Thursday, July 31, 2014

Ethiopian Photojournalist Aziza Mohamed Held Without Charge


 Ethiopian Photojournalist Aziza Mohamed. (Photo: Facebook)
July 31, 2014
Nairobi – CPJ is alarmed by the detention of Addis Guday (“Addis Affairs”) photojournalist Aziza Mohamed, who has been in custody for two weeks without charge. Police arrested Aziza on July 18 while she was covering Muslim protests near Anwar Mosque in the capital Addis Ababa, local journalists told CPJ. She is being held at the Addis Ababa police headquarters.
Police investigators presented Aziza before the Kirkos First Bench Court today but requested further time for their probe before bringing formal charges, local journalists said. According to local journalists who attended the hearing, police told the court that Aziza was inciting protesters to violence during the demonstration. However, Aziza told colleagues who visited her in detention that plainclothes policemen arrested her in a café near the protests, likely after noticing her camera. Police searched Aziza’s home on July 26 and confiscated several music compact discs, local journalists said.

- See more at: http://www.tadias.com/07/31/2014/ethiopian-photojournalist-aziza-mohamed-held-without-charge/#sthash.vRfkH8Yd.dpuf

መኢአድና አንድነት ፓርቲ በመኢአድ ጽ/ቤት መግለጫ ሰጡ




ውህደታችን የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ወደ ላቀ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል!

አንድነትና መኢአድ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ውህደቱ ነሐሴ 3 እና 4,2006 ዓ.ም እንደሚደረግና ለጉባኤው የሚደረገውም ዝግጅት እንደተጠናቀቀ ነገር ግን ለጠቅላላ ጉባኤ የሚሆን የገንዘብ እጥረት እንደገጠማቸውና ይህን የፋይናንስ እጥረት ለመቅረፍ ተዋሃዱ ሲለን የነበረው ሕዝባችን ያለብንን የፋይናንስ እጥረት ተረድቶ እንዲተባበረን ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የሁለቱ ፓርቲዎች ፕሬዚደንቶች እንደገለጹት ውህደቱን ለማድረግ በምናደርገው እንቅስቃሴ ብዙ ፈተናዎች እንደገጠሟቸው ጠቅሰው፣የገዢው ፓርቲ ውህደቱን በተለያየ መንገድ ለማደናቀፍ የሚያደርገው ሙከራና የፋይናንስ እጥረት ተግዳሮቶቻቸው እንደነበሩና ይህን ሁሉ አልፈን ውህደቱን በተባለው ጊዜ የምንፈጽም መሆኑን እናረጋግጣለን ብለዋል፡፡

የመግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ቀርቧል

ውህደታችን የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ወደ ላቀ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል



ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንደነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የውህደት ድርድራቸውን አጠናቀው ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም የቅድመ ውህደት መግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወቃል፡፡ የሁለቱም ፓርቲዎች ከፍተኛ የአመራር ተቋሞች የጋራ የውህደት አመቻችና ጠቅላ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ በማቋቋም መመሪያ በመስጠት ስራቸውን ጀምረዋል፡፡ የጋራ ኮሚቴው የራሱ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ፀሓፊ በተጨማሪ የሰነድ ዝግጅት፣ የጠቅላላ ጉባኤ ጠሪ ፣ የሕዝብ ግንኝነት፣ የመድረክ ዝግጅት እና መስተንግዶ፣ የህግና ፀጥታ እንዲሁም የፋይናንስ ንዑስ ኮሚቴዎችን በማቋቋም በሳምንት 3 ቀን ስብሰባ በማድረግ መሰረታዊ እና ዋናዋና ስራዎችን በማጠናቀቅ የጉባኤውን ቀን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡

የፓርቲያችን ውህደት የኢትዮጵያ ህዝብ ለረዥም ግዚያት ሲጠይቅና ሲመኘው እንደ ነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ይህንኑ ጥያቄ ለመመለስና ገዢውን ፓርቲ የሚፎካከር ፓርቲ ለመመስረት ብቻ ሳይሆን ትግሉ በይዘትም በቅርፅም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚያስችለን ቁመና ላይ ለመገኘት ተግተን በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡ የሁለቱም ፓርቲዎች ውህደት ለማደናቀፍ ከፍተኛ ሴራ እንደሚኖር በመገመትም ነቅተን በመጠበቅ ላይ ነን፡፡ በኛ በኩል ሥራዎቻችንን ብናጠናቅቅም ጉባኤያችንን ለማድረግ የገጠመን መሠረታዊ ችግር ወይም እንቅፋት የገንዘብ እጠረት ነው፡፡

አሁን ባላው ሁኔታ ከ1997 ዓም አገር አቀፍ ምርጫ በኂላ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ለማዳከም ተጠንተው የተሰሩ ጉዳዮች ፓርቲዎችን በአዋጅ የፋይናናንስ አቅማቸውን ማዳከም ነው፡፡ ለዚህም የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ማቋቋማያ አዋጅ እና የመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አዋጅ መጥቀሱ በቂ ማሳያ ነው፡፡ አሁን ፓርቲዎቻችን ይህንኑ ችግር ለመቅረፍ የባንክ አካውንት በመክፈት ለሕዝቡ ይፋ አድርገናል በዚህም አንፃር አፋጣኝ ድጋፍንም እንጠብቃለን፡፡

ዛሬ በአገራችን ኢትዮጵያ መጭውን የ2ዐዐ7 አገር አቀፍ ምርጫና ውህደታችን ታሳቢ ያደረገ እስር በፓርቲያችን ከፍተኛ አመራር አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ላይ የተካሄደውን እስር ከማውገዛችንም በላይ ለውህደታችን መሰናክል የሆነብን የገንዘብ እጥረት ጉዳይ ከሕዝቡ ጋር በመወጣት ውህደታችን ለመጨረሻ ጊዜ በተቀመጠለት የጊዜ ሠሌዳ እውን ይሆናል፡፡ ውህዱ ፓርቲ የአሸናፊነት መንፈስ ተላብሶ ከፍ ባለ የሞራል ልእልና ትግሉን ይመራል ለዚህም አንጠራጠርም ፡፡

SP 235 ቦሌ ቅርንጫፍ አቢሲኒያ ባንክ 
A/C 47 ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ አቢሲኒያ ባንክ 

ድል የሕዝብ ነው!
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ( አንድነት)
ሐምሌ 24 ቀን 2ዐዐ6 ዓም
አዲስ አበባ

ሊታሰብበት የሚገባ



አሸባሪነት በሃገራችን ትርጉሙን ገልብጦ ተሸባሪዎች በሙሉ አሸባሪ እየተባሉ በእስር በግርፋት በተለያዩ የማሰቃያ ዘዴዎች በመጠቀም ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በየእስር ቤቱ በስቃይ ላይ ይገኛሉ። ይህ የፀረ ሽብር ህግ በአግባቡና በቀጥታ ትርጉሙ ቢታይ በኢትዮጵያ ዜጎች በመንግስት እየተሸበሩ የሚገኙበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን በመንግስታችን እይታ ሙስሊሙ አሸባሪ፣ ክርስቲያኑ አሸባሪ፣ ጋዜጠኛው አሸባሪ፣ ፀሐፊዎች አሸባሪ፣ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ድርጅቶች አሸባሪ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉ ሰላማዊ ሰዎች አሸባሪ ባጠቃላይ የሐገራችን ሁኔታ ያገባናል ሐገራችን ኢትዮጵያ አንድነትዋን ጠብቃ እንድትቆይ የሚሰሩ የነፃለት ታጋዮችን በሙሉ አሸባሪ ናቸው ይሉናል።  ይሄ ነገር ያሰጋል እውነተኛ አሸባሪ ቡድን ሐገር ሊያጠፋ ቢመጣ ህዝቡ የሚሰማበት ጆሮ የለውምና ወያኔ በዚህ አካሄዱ ሐገራችንን አደጋ ላይ መጣሉን መገንዘብ አለበት የሰላም ትግሉን ሁሉ በአሸባሪነት በመፈረጁ ህዝቡ የአሸባሪነት ትርጉሙ ተዛብቶበታልና አሁን ባለው የሐገሪቷ ተጨባጭ ሁኔታ ዋናውን የሽብር ጥቃት ሰው በንቃት እንዳይጠብቅ ህዝብን እያዘናጋ ይመስላል። ሊታሰብበት ይገባል ወያኔዎች ልብ ይበሉ እላለሁ።

እነኚህ ሁሉ በፎቶ የምትመለከትዋቸው እና እጅግ በርካታ ንፁሐን ዜጎች ያለአግባብ በየእስርቤቱ ታጉረው እየተሰቃዩ ይገኛሉ ወያኔ የገዛ ህዝቡን ለማሰቃየት እየተጠቀመበት ያለው የማሰቃያ ዘዴ በሙሉ እጅግ የከፋና አሰቃቂ በመሆኑ የዜጎቻችን የየደቂቃው ህመም ሊያመን ይገባል ይህንን ግፍና በደል በቃ ብለን ከጫንቃችን ላይ ማስወገድ ያለብን እኛው እራሳችን ነን። አሁን የተፈጠረው አጋጣሚ ለሁላችንም ወደፊት የማይቀር ነውና አቅማችንን ሁሉ ተጠቅመን ሐገራችንን ከወራሪው የወያኔ አገዛዝ እንታደግ እያልኩ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

ሄለን ንጉሴ

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር


Wednesday, July 30, 2014

Local EU statement on the situation in Ethiopia

Local EU statement on the situation in Ethiopia
July 30/2014

The European Union Delegation issues the following statement in agreement with the EU Heads of Mission in Ethiopia:

“The EU Delegation is deeply concerned about developments in the case of the ten bloggers and journalists charged under the Anti-Terrorism Proclamation on 18 July, as well as recent arrests of opposition members. It calls on the Ethiopian authorities to ensure that proceedings are carried out according to the Ethiopian Constitution and respecting international and regional human rights standards, in particular granting access to legal counsel and family, as well as the right to apply for bail when applicable, and that the trial is transparent and free from political interference.

The EU Delegation recalls the European External Action Service statement of 6 May 2014 which underlined the importance of enhancing the political space, particularly in view of the elections next year. It calls on the Ethiopian Government to ensure that the Anti-Terrorism Proclamation is not used to curb freedom of expression or association.

The EU Delegation welcomed the additional commitments made by the government of Ethiopia to address areas of human rights concern in the recent Universal Periodic Review process in Geneva and called for early and continuing action to ensure implementation of all of the government’s human rights commitments.”

Delegation of the European Union to Ethiopia

Cape Verde Road
P.O.Box: 5570 Addis Ababa

Telephone: + 251 (0) 11 661 25 11
Fax: + 251 (0) 11 661 28 77

E-mail: Delegation-ethiopia@eeas.europa.eu
The European Union Delegation issues the following statement in agreement with the EU Heads of Mission in Ethiopia:
“The EU Delegation is deeply concerned about developments in the case of the ten bloggers and journalists charged under the Anti-Terrorism Proclamation on 18 July, as well as recent arrests of opposition members. It calls on the Ethiopian authorities to ensure that proceedings are carried out according to the Ethiopian Constitution and respecting international and regional human rights standards, in particular granting access to legal counsel and family, as well as the right to apply for bail when applicable, and that the trial is transparent and free from political interference.
The EU Delegation recalls the European External Action Service statement of 6 May 2014 which underlined the importance of enhancing the political space, particularly in view of the elections next year. It calls on the Ethiopian Government to ensure that the Anti-Terrorism Proclamation is not used to curb freedom of expression or association.
The EU Delegation welcomed the additional commitments made by the government of Ethiopia to address areas of human rights concern in the recent Universal Periodic Review process in Geneva and called for early and continuing action to ensure implementation of all of the government’s human rights commitments.”
Delegation of the European Union to Ethiopia
Cape Verde Road
P.O.Box: 5570 Addis Ababa

Telephone: + 251 (0) 11 661 25 11
Fax: + 251 (0) 11 661 28 77

E-mail: Delegation-ethiopia@eeas.europa.eu

ዓረና ትግራይ በህወሓት ዳስ እስክስታ የሚመቱ ባንዳዎች ወለደች

በመ/ር ታደሰ ቢተውልኝ፣ መ/ር ገብሩ ሳሙኤል ፣ ሽሻይ አዘናው እና አስገደ ገ/ስላሴ በዓረና ትግራይ ለ4 አመታት የቆዩ የተለያዩ ዝንባሌዎችና ባህሪ በመከሰታቸው ወደ አባላትና ህዝብ ያልወጣ ውስጣዊ ትግል ሲካሄድ ቆይቷል። እነዚህ ይታዩ የነበሩ ግልጽነት አለመኖር ፤ የዲሞክራሲ ጥበትና አሳታፊ አለመሆን ፤አባታዊነትና አምባገነንነት፤ ድርጅታዊ አሰራር አለመኖር ወዘተ ነግሰው እንደቆዩ እንዲሁም እንደ ብርሃኑ በርሀ የድሮ ም/ሊቀ መንበር ያሁኑ ሊቀ መንበር በፈጠሩት ኢ-ዲሞክራሲያዊ አሰራር ምክንያት ከተራ አባላት እስከ ከፍተኛ የፓርቲው አመራር ከፓርቲው ራሳቸው ተገልለዋል(ራሳቸው አግለዋል) ::  የአባላቱ መፍለስ ችግር ምንድነው ? ብለን እንዲፈታ ጥያቄ ብናነሳ ሰሚ ጀሮ ኣላገኘንም:: ይቅርና ተራ አባላት በማ/ኮሚቴና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባዎች ተነስተው በዲሞክራሲያዊና በመግባባት ተወያይተን እንድንፈታው በወቅቱ ሊቀ መንበር የነበሩ አቶ ገብሩ አስራት፤ ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ፤ የዛን ጊዜ ም/ሊቀመንበር ያሁኑ ሊቀ መንበር ብርሃኑ በርሄ ጠይቀን የሰማን አካል አልተገኘም :: እነዚህ ሰዎችና ሌሎች የነሱ ጥቂት አጃቢዎቻቸው ልክ በህወሓት አመራር ሁነው “እኛ ያልናችሁ አድርጉ” እያሉ ብዙ የትግራይ ወጣት እያከሰሙ እንደመጡ በኛ ላይም ለመፈፀም ሞክረው በትግላችን ያ የአባታዊነት ባህሪያቸው ግቡን ሳይመታ ቆይቷል :: ከጳጉሜ 2 እስከ 3/13/2005 3ኛ ጉባኤ ሲደረግ ብዙ አጀንዳዎች ተነስተው ፈጥረውት በቆዩት ቡድናዊነት ምክንያት በፓርቲው የነበሩ ፖሊሲዎች ፤አቋሞች ህገ ደንብና ፕሮግራም እንዲሁም ስለ የህወሓት ሰርጎ ገብ ባንዳዎች አደገኝነት ፤ ስለ ሃገራዊ አንድነት፤ ውህደት በሚመለከቱ በጥልቀት ተወያይተንበት ሳንተማመን በድፈንፍን ታልፏል :: በዛን ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎች በድፈንፍን እንዲታለፍ ያደረጉ
አቶ ገብሩ አስራት፣ ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ፣ ብርሃኑ በርሀና ሌሎች አጃቢዎች ነበሩ :: 

ሁኔታው ጥራት ይኑረው አይኑረው የነበረው ጉባኤተኛ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ጥራት የሌለው አመራር መርጦ መጣ :: በኛ
በኩልም ሁኔታው በሂደት ይጠራል ብለን ለጉባኤ ክብር በመስጠት በነአቶ ገብሩ አስራትና ብርሃኑ በርሄ ቡድን ተሸነፍን ብለን ስሜት ሳንይዝ በሁሉም አቅጣጫ ፓርቲው የሰጠን የስራ ምድብ ከመስራት አልፈን በግላችንም በአደረጃጀት፣ በፕሮፖጋንዳና ፋይናንስ እየሰራን ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ በፓርቲው ያሉት ለአላማችን እንቅፋት የሆኑ አመለካከቶችና ባህርያት የህወሓት ሰርጎ ገብነትና የህወሓት ፋሽሽታዊ አፈና ሳይበግረን ፊትለፊት እየተጋፈጥን ደማችን በጎዳና እየፈሰሰ እንደ አቅማዳ እየታሰርን እየተፈታን እስካሁን ቆይተናል :: ልብ በሉ! ይህ ሁሉ የምናደርገው በውስጠ ፓርቲ ያሉ ችግሮች ይፈቱ ? ችግር አለ እያልን እያመለከትን ልዩነት ሳይገድበን ነበር እየታገልን የቆየን። በዘንድሮ የትግል ጊዚያችን ጎን ለጎን ግን

1. መምህር ገብሩ ሳሙኤል፣ የአረና ቁጥጥር ኮሚሽን አባል ብዙ ጊዜ በቃልና በፅሁፍ
2. መምህር ታደሰ ቢተውልኝ፣ የአረና ማእከላዊ ኮሚቴ 14 ገፅ ያለው ፅሁፍ 2 ጊዜ
3. ሽሻይ አዘናው፣ የአረና ማእከላዊ ኮሚቴ አባል 4 ጊዜ በፅሁፍ
4. አሰገደ ገ/ስላሴ አረና ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ እስከ 2005 መጨረሻ የአረና ስራ አስፈፃሚ የነበረ፣ አሁን ተራ አባል 7 ጊዜ
በጽሁፍ ፤ በፓርቲው ውስጥ ያሉ ችግሮች እንዲፈቱ ስናመለክት ቆይተን መልስ ለመስጠት ወይም በግለ ሰብ ወይም በቡድን ወይም
በአስቸኳይ የማ/ኮሚቴ ስብሰባ ከመፍታት ይልቅ እጅግ ጠንካራ ታጋዮች በ20/11/2006 ለመ/ር ገብሩ ሳሙኤል በሌለበት ለጠየቀው ጥያቄ ምክንያት የሆነው ሳይጠየቅ በድብቅ ስብሰባ በማካሄድ እስከ መጪው ጉባኤ ማለት ለ2 አመት ከቁጥጥር ኮሚሽን እንዲታገድ ተወሰነበት:: 

ሽሻይ አዘናው በጋዜጣ ለሰጠው መግለጫ በ14 ቀናት ውስጥ ማስተባበያ እንዲሰጥ ካልሰጠ ግን ከአመራርነቱም ሆነ ከአባልነቱ
እንዲባረር ፤ መ/ር ታደሰ ቢተውልኝ ለጻፈው የአስቸኳይ ግምገማ ጥሪ ጥፋት ተቆጥሮ የህወሓት ባንዳዎች እንዲባረር የውሳኔ ሃሳብ ሲያቀርቡ በአብላጫ ድምፅ በማስጠንቀቅያ እንዲታለፍ ከተወሰነባቸው በኋላ የፓርቲው ማስታወቂያቸው ትተውላቸው ከፓርቲው ሁለቱም የማ/ኮሚቴ አባላት ፓርቲውን ለቀው ወጥተዋል። አስገደ ገ/ስላሴ ካሁን በፊት ያልነበረ ብርሃኑ በርሄ የመቀሌ ከተማ የአባላት መሰረታዊ ድርጅት የሚባሉ እንዲወስኑ በተሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት አቶ አስገደ ከፓርቲው እንዲባረር ተወስኗል :: 
ይህ የተደረገው በዓረና አመራር ውስጥ ስልጣን ያላቸው የህወሃት ባንዳዎች ስላሉ ሆን ተብሎ አስገደ ከተመታ ዓረና ይፈርሳል ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ ነው :: እጅጉን የገረመን ግን እኛ የምናከብራቸው የነበርን፤ ከዛ ወንጀለኛ ህወሓት ጋር ሁነው የሰሩት ወንጀል ምንም ሳይሸማቀቁ በትግሉ ወቅት የሰሩት አገርና ዜጎችን የሚጎዳ የሰሩት ወንጀል ህዝብ ይፍረድ ብለው ለህወሓት ፋሽሽታዊ ስርአት በመቃወም ከ21ኛ ክ/ዘመን ወጣት አስተሳሰብ ጎን በመሰለፋቸው እንወዳቸውና እናከብራቸው ፤ እንዲመሩን፣ ተሞክሮ እንዲያካፍሉን፣ ከነሱ የሚጠበቅ ሙያ እንዲያስተላልፉልን ነበር ምኞታችን :: ግን አልሆነም ::

አቶ ገብሩ አስራትና ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ በህወሓት ዳስ እስክስታ እየመቱ አገኘናቸው :: ይኸውም ብርሃኑ በርሄ ለህወሓት መሪዎች
ለማጋለጥ፤ በመድረክ ወጥተው ለመሞገት ፍቃደኛ ካለመሆን አልፈው የህወሓት ባለስልጣናትና ካድሬዎች የሚያናድድ ፅሁፍ
እንዳትፅፋ፣ እንዳትናገሩ፣ ተናደው በኛ ላይ እርምጃ እንዳይወስዱ እያለ ኦረነቴሽን የሚሰጥ ፤ አደገኛ በሚባሉ ቦታዎች በሚደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ተደብቆ እየቀረ፤ በተገኘባቸው ስብሰባዎችም አባሎቻችን እንዳይናገሩ በመከልከል ቅሬታ እየፈጠረ ራሱ የሚያስተላልፋቸው መልእክቶችም ከህወሓት እንዳይጋጭ በፍርሃትና ስግአት ንግግር ሲያደርግ እየታየ ባለበት ሁኔታ በሄድንባቸው ስብሰባዎች ህዝባችን ራሳችሁ ፈትሹ እያለ ምክሩን እየለገሰልን ባለበት ሁኔታ እሱና አጃቢዎቹ ተንደላቅቆ ከነነፍጡ ሲኖር በአንፃሩ እነ አስገደ ፤መ/ር ታደሰ ፤ ገብሩ ሳሙኤልና ሽሻይ አዘናውና ሌሎች አባሎቻችን ለ6 አመታት ጉልበታቸው፤ አእምሯቸው ገንዘባቸው ኢንቨስት ሲያደርጉና ዘርመንዘራቸው ጭምር በአፋኝ ኢ-ፍትሐዊ የህወሓት ስርአት ሲሰቃዩ ቆይተው አሁን ደግሞ አረና ውስጥ ባሉ የህወሓት ባንዳዎች ሲመቱ እነ አቶ ገብሩ አስራት ዋና መቺ ሃይል ሁነው መገኘታቸው ምን ያህል ክዳት መሆኑ አለማወቃቸው ነው ችግሩ :: 

በኛ እምነት ግን እነ አቶ ገብሩ እስራት ከህወሓት መሪዎች ልዩነት ነበራቸው ወይ? የሚል ጥያቄ ልናነሳ አድርጎናል :: ምክንያቱም
ብርሃኑ በርሄ ጭምር የክልል ትግራይ ባለስልጣናት ሁኖው ብዙ ምሁራን ከዚህ ክልል በማባረር በተለይ ለአስተማሪዎች ሞራላቸው
በመንካት በክልላችን ፍፁም አምባገነን የሆነ አሰራር ያራምዱ እንደነበረ ከትግራይ ህዝብ ጭንቅላት አልተፋቀም :: እንደውም በህዝብ ወርደን ስንቀሰቅስና ስብሰባ ስናደርግ እነ ገብሩ እኮ ትናንት አፋኞች ነበሩ በማለት ተቀውሟቸው ይገልፃሉ :: እኛም እነሱን ወክለን ህዝብን ለማሳመን ብዙ ጥረት አድርገናል :: አሁን ግን ፍፁም አባታዊና አምባገነን እርምጃ በላያችን ላይ ተወሰደብን :: በ2 ቀናት ስብሰባ የነ አቶ ገብሩ አስራት አነጋገር ልክ የህወሓት መሪዎች በትጥቅ ትግል ጊዜ በጫካ ሽፋን አድርገው ቢፈልጉ ያስራሉ ሲፈልጉ በነፍጥ ደብዛቸው ሲያጠፉ የጠሉት ሰው ሲያባርሩ እንደነበረ ሁሉ አሁንም እነ ገብሩ አረጋሽና ብርሃኑ የሚሸፍናቸው ጫካ ቢኖርና ነፍጥ ቢኖራቸው(ለነገሩ ያሁኑ ሊቀ መንበር አሁንም ነፍጥ እንደታጠቀ ነው ) ልክ እንደ ህወሓት መሪዎች እርምጃ ለመውሰድ የሚያግዳቸው አልነበረም :: 

እስቲ ልብ በሉ! አንድ የግለሰብ መብት አከብራለሁ የሚል አምናለሁ የሚል የፓርቲ ማ/ኮሚቴ ሃሳባችሁ በፅሁፍ ለመሪዎች
አቀረባችሁ: በሚዲያ ተናገራችሁ ብሎ ጠንካራ ታጋዮችን ማባረር እጅጉን የህዝብ ትግልን በሚያጨልም ማባረርና ሞራል በሚነካ ስም ማጥፋት ለነአቶ ገብሩና አረጋሽ ማንነታቸውን ያጋለጠ እርምጃ ከመሆኑ በላይ ህወሓትን ታግሎ ለመጣል ተነሳስቶ የነበረ ህዝብ እጅጉን ሞራል የሚነካ እርምጃ ነው :: እኛ ብንሆን ዛሬ ይሁን ነገ የህወሓት ኢህአደግ ስርአት እስካልተወገደ ድረስ ወይ እስከ ህልፈተ ህይወታችን ቆርጠን ከመታገል ውጪ ምንም ፍንክች አንልም :: ለህወሓትም ለአረና አባታዊና አምባገነናዊ አገዛዝ አንምበረከክም ።

 የሰላማዊ ትግልአቅጣጫ አስፈላጊውን መስዋእትነት እየከፈልን እንታገላለን :: 

በዚሁ ሓምሌ 19ና 20/2006 የአረና ማ/ኮሚቴ ስብሰባ እነ አቶ ገብሩ አስራት አነጋገር በውህደት ጉዳይ አንስተው ሲነጋገሩ ያ
ስንቃወመው የነበርን ፀረ ውህደት አቋም በመጠናከር የህወሓት መሪዎች እነ ገብሩ: አረጋሽና አውዓሎም የነበሩበት ጨምሮ
ከትምክህተኛው የአማራ ድርጅት ኢ.ህ.አ.ፓ አብረን አንታገልም ብለው በኢ.ህ.አ.ፓ ና ህወሓት መሪዎች የግል ፍላጎት ብዙ ወጣት
ምሁራን የቀጠፈው ጦርነት ተመልሰው አሁን ደግሞ ሲተነትኑት ሰንብተዋል :: 

 “ከጎሳ ፓርቲ ውህደት አናደርግም ከሚለው መኢአድ ውህደት አይቻልም፤ በውጭና በሃገር ውስጥ አንድነትና መኢአድ ለማዋሃድ
የሚጥር ሃይል አለ እነዚህ ተዋህደው ጠንካራ ፓርቲዎች ሁነው በመውጣት የአማራን የበላይነት የሚፈልጉ ናቸው ከዛ በኋላ ትግራይ ለመቆጣጠር ከተቻለ አረና በራሱ ካልተቻለ አባላቱ በመውሰድ ትግራይን መቆጣጠር የሚሉ ናቸው :: በአሁኑ ጊዜ በ3ት መንገድ ጦርነት ተከፍቶብናል 1. በህወሓት 2. በውስጣችን 3. በተቀዋሚዎችተቃማዊዎች ህወሓትን ለማሸነፍ ትግራይን መቆጣጠር አለበት። ለዚህም ከአረና አባላት በመውሰድ እንደ መሳርያ በመጠቀም ትግራይን መቆጣጠር አለብን የሚሉ ናቸው:: ” የነአቶ ገብሩ አስራት አነጋገር ምን ያመለክታል? በኛ እምነት አቶ ገብሩ የኢትዮጵያ አንድነትና እኩልነት የማይቀበሉ ሁነው ተገኝቷል። አንድነት ሊውጠን ነው ማለት ምን እርባና አለው ከመጠራጠር አልፎ?  በኛ እምነት እነ አቶ ገብሩ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለማምጣት ሳይሆን ወደ ፓርላማ ሸልኮው ለመግባት ወይም የፓርቲ መሪዎች ነን እያሉ በየኤምባሲው በር፤በፕሬስ ኮንፈረንስ አንድ ቃል እየተናገሩ ፓርቲው እንደ መደበቂያ ዋሻ ለመጠቀም ነው::  አዲስ አበባ ተወሽቀው ቆይተው በአመት አንድ ጊዜ የማ/ኮሚቴ ስብሰባ ብቅ እያሉ የተቀነባበረ አስተያየት መስጠት ለታጋዮች ሞራል መጉዳት አይደለምን? 
 ታጋዮች ከሆኑ በየከተማውና ገጠር ከባንዳዎች እየተጋፈጡ ለምን ህዝብን አያስተምሩም? እኛ 4ታችን የተባረርን አባላት 6 አመታት ሙሉ ከባንዳወችና ከሃዲዎች ጋር እየተላተምን ተታግለናል፤በጽሁፍ ለህወሓት ኢህአደግ አጋልጠናል (በተለይ አስገደ) በሃገር ውስጥም በውጭም ያሉ ኢትዮጵያዊያን ይመሰክራሉ :: 

አሁንም ምንም እንኳን አባታዊ አመራራቸሁና የብርሃኑ ቡድን (የህወሓት ባንዳዎች) ወንጀሉን ለመሸፈን ቢመታን ትግላችን ግን
አሁንም ይቀጥላል :: የ90 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ መዋኛ ባህር አለን :: ከወንድሞቻችንና እህቶቻችን ኦሮሞ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣
ሶማል፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ሃዲያ፣ ከምባታ፣ ጉራጌ ከሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ሁነን እንታገላለን :: ወየውላችሁ እነ አቶ ገብሩ አስራት
ለውርደት የታደላችሁ እንጂ አሁንም ልናረጋግጥላችሁ በህወሓት ዳስ እስክስታ አንመታም :: 

በመጨረሻም ለመላው የአረና አባላትና ደጋፊዎች በሃገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ ፤ በኢትዮጵያ የምትገኙ እውነተኛ ተቃዋሚ ፣
ፓርቲዎች አሁንም የአረና ማ/ኮሚቴ መጥፎ ውሳኔ ቢወስንም እኛ ልናረጋግጥላችሁ ምንፈልገው አሁንም ታጋዮች ነን :: ሰፊ የትግል ሜዳ አለን :: የአረና አባላት ከእንግዲህ ወዲህ በህወሓት ዳስ እስክስታ መምታት ይቁም :: የብርሃኑ በርሄና አንጃዎቹ መጫወቻ መሆን የለባችሁም :: በአረና ማ/ኮሚቴ ያላችሁ ንፁሃን ወጣት ሙሁራንና ታጋዮች ነገሩ በሙሁራዊ አይን እየተነተናችሁ ለዚህ ህዝብ የሚጠቅም ስራ በቅንነትና በንጽህና በመስራት ህዝባችን ከህወሓት የጨለማ ንሮ አድኑት :: እኛም በሆነ መንገድ ከጎናችሁ ነን 

በሃገራችን ያላችሁ ዲሞክራትና ሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች - አረና ትግራይ ለቅን አላማ ተነስቶ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት መንጋጋ
ያላቅቀኝ ይሆን ?ብሎ ተስፋ አድርጎ ነበር :: አሁን ግን እነ አቶ ገብሩ አስራት ለባንዳዎች ግንባር ቀደም በማሰለፍ ለህወሓት አሳልፈው በመስጠት ተስፋውን አጨልመውታል :: በመሆኑም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግዳጃችሁን ተወጡ :: 

በዲያስፖራ የምትገኙ የአረና ትግራይ ደጋፊዎች ከአሁን በፊት የአንድወገን ሰምታችሁ ምንም ሳታጣሩ የፃፋችሁት ትክክል አልነበረም፤ አሁንም ይህንን ድርጊታችሁ ሳትደግሙ ዳግም የህወሓት ባንዳዎች ውሸት ሳትሰሙ በአንድ እጃችሁ ማንጨብጨብ ትታችሁ በአረና ትግራይ ደርሶ ያለው የመፍረስ አደጋ አጥንታችሁ ተፈጥሮ ያለው የህወሓት ባንዳዎች ሰርጎ ገብነት እንዲወገድ የድርጅት ውስጣዊ ግጭቶችን የመፍታት ልምድና ተሞኩሮ ትለግሱ ዘንድ ጥሪያችን እናቀርባለን :: 

 ፀሃፊዎች፦
1.መምህር ታደሰ ቢተውልኝ ማ/ኮሚቴ
2.ሽሻይ አዘናው ማ/ኮሚቴ
3.መምህር ገብሩ ሳሙኤል ቁ/ኮሚሽን
4.አስገደ ገ/ስላሴ ተራ አባል
ከሰላምታ ጋር

ይቀጥላል
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
July 29, 2014

Tuesday, July 29, 2014

California Congressman demands the release of Andargachew Tsige

Press release


WASHINGTON – Rep. Dana Rohrabacher on Monday urged Ethiopia’s prime minister to release Andargachew Tsige, a native-born opposition leader with British citizenship who last month was extradicted to the African nation from Yemen under questionable circumstances.
In a letter to Prime Minister Hailemarian Desalegn, the California Republican wrote: “Mr. Andargachew is a British citizen and a leader for political reform in Ethiopia. He should be released and allowed to return to his family immediately. Any maltreatment or harm to him, or other prodemocracy activists, in your country only serves to widen the gap between our two countries.”
Andargachew was traveling from Dubai to Eritrea on June 23 when, stopping over in Yemen, he was forcibly flown back to Ethiopia, which he fled in 2005 following protests of the nation’s elections. He was granted asylum in Britain, where his wife currently lives. British officials have expressed concerns that his extradition was not properly handled.
The activist was charged with terrorism and sentenced to death in absentia. In his letter to the Ethiopian prime minister, Rohrabacher added concerns from the United States. His letter follows:
July 28, 2014
His Excellency Hailemariam Desalegn
Prime Minister
Federal Democratic Republic of Ethiopia
Office of the Prime Minister
P.O. Box 1031
Addis Ababa, Ethiopia
Dear Mr. Prime Minister,
According to recent news reports, late last month the Ethiopian government arranged for the international kidnapping of opposition leader Andargachew Tsige and his forcible return to your country.
Mr. Andargachew is a British citizen and a leader for political reform in Ethiopia. He should be released and allowed to return to his family immediately. Any maltreatment or harm to him, or other pro-democracy activists, in your country only serves to widen the gap between our two countries.
All legitimate national governments have a responsibility to respect the human rights of their citizens. The current rulers of Ethiopia only continue to isolate themselves by violating the human rights of Ethiopian citizens, especially democratic political leaders. Mr. Andargachew should be released without delay and allowed to return home.
Sincerely,
Dana Rohrabacher
Chairman
Subcommittee on Europe, Eurasia, and Emerging Threats
House Committee on Foreign Affairs

Friday, July 25, 2014

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ደብረዘይት አየር ሃይል ግቢ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው

ሐምሌ ፲፰ (አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሰኔ 18 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ ደብረዘይት በሚገኘው የአየር ሃይል ግቢ ውስጥበአንድ አነስተኛ ክፍል ውስጥ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።


ኢሳት የተለያዩ ምንጮችን አነጋግሮ ባሰባሰበው መረጃ አቶ አንዳርጋቸው በመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ድበደባው ቆሞ፣ የማሰቃያ መርፌዎችን እየተወጉና በኤልክትሪክ ሾክ እየተሰቃዩ መረጃ እንዲያወጡ እየተገደዱ ነው።

መርማሪዎች ከአቶ አንዳርጋቸው የሚፈልጉት መረጃ ከግንቦት7 ጋር በጋራ የሚሰሩ  አሁን በስልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግን አመራሮችን እንዲሁም በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያሉ አዛዦችን ስሞች ሲሆን፣ አቶ አንዳርጋቸው ግን እስካሁን ምንም አይነት መረጃ ባለመስጠታቸው ፣ መርማሪዎች ሲበሳጩ መታየታቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ለወትሮው አንድ መረጃ ሲያገኙ በታላቅ ደስታ የሚፈነጩት መርማሪዎች፣ ምርመራቸውን ጨርሰው ሲወጡ የሚያሳዩት ብስጭት፣ እስካሁን ድረስ የሚፈልጉትን እንዳላገኙ የሚያሳይ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ገልጸዋል።

አቶ አንዳርጋቸው እንዳስፈላጊነቱ በቀን ሶስት ጊዜ ምርመራ እንደሚካሄድባቸው የሚናገሩት ምንጮች፣ ምርመራውን የሚያካሂዱት የተመረጡ የህወሃት የደህንነት ሰራተኞች መሆናቸውንና በግቢው ለበረራ የሚሰለጥኑ የሌሎች ብሄር ተወላጆች ወይም የደህንነት ሰራተኞች ወደ አካባቢው እንደማይሄዱ ገልጸዋል። ምሽት አካባቢ የሚሰማው የጣር ድምጽ የሚረብሻቸው የእለት ተረኛ ጠባቂ መኮንኖች በሁኔታው እያዘኑ አንዳንዶች ስሜታቸውን መቆጣጠር እንደማይችሉ ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

ስለ አቶ አንዳርጋቸው የእለት ውሎ ማወቂያ ብቸኛው ዘዴ የመርማሪዎች ፊት ነው የሚሉት ምንጮች፣ እስካሁን ድረስ ምርመራ በሚያካሂዱ የህወሃት አመራሮች  ዘንድ የደስታ ፊት እንደማይነበብ ገልጸዋል።

የኢህአዴግ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታሰሩበትን ቦታ ይፋ ለማድረግ እስካሁን ፈቃደኛ አልሆነም። የእንግሊዝ ባለስልጣናት ለአቶ አንዳርጋቸው የኮንሱላር የማማከር አገልግሎት ለመስጠት ጥያቄ ቢያቀርቡም ኢህአዴግ ባለስልጣናት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ከዚህ በተቃራኒ ኢህአዴግ በአቶ አንዳርጋቸው እና በግንቦት7 ላይ ለሚሰራው ድራማ ግብአት ይሆን ዘነድ የተለያዩ ሰዎችን ማሰማራቱን ምንጮች ገልጸዋል። ቀደም ብለው በአገዛዙ ለስለላ ወደ ኤርትራ ተልከው እና ለተወሰኑ ወራት ግንቦት7 ትን ተቀላቅለው በመጨረሻ የኢህአዴግ የስለላ አባላት መሆናቸው ሲታወቅ የጠፉ እንዲሁም ፈንጅ ሊያፈነዱ ሲሉ ተያዙ የተባሉ እና በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ለመጠቀም እንቅስቃሴ መጀመሩን ለማወቅ ተችሎአል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ያሳየው ቁጣ ያስደነገጣቸው ደህንነቶች ለማንኛውም በሚል በደንበር አካባቢ ጥበቃቸውን እያጠናከሩ ነው። የአቶ አንዳርጋቸውን መያዝ ተከትሎ ግንቦት7ትን የሚቀላቀሉ ሰዎች መጨመራቸውንም ከድርጅቱ የወጣው መረጃ ያመለክታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቤልጂየም ብራሰልስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ኢህአዴግ አቶ አንዳርጋቸውን ለመያዝ የሄደበትን እርቀት ከማውገዝ በተጨማሪ የእንግሊዝ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ አጥብቆ እንዲከታተል ጠይቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በአውሮፓ ህብረት ቆንስላ ጽ/ቤት ፊት ለፊት የተቃውሞ ድምጻቸውን በከፍተኛ ቁጣ ከማሰማት በተጨማሪ፣ ያዘጋጁትን ደብዳቤ ለአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናትና ለእንግሊዝ መንግስት ኮንስላ ጽ/ቤት ሃላፊዎች አስረክበዋል።

ሁለት ከአማራው ክልል በመጡ የደህነንት የበታች ሃላፊዎች በአቶ ኢሳያስ ጠባቂዎች መገደላቸው ተዘገበ


ባለፈው ማክሰኞ ከምሽት ጀምሮ ቦሌ መስመር ወሎ ሰፈር ከአይቤክ ሆቴል ፊትለፊት ገባ ብሎ ከሚገኘው የደህንነት ቢሮ ውስጥ በተደረገ ስብሰባ ላይ በተፈጠረ የፖለቲካ አለመግባባት ከአቶ ኢሳያስ ወ/ጊ ጠባቂዎች በተተኮሱ ጥይቶች ሁለት ከአማራው ክልል በመጡ የደህንነት የበታች ሃላፊዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን ታውቋል።


በአማራው ክልል ያሉ እና በህግ በተመዘገቡ ፓርቲዎች ሽፋን የህገወጥ ዲያስፖራ ፓርቲዎችን አላማ የሚያራምዱ የተቃዋሚ አመራሮች ላይ ከምርጫው ቀደም ብሎ ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃ ለመወያየት የተሰበሰበው የደህንነት ጓድ በስብሰባው ወቅት ከፍተኛ አለመግባባት ፈጥሮ እንደነበር የታወቀ ሲሆን በወቅቱም ከአዲስ አበባ ከ13 አመት በፊት ተመልምለው ወደ አማራው ክልል የተላኩት በክልሉ ምስጢራዊ የሆኑ የግድያ እና የአፈና እንዲሁም የስለላ መመሪያዎችን በመቀበል ለጽጥታ ሃይሎች በማስተላለፍ ሲያስፈጽሙ እና ሲፈጽሙ የነበሩ እና በደህንነት ኮድ ስማቸው (አለልኝ እና ብቸናው) የተባሉ የደህንነት የበታች ሹሞች እዛው ስብሰባው መሃል በጸጸት እና በብሶት በቁጣ የተሞላ ጠንካራ ጥያቄዎች በማቅረባቸው በተፈጠረ አለመግባባት የማያዳግም እርምጃ እንደተወሰደባቸው ታውቋል።

የሕወሓት የደህንነት ከፍተኛ ሹሞች ምን ያህል በጥጋብ እና በትእቢት እንደተወጠሩ የሚያመለክተው ይህ ግድያ በስብሰባው ላይ ያሉትን የደህንነት ጓዶች ለማሸበር እና ለመጪው ምንም ዓይነት ጥያቄ እንዳያነሱ እና አለመግባባት እንዳይፈጥሩ ለማስደንገጥ የተደረገ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል።

ምንጭ፦ ምኒልክ ሳልሳዊ 

Grand demonstration in Oslo July 14,2014

Furious Ethiopians held demonstration in front of Norway Foreign Minister and UK Embassy about Mr. Andargachew Tsige July 14, 2014 Oslo, Norway

41 organizations call for release of bloggers, jornalists

Thursday, July 24, 2014 @ 09:07 AM ed
Washington, D.C.: Today, Freedom Now joined 40 other human rights and civil society organizationsin a letter to Ethiopian Prime Minister
Hailemariam Desalegn expressing grave concern at the continued targeting of journalists and bloggers on terrorism charges. The letter, also joined by organizations such as Human Rights Watch, Amnesty International, the PEN American Center, and the Committee to Protect Journalists, highlighted the recent terror charges laid against seven bloggers associated with the Zone 9 website (one in absentia) and three independent journalists in Ethiopia.
In calling on the Prime Minister to facilitate the immediate release of those writers detained under the widely-criticized 2009 Anti-Terrorism Proclamation, the letter (below) noted that previous prosecutions under the same law have been found by international institutions, such as the UN Working Group on Arbitrary Detention, to violate Ethiopia’s obligations under international law. In closing, the regional and international organizations urge the Prime Minister to facilitate the immediate release all Ethiopians wrongly detained on terrorism charges and amend the law so that it complies with international human rights standards.
###
Prime Minister Hailemariam Desalegn
Federal Democratic Republic of Ethiopia
Office of the Prime Minister
P.O. Box 1031
Addis Ababa, Ethiopia
24 July 2014
Re: Detained Journalists and Bloggers
Dear Prime Minister Hailemariam Desalegn,
We write to you to express our grave concern regarding the terrorism charges laid against seven bloggers associated with the “Zone 9” website and three independent journalists in Ethiopia. Ethiopia is a party to the International Covenant on Civil and Political Rights and the African Charter on Human and Peoples’ Rights—which both expressly protect the right to freedom of expression. We therefore urge your government to fulfill its obligations under international law and release all individuals who have been arbitrarily detained in violation of their fundamental rights.
As you may be aware, six of the bloggers (Zelalem Kibret, Atnaf Berahane, Natnael Feleke, Mahlet Fantahun, Befeqadu Hailu, and Abel Wabela) and the three journalists (Tesfalem Waldyes, Asmamaw Hailegeorgis, and Edom Kassaye) were arrested in late April, shortly after it was announced that the Zone 9 website would resume its activities after suspending operations because of increasing harassment and surveillance. All nine detainees were subsequently held for nearly three months before any specific allegations were presented or formal charges filed against them. Most concerning, however, are reports that some of the detainees have complained of serious mistreatment by investigators and that defense lawyers and their clients have been excluded from some of the proceedings.
Recent reports now indicate that the detained bloggers and journalists have been charged under the widely-criticized 2009 Anti-Terrorism Proclamation, including provisions that provide for the death penalty, in addition to charges of committing “outrages against the constitution.” A seventh blogger, Soleyana Shimeles, was also charged in absentia. In accordance with the requirements of both Ethiopian and international law, we call on you to ensure that all allegations of torture or other forms of ill-treatment are promptly investigated and that no statements obtained through such means are admitted in court. Further, we call on you to ensure that the detainees have full access to the assistance of legal counsel and that the proceedings related to this case are open to the public, the media, and members of the diplomatic community.
Unfortunately, these prosecutions are only the most recent example of a worrying pattern. Outspoken Ethiopian journalists Eskinder Nega, Reeyot Alemu, and Woubshet Taye have all received long prison terms under the 2009 Anti-Terrorism Proclamation, in trials marred by procedural flaws. Similarly, opposition activists including Andualem Arage have received sentences of up to life imprisonment on such grounds.
While your office has asserted that the prosecution of these individuals is unrelated to their work as journalists, independent inquiries have found that this is not the case. For example, the United Nations Working Group on Arbitrary Detention held that the imprisonment of Mr. Nega violated Ethiopia’s obligations under international law and requested his immediate release. In addition to procedural violations, the Working Group found that the detention of Mr. Nega resulted directly from his exercise of free expression and that the overly broad offenses established by the 2009 Anti-Terrorism Proclamation constituted “an unjustified restriction on expression rights and on fair trial rights.” Despite such a finding, however, Mr. Nega remains in prison.
Other international bodies have similarly criticized your country’s Anti-Terrorism Proclamation for being overly broad and a tool through which freedom of expression is limited. The African Commission on Human and Peoples’ Rights adopted a resolution in 2012 stating that it was “gravely alarmed by the arrests and prosecutions of journalists and political opposition members, charged with terrorism and other offences, including treason, for exercising their peaceful and legitimate rights to freedom of expression and freedom of association.” This message reinforced an earlier statement by five United Nations special procedure mandate holders, including the Special Rapporteur on Counter-Terrorism and Human Rights, which expressed their “dismay at the continuing abuse of anti-terrorism legislation to curb freedom of expression in Ethiopia.” During Ethiopia’s Universal Periodic Review earlier this year, similar concerns were raised by a number of countries, including security allies of Ethiopia such as the United States of America.
Despite these clear findings that the targeting of writers under the 2009 Anti-Terrorism Proclamation is inconsistent with Ethiopia’s international obligations, prosecutors have now charged the seven Zone 9 bloggers and three independent journalists under that very law. As a result, they face exceedingly long prison sentences or even death. Such a practice violates international law and threatens to undermine the legitimacy of international security efforts in the region.
In light of these serious concerns, we urge you to facilitate the immediate release of all journalists and bloggers imprisoned under the 2009 Anti-Terrorism Proclamation and to revise the Proclamation to comply with regional and international human rights standards.
Sincerely,
1.    Amnesty International
2.    ARTICLE 19 Eastern Africa
3.    Central Africa Human Rights Defenders Network (REDHAC), Central Africa
4.    CIVICUS: World Alliance for Citizen Participation
5.    Civil Rights Defenders, Sweden
6.    Coalition pour le Développement et la Réhabilitation Sociale (CODR UBUNTU), Burundi
7.    Committee to Protect Journalists
8.    Community Empowerment for Progress Organization (CEPO), South Sudan
9.    Conscience International (CI), The Gambia
10.    East and Horn of Africa Human Rights Defenders Project
11.    Egyptian Democratic Association, Egypt
12.    Electronic Frontier Foundation
13.    Ethiopian Human Rights Project (EHRP)
14.    Elma7rosa Network, Egypt
15.    English PEN
16.    Freedom Now
17.    Front Line Defenders, Dublin
18.    Human Rights Watch
19.    International Women’s Media Foundation (IWMF)
20.    Ligue des Droits de la personne dans la region des Grands Lacs (LDGL), Great Lakes
21.    Ligue Iteka, Burundi
22.    Maranatha Hope, Nigeria
23.    Media Legal Defence Initiative
24.    National Civic Forum, Sudan
25.    National Coalition of Human Rights Defenders, Kenya
26.    Niger Delta Women’s movement for Peace and Development, Nigeria
27.    Nigeria Network of NGOs, Nigeria
28.    Paradigm Initiative Nigeria, Nigeria
29.    PEN American Center
30.    PEN International
31.    Réseau africain des journalistes sur la sécurité humaine et la paix (Rajosep), Togo
32.    Sexual Minorities Uganda (SMUG), Uganda
33.    South Sudan Human Rights Defenders Network (SSHRDN), South Sudan
34.    South Sudan Law Society, South Sudan
35.    Tanzania Human Rights Defenders Coalition, Tanzania
36.    Twerwaneho Listeners Club (TLC), Uganda
37.    Union de Jeunes pour la Paix et le Développement, Burundi
38.    WAN-IFRA (The World Association of Newspapers and News Publishers)
39.    West African Human Rights Defenders Network (ROADDH/ WAHRDN), West Africa
40.    Zambia Council for Social Development (ZCSD), Zambia
41.    Zimbabwe Human Rights NGO Forum, Zimbabwe

Thursday, July 24, 2014

ለብሔራዊ አንድነትና ነፃነት – ህወሓትን ከትግራይ ሕዝብ መነጠል!!!

በአለፉት ጥቂት ሣምንታት በወያኔ የተፈፀሙ የእብደት ተግባራትን ስናጤን ከፊት ለፊት ኢትዮጵያችንን እየጠበቀ ያለው መንታ መንገድ አመላካች ነው። ይህ ከፊት ለፊት የሚጠብቀን መንታ መንገድ አንዱ ወደ ብሔራዊ አንድነት፣ ነፃነትና ብልጽግና ሌላው ወደ እርስ በርስ ትርምስና ውድቀት የሚያመሩ ናቸው። የአንድነት፣ የነፃነትና የብልጽግና መንገድ ለመያዝ መስመራችንን ማስተካከል ያለብን ከአሁኑ ነው።
ለመሆኑ ከላይ ያልነውን ለማለት ያስቻሉን በአለፉት ጥቂት ሣምንታት በወያኔ የተፈፀሙት ተግባራት ምንድናቸው?
አንደኛ፤ ወያኔ፣ ዓለም ዓቀፍ ህግንና ሥርዓትን በጣሰ መንገድ ከየመን ባለሥልጣናት ጋር በማበር የንቅናቄዓችንን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ማፈኑ በአለፉት ጥቂት ሣምንታት ውስጥ ውስጥ የተደረገ አብይ ክስተት ነው። ይህ የወያኔ የውንብድና ተግባር ኢትዮጵያዊያንን በእጅጉ አስቆጥቷል። ወያኔ፣ ለሀገር ነፃነትና ለእኩልነት የሚታገልን አንድ ታላቅ ሰውን ማፈንኑና ከእይታ ከልሎ እያሰቃየው መሆኑ በሕዝቡ ውስጥ ያለው ቁጣ ወደ መገንፈል አስጠግቶታል። አቶ አንዳርጋቸው በጠላት እጅ ከወደቀም በኋላ ኢትዮጵያዊያንን አሰባሳቢ ኃይል ሆኗል።
ሁለተኛ፤ ሰላምተኞቹን ብሎገሮችንና ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት በመክሰስ በቋፍ ላይ የነበረውን የወጣቶች ትዕግሥት እንዲሟጠጥ አድርጓል። ስለኢንተርኔት አጠቃቀምና ጥንቃቄ ሥልጠና መውሰድ በክስ ቻርጁ ውስጥ መካከቱ ሥርዓቱ ከእውቀት ጋር የተጣላ መሆኑ በግልጽ አሳይቷል። ከዚህም በተጨማሪ በህጋዊ ፓርቲዎች ውስጥ በንቃት የሚሳተፉ ወጣት መሪዎችን መርጦ በማሠርና በሽብርተኝነት በመወንጀል የወያኔ የአፈና መዋቅር ወጣቱ ላይ ማነጣጠሩ ግልጽ ሆኗል።
ሦስተኛ፤ እጅግ ሰላማዊና ጨዋነት በተሞላበት መንገድ አቤቱታቸውን በማቅረብ ላይ የነበሩትን ሙስሊም ወገኖቻችንን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በመደብደብ እና በጅምላ በማሠር በወያኔ መድብለ ቃላት ውስጥ “ሰላማዊ ትግል” የሚባል ነገር አለመኖሩ፤ ተቃውሞ ሁሉ “ሽብር” እንደሚባልና በሽብርተኝነት እንደሚያስከስስ በማያሻማ ሁኔታ አረጋግጧል። ይህም የሥርዓቱ አውሬዓዊ ባህሪ መገለጫ ሆኗል።
አራተኛ፤ አፈናውና እስሩ ወደ ትግራይም በመዛመቱ ወያኔ የቆመበት ምድር እየራደ መሆኑ አመላካች ሆኗል። ትግራይ ውስጥ የነበረው አፈና ድብቅ የነበረ ከመሆኑም በላይ ከወያኔ የውስጥ ሽኩቻ ጋር ሲያያዝ ቆይቷል። አሁን ግን ሁኔታዎች እየተቀየሩ ነው። አገራዊ ርዕይ ያነገቡ፤ ወያኔን በጽናት ለመታገል የቆረጡ የትግራይ ወጣቶች ወደፊት እየመጡ ነው። እነዚህ ወጣቶች የተጫነባቸውን ድርብርብ ጫና በመበጣጠስ ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጎን መቆማቸውን በተግባር እያረጋገጡ፤ ለዚህም መስዋዕትነት እየከፈሉ ናቸው።
ከላይ የተዘረዘሩት አራት ጉዳዮች በጋራ ሲታዩ የተበታተነ የሚመስለው እና በተለያዩ ስልቶች የሚደረገው ትግል የሚሰባሰብበትና የሚቀናጅበት ወቅት ላይ መደረሱ አመላካቾች ናቸው። ዛሬ የምንገኘው የተለያዩ የትግል ስልቶች እንዲናበቡና እንዲደጋገፉ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ የሆነበት ወቅት ላይ ነው።
በተለይም ወያኔ፣ መሸሸጊያ ምሽጉ አድርጎ በሚቆጥረው ትግራይ ውስጥ እየዳበሩ የመጡት የአመጽም አመጽ-የለሽ ትግሎችም አስተዋጽኦ ከፍተኛነት ሌላው ኢትዮጵያዊ እንዲረዳ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ተግባር ነው። የወያኔ የአፈናና የመጨቆኛ መዋቅሮች የህወሓት አባላት በሆኑ የትግራይ ዘውጌ ማኅበረሰብ አባላት የሚዘወሩ መሆኑ እውነት ነው። ይህ ማለት ግን ህወሓት የትግራይ ሕዝብ ወኪል ወይም ጠበቃ ነው ማለት አይደለም። ትግላችን ከወያኔ ፋሽስታዊ አገዛዝ ጋር መሆኑ እና የትግራይ ሕዝብ የዚህ ትግል አጋር፣ የውጤቱም ተጠቃሚ መሆኑ ማስረገጥ ተገቢ ነው።
ከፊት ለፊታችን ካሉት መንታ መንገዶች መካከል የአንድነትን፣ የነፃነትና የብልጽግናን መንገድ ለመምረጥ የትግራይ ሕዝብ በስፋት ትግሉን እንዲቀላቀል ማድረግ ተገቢ ነው። ትግራይ የህወሓት የግል ጓዳ መሆኗ የማብቂያ ጊዜ ማፋጠን ይቻላል። በዲሞክራሲያዊ ትግል ውስጥ ያሉ ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ የጋራ ግንዛቤ ከያዙ ወያኔን ማንሳፈፍ የሚቻልበት እድል በስፋት ተከፍቷል።
ስለሆነም፣ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዘረኛውና ፋሽስታዊው ህወሓትን ከትግራይ ሕዝብ መነጠል አንዱ የትግላችን ስትራቴጂ ሊሆን ይገባል ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Saturday, July 19, 2014

ወይንሸት ሞላ ክፉኛ ተደብድባ ዝግ ችሎት ቀረበች!

በትላንትናው እለት አንዋር መስጊድ ህዝበ ሙስሊሙ ሲደበደብ ወይንሸት ሞላ በስፍራው ነበረች። አንድ ከዚህ በፊት የሚያውቃት የደህንነት አባል በቀጥታ ወደሷ መጥቶ ይደበድባት ጀመር። በወቅቱ በስፍራው የነበረው በፍቃዱ ጌታቸው ስለሁኔታው እንዲህ በማለት ጽፎ ነበር።

በወቅቱ የሰማያዊ ፓርቲ የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆነችው ወጣት ወይንሸት ሞላ አብራኝ ነበረች፡፡ አንዋር መስጊድ በወንዶች መግቢያ ፊት ለፊት ካለው ህንጻ ላይ ሆነን ሁነቱን ስንከታተል ከአሁን ቀደም የሚያውቃትና ከህንጻ ላይ ሆኖ ሲቀርጽ የነበር ደህንነት ብቻዋን ነጥሎ እየደበደበ ወሰዳት፡፡  ‹‹ለምን ተወስዳታለህ!›› ብዬ በጠየኩበት ወቅት ከእነዛ ከመንገድ ተለቃቅመው ለድብደባ የተሰማሩት ወጣቶች መካከል አንዱ ሽጉጥ አወጣብኝ፡፡ ለመሳሪያ ልምድ የሌለው በመሆኑ ካርታው እግሩ ስር ወደቀበት፡፡ ወይንሸትን ይዘውም ወደ ውጭ ከነፉ!
ወይንሸት ሞላ
ወይንሸት ሞላ
ዛሬ ፍርድ ቤት ይዘዋት ቀርበዋል። ሁኔታውን የተከታተለው ዮናታን ተስፋዬ የታዘበውን እንዲህ በማለት ነው ያቀረበው። “እጇቿ ክፉኛ ተጎድተዋል፡፡ ጣቷ አብጧል፡፡ ፊቷ ገርጥቷል፡፡ የግራ እጇ በፋሻ ተጠቅልሎ አንገቷ ላይ እንደታሰረ በአንድ ፖሊስ እርዳታ ወደ ፍርድ ቤቱ ግቢ ገብታለች፡፡” ብሎ ነበር። ጥቂት ቆይቶ ባስተላለፈው መልእክት ደግሞ “ወይንሸት ጭንቅላቷን በቀኝ በኩል ተፈንክታለች፡፡ ተሰፍቶ ይታያል፤ ቀኝ እጇ መሰበሩ ተረጋግጧል፡፡ ሰውነቷ በጣም መጎዳቱ ያስታውቃል፡፡ ከፍርድ ቤት መልሰው አዲስ አበባ ፖሊስ ከሚሽን ወስደዋታል፡፡ ማንም እንዲያያት አልተፈቀደም የፍርድ ሂደቱንም ማንም መከታተል አልቻለም፡፡ ስንቅ ማቀበልም ተከልክሏል፡፡” በማለት ሁኔታውን አስረድቷል።
አሁን በደረሰን ዘገባ መሰረት በዝግ ችሎት የቀረበችው ወይንሸት ሞላ 14 ቀን ተጨማሪ ምርመራ ተጠይቆባት፤ 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባታል፡፡ የፍርድ ቤቱን ሂደት ማንም ሰው እንዲከታተል አልተፈቀደም የህግ ሰውም እንዳያናግራት ተከልክሏል፡፡  አሁን ከማዕከላዊ አጠገብ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ነች፡፡ የፖሊስ ጣቢያው ኃላፊዎች ማንም ሰው ሊያያት እንደማይችልና ስንቅም ሆነ ልብስ ላልተወሰነ ቀናት እንዳይመጣ በማለት መልሰውናል፡፡
አሁን ያለው ሁኔታ ይህን ይመስላል። ትንሽ ቆይተው እሷንም አሸባሪ ብለው መክሰሳቸው የማይቀር ነው። ሌላ የሽብር ክስ ከመስማታችን በፊት፤ ትክክለኛውን ነገር ከወዲሁ እንዲረዱት፤ ወይንሸት ሞላ ወደ አንዋር መስጊድ ከመሄዷ በፊት አግኝቷት የነበረው ዮናታን ቀደም ብሎ የዘገበውን እናስነብብዎ። እንዲህ በማለት ጽፎ ነበር።
ወይኒ ትናንት ጠዋት ላይ ቢሮ ቁጭ ብዬ ከላፕቶፕ ላይ እንደተደፋሁ መግባቷንም ሳላስተውል . . .
“እዚህ አፍንጫችን ስር ይህን የመሰለ ሰላማዊ ትግል ሲካሄድ ቢያንስ ሄደን አንታዘብም!? እዚህች መርካቶ አጠገብ ተቀምጠን ዘመን እየተጋራን – ታሪክ እየተጋራን . . .” ስትል ቀና ብዬ አየኋት።  . . . ምንም ማለት አልደፈርኩም. . . ለብዙ ጊዜ አንዋር መስጂድ እሄድ ነበር (በተለይ ባለፈው ዓመት)  የግልና የፖለቲካ ስራ ጊዜ አይሰጥም እንጂ አሁንም ብገኝ ምኞቴ ነው ፤ ሰው በጨካኞች ተከቦ ለመብቱ በፅናት ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ሲጮህ መመልከት በራሱ ትልቅ መነቃቃት እና ተስፋ ይሰጣል፡፡
ወይኒን ተረዳኋት ግን ሰጋሁ፡፡ ምክንያቱም ወይኒ ቀጥተኛ ሰው ነች . . . የሰው ጥቃት አትወድም . . . ሰው ሲበደል እያየች ዝም የሚል አፍ አልፈጠረባትም . . . ትናገራለች በጣም ተቆጥታ ትናገራለች . . . እንኳን በቆመጥ ሲደበደቡ እያየች በክፉ ሲታዩም ይተናነቃታል . . . ከእንባዋ እየተናነቀች ምራቋን ውጣ ትናገራለች . . . ወይኒ እንዲህ ነች . . . ምናልባትም ይህ ተቆርቆሪ ስብዕናዋ ይሆናል ሰማያዊ ፓርቲ ከትማ ያገናኘን፡፡ እናም ሰጋሁ፡፡
እንጃ ቀልቤ የሆነ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል አስቀድሞ አሳወቀኝ መሰል . . .  “ምንም እኮ አዲስ ነገር አይፈጠርም I’ve been there, you know, it’s all the same every Friday” ከልቤ አልነበረም …
“መርካቶ ጉዳይ አለኝ በዛው ሙስሊም ወገኖቼን አየት አየት አድርጌ እመለሳለሁ” ከነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ሽፈራዉ ጋር እንደምትሄድ ነግራን ሄደች። ጌች ተደብድቦ ሲመለስ እሷ በዛው ቀረች . . . የፈራሁት ሆነ የህወሓት ካድሬዎች እንደሚጠሏት አውቃለሁ፤ ግን ፅናቷ ያፅናናኛል፡፡
ጎንደር አብረን ታስረን የማይረሳ ትዝታ ቀርፃብኝ ነበር . . . የሳዑዲ መንግስትን ተቃውመን አደባባይ ስንወጣ ሶስት ጨካኝ ፌደራሎች ብቻዋን ደብድበዋት ኢያስፔድ ታቅፎ ከወደቀችበት ነጥቆ አስጥሏት ሮጦ ከጨካኞች ሲያመልጥ እንኳን በደከመ ሰውነቷ ወደ ተቃውሞው ለመመለስ ፍላጎት ነበራት . . . ማርች 9 የሴቶች ሩጫ ጊዜ ከጣይቱ ልጆች ጋር ከፊት ሆና እየመራች የህወሓት ደህንነቶች አይን ውስጥ መግባቷ በምርመራ ወቅት ለረጅም ሰዓት ያቆዩአት ነበር . . .
የሆነ ሆኖ የወይንእሸት ሞላ ዛሬ በእጃቸው ድጋሚ ገብታለች . . . በመጥፎ ሁናቴም ተደብድባ ተጎድታለች፡፡ ደስተኛ እንደሆነች ግን ውስጤ ይነግረኛል . . . እሷ ነፃ ነች የውስጧን ጥያቄ መልሳ ሰላም አግኝታለች፡፡
በርካታ ሙስሊም ወገኖቻችንም ይህ ሰላምና እርካታ በመከራና በእስር ውስጥ ሆነው እንደሚሰማቸው አምናለሁ፡፡ ለእውነት በፍቅርና በይቅርታ የቆሙ አይወድቁም ነብዩም መሲሁም ያስተማሩን ይህን ነው!!! በርቱ!” በማለት ነበር የትላንቱን ውሎ የገለጸው። ዛሬ ደግሞ ሌላ ቀ ነው፤ ወይንሸት ክፉኛ ተጎድታ ጉዳይዋ በዝግ ችሎት ታየ። መልሰውም ወሰዷት። እኛም መጨረሻዋን ሰላም ያድርገው፤ በማለት እንሰናበታለን።

ከእስሩም በላይ - “ሽብርተኝነት”

እስረኞቹ በሽብር መከሰሳቸውን አያውቁም
ጽዮን ግርማ
tsiongir@gmail.com
አንድ ዓመት ከአንድ ወር ኾኖታል፡፡ እስክንድር ነጋ ከታሰረ ከዐስራ ስምንት ወራት በኋላ ከባለቤቱ ከጋዜጠኛ
ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ከናፍቆት በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ሌላ ሰው እንዲጠይቀው በሰኔ የመጀመሪያ
ወር ላይ በ2005 ዓ.ም እንደተፈቀደለት ነው፡፡ በወቅቱም እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ወደሚገኘው እስር
ቤት አምርቼ ነበር፡፡

ተገናኝተን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላም እንዲህ አለኝ፤‹‹ሽብርተኛ አይደለኹም፤ሀገሬ በማንም እንድትሸበር
አልፈልግም አልፈቅድምም እኔ የምፈልገው የሀገሬ ሕዝቦች በነጻነት የሚያስቡባትና የሚንቀሳቀሱባት ሰላማዊ
ሀገር እንድትኾን ነው››፤እስክንድር ‹‹ሽብርተኛ›› አይደለምና ከእስሩም በላይ ያንገበገበው ‹‹አሸባሪ›› መባሉ
ነበር፡፡

እስክንድር ‹‹ጋዜጠኛ›› ነው፡፡ እስክንድር ሲጽፍ ሀገሪቱ ላወጣችው ሕግ ራሱን አስገዝቶ፣በሀገሪቱ ሕግ
ማዕቀፍ ሥር ራሱን ገድቦ ነው፡፡ ይህም ኾኖ ግን ሲጽፍ ሕግ ተጥሶ አደጋ ሊደርስበት እንደሚችል፣ሲጽፍ ሕግ
ተጥሶ ሊታሰር እንደሚችል ያውቃል፡፡ ግን ደግሞ ቢታሰር በቀጫጭን መስመርም ቢኾን በሀገሪቱ ሕግ ተዳኝቶ ከእስር ሊለቀቅ
እንደሚችል ያምን ነበር፡፡በዚህ እምነቱም የመጣበትን ለመቀበል ተዘጋጅቶ ሀገሩ ላይ ቁጭ ብሎ ይጽፋል፡፡

ከመጻፍ እና ሐሳቡን በአደባባይ ከመግለጽ ውጭ ያሉት መንገዶች እስክንድርን አይመቹትም፡፡ እስክንድር ሐቀኛና ቀጥተኛ የኾነ
አስተሳሰብ ያለው ላመነበት ነገር የታመነ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ምናልባት ይህን ‹‹እስክንድርን›› ለመረዳት እስክንድርን ማወቅ
ሊጠይቅ ይችላል፡፡ እስክንድርን ያኔ ቃሊቲ ሳገኘው ሽብርተኛ አለመኾኑን ደጋግሞ ነገረኝ፡፡ ‹‹እስክንድር ለማነው የምትነግረው ሽብርተኛ አለመኾንህን ከቀረበብህ ክስ ጋር አንዳችም ግንኙነት እንደሌለህ እኮ ዓለም ያውቃል፤አሳሪዎችህም ይህን ጠንቅቀው ያውቃሉ›› አልኩት፡፡

እርሱን ግን ያበሳጨው ከታሰረውም፣ከተንገላታውና ከተፈረደበትም በላይ በውሸት የተወነጀለበት “ሽብርተኝነት’’ ነበር፡፡
አሁንም ሽብርተኝነት አሁን እስክንድር ከታሰረ ሁለት ዓመት ከሰባት ወር ኾኖታል በእርሱ የተጀመረው ጋዜጠኛን፣ጸሐፊዎችንና መብቱን በአደባባይ የሚጠይቀውን ሁሉ ሰብስቦ ‹‹ሽብርተኛ›› ብሎ መክሰስ ዕለት በዕለት እየጨመረ የታሳሪዎቹን ቁጥር አበራክቷል፡፡ ላለፉት ሰማንያ ሦስት ቀናት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ታስረው የሚገኙትና በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ በቀጠሮ ሲመላለሱ የቆዩት ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስና፣ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ የሕግ መምሕርና የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ዘለዓለም ክብረት፣ የዞን ጦማሪዎቹ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃኑ ለቅዳሜ ሐምሌ 5 ቀን የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎቹ ማኅሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ኃይሉና አቤል ዋበላ በዚሁ በፈረደበት
‹‹ሽብር›› ተጠርጥረው የታሰሩ ናቸው፡፡

የምርመራ መዝገቡ በሌሉበት መዝገቡ ተዘግቶ ከሕግ ውጪ በእስር የከረሙት እነዚህ እስረኞች ግንቦት ዘጠኝ በነበረው ቀጠሮ
ቀን ፖሊስ ፍርድ ቤት ቀርቦ ተጠርጣሪዎችን በሽብር መጠርጠሩን ሲናገር ወጣቶቹ በድንጋጤ አንገታቸውን ሲሰብሩ ታይተው
ነበር፡፡ የሚያስደነግጠው እስሩ አይደለም ሕግን አስከብራለሁ የሚል አንድ ተቋም ወጣቶችን ሰብስቦ አስሮ ባልዋሉበት
የሚያውል የፈጠራ ክስ ሲጭን መስማቱ ነው፡፡ማንነቱን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው እንዲህ ያለ የውሸት ክስ ሲቀርብበት
የሚሰማውን ስሜት ለመገመት ያስቸግራል፡፡ እናም ወጣቶቹ በሽብር ተግባር አለመሳተፋቸውን ያውቃሉና የቱንም ያህል
ኢሕአዴግን ባህሪ ጠንቅቀው ቢያውቁት ‹‹በሽብር እንከሰሳለን›› የሚል ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ ሊኖራቸው አይችልም፡፡
ምናባት የመጨረሻውን ጣሪያ ቢገምቱ እነርሱን አስሮ ሌሎች ጸሐፊዎችን ለማስፈራራት የተነደፈ ስልት ይኾናል ከሚል
ግምታዊ መላምት ‹‹ምርጫው እስኪያልፍ ታስረን እንቆያለን›› የሚለውን ነው፡፡ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ዛሬ ጠዋት ልደታ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ሲቀርቡም ከዚሁ ሐሳብ ሊኖራቸው እንደማይችል እገምታለሁ፡፡

ወጣቶቹ ከታሰሩ ጀምሮ ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ጠበቃ፣ቤተሰብና ሌሎች ሰዎች ከትናንት ጀምሮ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ይችላሉ በሚል ይቀርቡበታል በተባለው ፍርድ ቤት ግቢ ክትትል ሲያደርጉ ቢቆዩም ዛሬ ጠዋት ማንም ሰው ባልተገኘበት ዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ከፍቶባቸዋል፡፡ ነገር ግን የክስ ቻርጁ እንዲሰጣቸውና መቃወሚያ ካላቸው እንዲናገሩ ተጠይቀው ዘጠኙም እስረኞች ጠበቆቻቸው ባልተገኙበት ክሱ እንዲነበብላቸው እንደማይፈልጉ ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነትን አግኝቶ ጠበቆቻቸው በተገኙበት ነገ ጠዋት እንዲቀርቡ ታዟል፡፡ በሌላም በኩል ዛሬ ጠዋት እስረኞቹን ለመጠየቅ ማዕከላዊ ሄደው የነበሩ ቤተሰቦችና ጠያቂ ወዳጆች መግባት እንደማይችሉ ተነግሯቸው ተመልሰው ነበር፡፡ ከሰዓት በኋላም ሊጠይቋቸው በሄዱ ጊዜ ስለተከሰሱት ክስ የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ አብዛኞቹም (አብዛኞቹ ስል ስለ አስተያየታቸው መረጃ ያገኘኹት ማለቴ ነው) በሽብርተኝነት እንከሰሳለን የሚል እምነት አልነበራቸውም፡፡ነገ የሚኾነውን ለማየት በይደር አቆይተው ቤተሰቦቻቸውን ተሰናብተው ወደ ማደሪያቸው ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል፡፡

የሽብርተኝነት ክሱ የሪፖርትር ጋዜጣ ዘጋቢ ታምሩ ጽጌ ደግሞ ሰበር ዜና በሚል በጋዜጣው ድረ ገጽ ላይ፤ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት)፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ አቤል ዋበላ፣ እንዲሁም ጋዜጠኞቹ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሣዬና ተስፋለም ወልደየስ ላይ ዐቃቤ ሕግ በሽብርተንነት ክስ መመስረቱን አስነብቦናል፡፡

ዜናው እንደሚለው፤ ተጠርጣሪዎቹ በሕቡዕ በመደራጀት፣ የአጭርና የቅርብ ጊዜ ግብ በማቀድና በመንደፍ ከግንቦት 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እጃቸው እስከተያዘበት ጊዜ ድረስ በፓርላማ ሽብርተኛ ተብለው ከተሰየሙት የግንቦት 7 እና የኦነግ ድርጅቶች መመርያና ሐሳብ ሲቀበሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡ ከተጠርጣሪዎቹ አንዷ የሆነችው ሶሊያና ሽመልስ የቡድኑ መሥራችና አስተባባሪ በመሆን ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. መቆየቷና ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ በውጭ አገር አስተባባሪና የውጭ ግንኙነት ሆና ከመሥራቷም በተጨማሪ፣ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በማደራጀትና በመመልመል ስትሠራ መቆየቷን ክሱ ያስረዳል፡፡የህቡዕ ቡድኑ ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. ‹‹ሴኩሪቲ ኢን ቦክስ›› የተባለ ሥልጠና እንዲሠለጥንና እንዲደራጅ ስትመራ መቆየቷም በክሱ ተካቷል፡፡

ሌላኛው ተጠርጣሪ በፍቃዱ ኃይሉ የአገር ውስጥ የሽብር ቡድንን በመምራትና የሥራ ክፍፍል በማድረግ፣ እንዲሁም ግብ በማስቀመጥና ስትራቴጂ በመንደፍ ከሽብርተኛ ኃይሎች ጋር ግንኙነት ሲፈጥር መቆየቱ በክሱ ተጠቅሷል፡፡
የዓቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው ከሆነ ተጠርጣሪ ናትናኤል ፈለቀ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን የህቡዕ ድርጅቱ የአገር ውስጥ አስተባባሪ በመሆን በሥሩ ላሉት አባላት የሥራ ክፍፍል መመርያ በመስጠት፣ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት በመፍጠር መመርያ ከመቀበሉ በተጨማሪ፣ ለአመፅ ተግባር የሚውል የተላከለትን 48,000 ብር ማከፋፈሉንም ክሱ ያብራራል፡፡

ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች በህቡዕ ድርጅቱ ውስጥ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ መሥራችና አባል በመሆን የግንቦት 7 እና የኦነግን ስትራቴጂና ዕቅድ በመቀበል በውጭና በአገር ውስጥ ባሉ የቡድኑ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ በውጭና በአገር ውስጥ ሥልጠና በመውሰድ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈጸም በማቀድ፣ በመዘጋጀት፣ በማሰርና በማነሳሳት ወንጀል መከሰሳቸውን ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ክስ ያስረዳል፡፡

በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ሁለተኛ ክስ እንደሚያስረዳው ተጠርጣሪዎቹ በወንጀሉና በሚያስገኘው ውጤት
ተስማምተው በሕገ መንግሥት ሥርዓት የተቋቋመን መንግሥት በአመፅ፣ በሁከትና በብጥብጥ ለመለወጥ በማሰብ ከግንቦት 2004 ዓ.ም. እስከተያዙበት ዕለት ድረስ በህቡዕ ተደራጅተው፣ የሥራ ክፍፍል በመፍጠር፣ ሥልጠናዎችን በመውሰድ፣ አመፅ የሚቀሰቅሱ ጽሑፎችን በመበተን፣ የአመፅ ቡድኖችን በማደራጀት ሕገ መንግሥቱና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመፅና በሁከት ለመለወጥ በመሞከር ወንጀል መከሰሳቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

በመጨረሻ ይህን ክስ የሰማ ማንም ሰው እነዚህ ወጣቶች ሽብርተኛ አለመኾናቸውን እንደሚረዳው ኹሉ ከሳሻቸው ዐቃቤ ሕግም የውሸት ክስ እንደመሰረተባቸው ልቦናው ያውቀዋል፡፡ በተለይ ደግሞ ወጣቶቹን በቅርበት ለሚያውቃቸው ሰው በእነሱ ላይ እንዲህ ያለ ክስ ሲመሰረትባቸው ምን ዐይነት ስሜት እንደሚፈጥር ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡ጠንካራና ሀገር ወዳድ ወጣቶች በሽብርተኝነት
ሲከሰሱ መስማት የሚፈጥረውን ቁጭት ከቃላትም በላይ ነው፡፡ይህ ስሜት እነርሱ ላይ ሲደርስ ምን ሊኾን እንደሚችልምመገመት ያስቸግራል፡፡ እስክንድርን ከመታሰሩም በላይ ያስከፋው እንኳን ክፉ ሊያደርስባት ክፉ እንዳይነካት ቀን ከሌሊት
የሚጸልይላትን የሚወዳትን ሀገሩን ገንዘብ ተቀብለህ ልትበጠብጣት ነው መባሉ ነበር፡፡

‹‹ዴሞክራሲያዊነቷ›› የታወጀላት ታሀገር ስትበደል ሕግ በሚፈቅድላቸው መሰረት ተቃውሟቸውን በጹሑፍ ያሰሙ፣ለሀገሪቱ
ሕግ ራሳቸውን አስገዝተው የጋዜጠኝነት ሥራን የሠሩ በሽብርተኞች እጅ የወደቁ እንጂ ‹‹ሽብርተኛ›› ያልኾኑት ወጣቶች ነገ
ጠዋት በሽብርተኝነት መከሰሳቸውን ሲሰሙ ምን ይሉ ይኾን? 

ሀገር የኮምፒዩተር ቫይረስና ሀከር ነው እንዴ? 

ከዓመታት በፊት የቅንጅት አመራሮች፣ጋዜጠኞች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት አባሎችና ሌሎች ሰዎች ተከሰው ፍርድ ቤት
ሲቀርቡ ‹‹የቅንጅት አመራሮች የፍርድ ቤት ውሎ›› በሚል ርእስ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ተከታታይ ዘገባ አቀርብ ስለነበር ችሎቱ
እስኪጠናቀቅ አንድም ቀን ከፍርድ ቤት ቀርቼ አላውቅም ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ክሱና የክርክር ሂደቱ ምን እንደሚመስል
መናገር የሚያስችል መረጃ አለኝ ለማለት እደፍራለሁ፡፡

በወቅቱ ዐቃቤያነ ሕግ ሽመልስ ከማል፣አብርሃም ተጠምቀና ሚካኤል ተክሉ (እንዲሁም በስነ ምግባር ጉድለት ከዳኝነት ተባሮ
ዐቃቤ ሕግ የኾነ ሰኢድ መሐመድ የተባለ ዐቃቤ ሕግ ነበር በኋላ መምጣት አቆመ) ‹‹ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ
ሥርዓቱን በኃይል ለማፍረስና ሀገሪቱን ለማተራመስና ለማናወጥ ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል›› የሚል የሀገር ክህደት ክስ ይዘው
ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የክስ ቻርጁ ይዘትና የተጠቀሱት አንቀፆች የሞት ፍርድን ጭምር የያዙ ስለነበሩ ለማሰብ የሚከብዱ እጅግ
አስፈሪ ነበሩ፡፡

ተጠርዘው በማስረጃነት የቀረቡት ሰነዶችም የገጽ ብዛት ለሸክም የከበዱ ስለነበሩ የታደላቸው ዕለት ‹‹ምን ተገኝቶባቸው
ይኾን?እነዚህ ሰዎች ዘንድሮ አለቀላቸው›› በሚል ስጋት ውስጥ ያልገባው ሰው አልነበረም፡፡ ነገር ግን የሰነድ ማስረጃዎቹ
ፓርቲው በግልጽ ሲሰጣቸው የነበሩ ጋዜጣዊ መግለጫዎች፣የፓርቲው ግልጽ ማኒፌስቶ፣በግልጽ ታትመው ሲሰራጩ ነበሩ
የጋዜጣ ቅጂዎች፣ በኢንትርኔት ላይ ታትመው የወጡ ጹሑፎች ብቻ ነበሩ፡፡ ቀኑን ሙሉ ፍርድ ቤት ሲታዩ ይውሉ የነበሩ
የምስል ማስረጃዎቹ ደግሞ ፓርቲው በግልጽ ለጋዜጠኞች ሲሰጣቸው የነበሩ መግለጫዎች ነበሩ፡፡ በእነዚህ ተከሳሾች ላይ እንደ
ክሱ አቀራረብ ሊያስረዳ የሚችል አንድም የሰነድም ኾነ የምስል ማስረጃ አልቀረበባቸውም፡፡ የክሱና የክርክር ሂደቱ ግን አንዳች
የተለየ ድብቅ ዓላማ ሲራመድ የተደረሰበት ይመስል እጅግ የተካበደ ነበር፡፡

ከዓመታት በኋላ ደግሞ ልክ እንደ ቅንጅቶቹ ክስ ስለ ጦማሪያኑና ጋዜጠኞቹ አካብደው እየነገሩን፤‹‹በህዕቡ ተደራጅተው አገር
ሊያተራምሱ›› ሲሉ ተደረሰባቸው ይሉናል፡፡ወጣቶቹ ራሳቸውን ደብቀው ሲያሴሩ በደህንነት የስለላ መረብ የተገኙ ይመስል
በሰላምና በግልጽ ከተማ ላይ የሚንቀሳቀሱትን ልጆች ‹‹ሽብርተኛ›› ይሏቸዋል፡፡ እስረኞቹን ይዘው ሲጠይቋቸው የነበረው
ጥያቄ ግን‹‹እዚህ ጋዜጣ ላይ እንዲህ ብላችሁ ጽፋችኋል፣በማኅበራዊ ድር ገጽ ላይ እንዲህ ብላችሁ አውጥታችኋል፣እንዲህ ቦታ
ላይ እንዲህ ዐይነት ሥልጠና ወስዳችኋል››የሚል ነው፡፡ወጥተው አደባባይ ላይ ሲናገሩና ክሱን በፍርድ ቤት ሲያቀርቡት
ደግሞ ሌላ ነገር አስመስለው ልክ እንደ ኩይሳ(የጉንዳኖች ቤት ወደላይ ተቆልሎ የሚሠራ ሲፈርስ ውስጡ ባዶ)ቆልለው ትልቅ
አድርገው አዲስ በመጣው ፋሽን በዶክመንተሪ አዋዝተው ያቀርቡታል፡፡

ለምሳሌ ዛሬ ስለ ክሱ በከፊል ካነበብነው ላይ፤‹‹ከተጠርጣሪዎቹ አንዷ የሆነችው ሶሊያና ሽመልስ የቡድኑ መሥራችና
አስተባባሪ በመሆን ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. መቆየቷና ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ በውጭ አገር አስተባባሪና የውጭ ግንኙነት
ሆና ከመሥራቷም በተጨማሪ፣ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በማደራጀትና በመመልመል
ስትሠራ ቆየች››ይላል፡፡ ይህ አንቀጽ ያነበበ ሰው በቃ የኾነ የተለየ የጦር መሳሪያ ምናምን የታከለበት ስልጠና ጉድጓድ ቆፍረው
ከመሬት ስር ተደብቀው ሲወስዱና ወይም ደግሞ የኾነ የኮድ ስም ኖሯቸው ተከታዮች አፍርተው ጦርነት የሚያዘጋጅ ሥልጠና
ሲወስዱና ሲሰጡ የቆዩ ዐይነት ነገር ያስመስላል፡፡ሴኪዩሪቲ ኢን ኤ ቦክስ (Security in-a-box) የተባለው ይህ ሥልጠና ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ በጋዜጠኞች ዐቅም ግንባታላይ የሚሠሩ ድርጅቶች ሳይቀሩ ለጋዜጠኞች ሲሰጡት የነበረ በኢንተርኔት ሴኪዩሪቲ ስር የሚሰጥ፤ደኅንነቱ የተጠበቀየኢንተርኔት ግንኙነት እንዲኖረን፣ ኮምፒዩተሮቻችንና ስልኮቻችን ከቫይረስና ከሀከሮች የተጠበቀ እንዲሆን፣ ፋይሎችከኮምፒዩተሮቻችን ላይ ሲጠፉብን እንዴት ማግኘት እንደምንችል በአጠቃላይ የኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ለጋዜጠኞች የሚሰጥ ዓለም አቀፍ ሥልጠና ነው፡፡ መቼም ጋዜጠኛና ሥልጠና አይተጣጡምና እኔ እራሴ ከሦስት ዓመትና
ከወራት በፊት ናይሮቢ ከተማ ሁለት ጊዜ ይህን ሥልጠና ወስጃለሁ፡፡ሥልጠናው ለጋዜጠኛ ብቻ ሳይኾን ለማንኛውም
ኢንተርኔት ተጠቃሚ እጅግ ጠቃሚ የኾነ ሥልጠና ነው፡፡ ሥልጠናው ተደጋጋሚ የሚኾነውም አዳዲስ ቫይረስና አዳዲስ ሃክ
ማድረጊያ ሶፍትዌሮች ስለሚፈጠሩ እነሱን ለመከላከል የሚረዱ ሌላ አዳዲስ ሶፍትዌሮች ስለሚሠሩ ነው፡፡

ሥልጠናውን የሚያዘጋጁት በጋዜጠኞች ዐቅም ግንባታ ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማትም አሰልጣኞቹን የሚያመጧቸው የጦር መሳሪያ
አገጣጠም፣አፈታትና አተኳኮስ ልምድ ካላቸው ታጋዮች መካከል መልምለው ወይም ከአንድ ስለላ ድርጅት መርጠው ሳይኾኑ
ከማይክሮሶፍት ኦፊስ ልምድ ያላቸው ሶፍትዌር ኢንጅነሮችና ከሞያው ጋራ የተያያዘ ዕውቀት ያላቸው ባለሞያዎችን ነው፡፡
እንዲህ ያለውን ሥልጠናም በርካታ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ክሱን ይዘው ከቀረቡት ዐቃቤያነ ሕግና ዳኝነት ሊሰጡ ከተሰየሙት
ዳኞች መካከልም ብዙዎች ሠልጥነዋል፡፡ ይህ ኮምፒዩተሮችንና ስልኮችን ከቫይረስና ከሀከሮች ለመጠበቀ የተሰጠ ሥልጠና
ወጣቶቹ ጋር ሲደርስ ‹‹ሀገርን በአመፅ፣ በሁከትና በብጥብጥ ለመለወጥ›› የተወሰደ ሥልጠና ተብሏል፡፡ እኔ የምለው ሀገር
የኮምፒዩተር ቫይረስና ሀከር ነው እንዴ?

ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
July 18, 2014