አሸባሪነት በሃገራችን ትርጉሙን ገልብጦ ተሸባሪዎች በሙሉ አሸባሪ እየተባሉ በእስር በግርፋት በተለያዩ የማሰቃያ ዘዴዎች በመጠቀም ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በየእስር ቤቱ በስቃይ ላይ ይገኛሉ። ይህ የፀረ ሽብር ህግ በአግባቡና በቀጥታ ትርጉሙ ቢታይ በኢትዮጵያ ዜጎች በመንግስት እየተሸበሩ የሚገኙበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን በመንግስታችን እይታ ሙስሊሙ አሸባሪ፣ ክርስቲያኑ አሸባሪ፣ ጋዜጠኛው አሸባሪ፣ ፀሐፊዎች አሸባሪ፣ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ድርጅቶች አሸባሪ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉ ሰላማዊ ሰዎች አሸባሪ ባጠቃላይ የሐገራችን ሁኔታ ያገባናል ሐገራችን ኢትዮጵያ አንድነትዋን ጠብቃ እንድትቆይ የሚሰሩ የነፃለት ታጋዮችን በሙሉ አሸባሪ ናቸው ይሉናል። ይሄ ነገር ያሰጋል እውነተኛ አሸባሪ ቡድን ሐገር ሊያጠፋ ቢመጣ ህዝቡ የሚሰማበት ጆሮ የለውምና ወያኔ በዚህ አካሄዱ ሐገራችንን አደጋ ላይ መጣሉን መገንዘብ አለበት የሰላም ትግሉን ሁሉ በአሸባሪነት በመፈረጁ ህዝቡ የአሸባሪነት ትርጉሙ ተዛብቶበታልና አሁን ባለው የሐገሪቷ ተጨባጭ ሁኔታ ዋናውን የሽብር ጥቃት ሰው በንቃት እንዳይጠብቅ ህዝብን እያዘናጋ ይመስላል። ሊታሰብበት ይገባል ወያኔዎች ልብ ይበሉ እላለሁ።
እነኚህ ሁሉ በፎቶ የምትመለከትዋቸው እና እጅግ በርካታ ንፁሐን ዜጎች ያለአግባብ በየእስርቤቱ ታጉረው እየተሰቃዩ ይገኛሉ ወያኔ የገዛ ህዝቡን ለማሰቃየት እየተጠቀመበት ያለው የማሰቃያ ዘዴ በሙሉ እጅግ የከፋና አሰቃቂ በመሆኑ የዜጎቻችን የየደቂቃው ህመም ሊያመን ይገባል ይህንን ግፍና በደል በቃ ብለን ከጫንቃችን ላይ ማስወገድ ያለብን እኛው እራሳችን ነን። አሁን የተፈጠረው አጋጣሚ ለሁላችንም ወደፊት የማይቀር ነውና አቅማችንን ሁሉ ተጠቅመን ሐገራችንን ከወራሪው የወያኔ አገዛዝ እንታደግ እያልኩ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።
ሄለን ንጉሴ
No comments:
Post a Comment