Friday, August 30, 2013

“በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ” እንዳይሆን እንጠንቀቅ


ቢከፍቱት ተልባ የሆነውና ላይ ላዩን ሲያዩት ልማት የሚመስለው የወያኔ ኢኮኖሚ “ልማትና እድገት” የገንዘብ ካፒታል የሚያገኘው እንደሌሎቹ በእድት እንደሚገሰግሱ ታዳጊ አገሮች የእንዱስትሪ ሸቀጥ አምርቶ ለአለም ገቢያ አቅርቦና ሽጦ አይደለም። ተሰራ የተባለው ብልጭልጭ ነገር ሁሉ የሚሰራው የድህነት ጌቶች “Lords of Poverty” በሆኑት አለም አቀፍ ተቋሞችና ሀገሮች በሚገኝ እርዳታ ነው። ወያኔ እራሱ በፈጠሩ ችግር ተሰዶ በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊም ለወዳጅ ዘመድ የሚልከው የውጭ ምንዛሬም ሌላው የወያኔ የገንዘብ ምንጭ ነው። በዚህ ላይ የሀገሪቱ የተፈጥሮ ሀብት የሆነውን ለም መሬት በገፍ ለባዕድና ለሀገር ውስጥ የወያኔ ቤተኞች በመቸብቸብ የሚገኝ ገንዘብ አለ። መቼም ኢትዮጵያዊው በገዛ ሀገሩ የኩርማን መሬት ባለርስትና መብቱ ከተነጠቀ ቆይቷል። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለርሰተቹ ወያኔና ጉጅሌዎቹ ብቻ ናቸው።

የሀገሪቱ የገንዘብ ሀብት ብዙ ጊዜ የሚገባው ከግርጌው በተቀደደ ቋት ውስጥ ስለሆነ ለዘላቂ ልማትም ሆነ ገንዘቡን ለሚቀራመቱት ወያኔዎች በቂ አልሆነም።
ይህንን ቀዳዳ ቋት ለመሙላት ወያኔ ሰሞኑን የፈጠረው ዘዴ ህዝቡን የቤት ባለቤት ላደርግህ ስላሰብኩ አስቀድመህ ገንዘብህን አምጣ የሚል ዘዴ ነው። ሃያ-ሰማኒያ አርባ-ስልሳ ወዘተ የሚል ዘዴ ተገኝቷል። ይህ አርባ ስልሳና ሃያ ሰማንያ የሚሉት ፈሊጥ የኢትኦጵያ ደሃ ህዝብ ነገ ያልፍልኛል እያለ ሆዱን ቋጥሮና አንጀቱን አስሮ ያፈራትን ገንዘብ እንዲሰጣቸው የታለመ የጮሌዎች የገንዘብ መሰብሰቢያ ዘዴ ነዉ።
በተለይ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል ተብሎ የታመነበት 40/60 የሚባል ዘዴ በየኢምባሲው በወረቀት ላይ በተሰሩ ቆንጆ የቤትና የኮንዶሚኒየም ንድፎች አሸብርቆ መጥቷል።
ይህችን የጭልፊት ኢኮኖሚ ማየት የተሳናቸው የዋህ ኢትዮጵያውያን በየባዕድ ሀገሩ ለፍተው ያፈሯትን ጥሪት ይዘው በየኢምባሲው ለምዝገባ ሲጋፉ ማየት እጅግ በጣም ያሳዝናል። ብዙ ኢትዮጵያውያን ይህንን የዝርፊያ ኢኮኖሚ የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ በሚል ፈሊጥም የገቡበት አሉ። ራሳቸውንም ሀገራቸውንም እያዘረፉ መሆኑ የገባቸው አይመስልም። ወያኔ ይልቁንም የገቢያው መድራት ስላስጎመጀው ለውጭ ነዋሪ ያዘጋጀውን 40/60 አቁሞ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ መንገድ እያሰላ ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህን የድቡሽት ላይ ቤት እንሰራለን ብለው ያሰቡ ወገኖች ሁሉ የወያኔን ቀዳዳ ኪስ ከመሙላታቸው በፊት ጥቅሙን፤ ጉዳቱንና ትርጉሙን አገላብጠው እንዲያዩ ይመክራል። በተለይ በወያኔ ስር በሚገኝ ንብረት ያልፍልኛል ብለው በስደት ኑሮ ያፈሩትን ገንዘብ የነጻነታቸዉ መያዣ ተደርጎ ለባሰ ውርደት እንዳይዳርጋቸው ግንቦት ሰባት ወገናዊ ምክሩን ይመክራል።
ቤት አልባ ሆኖ በየመንገዱ ላይና በየደሳሳ ጎጆዉ ታጉሮ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ወገናችን በየዕለቱ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከነሱ እየተዘረፈ በሚሸጥ ንብረት ሀብት ለማፍራት መሞከር ለህሊናም የሚቀፍ ነው።
የወያኔ የቤት ስራ ፕሮጀክት ገንዘብ መልቀሚያና ጥቂት ባለሟሎቻቸውን መጥቀሚያ እንጂ ለዚህ ሁሉ የውጭ ነዋሪ የሚደርስም አይደለም። ወያኔ አስቀድሞ ከወለድ ነጻ የሆነ ገንዘብ ከሰበሰበ በኋላ ገንዘቡን ተጠቅሞ ከአምስትና አስር አመት በኋላ ቤቱንም ገንዘቡንም ማግኘት ላይቻል ይቻላል። ወያኔም ተጠያቂነትን የማይወድ አገዛዝ መሆኑን ካሁኑ አለመገንዘብም ራስን ጨፍኖ ለመሞኘት መፍቀድ ነው።
የወያኔ 40/60 ገንዘብ መሰብሰቢያ እንጂ ህዝብ መጥቀሚያ አይደለም። ወያኔዎች ሊጠቅሟቸው የሚፈልጉ ዜጎችን ከፈለጉ በየጎዳናው ላይ ያገኟቸዋል ለምን እነሱን አየረዷቸዉም?
በተለይ በውጪ የምንኖር ኢትዮጵያውያን በፍጹም ድህነትና የወያኔ ዝርፊያ ተዋርዶ የሚኖረውን ህዝባችንን እያየን የዚህ ግፈኛ መንግስት መሳሪያ ከመሆን አልፈን ራሳችንንም ለተዋራጅነት እንዳንዳረግ እንጠንቀቅ!
ድል ለኢትዮጵያ ሀዝብ!!

የእኛ “መንግስት”


 (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

August 29, 2013

“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡ ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም” ይህንን መግቢያ የወሰድኩት በልዑል የኢትዮጵያ መንግስት አልጋ ወራሽ ተፈሪመኮንን ማተሚያ ቤት የካቲት 1 ቀን 1917 ዓ.ም ከታተመው የነጋ ድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ‹‹መንግስትና የሕዝብ አስተዳደር›› መፅሀፍ ነው፤ ዛሬም ያለንበትን ዘመን ይዋጃልና፤ በተለይ ስለ‹‹ነገድ›› የተጠቀሰውን አርቀን ሰቅለን፣ ‹‹ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት›› የምትለዋን ሀረግ በወጉ ካጤንናት ለጊዜያችን በልክ የተሰፋች መሆኗን ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡
Journalist Temasegan Dasaleg
እናም የስርዓቱን የአስተዳደር ዘይቤ ያለፍርሃት አደባባይ ካዋልነው የቀድሞ ገዥዎቻችን የተጓዙበትን ጎዳና እየተከተለ መሆኑን ለመተንተን የምሁራንን ጥናት መጠበቅ ግድ አይለም፤ ምክንያቱም ለዓመታት የተመለከትነው እውነታ የሚነግረን የአመራሩን እና በዙሪያው የሠፈሩ የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦችን ብልፅግና ታሳቢ ያደረገ፣ ከታግሎ መጣል ህግ የተቀዳ፣ የራስ ሀገርንና የራስ ሕዝብን በምርኮ ያስገበረ ፖለቲካ መንበሩን ነው፤ ገብር፣ ገብር፣ ገብር…!!
ዛሬ መንገድ ዳር ረሀብ አዙሮ የጣለው ወንድምህ ስቃይ እንደ ጥላ የሚከተልህ፤ ህፃናት በትምህርት ገበታቸው ላይ በጠኔ ተሸንፈው መመልከቱ የሰርክ አሳዛኝ ክስተት የሆነብህ ከሰው ሰራሽ ችጋር፣ ከሰው ሰራሽ የቀዬ ፍንቀላ፣ ከሰው ሰራሽ እርዛት… የመነጨ መርገምት እንጂ የሰማይ ቁጣ አይምሰልህ፤ እመነኝ መለስም ሆነ ተተኪዎቹ ስኬት አድርገው የሚሰብኩትም ይህንን ነው፤ ‹ሀገር አቀናን!› የሚሉትም ይህንን ነው፤ ሰሞኑን የሚያሰለቹህ ተረኛ ምሁራንም ‹‹ትምህርትና ጤናን በተመለከተ መለስ ‹እልል› የሚያስብል ሥራ ሰርቷል›› የሚሉህ ጣራና ግድግዳ እየቆጠሩ ነው፤ ይህ አይነቱ መደዴ ሙገሳም ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ሪፖርት ለማዘጋጀት ከሚረዳ ቁጥር የዘለለ አበርክቶ አንደማይኖረው አትዘንጋ፡፡
እውነት እውነት እልሀለሁ፡- ይህ የሆነበት ብቸኛው ምክንያት መንግስት በስልጣን ላይ ስለሚቆይበትመንገድ ብቻ መጨነቅን ግዴታው በማድረጉ ነው፤ ይህንን ለመረዳትም እያገባደድን ባለው ክረምት የመንግስት ትኩረት በምን ላይ አንደሆነ የሚያሳይ ማስረጃን ጨርፌ ላሳይህ፡፡
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የእስልምና እምነት ተከታዮች መንግስት በሃይማኖታቸው ጣልቃ መግባቱን በመቃወም እና የታሰሩ ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱ በመጠየቅ እያደረጉ ያለውን ትግል በሰላማዊ መንገድ አጠንክረው ሲቀጥሉ፤በተቃራኒው ‹‹ፀጥታ አስከባሪዎች›› አንዳንዴ በጥይት፣ አንዳንዴ በአስለቃሽ ጢስ፣ አንዳንዴ በማጋዝ…ምላሽ ሲሰጡ…
በርግጥ መንግስት ከኃይል እርምጃው በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎችን (በምን አግባብቶ ወይም በምን አስፈራርቶ እንደሆነ ባይታወቅም) ወደ አደባባይ በማስወጣት መብት ጠያቂዎቹን ከ‹‹አክራሪ››ነት እና ‹‹ወሃቢዝም››ነት ጋር አያይዘው የውግዘት በረዶ እንዲያዘንቡባቸው እያደረገ ነው፡፡ ኢቲቪም ይህንን ኩነት እየተከታተለ ማራገቡን ቀጥሎበታል፤ ‹‹የቲፒ ከተማ ነዋሪዎች ‹አክራሪዎችን አወገዙ››፤ ‹‹በደቡብ ወሎ ኩታ በር ዞን አንድነት ፓርቲ ህገ-ወጥ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰልፍ ተካሄደ››፤ ‹‹የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ‹የሼሁ ግድያ ድራማ አይደለም› አሉ፣ ‹የሼህ ኑሩ ኢልም ነው፣ የአሸባሪዎች ብር ነውም›ብለዋል››፤‹‹የመርሀቤቴ ነዋሪዎች ፅንፈኞችን በመቃወም የአቋም መግለጫ አወጡ››፤…
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- አንድነት ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የ‹‹ፀረ-ሽብር ሕጉ›› እንዲሰረዝና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ እና የአዳራሽ ስብሰባዎችን እያካሄደ ነው፤ መንግስትም አንዳንዴ የአፀፋ የድጋፍ ሰልፍ ሲያካሄድ፤አንዳንዴ የአዳራሽ ስብሰባዎች ከመካሄዳቸው አስቀድሞ ‹መጋኛ› ሲሆንባቸው፤ አንዳንዴም የአስተባባሪዎቹን መኪና ጎማ ሲያፈነዳ፤ አንዳንዴም አዳራሽ ከልክሎ ሲያደናቅፋቸው… መዋሉ ፋታ የነሳው ይመስላል፤ በወላይታ የተጠራውን የአዳራሽ ስብሰባም ‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ ቦታ እንዴት ተደርጎ!›› ያሉ ካድሬዎች የአንድነት ሰዎችን አዋክበው ስብሰባውን አክሽፈዋል፤
ክረምቱእንዲህእየተገባደደነው፡-ገዥው ፓርቲ ‹የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ አንደኛ ሙት ዓመት አከብራለሁ› በሚል መላ ኢትዮጵያን ችግኝ መትከያ፣ መላ ዜጎቿን ደግሞ ወደ አርሶ አደርነት በአስማት የቀየራቸው አስመስሏቸዋል፤ቴሊቪዥንና ራዲዮንም አስፈላጊነታቸው በየመንደሩ ችግኝ መተከሉን እየተከታተሉ መዘገብ ብቻ እስኪመስል ድረስ እንዲህ ሲሉ ጀምበር ወጥታ ትጠልቃለች፡- ‹‹የላይ አርማጮህ ነዋሪዎች ችግኝ ተከሉ››፣ ‹‹በመቀሌ ከተማ ‹ዘመቻ መለስ› በሚል የችግኝ ተከላ ተካሄደ››፣ ‹‹አቃቂ ኮረብታ ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ችግኝ በኦሮሚያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ተተከለ፤ ቦታውም ‹መለስዜናዊ ኮረብታ› ተብሎ ተሰይሟል››፣ ‹‹በምዕራብ ሀረርጌ አስራ ሰባት ሚሊዮን፣ በወልበራ አስራ አራት ሚሊዮን ችግኝተ ተክሏል››፣ ‹‹በመንዝ ላሎ ወረዳ ተቆጥሮ የማያልቅ ችግኝ ተከላ ተደርጓል››፣ ‹‹የብአዴን አመራርና ካድሬ በባህር ዳር ከተማ በቢሊዮን የሚቆጠር ችግኝ ተከሉ፤ በፕሮግራሙ ላይ ጓድ አዲሱ ለገሰ ‹ችግኝ የምንተክለው አገሪቱ በአረንጓዴው ልማት በአለማችን ማግኘት የሚገባትን ቦታ እንድታገኝ ለማድረግ ነው› ሲል፣ ጓድ በረከት ስምዖን ደግሞ ‹ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአለማችን በአንድ ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ችግኝ እየተከሉ ያሉባት ብቸኛ ሀገር ናት› ብሏል››፤‹‹ዝክረ መለስ 1ኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ከሐምሌ አስራ አምስት ቀን ጀምሮ ሁሉም ቀበሌዎች በስሙ ‹ፓርክ› ሰይመው ችግኝ ተከላ እያካሄዱ›› መሆኑን ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ መግለፁን የአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ ዘግቧል፤ ‹‹በወልቂጤ ከተማ በተደረገው ችግኝ ተከላ ላይም አንዲት ወጣት ‹መለስ ለሴቶች የተለየ አመለካከት ነበረው›› ማለቷም በዘገባው ተጠቅሷል፤ …ማን ነበር የመለስ ራዕይ ‹ችግኝ መትከል ነው› ያለው? …ኢህአዴግ ይሆን?
ከዚሁ ጎን ለጎን (አሁንም ሙት ዓመቱን ለማሰብ) በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የእግር ጉዞ ተደርጓል፣ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓትም ተካሄዷል፤መነሻውን መቀሌ፣ መድረሻውን አዲስ አበባ ያደረገ ‹‹የመለስ ቱር አረንጓዴ ልማት›› የብስክሌት ውድድርም ሊጠናቀቅ ገና አንድ ሳምንት ይቀረዋል፤ በብሄራዊና ሀይማኖታዊ በዓላት ቀንለሃያ አንድ ጊዜ ይሰማ የነበረው የመድፍ ድምፅም፣ የመለስን አንደኛ ሙት ዓመት ለማብሰር ተተኩሷል፤ …በግድ አልቅሱ፣ በግድ ተዝካር አውጡ፣ በግድ ችግኝ ትከሉ፣ በግድ ተወያዩ፣ በግድ አደባባይ ውጡ፣ በግድ የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን ጎብኙ፣ በግድ.. ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ እና የትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ በላይ ለሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ከፍተኛ መምህራን ‹የአቅም ግንባታ ስልጠና› እየሰጡ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምሁራኖቹን ማሰልጠን ያስፈለገበት ምክንያት ‹‹ብቃት ያለው ምርጥ የተማረ ኃይል ለማፍራት››መሆኑን ቢነግርህ አይግረምህ፤ ይህ ኢትዮጵያ ነውና የዐዋቂነት ማረጋገጫው መማር፣ ማንበብ፣ መመራመር… አይደለም፣ የፖለቲካውን ኃይል መያዝ እንጂ፤ ‹ስልጣን ላለው ሁሉምሚስጥረ-ጥበብይገለፅለታል› እንዲል አብዮታዊ ዲሞክራሲ መለስ ዜናዊም በሁሉም መስክ ‹አስተማሪ› ነበር፤ የህግ ባለሙያዎችን ሰብስቦ የሀገሪቱን ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ትርጓሜ ሲተነትን ደጋግመህ ሰምተኸዋል፤ በቀጣዩ ቀን ደግሞ ለግብርና ባለሙያዎች ከውሃ ማቆር እስከ በላብራቶሪ የሚዳቀል ምርጥ ዘር ድረስ ባሉጉዳዮችዙሪያ የሁለት ቀን ማብራሪያ መስጠቱን ታስታውሳለህ፤ እመነኝ ተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ነው እያደረገ ያለው፤ የሆነ ሆኖ ኃ/ማርያም ለምሁራኖች ከሙያቸው ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ጭምር በሰጣቸው ስልጠና ላይ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር ‹‹የኢንዱስትሪዎች በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ፣ በክፍል ውስጥ የምናስተምረውን ንድፈ ሃሳብ በተግባር ለማሳየት እንቅፋት ሆኖብናል››፤ በርግጥጠቅላይ ሚንስትሩ‹‹መፍትሄ››ያለውን የተናገረው ብዙም ሳይጨነቅ ‹‹እኔ ኢንዱስትሪን ‹ዲፋይን› የማደርገው ግብርናም ኢንዱስትሪ ነው ብዬ ነው››በማለት ነበር፤…ግና!ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል በተጨባጭ አላብራራም፡፡ለምሳሌ ህክምና የሚያጠና ተማሪ በምን መልኩ በሞፈርና ቀንበር የተግባር ልምምድ ማድረግ እንደሚችል፤ወይም ፖለቲካ ሳይንስ የሚያጠና ተማሪ የተግባር ልምምዱን በግብርና ኢንዱስትሪ እንዴት ሊወጣው እንደሚችል? ማለቴ ነው፡፡
ለዓመታት በርካታ ምሁራን ብቃት አልባ ተማሪዎች እንደ ሰማይ ከዋክብት የመብዛታቸው መንስኤን ከትምህርት ፖለሲው ጋር የሚያነፃፅሩበትን ሀቲት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ባገኘው የሀገር መሪነት ስልጣን ገልብጦ በዩንቨርስቲ ቆይታው መምህራኖቹ የነበሩትንም ጭምር ‹‹አቅም አንሷችኋልና-እገነባችኋለሁ›› ሲል ከመስማት የከፋ እንደ ሀገር ክሽፈት የለም (በነገራችን ላይ ከወራት በፊት ለኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ ቴውድሮስ አዳህኖም፣ ሶፍያን አህመድ በአጠቃላይ ሁሉም የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አንድ ህንዳዊ ፕሮፌሰር በኢህአዴግ ጽ/ቤት ‹‹ልማታዊ መንግስት›› እንዴት ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ሲተነትንላቸው፣ እነርሱም ደብተርና እስክርቢቶ ይዘው በንቃት ሲከታተሉ የቴሌቪዥ ዋና ዜና ሆኖ የቀረበበትን ምክንያት ዛሬም ድረስ ሊገለፅልኝ አልቻለም፤ በተለይም ፕሮፈሰር እንድርያስ እሸቴ ‹‹በቃሉ የፀና…›› በሚል ርዕስ መለስን አስመልክቶ በተዘጋጀ ዶክመንተሪ ፊልም ላይ ‹‹በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ልማታዊ ስርዓተ መንግስት ‹ዴሞክራሲያዊ ሊሆን ይችላል፤ መሆንም አለበት› ብሎ በአደባባይ የተከራከረው እኔ እስከማውቀው ድረስ መለስ ነበር›› ማለቱን፣ ተተኪዎቹ ፍልስፍናውን ገና እየተማሩት ከመሆኑ አንፃር ስናየውሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ጉዞው ወዴት ነው? ያስብላል፡፡ …ከቶስ በተማሪ ፖለቲከኛ የሚተዳደር ሕዝብ ከኢትዮጵያ በቀር ወዴት ይኖራል?)
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የህዳሴውን ግድብ ከዳር ለማድረስ በቂ ገንዘብ ስላልተገኘ ተደጋጋሚ የቦንድ ሽያጭ እየተካሄደ ነው፤ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞችም በካድሬ ባልደረቦቻቸው ጫና በድጋሚ ቦንድ ለመግዛት መወሰናቸው ተሰምቷል፤ በርግጥ ከፍተኛ የኢህአዴግ የአመራር አባላት በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቦንድ እንዲገዙ ለመቀስቀስ የአዘጋጇቸው ስብሰባዎች ‹‹ቅድሚያ የዜጎች መብት ይከበር›› ባሉ የሀገራችን ልጆች መክሸፉም የክረምቱ የመንግስት ዋና ሥራ ነው፤ ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- በነቢብ የኢትዮጵያ፣ በገቢር የገዥው ፓርቲ የግል ንብረት የሆነው ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለፉት ሶስት ወር ብቻ ከሃያ በላይ ‹‹ዶክመንተሪ ፊልም›› አሳይቷል (ገና ይቀጥላልም) በርዕሳቸው እንደሚከተለው እንዘርዝራቸው፡- ‹‹ኢፍቲን›› በሶማሊያ ላይ የሚያጠነጥን፣ ‹‹የጥቁር ህዝቦች ልሳን (መለስ በአፍሪካ)››፣ ‹‹ከፓን አፍሪካ እስከ አፍሪካ ህዳሴ›› የጠቅላይ ሚንስትር መለስን ህይወት የሚዳስስ፣ ‹‹ዘመነ አፍሪካ››፣ ‹‹የአፍሪካ ልሳን-መለስ››፣ ‹‹መለስ ማን ነው?››፣ ‹‹ሀገሬ-ቤቴ››፣ ‹‹ባለራዕዮቹ›› ስራ ፈጠራ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ደውል›› እና ‹‹ደውል 2›› ህገወጥ-የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ (በተለያያ ጊዜ የተላለፉ)፣ ‹‹የዲያስፖራ የልማት እንቅስቃሴ››፣ የካርታ ስራ ድርጅትን በተመለከተ፣ ‹‹የጥልቅ አስተሳሰብ ባለቤት›› በፕ/ር እንድርያስ እሸቴ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን፣ ምድር ባቡር ኮርፕሬሽንን በተመለከተ፣ ‹‹ያልተለመደ ጉብኝት›› የአዲስ አበባ አስተዳደር የአምስት ዓመት የመንግስት ግንባታዎችን በተመለከተ፣ ‹‹ሼህ ኑር ለምን ሞቱ?›› የደሴውን ሼህ ኑር ይማምን ግድያ በተመለከተ፣ ‹‹የተስፋ ስንቅ››፣‹‹በቃሉ የፀና›› በድህረ መለስ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ያልተጠኑ ገፆች›› በመለስ ዜናዊ ህይወት ዙሪያ (በርግጥ በዚህ ፊልም እህቱ ጠላ፣ ወንድሙ አንባሻ በመሸጥ መተዳደራቸውን በምስልም በድምፅም ማቅረቡ ምን የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ እንደሆነ ለማወቅ ግራ ያጋባል፤ …ምናልባት እንዲያ እየዘረፈ ለቤተሰቦቹ ‹ሶልዲን› የማይሰጥ ‹ቆነቋና› ነበር ለማለት ይሆን? ወይስ ለአዜብ መስፍን ‹የወር ቀለባችንን እንቸገራለን› የአንድ ሰሞን ማስተዛዘኛ ምስክር ፍለጋ ነው?
በጥቅሉ ለኢህአዴግ ሕዝብን የማስተዳደር፣ ሀገርን የመምራት መገለጫ ይህ ነው፤ ሌላ አይደለም፤ ግና! ለዘመናት ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችን ዛሬም መጮኻቸውን አላቋረጡምና እነሆ እንዲህ ቀጥለዋል፡- ሀገር ማስተዳደር ‹መለስ ጀግና ነበር› እያሉ ማሰልቸት ነውን? የመንግስትስ ስራ (ግዴታ) ምንድር ነው? ሀገሪቱን ‹‹መለስ-ፓርክ›› ወደሚል ስያሜ ከመቀየራችሁ በፊት፣ ለጤፍ ዋጋ አለቅጥ መናር ምክንያቱን ስለምን መመርመር ተሳናቸው? ሀገሪቱን በ‹አራጣ› እንደያዘ ስግብግብ ነጋዴ በሚሊዮኖች ህይወት ላይ የማይሞላ ‹ሳፋ› ደቅኖ አዋጣ፣ ግዛ፣ ክፈል፣ ገብር… እያለ የሚያስጨንቀው ማን ነው? ስለመለስ ‹የሃሳብ ምጡቅነት› መስካሪ ምሁራኖቻችን ለጎዳና ኑሮ የተዳረጉ ኢትዮጵያውያን ስንት ሚሊዮን እንደደረሱ እና እልፍ አላፍት ታዳጊዎቻችን በሴተኛ አዳሪነት እንደተሰማሩ የምትነግሩን መቼ ነው?እንዲህ የመሆኑ ምክንያትስ በማን ይሆን? ‹የሁለት ዲጂቱ›ዕድገት ሸክምን የማለዘብ አቅም ከሌለውፋይዳው ምንድር ነው? ‹ሳቅ ትዝታ› ስለሆነባቸው ጎጆዎች ለምን አትነግሩንም? መለስ ‹ያለመለማት› ኢትዮጵያ ወዴት ትሆን? ‹ፖለቲካ› ማለትስ ይህ ነውን? …ነጋ ድራስ ገ/ህይወት እንዳሉት ‹‹…መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡›› የመተራረሚያው ጊዜም በጣም ያለፈ ይመስለኛል፡፡ አገዛዙን ‹እንደ መንግስት› መቀበሉም እንዲሁ፡፡

በፍቼ በአንድነት ፓርቲ አባላት ላይ የደረሰ ድብደባ


በፍቼ በአንድነት ፓርቲ አባላት ላይ የደረሰው ድብደባ የሚያሳየው በሀገራችን ላይ  ያለው መንግስት

ማፍያ መሆኑን የሚያሳይ ነው ቪዲዮውን ይመልከቱ ምን  አይነት ግፍ ነው የሚሰራው



የሕወሐት ባለስልጣናት የአሜሪካ ቆይታ፤ የከዱ አሉ


August 29, 2013

ከኢየሩሳሌም አርአያ

በአባይ ወልዱ የሚመራውና ሰባት ከፍተኛ የሕወሐት ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን በአሜሪካ አራት ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠመው በስፍራው የተገኙ ምንጮች አስታወቁ። ቡድኑ በዋሽንግተን ኢትዮጲያ ኤምባሲ በጀመረውና በመቀጠል በላስቬጋስ፣ ሲያትልና ካሊፎርኒያ ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ “አላማ” አድርጎ የያዛቸው ጉዳዮች እንደነበሩ የጠቆሙት ምንጮች፣ እነሱም፥ “የመለስ ፋውንዴሽን፣ የአባይ ግድብና የ40/60 የቤቶች ግንባታ.” ሲሆኑ፣ ለነዚህ ማስፈፀሚያ “ገንዘብ አዋጡ” የሚለው ዋናው ግብ እንደነበር አስረድተዋል። በተለይ ደግሞ « በትግራይ ተወላጁ ዘንድ ሕወሐት የለም፣ ተከፋፍሏል፣ ተዳክሟል፣ ፓርቲው ሰው የለውም፤» የሚለውን እራሱ ቡድኑ በማንሳት ለገዛ ጥያቄው መልስ ሲሰጥ « ሕወሐት አሁንም ሃይል አለው፤ አልተዳከመም» በማለት አድራጊ- ፈጣሪ በመሆን ስልጣኑን በበላይነት ተቆጣጥሮ እንደያዘና ቡድኑ የመጣውም “አይዟችሁ” ለማለት እንደሆነ መገለፁን በቅርብ የተከታተሉት ምንጮች አስታውቀዋል። ቡድኑ በተጨማሪም ፥ « ልማት አልምተናል፤ ትግራይ እየለማ ነው፤ ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረገነው ነው» ከማለቱ ባሻገር « በትግራይ ተወላጁ ላይ አደጋ ተደቅኗል፤ የሙስሊሙ፣ የትምክህተኞችና የሽብርተኞች አደገኛ እንቅስቃሴ እያንዣበበ መሆኑን፣…የተደቀነብህን አደጋ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤ ያለበለዚያ ግን ሊያጠፉህ ነው፤» ሲሉ መናገራቸውን የገለፁት ምንጮች አክለውም፣ « አባላት የሆናችሁ ተወደደም ተጠላ መሬትና መኖሪያ ቤት እንሰጣችኋለን፤ ለዚህም ከእኛ ጎን መሰለፍ አለባችሁ» በማለት ሊሸነግሉ መሞከራቸውን ጠቁመዋል።
ከዋሽንግተን ስብሰባ (ለሁለት ተከፍሎ ነው የተካሄደው) በኋላ ወደ ሶስቱ ከተሞች ተከፋፍለው እንደሄዱ ሲታወቅ፥ ሲያትል አቶ ብርሃነ ማረት፣ እንዲሁም ላስቬስጋስ አባይ ወልዱና ተክለወይኒ አሰፋ መሄዳቸው ታውቋል። በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ የገጠማቸው እነአባይ ስብሰባው ከቀኑ 2፡00 ሰዓት ይጀመራል ተብሎ ከአራት ሰዓት በኋላ ዘግይቶ አመሻሽ ላይ መጀመሩን ምንጮች ገልፀዋል። ስብሰባው ሲጀመር ከላይ የተገለፁትን ጉዳዮች ያደመጠው ተሰብሳቢ ተከታዮቹን ጥያቄ አቀረበ፤ « ዴሞክራሲ አለ ትላላችሁ፣ ነገር ግን ዴሞክራሲ የለም፤ በሃሳብ የሚቃወማችሁን ታስራላችሁ፣ ታንገላታላችሁ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ ታካሂዳላችሁ፤ ከእናንተ የተለየ ሃሳብ ያለውን ትፈራላችሁ፤ ለምንድነው ይህን ሁሉ የምታደርጉት?….በማ.ረ.ት.(ማህበር ረድኤት ትግራይ) በትግራይ ሕዝብ ስም የምትሰበስቡትን ገንዘብ ለአራጣ ብድር እና ለፖለቲካ መጠቀሚያ በመሳሪያነት እያዋላችሁት ነው። ለምን?….ትእምት (ኤፈርት) ማነው ባለቤቱ?..በማን ነው የሚመራው?..ማነው የሚቆጣጠረው?..ለመሆኑ ኦዲት ተደርጎ ያውቃል ወይ?..እነማናቸው እየተጠቀሙበት ያለው?» የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ጥያቄዎች እንደነበሩ ምንጮቹ የጠቆሙ ሲሆን፣ አባይ ወልዱ « እኔ አልመልስም፣ ተ/ወይኒ መልስ ይስጥበት» ቢሉም ነገር ግን ግልፅና አግባብ ያለው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ወደ ማመናጨቅና ቁጣ ያመሩት ተ/ወይኒ በዚህ ድርጊታቸው በርካታ ተሰብሳቢዎችን እንዳሳዘኑ አስረድተዋል። በዚህ የተበሳጨው ተሰብሳቢ « ጥያቄያችን አልተመለሰም» በማለቱና ሁከትና ያለመደማመጥ በማየሉ ስብሰባው እንዲቋረጥ መደረጉን የጠቆሙት ምንጮች፣ የጥያቄና ተቃውሞው መብዛት ያስደነገጣቸው ባለስልጣናቱ የመረጡት ማምለጫ በላስቬጋስ ተወካያቸው በሆነውና መድረክ ሲመራ በነበረው አቶ ተወልደ በኩል፥ « አዳራሹን የተከራየንበት ሰአት አብቅቷል፤ ስለዚህም ስብሰባው አብቅቷል » በማለት በአስቂኝ ሰበብ መቋረጡን አያይዘው ገልፀዋል። እነአባይ ከአዳራሹ ሲወጡ ቀድሞ ውጭ ሆኖ ይጠብቃቸው በነበረው ተሰብሳቢ ውግዘትና ስድብ እንደደረሰባቸው ያስታወቁት ምንጮች « ሌባ..ሌባ…ሙሰኞች..» የሚሉ ተቃውሞዎች ጎላ ብለው እንደተሰሙ አመልክተዋል።
ስብሰባዎቹን የታዘቡ ወገኖች በሰጡት አስተያየት እንዲህ ብለዋል፤ « በአንድ በኩል ልማት እያካሄድን ነው፤ እያሉና ገንዘብ እየጠየቁ በሌላ በኩል “ትግራዋይ አደጋ ተደቅኖብሃል፣ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤” ማለት እርስ በርሱ የሚጋጭና ድጋፍ የማግኛ የፖለቲካ የፖለቲካ ቁማር ነው። ያልተጠየቁትን የፓርቲውን ህልውና (ስለ ሕወሐት) አንስቶ መነገሩም አስገራሚና አጠያያቂ ነው።» ሲሉ ትዝብታቸውን የጀመሩት እነዚህ ወገኖች በማያያዝም፥ « እነዚህ ሰባት ባለስልጣናት ወደ አሜሪካ የመጡት ከነዘመዶቻቸው፣ ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ሲሆን፣ ባለስልጣናቱ የመንግስት ወኪሎች እንደመሆናቸው – በማን ገንዝብ ነው የሚንቀሳቀሱት?..የሚለው መጠየቅ አለበት። በሕዝብ ገንዝብ እየተንፈላሰሱ እንደሆነ ግልፅ ነው። የትግራይ ተወላጁን ብቻ ለይተው ስብሰባ የሚጠሩት ለምንድነው?…በእርግጥ ስላሰቡለት ነው?…የሚሉት ሲፈተሹ .መልሱ በጭራሽ አይደለም ነው። አላማቸውና ትኩረት የሰጡት የትግራይ ተወላጁን እየተንከባከቡት እንደሆነና ተጠቃሚ መሆኑን ለማሳየት በመፈለግ፣ እግረ-መንገዳቸውን ከቀሪው ኢትዮጲያዊ ወገኑ ጋር በመነጠል..ድጋፍ ለማግኘትና በውስጣቸው የተፈጠረውን ቀውስ በዚህ በኩል ቀዳዳውን ለመድፈን የሚደረግ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ስልት ነው። ..ደግሞስ ሕወሐት “አጋር” ከሚላቸው ብ.አ.ዴ.ን፣ ኦ.ህ.ዴ.ድ.፣ ደቡብ ሕዝቦች ተለይቶ፣ በሕዝብ ገንዘብ ስብሰባ የሚጠራበትና ያሻውን የሚያደርግበት አግባብ ምንድነው?..የሚለው ከዚህ ጋር መታየት ያለብት ነው። ፖለቲካዊ ፍጆታና ማንአለብኝነት በፓርቲው በመነገሱ እንደሆነ ደግሞ ግልፅ ነው።» ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ አሜሪካ ከመጡት ሰባት የሕወሐት ባለስልጣናት መካከል- ማለትም አባይ ወልዱ፣ ብርሃነ ኪ/ማሪያም፣ ተ/ወይኒ አሰፋና ዳንኤል አሰፋ በዋነኛነት ሲጠቀሱ፣ ከሰባቱ ሶስቱ ስብሰባውን ሳያካሂዱ ከቡድኑ ተገንጥለው በአሜሪካ መቅረታቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል። ቤተሰቦቻቸውን ይዘው (ልጆቻቸውን ጭምር) በመምጣት አሜሪካ ጥገኝነት ጠይቀው መቅረትን የመረጡት ባለስልጣናት ውስጥ የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባላት እንዳሉ ያረጋገጡት ምንጮች በቅርቡ ዝርዝሩን ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

Tuesday, August 27, 2013

በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር የተደጋገመው የጎሣዎች ግጭት


በኢትዮጵያና በኬንያ የድንበር አካባቢዎች ከከትናንት በስተያው ቅዳሜ ወዲህ በተፈጠሩ የጎሣዎች ግጭቶች ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን አንድ የኬንያ ራዲዮ ጣቢያ ዘገበ፡፡

ሞያሌዎቹ
ሞያሌዎቹ
በኢትዮጵያና በኬንያ የድንበር አካባቢዎች ከከትናንት በስተያው ቅዳሜ ወዲህ በተፈጠሩ የጎሣዎች ግጭቶች ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን አንድ የኬንያ ራዲዮ ጣቢያ ዘገበ፡፡

ካፒታል ኤፍኤም የሚባል አንድ ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የሚያሠራጭ ራዲዮ ጣቢያ በከትናንት በስተያ - ዕሁድ ዜናው በኬንያና በኢትዮጵያ አዋሣኝ አካባቢዎች የሚኖሩት የቦረናና የገርባ ማኅበረሰቦች አባላት መጋጨታቸውን ተናግሯል፡፡ሁለቱ ጎሣዎች ሞያሌ ውስጥ አዲስ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ያስታወቁት የሃገር ውስጥ ጉዳይና የብሔራዊው መንግሥት ማስተባበሪያ ሚኒስቴር ዋና ፀሐፊ ሙቲያ ኢሪንጎ መሆናቸውንም ራዲዮ ጣቢያው አስታውቋል፡፡
ሞያሌዎቹሞያሌዎቹ

ግጭቱ የተካሄደው በቦረናና በገርባ ጎሣዎች መካከል በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር ላይ መሆኑ ከመገለፁ በስተቀር ተገደሉ የተባሉት ወይም የተጎዱት ሰዎች የየትኛው ሃገር ዜጋ ስለመሆናቸው፣ በግጭቱ ውስጥ የኢትዮጵያ ወገን ሰዎች ተሣትፈው ይሁን አይሁን አልተገለፀም፡፡የዛሬ ሁለት ሣምንትም በቱርካና አካባቢ ኢትዮጵያዊያኑ የሚሪሌ ጎሣ አባላት በኬንያ አሣ አስጋሪዎች ላይ አደረሱ በተባለ ጥቃት አሥር ሰው መገደሉን ናይሮቢ ስታንዳርድ ኦንላይን የሚባል የኢንተርኔት ዜና ማሠራጫ ዘግቧል፡፡ስለሁኔታው ቪኦኤ ያነጋገራቸው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጅሎ ቦኔታ ሁኔታውን ለማጣራት አንድ ቡድን ወደ ቱርካና አካባቢ መላኩን ገልፀዋል፡፡የዛሬውን የሞያሌ ሁኔታ አስመልክቶ የኢትዮጵያን ወገን መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሣካም፡፡
VOA NEWS

ተስፋሁንን መግደል ለኢህአዴግ ተስፋ ይሆናታልን….!?


bbb
አብዲሳ የብዙ ጊዜ ወዳጄ ነበር፡፡ በየገጠሩ እየዞርን በርካታ ስራ አብረን ሰርተናል፡፡ የዋህነቱ እጅግ በጣም አስገራሚ ነበር፡፡ በየክልሉ ስንዞር አበሉን የሚጨርሰው “ቸገረኝ” ላለው ሁላ መበስጠት እንደነበር አብረነው የሰራ ሁላ እርሱን የምንለይበት ባህሪው ነው፡፡ ይሄ ልጅ በአንዱ ቀን ለስራ ልንሄድ የተቀጣጠርንበት ቦታ ሆነን ስንጠብቀው ስንጠብቀው ሳይመጣ ቀረ… ስልኩን ብንደውልልት አይሰራም፡፡ ካለንበት እየተንቆራጠጥን… ወደ ሶስት ሰዓት ድረስ ዘግይተን ጠበቅነው የውሃ ሸታ ሆነብን… ምን ሆነ ብለን እየተጨነቅን እንጀራ ነውና ጉዟችንን ቀጠልን…
አብረን ስንጓዝ ከነበርነው መካከል አብዲሳን በቅጡ የምናውቀው ሰዎች “ይሄኔ አንድ የታመ ሰው አጋጥሞት ሆስፒታል ሳላደርስ አልሄድም ብሎ ነው…” ….ወይ ደግሞ “…አንዱ ገንዘብ ተቸግሮ አጋጥሞት  ምንም ሳያስቀር ገንዘቡን ሰጥቶ ወደ እኛ መምጫ ራሱ ተቸግሮ ይሆናል …” ካልሆነ ግን “…ዘራፊዎች አግኝተው ጉድ አድርገውት ሊሆን ይችላል…. እያልን መገመታችንን ተያያዝነው…
ግምታችን ሁሉ ትክክል አልነበረም፡፡
አብዲሳ በስንተኛው ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት መታየቱን ሰማን… በየዋህነቱ የተቸገረ በመርዳቱ የምናውቀው አብዲ “አሸባሪ” ተብሎ በመንግስት ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ አብዲሳ “አሻባሪ” ከተባለማ እኛ ምን ልንባል ነው… ብለን ራሳችንን እንደ ነውጠኛ የምናየው እኛ በጣም ተደነቅን!
አብዲ ወደ አምስት ወራት በማዕከላዊ፣ ወደ አምስት አመት በቃሊቲ እንዲሁም ሁለት ሶስት አመት ነው መሰለኝ በዝዋይ ማሰሪያ ቤቶች ቆይቶ ነፃ ነህ ተብሎ እስኪሰናበት ድረስ በአስር ቤቱ ውስጥ ሲደርስበት በነበረው መከራ ብዙ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ታድያ ከእስር ቤት ሊወጣ አካባቢ አንድ ባለስልጣን ብጤ ሰውዬ ጎብኝተውት ነበር፡፡
እስር ቤቱ እንዴት ነበር… ሲሉ ጠየቁት፡፡ አብዲሳ ምን አላቸው መሰልዎ… እስር ቤቱ እንዴት እንደሆነ ራስዎት ገብተው ካላዩት በስተቀር እንዲህ ነው ብዬ  ብነግሮት አይገባዎትም ፡፡ አላቸው፡፡
ይሄው ሰሞኑን ወንድማችን ተስፋሁን ጫመዳ በእስር ቤት በደረሰበት ስቃይ የተነሳ ህይወቱ ማለፏን ሰማን፡፡ ተስፋሁን በ1999 ዓ.ም መንግስት ኬኒያ ድረስ አፍኖ ወሳጆቹን ልኮ ለኬኒያ ፖሊስ ሽልጉን ከፍሎ፤ (የኬኒያ ፖሊስ እንኳንስ ከፍለውት እንዲሁም ጤዛ ነው) ብቻ በትብብር ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ ነበር… ከዛም በታሰረበት ሆኖ ሞተን ሰማን!
ለዚህ ጉዳይ የሚሰማ ቢኖር የኬኒያን መንግስት ራሱ ፍርድ ቤት ማቆም የሚገባ ይመስለኛል፡፡
ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ራሱ፤ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል እግዜሩም እኛም የምንጠይቀው ግን የገዛ መንግስታችን ነው፡፡ አዎ መንግስታችን እጁ ላይ የተለያዩ ሀገራት ብድር ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሰዎች እምባ የተለያዩ ሰዎች ደምም አለበት፡፡
ተስፋሁን ለምን እንዲሞት ተፈረደበት… እውን ለሀገሪቱ ደህንነት ስጋት ሆኖ ነውን… የሚለውን በፍጹም!!! ለማለት፤ እነ አብዲሳን ያየነው እኛ ምስክሮች ነን፡፡ ምስኪኑ አብዲሳ ስምንት አመት ታስሮ በነፃ ከመፈታቱ በፊት “የሀገር ስጋት ሽብርተኛ!” ተብሎ ነበር የታሰረው፡፡  በእስር ቤት የደረሰበትን ስቃይ ሰው ሆኖ መፈጠርን የሚያስጠላ ነው፡፡ የነገረኝን በሙሉ ለማሳየት በፊልም እንጂ ጽሁፍ የሚገልፀው አይደለም፡፡
እሺ ኢንጂነር ተስፋሁን የኦነግ ወይም የሌላ ተቃዋሚ አባል ወይም ደጋፊ ወይም እንዳሻቸው ይሁኑ ባይ ነው እንበለው፡፡ ግን እርሱን በመግደል የሚቃወሙ ሰዎችን ተስፋ ማስቆረጥ አልያም  ቁጥራቸውን መቀነስ ይቻላል….
ኢህአዴግ በጫካ እያለች ታጋዮቿ እና ሰላዮቿ ደርግ በቁጥጥር ስር ሲያውላቸው ቀጥታ አብዮታዊ እርምጃ ይወስድባቸው ነበር፡፡ ውጤቱ ግን ምንድነው  የሆነው… ብለው የጠየቁ እንደሆ፤  ውጤቱ ብሶቱን እያጠነከረው ቁጭቱን እያባሰው እምቢ ባይነቱን እያበረታው ነው የሄደው…!
ዛሬ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት ውስጥ ፍዳቸውን እያዩ ነው… የምር ለኢህአዴግ እናስባለን የምትሉ ሰዎች የእነ ተስፋሁን ግድያ የኢህአዴግ ተስፋ ሟጠጡን ያሳያልና…. ይሄ ነገር መሞቻሽ ነው ብላችሁ ምከሯት፡፡ እምቢ ካለች ግን መከራው ይመክራታል፡፡
ምክር!
ባለስልጣኖቻችን ሆይ እናንተ ማረሚያ ቤት የምትሏቸው እስር ቤቶች መግደያ ቤት እየሆኑ ነው፡፡ ብልጥ ከሆናችሁ…. አብዲሳ እንዳለው ራሳችሁ ገብታችሁ ሳታዩት በፊት በእስር ለሚማቅቁ ወገኖቻችን መላ ፈልጉ!
ተስፋሁን ጫመዳ ነፍሱን ከደህናው ስፍራ ያሳርፍልን! ለቤተሰቦቹም መጸናናትን ይስጥልን!
አቤ ቶክቻው

Monday, August 26, 2013

የአቶ መለስ ሞት እና ጥቅማጥቅሞቹ፤ ስላቅ እና ሀቅ



2012-03-02t171851z_319859376_gm1e83303nh01_rtrmadp_3_kenya
የአቶ መለስ ሞት እና ጥቅማጥቅሞቹ፤ ስላቅ እና ሀቅ
ሰላም ወዳጄ… ተጠፋፍተናል ግዴለም እቅ….ፍ አድርጌ ሰላም ልበልዎት… እንዴት አሉልኝ.. እኔ የምለው አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሞቱ እንደዋዛ አንድ አመት ሞላቸው አይደለም እንዴ… ወይ ጉድ ጊዜው እንዴት ይሮጣል ጃል… ምን እንደሚያመጣልን እንጃለቱ፤ አሯሯጡ ግን ወርቅ በወርቅ እንደሚያንበሻብሽ አትሌት ነው፡፡ ይሁና እኛ እንደሆነ “በርታ ግፋ” እያልን ከመደገፍ ወደ ኋላ አንልም… አረ እንደውም ጊዜ ሆይ፤ …ሩጥልኝ ልጄ አምልጠልኝ ልጄ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ለኔውም አልበጄ… ብለን እንደ ዶክተር ፈቃደ አዘዘ እንቀኛለን፤
እናልዎ ወዳጄ ዛሬ የመጣው ይምጣ ብዬ ሙት ወቃሽ አታድርገኝም ሳልል የአቶ መለስ መሞት ለሰፊው ህዝብም፣ ሰፊ መሆን ለተሳነው ኢህአዴግም፣ መጠን አልባ ለሆኑት ተቃዋሚዎችም በጣም ስንሳለቅ ደግሞ ለወይዘሮ ሀዜብ ሳይቀር በርካታ ጥቅማጥቅሞች አሉት ብዬ ልሟገትልዎ ነው…!
በ22 ዓመት ውስጥ ያየናቸው አቶ መለስ እንደው ዝም ብለው የእነ ስምሃል አባት እንደው ዝም ብለው የነ ወይዘሮ አዜብ ባለቤት እንደው ዝም ብለው የአቶ ዜናዊ አስረስ ልጅ ብቻ አልነበሩም፡፡ አቶ መለስ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ኢህአዴግ ሊቀመንበር ከዛም ውስጥ ደግሞ እጅግ አደገኛ የሚባለው ህውሃት አባወራ የሀገሪቱ ጦር ሃይሎቹ አዛዥ (አሃ ለካስ ጦር ሃይሎች የድሮው ነው… እንደው የድሮ ስርዓት ናፋቂ የሆንኩ ሰውዬ… አሁን መከላከያ ነው ማለት ያለብን… በመከላከያው ውስጥ ጦር አለ ከተባለ እንኳ ጦሩ አቶ መለስ ነበሩ… ስለዚህ የጦር ሃይሎች አዛዥ ሳይሆኑ በመከላከያ ውስጥ ጦር የሆኑ ሰውዬ ነበሩ ብሎ አለመመስከር ጡር ነው… ) በጥቅሉ ሰውዬው የመላዋ ኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ ነበሩ፡፡
አሁን እኒህ ሰውዬ ሞተዋል… እስቲ ከተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ጋር አያይዘን የሞታቸውን ጥቅማ ጥቅሞች እንዘርዝር…
ለአባይ ግድብ ሲሉ አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!
አባይን አቶ መለስ እንዴት እንዴት ይገደብ ብለው እንደጀመሩት ተነጋግረን ተነጋግረን መቼም ከስምምነት ላይ የደረስን መስለኛል፡፡ አባይዬ ድንገት ያለ ዕቅድ… ያቺ እነ ሙባረክን እንደ ሾላ ፍሬ ርግፍ ርግፍ ያደረገች አብዮት ወደ እኛም ትመጣ ይሆናል… በሚል ስጋት ነው ለማስቀየሻ ተብላ ነው የተጀመረችው፡፡
ለዚህ ዋና ማስረጃ በአምስት አመቱ ትራስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ አለመፃፏ ሲሆን ሌላው ደግሞ የፕሮጀክቷ ስም አሁንም አሁንም መቀያየሩ ድሮውንም ቃሚዎች “በምርቃና” እንደሚሉት አይነት የታሰበች ድንገቴ ስራ መሆኗን ያሳብቃል፡፡ በነገራችን ላይ አሁንም ጭምር በተለይ ውጪ ሀገር የሚኖሩ “የኢህአዴግ ወጣት ክንፎች” የአባይን ግድብ “ሚሊንየም ዳም” ነው የሚሏት…! ህዳሴ መባሏን ከነጭርሹም አለሰሙም!
የሆነው ሆኖ አባይን አቶ መለስ ድንገት እንደጀመሯት ሁሉ ድነገት ያቋርጧታል የሚል ስጋት ሰቅዞ የያዛቸው ብዙዎች ነበሩ… (ብዙዎች ያልኩት አካብዶ ለማውራት እንዲመቸኝ ብዬ እንጂ… እንዲህ የሚያስቡት ምን ያህል ብዙ እንደሆኑ ስታስቲክስ አልሰራሁም፡፡ ነገር ግን ያናገርኳቸው ሁሉ የሰጡኝ ማብራሪያ አሳማኝ ነበር፡፡)  እንደሚታወቀው አባይን ለመገደብ የሚጠይቀው የገንዘብ አቅም ቀላል አይደለም፡፡ በየመስሪያቤቱ በጥፊም በርግጫም የሚደረገው መዋጮ አስከምን ድረስ እንደሚያስኬድ የሚያውቁት እርሳቸው ብቻ ነበሩ… እናም የሆነ ቀን የሆነ ቀን ማጣፊያው ያጠራቸው ቀን መለኛው መሌ በሆነ መላ ግንባታው እንዲቋረጥ ያደርጉ ነበር የሚለው ነገር ውሃ የሚያነሳ ሆኖ አግኝቼዋለሁ… ይህንን እያንሰላሰልን ታድያ ምን ይበጃል እያልን ስንጨነቅ አቶ መለስ ሞቱ… ለአባይ ሲባልስ እንኳን ሞቱ! ልክ እርሳቸው ሲሞቱ ሌጋሲን ማስቀጠል በሚለው መርህ ከዋናዎቹ አንዱ አባይ ግድብ አይቋረጥም የሚለው ሆነ፡፡ እሰይ እንኳንም አልተቋረጠ፡፡ እንኳንም ሞቱልን…!
ለተቃዋሚዎች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!
ተቃዋሚዎች በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግን ሲቃወሙ ከሁሉ በላይ የሚበረታባቸው የአቶ መለስ ግልምጫ ሽሙጥ እና እርምጃ ነበር፡፡ ሲያሻቸው ጣት እንቆርጣለን እያሉ ሲያሰኛቸው ሰብስበው እስርቤት እየላኩ አቶ መለስ ተቃዋሚዎች ላይ እንደሚጨክኑት ኢህአዴግ አይጨክንባቸውም፡፡ እውነቱን እንበለው ካልን ደግሞ መጨከን ብቻም ሳይሆን በፖለቲካው ቼዝም አቶ መለስን ተቃዋሚዎቹ አይችሏቸውም ነበር፡፡ ተቃዋሚዎቹ ፈረሳቸውን ቆስቁሰው ገና “ቼ…” ብለው ሮጥ ሮጥ ማለት ሲጀምሩ መለስ በወታደሮቻቸው ፈረሶቻቸውን እየሰነከሉ፤ ንግስታቸውን “ቼዝ” እያሉ ተቃዋሚዎቹን መላወሻ አሳጥተዋቸው ነበር፡፡
አሁን አቶ መለስ ሞተውላቸዋል፡፡ ተቃዋሚዎች መቼም ጨካኞች እንዳይባሉ ሰግተው በአቶ መለስ ሞት ሀዘናቸውን ሲገልፁ ቢሰማም ውስጥ ውስጡን ግን እሰይ ግልግል እንደሚሉ ማወቅ አያቅተንም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ተቃዋሚዎቹ ትንሽ ጠንከር ካሉ ኢህአዴግ ውስጥ ክፉኛ የሚገዳደራቸው አለ ብሎ ማመን ይቸግራል፡፡ ስለዚህም ለተቃዋሚዎች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!
ለራሱ ለኢህአዴግ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!
በተለይ ከሆነ ጊዜ በኋላ ይመስለኛል ህውሃት ለሁለት ቃቃቃ…ቃ ብሎ ከተሰነጠቀ ጊዜ በኋላ የኢህአዴግ ስብዕና ኮስምኖ የአቶ መለስ ዜናዊ ስብዕና ደግሞ እጅግ በጣም የጎላበት ወቅት ነበር፡፡ አረ ከነጭርሹ መለስ ከልለውን ኢህአዴግን ማየት ተስኖን ነበር…! በዛ አያያዙ ጥቂት አመታት ቢገፉ ኖሮ ኢህአዴግዬ መለስ በተባለ ቅብ ተሸፍና እሰከመፈጠሯም እንረሳት ነበር፡፡
አሁን ግን መለስ ሞቱ ኢህአዴግ የሚባል ፓርቲም ምን አይነት ቅርጽ እና መልክ እንዳለው ሊታወቅ በቃ፡፡ ታድያ ለኢህአዴግ ሲባል ቅርፀ ግንባሯ እንዲታይ ሲባል፤ ያለ መለስ መኖር እንደምትችል ለማሳየት ሲባል፣ እንኳን መለስ ሞቱላት ብንል ምን ግፍ ተናገርን ይባላል፡፡
ወላ ለወይዘሮ አዜብ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!
መጣች ስላቋ… ወይዘሮ አዜብ ቀላል ክብሮ ሆኑ እንዴ…! ክብሮ ማለት አራዶቹ ከበረ ከሚለው አማርኛ ቃል የወሰዷት ስትሆን የተከበረ ለሚባል ሰው የሚሰጥ ማዕረግ ነው፡፡ አዎ ወሮ አዜብ ክብሮ ሆነዋል፡፡ የመለስ ፋውንዴሽን ፕረዘዳንትነት አቶ  መለስ ባይሞቱ ኖሮ ከየት ይመጣ ነበር… አረ እንኳን ሞቱላቸው… (እዝችጋ እንኳ ጨክኛለሁ ይቅር ይበለኝ!) የምር ግን ወይዘሮ አዜብ እንደልቸው መልካም ገፅታቸውን እንዲገነቡ የአቶ መለስ ሞት ትልቅ እድል ሰጥቷቸዋል ብዬ አምናለሁ… ዝም ብለን ከመረመርን ወይዘሮ አዜብ በአቶ መለስ ሞት ጉዳት እንደገጠማቸው ሁላ በርካታ ትቅማጥቅሞችንም እንዳገኙ ግን መጠርጠር አያቅተንም!
ለችግኝ ተከላ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!
አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት ዘመናቸው እና በበትረ ስልጣናቸው ጊዜ ሰዎች አጥብቀው የሚያማርሯቸው በችግር ተከላ ነበር፡፡ አሁን ግን ሞቱ፣ አመትም ሞላቸው በስማቸውም በርካታ ችግኞች እየተተከሉላቸው ነው፡፡ በእውኑ ለእነዚህ ችግኞች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ ብንል ማነው እርኩስ የሚለን…! ማንም!

ኖርዌይ ኤምባሲ እና ኢ/ር ኃይሉ እየተወዛገቡ ነው


August 26, 2013 Sodere News in Amharic - ሶደሬ ዜና 



“ያከራየኋቸውን ቤት ለመልቀቅ እምቢተኛ ስለሆኑ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቄያለሁ” ኢ/ር ኃይሉ ኖርዌይ ኤምባሲ ከኢ/ር ኃይሉ ሻውል የተከራየውን ባለ ሁለት ፎቅ የመኖሪያ ህንፃ ለ15 አመታት ሲጠቀምበት እንደቆየ የገለፁት የአዲስ አድማስ ምንጮች፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ውዝግብ የተፈጠረው ቤቱን ልቀቅ፣ አልለቅም በሚል ነው ብለዋል፡፡ በ97 ምርጫ የምርጫ ዘመቻ ቅንጅትን በፕሬዚዳንትነት የመሩት ኢ/ር ኃይሉ ሻውል፣ ከኤምባሲው ጋር በነበራቸው የኪራይ ውል መሰረት ከ7 ወራት በፊት ቤቱን እንዲያስረክባቸው እንደጠየቁ ተናግረዋል፡፡ በ3200 ካሬ ሜትር ግቢ ውስጥ የተሰራው ባለ ሁለት ፎቅ መኖሪያ ህንፃ በ1200 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ነው፡፡

ቤቱን ስለምንፈልገው ልቀቁልን በማለት ከሰባት ወራት በፊት በደብዳቤ ብንጠይቅም፤ ኤምባሲው ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነም የሚሉት ኢ/ር ሃይሉ፣ ከአንድ አመት በፊትም ኤምባሲው ቤቱን እለቃለሁ ቢልም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል ብለዋል፡፡ “ቤቱን በትክክል ከፈለጋችሁት ግዙን” በማለት ለኤምባሲው አማራጭ አቅርበው ተቀባይነት እንዳላገኘም ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ጉዳዩን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሳወቃቸውን ኢ/ር ኃይሉ ጠቅሰው፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ኤምባሲው ቤቱን እንዲለቅ ጥያቄ አስተላልፏል ብለዋል፡፡

“ህግና ስርዓትን ተከትዬ ቤቱን እንዲለቁ በትዕግስት ጠብቄያለሁ፡፡ እምቢ ካሉ በግል ንብረቴ ከእነርሱ ጋር እንካ ሰላንቲያ አልገጥምም” ያሉት ኢ/ሩ፤ ጥቁርን በመናቅና በማን አለብኝነት የሚካሄደውን ህገወጥነት ፈፅሞ አልቀበልም ብለዋል፡፡ ኤምባሲው የያዘብኝ ቤት ከመኖሪያ ቤቴ ጋር በአጥር ስለሚገናኝ በቤቴ በኩል አፍርሼ በመግባት ግቢውን ለማስተካከል ወስኛለሁ ብለዋል ኢ/ር ኃይሉ፡፡ ወደ ኤምባሲው በተደጋጋሚ ደውለን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ምክትል አምባሳደሯን ለማነጋገር ብንሞክርም “አሁን ቴሌ ኮንፈረንስ ላይ ነኝ፤ ማናገር አልችልም” የሚል ምላሽ በፀሀፊያቸው በኩል ተናግረው፤ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡

ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፕሮቶኮል ክፍል ደውለን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሀላፊ ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም ለስብሰባ ከግቢ ውጭ ናቸው በሚል ምላሽ ልናናግራቸው አልቻልንም፡፡


Written by ናፍቆት ዮሴፍ, AddisAdmassNews.com

Small plane crashes; Ethiopian family escape without injury


BOWIE, Md. — A single-engine airplane crashed in a cornfield near an airport in Bowie and all four occupants escaped without injury.

The Maryland State Police says the crash happened Saturday before 10 a.m. at the Freeway Airport. Officials say the plane, a Cessna Skyhawk, was trying to land when the aircraft veered from the runway and wound up upside down in the cornfield.


The plane is owned by the airport, and officials say the group had rented the aircraft and were on a sightseeing flight.

Maryland State Police identified the pilot as 43-year-old Edwardo Grigsby of Brandywine, Md. His passengers were 38-year-old Tsige Safo of Alexandria, Va., and her son and daughter, 14-year-old Nahom Ebssa and 9-year-old Eban Ebssa.

By the time troopers arrived all four had exited the aircraft.

Sunday, August 25, 2013

የሌላውን ትግል ለማዳፈን መሯሯጥ ለውድቀት!


August 24, 2013

ነሃሴ 18 ቀን 2005
ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ የገባው የሰማያዊ ፓርቲና የ‘33ቱ’ ፓርቲዎች የውዝግብ ዜና የተስፋ ጭላንጭል የተፈጠረለትን የዋህ ህዝብ እጅግ ቅር ያሰኘና ያሳዘነ እንደሆነ ከራሳችን የተጎዳ ስሜት በመነሳት ስለተረዳን፤ ‘የተቃዋሚ ድርጅቶቻችን ይማሩበት ዘንድ’ በሚል የየዋህ መንገድ ይህችን ኣጭር መልዕክት ለማስተላለፍ ተገደድን።
በሃገራችን የፖለቲካ ታሪክ ድርጅቶች በሰለጠነ መንገድ ልዩነታቸውን በውይይት መፍታት ሲችሉ አልያም በልዩነታቸው ተቻችለው ሲጓዙ ሰምተን አናውቅም። ተቃዋሚ ድርጅቶቻችን በጋራ ለነፃነት ከመታገል ይልቅ እርስ በእርስ ከመናቆር ጀምሮ እስከመጠላለፍ ሲደርሱ ማየት የተለመደ ሆኗል። ይህ የድርጅቶች የእርስ በእርስ ግጭት የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነትና ፍትህን እየናፈቀ እንዲኖርና ገዢዎች በማናለብኝነት ያሻቸውን እየፈጸሙ፤ ህዝብም ሰባዊነቱን ተገፎ፣ አንገቱን ደፍቶ፣ እንዲኖር ከማድረግ ሌላ ምንም ፋይዳ እንዳላስገኘ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያውቃል። ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመኘው ድርጅቶች መጠላለፉን ትተው በጋራ የሚሰሩበትንና በመቻቻል የሚኖሩበትን ጊዜ ብቻ ነው። እዚህ ላይ ተቃዋሚ ድርጅቶቻችን ሊረዱት የሚገባው፤ እነርሱ እርስ በእርስ ሲጠላለፉ፤ ስንቱ ንጹህ ዜጋ በማያውቀው ሃጥያት በዘረኛው የወያኔ መንግስት እየተደበደበ፣ እየተገደለ፣ እየተሳቀቀ፣ በገዛ ሃገሩ እያለው እንደሌለው በረሃብና በእርዛት እያለቀ እንደሚገኝ፣ ሳይወድ በግዱ በቁጭት ባዶ ተስፋን እያለመ እንደሚኖር ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በምናያቸው የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች በሚያደርጉት ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች ያልተደሰተ ፍትህ ናፋቂ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብለን መገመት እጅግ ከባድ ነው። እኛም እንደ ኢትዮጵያዊነታችን ስንመኘው ለነበረው የትግል አቅጣጫን ስላመላከተን በቅርበት ከመከታተል ጀምሮ እስከ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን የምንችለውን ሁሉ ልናበረክት ቃል በመግባት እየተንቀሳቀስን እንገኛለን። ይህ የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች እንቅስቃሴ በዚሁ ከቀጠለ የምንናፍቀውን ዲሞክራሲ፣ የምንመኘውን ነፃነትና፣ የምናልመውን የህዝብ የበላይነት ከማየት የሚያግደን አንዳችም ምክንያት አይኖርም። ስለሆነም ድርጅቶቻችን ሊወደሱና ተግባራቸውም እሰየሁ ሊባልና ሊበረታታ ይገባል እንላለን።
ምንም እንኳን እያንዳንዱ የፖለቲካ ድርጅት በትግሉ ዙሪያ መሳተፍ የራሱ የሆነ አስተዋፅዎ ቢኖረውም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሌላውን ለመጥለፍና ትግሉን ለማሰናከል ቅርብ የሆኑ ተቃዋሚዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ግልፅ ነው። አበው እንዳሉት “እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር” ይበጃልና፣ ህገመንግስቱ የሚፈቅድለትን መብት በመጠቀም በዘረኛው የወያኔ መንግስት የተጫነብንን አመታት ያስቆጠረውን የተቃውሞ ሰልፍ የማድረግ እገዳን በመስበር ፍርሃታችንን መሰባበር የቻለውን የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባላትን ልናመሰግን እንወዳለን።
በዚህ ኣጋጣሚ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባላት ነፃነት በትግል እንጂ በልመና አይገኝምና በርቱ እያልን፤ ለሌሎች የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎቻችን የዲሞክራሲን የመናገርና የመፃፍ ነፃነት ምን ማለት እንደሆነና እንዴት ማስተናገድ እንዳለባቸው ቀድመው ማወቅ ይገባቸዋል ብለን እናምናለን።ይህ ካልሆነ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ ስርዓት ለይቶ እንደማያያቸው እናምናለን። የኢትዮጵያ ህዝብ እውነትን የመለየት ችሎታውም፣ ብቃቱም፣ ልምዱም እንዳለው ሁላችንም ልንረዳ ይገባል። ስለሆነም ተቃዋሚ ድርጅቶቻችን የዲሞክራሲን ምንነት ለማወቅና ስ ህተታቸውን ለማስተካከል ቢሞክሩ እጅግ የተሻለ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ሌላ ዲክታተር የሚያስተናግድበት ጫንቃና ጀርባ ከእንግዲህ የለውም።ስለዚህ ከምቾትና ከፍርሃት ዞናቸው በመውጣትና በመተባበር ህዝብ ለነፃነቱ የሚያደርገውን ትግል ሊቀላቀሉ ይገባል። ይህ ካልሆነ ደግሞ ቢያንስ በመሬት ላይ ጥሩእየሰሩና እየሞከሩ የሚገኙትን ለመጥለፍና ትግሉን ለማፈን ከመሞከር ቢታቀቡ እጅግ መልካም ነው ስንል ምክራችንን እንለግሳለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
ስምንቶቹ

ሕወሐት በአዜብ ጉዳይ ተወጥሯል (ኢየሩሳሌም አርአያ)


August 25, 2013

ከኢየሩሳሌም አርአያ

ለስድስት አመት ኤፈርትን ሲመሩ የቆዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከሃላፊነት መነሳት ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ውጥረት መንገሱን ምንጮች አመለከቱ። የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ባለቤታቸው አቶ መለስ አማካይነት ዳይሬክተር ተደርገው አዜብ መሾማቸውን ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ ቦታውን የተረከቡት ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሃጎስ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የቦርዱ መሆኑን ያስረዳሉ። አዜብ ከኤፈርት እንዲወገዱ የተደረገው ግን በነቴዎድሮስ ሃጎስ ሳይሆን ስብሃት ነጋ ባቀነባበሩት ጣልቃ ገብ ውሳኔ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀዋል። በኤፈርት የተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች አዜብ በመባረራቸው ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ አያይዘውም ደስታቸውን በስብሰባ ጭምር ከመግለፅ ባለፈ፥ « አዜብ ከኤፈርት ጀምሮ ለፈፀሟቸው የሙስና ወንጀሎች በሕግ መጠየቅ አለባቸው» በማለት አቋም እስከ መያዝ መድረሳቸውን አስታውቀዋል። 

ከዚህ በስተጀርባ በበቀለኝነታቸውና የጥፋት ሴራ በማቀነባበር የሚታወቁት ስብሃት ነጋ እንዳሉበትና ከኤፈርት ስልጣናቸው ያስነሷቸውን አዜብ ከጨዋታ ውጭ ከማድረግ ባለፈ በሙስና እንዲጠየቁ በየአቅጣጫው ጫና እያሳደሩ መሆኑን ምንጮቹ አስረድተዋል። በአዜብ ተፈፀሙ ተብለው ከተነሱት የሙስና ወንጀሎች በኤፈርት ስም 200 ከባድ ተሽከርካሪዎች አቶ ነጋ ገ/እግዚያብሄር ቀረጥ ሳይከፍሉ እንዲያስገቡ ማድረጋቸውን፣ በሚሊዮን የሚገመት ቀረጥ ሊከፈልባቸው የሚገቡ የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎች፣ በኤፈርት ገንዘብ ሶስት መርከብ ስሚንቶ የፍራንኮ ቫሉታን ሕግ በመተላለፍ ቀረጥ ሳይከፈልበት አገር ውስጥ መግባቱ፣ ክሶች እንዲቋረጡ ትእዛዝ በመስጠት..የሚሉት በዋነኛነት መነሳታቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል። ( አዜብ ከኤፈርት እንደሚነሱ ከዚህ ቀደም በወጡ ዘገባዎች ምንጮችን በመንተራስ መገለፁ ይታወሳል)
Azeb Mesfin, the wife of Meles Zenawi
ይህ በእንዲህ እንዳለ – በአዜብ ቦታ የተተኩት ብርሃነ ኪ/ማርያም (በቅፅል ስማቸው ብርሃነ “ማረት”) ሲሆኑ፣ ከመለስ በፊት የአዜብ ፍቅረኛ የነበሩና ከሱዳን ተያይዘው በመምጣት ሕወሐትን እንደተቀላቀሉ ምንጮች አስታውሰዋል። ድርጅቱን ከተቀላቀሉ ከጥቂት ወራት በኋላ ሁለቱ (አዜብና ብርሃነ) የፍቅር ግንኙነታቸውን እንዲያቋርጡ ከበላይ አመራር መወሰኑን፣ አዜብ ከመለስ ጋር ግንኙነት መቀጠላቸውን ይገልፃሉ። ፓርቲው ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ብርሃነ በመቀሌ ማዘጋጃ ቤት ተመድበው ሲሰሩ «ለመንገድ ስራ ከተመደበ ገንዘብ አምስት ሚሊዮን ብር ተዘርፏል» በሚል በሙስና እንዲባረሩ መደረጉን ምንጮች ጠቁመዋል። አዲስ አበባ የመጡት ብርሃነ ብዙ ጥረት አድርገው አዜብ ዘንድ (ቤተ መንግስት) የመግባት አጋጣሚ ያገኛሉ። ባቀረቡት አቤቱታና ተማፅኖ መሰረት ሲቪል ሰርቪስ እንዲገቡ አዜብ ትእዛዝ ያስተላልፋሉ። ከኰሌጁ እንደወጡ የማ.ረ.ት. ሃላፊ ተደርገው በመለስ የተሾሙት ብርሃነ፣ በተለይ ከ1993ዓ.ም በኋላ የመለስ ቀኝ እጅ በመሆን በአውሮፓና አሜሪካ ያለውን የፓርቲውን መዋቅርና ስለላ በመምራት፣ አምባሳደሮችን በማስፈራራት፣ በማዘዝና ፈላጭ ቆራጭ ውሳኔ በማሳለፍ ታማኝ አገልጋይ ሆነው እንደቆዩ ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሞት በኋላ ግን የስብሃት ነጋ ተከታይና አስፈፃሚ በመሆን አሰላለፋቸውን ቀይረው እንደቀጠሉ አያይዘው ገልፀዋል። ስብሃትና ብርሃነ ዝምድና እንዳላቸው የጠቆሙት ምንጮች፣ አዜብን በማስነሳት ብርሃነ እንዲቀመጡ ያደረጉት ስብሃት መሆናቸውን አመልክተዋል።