
ሀገራችን
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት ተርታ መሆኗ ይታወቃል፡፡ ከአፍሪካ ብቻ ደግሞ
እንዳይመስለን ከአለምም ፈጣን እድገት እስመዘገቡ ካሉ ግንባር ቀደሞቹ ውስጥ ናት፡፡ ከዚህ አርፍተ ነገር ጋር
ልንጋጭ ነው… ልንጋጭ ነው…. ቀበትዎትን ያጥብቁ ራስዎን ያዘጋጁ….
ኢትዮጵያ በምድር ላይ ካሉ ደሀ
ሀገሮች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
በዚህ ዝርዝር ውስጥ የሚገኙት ሀገሮች በሙሉ አፍሪካዊ ሀገሮች ሲሆኑ ሱማሌ እንኳ
ከአቅሟ ስድስተኛ ሆና፤ ባለ ፈጣን እድገቷ ኢትዮጵያ እንደ አትሌቲክስ ሩጫው ሁሉ በድህነት ሩጫም የሚደርስባት
ሳይገኝ ሁለተኛ መውጣቷ የሃያ ሁለት አመት ልፋታችን ውጤት ነው ሲሉ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የለመኑን ባለስልጣን
ጠቅሰዋል፡፡ ወሬው የተገኘው ዘ አፍሪካን ኢኮኖሚስት ከተባለ ድረ ገጽ ነው፡፡
ቆይማ እንደውም ከአንድ እስከ አስር ያለውን ዝርዝራቸውን ኮፒ ፔስት ላድርግልዎ…
- Niger
- Ethiopia
- Mali
- Burkina Faso
- Burundi
- Somalia
- Central African Republic
- Liberia
- Guinea
- Sierra Leone
አሁንም እንላለን፤ እንኳንም ሁላችንም ተያይዘን ደሃ አልሆንን፡፡ የሀብታም ሀገራት ባልስልጣኖች ልብ ካላቸው፤ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እስመዘገቡ ካሉት ባለስልጣኖቻችን እና ከልጆቻቸው ጋር ጋር ይፎካከሩ!
No comments:
Post a Comment