፣ ከአፍቅሮተ-ስልጣን አና ከመሳሰሉት ነፃ ሲሆኑ ነው፡፡ በአናቱም የጥናትና ምርምር ዘርፍ መሰል እያቋቋሙ እውቀትና መረጃን ወደላይም ወደታችም በማሰራጨት አመራሩንና አባላትን ማብቃት፣ እንዲሁም ግልፅነትን በመተግበር፣ የ‹ጀርባ ፖለቲካ›ን ማዳካም ይቻላል፡፡ ይህ ሲሆን ነው ኩነቶችን ከመበለጥና ያለመበለጥ፤ ከመሸነፍና ያለመሸነፍ አኳያ ብቻ የማየቱ አባዜ የሚለወጠው፡፡ ከእዚህ ሁሉ ስንክሳር በላይ ደግሞ በምሬቷ ብዛት በአማራጩ ኃይል ላይ ተስፋ የጣለች ሀገር መኖሯም ከእያንዳንዷ እንቅስቃሴ ጋ መታወስ ይኖርበታል፡፡

በመጨረሻም-የአልባራዲ መንገድ
ሀገሪቱ ካለችበት ወሳኝና ታሪካው ወቅት አኳያ ቢያንስ በመንግስት ጥቁር መዝገብ ስማቸው ያልሰፈረ፣ እውቀትና አቅም ያላቸው፣ በየትኛውም ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው መንገድ ወደ ሀገራቸው ገብተው ትግሉን ማገዝ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁናቴ የሚያስገድደው ነው፡፡ በተለይም በእንዲህ አይነት ጉዳዮች ከትምህርትም ሆነ ከመስክ ልምድ ያካበቱ ወንድምና እህቶች የግብፃዊውን መሀመድ አልባራዲ መንገድ ቢከተሉ፣ አንድም ሁኔታዎች ከቁጥጥር እንዳይወጡ ማገዝ ይችላሉ፤ ሁለትም አብዮቱን ከሽንፈትና ቅልበሳ ይታደጋሉ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

Monday, September 23, 2013

The Fake ‘Amharas’ – To milk “Lamie Bora – ላሜ ቦራ”


September 22, 2013

Wondimu Mekonnen, London

Recently, someone one visited Britain from home on business tour and entertained us with an amusing story of Lamie Bora, the fictional character in the children’s stoy. Woyyane officials call us, Diaspora Lamie Bora (ላሜ ቦራ)።Are we really that “milka-cow?”
Woyane officials call us, Diaspora Lamie Bora
I am sure everyone who went to school in Ethiopia at my age knows the children story of Lamie Bora. Lamie Bora is a very touching story. The story goes like this. A dying mother entrusts her two children unto a cow, called “Lamie Bora.”Just before she died, she sung to the cow: “Lamie Bora! Lamie Bora! I leave my children’s wellbeing to you” (ላሜ ቦራ! ላሜ ቦራ! የልጆቼን ነገር አደራ). After a while the children’s father remarried another woman, whoturned out to be acruel stepmother. Every time she denied them food, the two children would go to Lamie Bora and sing “Lame bora! Lamie Bora! Don’t forget Mammie’s plea (ላሜ ቦራ! ላሜ ቦራ የእማምዬን አደራ!)Then Lamie bora would let the children suckle directly from the tits on her breast. Lamie Bora is supposed never to stop giving milk all year round.
This story is now retold among Woyyane agents referring to Diaspora as Lamie Bora, for the simple reason that whenever Woyyane runs out foreign currency it runs to the Diaspora – a cow full of milk all the year round. Every year, Woyyane officials fly to London, Washington and other major cities of the world, where exiled Ethiopians live in abundance with the hope of harvesting cash from the unsuspecting Diaspora – the cash cow. Their embassies have been instructed to implement the design for the purpose using various tactics. One such means is the Millennium Dum, (sorry I meant Dam), development associations, “Investors” and the recent 40/60 formula to own a house in Ethiopia! Recently, one of our church clergy renegades went for it, but fell out with the guys doing the business on some procedural grounds.
A good way of milking the milka-cow is to organise the Lamie Bora’s along their ethnic blood lines – such as the ‘Amhara’ Development Association, the Guragea Development Association, etc. This time, it is the ‘Amhara’ Lamie Bora’s turn to be milked in Queens capital city. The fake ‘Amhara’s (ቁጩ አማሮች)[1]are used as tools for the purpose. You rarely find any ‘Amhara’ among their leaders. Their organisation, The ‘Amhara’ National Democratic Movement (ANDM) was found in November 1980 in Tigray, at a place known as Tekrarwuha. The mission of ANDM – It’s all about shutting down the ‘Amhara’ threat. ANDM was the favoured puppet organization. They leadership was made up of various ethnic groups, but ‘Amhara’! They were then and are now actually predominantly Woyyanes disguised as Amaras. They are all fake-fake-fake to the root third rated ‘Amharas’. Take for Example, Bereket Simon. He is a Shabbo-banda whose mother and father hail from Eritrea.  Hilawi Yosef is either a Tigre or a Shabo-Banda like Bereket, but has no drop of ‘Amhara’ blood in him. Tefera Walwa is a Gimira. Well at least Gimira sounds like ‘Amhara’. The only ‘Amhara’ thing in Addisu Legesse is his name. He is an Oromo from Harar. Did you know who Tamirat Layne was before he became Tamirat Layne? His real name was Getachew Mamo Waqkenie. Go and figure out that. Tadesse Tinqishu, regardless of his beautiful name, is a Tigre? Is Kassu Ilalla sound ‘Amhara’? Give me a break! All the ethnic based organisations, except the TPLF were formed using the same formula. Their extensions in the Diaspora are called “development associations” followed by the appropriate suffixes. The “associations” are kind of support groups for the “forged” ethnic groups.
Coming back to the Lamie Bora story, the fake ‘Amharas’ in London are organised under “‘Amhara’ Development Association – UK”. Do you want to see, who they are exactly, from their 2011 fund raising event? http://www.youtube.com/watch?v=8fmeHCLPgpU. Those of you who reside in London should be able to tell who is who in that video. The majority are Tigres, followed by Jamaicans and then some hod-aders like Yalew Kebede. Gondares have yet to tell us about the ethnic background of Yalew Kebede. Could he be another fake ‘Amhara’ like Bereket from Gondar?
This year, Lamie Bora – Diaspora is planned to be milked on 28 September 2013 at the Ethiopian Embassy. The entrance fee is free. Why not invite ourselves to the abundant food and drink? Oh, one more thing. Where are they advertising their event? Not of course mainstream websites, but Tigrai Online. This is yet another proof that this is another Woyyane organisation camouflaged as ‘Amhara’s! See for yourself.http://www.tigraionline.com/’Amhara’-ada-event-uk.html
 The forged Amaras are disgusting who trade in the name of ‘Amhara’ to milk the Diaspora, to fill in the never quenching thirst of Woyyane for hard currency. It looks like its recent attempt to milk Lamie Bora did not work at fund raising events for the millennium dam, so they are punishing their Ambassadors for failing to trap Lamie Bora – the milka-cow. Many lost their jobs this week. May be the 40/60 formula for owning a house in Addis might attract some fools to sacrifice their hard earned currency. The idea is the Diaspora would pay 40% down payment in hard currency. The 60% would be lent in birr by the TPLF. Don’t you even think of owning the land on which the house is going to be built. It belongs to the TPLF. Whenever the TPLF wants the land, it will ask you to carry away your bricks and mortars as the land is needed by the landlord to be sold to foreign investors!
The Diaspora has to cease being treated like Lamie Bora. It has to distance itself from these corrupt and human rights abusers. Whenever one needs to do business with the TPLF, it is that person’s morale obligation to remember prisoners like Reyyot Alemu, Andualem Arage, Eskinder Nega, Nathnael Mekonen, Kinfemichael Debebe, Yohannes Terefe, Shambel Yeshewas Yehunealem and Andualem Ayalew, tens of thousands of members of the Oromo ethnic group and the illegally imprisoned Muslim leaders.
The Woyyane is a No. 1 corrupt regime in Africa. One would better avoid dealing with Woyyane at all levels unless that person wants to be milked dry. One can invest his/her money elsewhere, where a good return is expected without risk of being fleeced. The least, if you don’t want to invest, just drink your own milk rather than giving it to the Woyyane. Even some cows have become smarter and drinking their own milk rather than giving it away. Don’t you believe me? Watch the next clip!
Good for you, cow! Well done! You are much better than some Ethiopians that are regularly milked dry by the Woyyane!