ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት 16 ቦታዎችን መምረጧል አስታወቀች፡፡

የኅዳሴ ግድብ ወደ ግብፅ የሚወርደውን ውኃ መጠን ይቀንስብናል ሲሉ ግብፃዊኑ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ሥጋታቸውን በየጊዜው እየገለፁ ነው፡፡ በዚህ ወር መጀመሪያ ደግሞ የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ በውኃ ደኅንነታቸው ላይ የሚፈጠርን “ማንኛውንም ሥጋት ለመያዝ ‘ሁሉም አማራጮች ክፍት’ ናቸው” ባሉ ጊዜ በውኃው አቅርቦት ላይ ያላቸውን ፍርሃት ጠቁመው እንደነበርና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በሰጡት ምላሽ የግብፅ መሪዎች “… ካላበዱ በቀር የጦርነትን አማራጭ ይወስዳሉ ብለን አናምንም …” ብለው ነበር፡፡
የኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑም ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የጀመረችውን ግድብ ግንባታ ሥራ እንደማታቆም አስታውቀዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የማንንም ሃገር የመሻሻል ዕድል እንደማትቃወም የተናገሩት የግብፅ የውኃ ኃብቶች ምክትል ሚኒስትር አሕመድ ባህ ኤልዴይን ይሁን እንጂ ናይል ወንዝን በተመለከተ ማንኛቸውም ዕቅዶች ከመነደፋቸው በፊት መዘዞች ሁሉ ግምት ውስጥ ሊገቡ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
No comments:
Post a Comment