Thursday, November 28, 2013

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!



በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንምመከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።

ወያኔ ስላልቻለ ነው እንጂ ይህንን ከአለም አጽናፍ እስከ አለም አጽናፍ ያስተጋባ የወገን ደራሽ ድምጻችንን አዲስ አበባ ላይ እንደ አደረገው በሃይል ለማፈን ወደኋላ አይልም ነበር።
ሀፍረት የለሾቹ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች ይህን የተጋለጠ ሀገርና ህዝብ አዋራጅ ተግባራቸውን እና በውሸት የተበከለ ገመናቸውን ለመሸፈን ከዚያም አልፈው የዋሆችን በማታለል የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ የተለመደ ቲያትር መስራቱን ተያይዘውታል። ቴዎድሮስ አድሃኖም ችግሩ ባለበት በሳውዲ መሬት ላይ ሳይሆን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በራሱ ወጪ አሳፍሮ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ባፈሰሳቸው ኢትዮጵያውያን መሃል እየተጎማለለ ያዛኝ ቅቤ አንጓች ቲያትሩን ሲሰራ ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይታይበትም።
እነዚሁኑ ወደ ሀገር የተመለሱ አእምሯቸው በችግር የተመሰቃቀለ ዜጎች ወደ ካሜራ እየገፉ ስለ ሳውዲ ኤምባሲያቸውና ስለመንግስታቸው ‘ድንቅ” አገልግሎት እንዲናገሩ ያስጠኗቸውን ተመሳሳይ አረፍተ ነገር መስማት የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ ተወዳዳሪ የሌለው ኮሜዲ ይወጣው ነበር።
እውነቱ ዛሬ በሀገራችን የሰፈነው ስደትና አብሮት የሚመጣው መከራ ሁሉ ዋናው አምራች ፋብሪካ ወያኔ መሆኑ ነው። ወያኔ የገነባው ጥቂት ጀሌዎቹንና ሎሌዎችን ተጠቃሚ ያደረገና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተለይ ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደረገው ስርአት ነው። የስደታችንና የመከራችን ምንጭ ስደት የሚመጣው በሀገር ተስፋ መቁረጥ ነው። እንጀራ ፍለጋና ጭቆናና አፈና ሽሽት አምልጠን በየባዕድ ሀገሩ እንድንከራተት የሚያደርገን የወያኔ ስርአት ነው። በታሪካችን ውስጥ ተሰደን በባዕድ የተዋረድነው በወያኔ ምክንያት ነው።
በሀገር ውስጥ በአፈና ስር ሆናችሁ፣ በውጪው አለምም በየኢምባሲው የምታሰሙት ጩኸትና የምታፈሱት እምባ እብሪትና ትእቢት ያደነደነውን፣ ዝርፊያ ያደነዘዘውን የወያኔን ልብ እንደማያሸብረው ማወቅ አለብን።
የወያኔ ሹማምንቶች ይግረማችሁ ብለው ከአላንዳች ሀፍረት ያውም በሳውዲ አረቢያ ወጪ ተጓጉዘው ሀገር የገቡትን ግራ የተጋቡ ስደተኞች ለፖለቲካቸው ማሳመሪያ በቴሌቪዥን ስእልና ፎቶግራፍ መነሻ ሲያደርጉትና ለፖለቲካ ስራ መሳሪያ ሲያውሉት እያየን ነው። በነሱ ቤት ብልጥ ፖለቲከኞች መሆናቸው ይሆናል። በኛ ቁስል ላይ እንጨት እየሰደዱ መሆናቸውን ግን ፈጽሞ አይሰማቸውም።
ወያኔ በመካከለኛው ምስራቅ ተሰደው ለፍተው የሚኖሩት ወገኖቻችን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ያውቃል። ቢያንስ በየኢምባሲው ያስቀመጣቸው ነጋዴዎች ይነግሩታል። ችግሩን እንዳላየና እንዳልሰማ የሚያየው ከዜጎች ይልቅ እነሱ አፈር ግጠው ለፍተው ለሚያመጧት የውጪ ምንዛሬ የበለጠ ፍቅር ስላለው ነው። በዚህ ተግባሩ ወያኔ ወገኑን የሸጠ ባሪያ ፈንጋይ ነጋዴ እንጂ የመንግስት መሪ መሆኑ ያጠራጥራል።
ግንቦት 7 የፍትህና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዘወትር እንደሚለው ሁሉ ይህ የዜግነትና የሀገር ውርደት፣ ይህ ሁሉ የወገን መከራ የሚቆመው የዚህ ሁሉ መሰረት የሆነው ወያኔና ስርአቱ ከመሰረቱ ሲነቀልና ሲወገድ መሆኑን ላፍታም አይዘነጋውም።
እንባችን የሚደርቀው ደማችን በየቦታው መፍሰሱ የሚቆመው መብታችን እንደዜጋ ተከብሮ ቀና ብለን የምንሄድበት ሀገር በትግላችን የተቀዳጀን ጊዜ ብቻ ነው።
ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ በያላችሁበት ግንቦት 7 ሁኑ!! እኛ ከዚህ ውርደት ሞቶ የሚገኘው ነጻነት ይሻላል ብለን የተነሳን ልጆቻችሁ ነን። እርሰዎስ?
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ኢትዮጵያና ዩኤስ አሜሪካ በኬኔዲ ዘመን

ባለፈዉ ሳምንት ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ የተገደሉበትን 50ኛ ዓመት ዘክራ ዉላለች። እንደ ጎርጎረሳዉያኑ ህዳር 22 ፤ 1963 ዓ,ም ቀትር ላይ በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በጥይት የተገደሉት ፕሬዚደንት ኬኔዲ ሰለባ የሆኑት ስልጣን ላይ ከወጤ ሶስተኛ ዓመታቸ ን ሊይዙ ትንሽ ወራቶች እንደቀራቸዉ መሆኑን ዘገባዎች ያሳያሉ።
USA _Präsident John F. Kennedy und Kaiser Haile Selassie von Äthiopien im Weißen Haus. Fahrzeugkolonne durch Washington, Oktober 1 1963 
Titel: In Memory of 50th Anniversary of JFK 
Autor/Copyright: Prince Ermias Sahle-Selassie 2013(der Enkel von Kaiser Haile Selassie von Äthiopien lebt in USA)
Rechte geklärt, via: DW/Azeb Tadesse Hahn
ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ በዚያ ወቅት ከኢትዮጵያዉ ንጉሰነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደነበራቸዉ ተመልክቶአል። በተለይ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ከመገደላቸዉ ከአንድ ወር ቀደም ብሎ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አሜሪካንን መጎብኘታቸዉ ይነገራል። በለቱ ዝግጅታችን ጆን ኤፍ ኬኔዲ የተገደሉበትን 50ኛ ዓመት በማስመልከት፤ ኢትዮጵያ በጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ዘመነ ሥልጣን ከአሜሪካ ጋር የነበራትን ግንኙነት እንቃኛለን ።
ዩናይትድ ስቴትስ በታጣቂ የተገደሉትን የሀገሪትዋን 35 ተኛ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ 50 ዓመት ዘክራ ዉላለች። በዚህ ቀን የሀገሪትዋ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ ተዉለብልቦአል። ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ በተገደሉበት ሃምሳኛ ዓመት በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ ልክ ከ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ተኩል ላይ ልዩ ስነ-ስርዓት መካሄዱ ተነግሮአል። ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ካለፉት 50 ኛ ዓመታት ወዲህ እጅግ ተወዳጁ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት መሆናቸዉም ተዘግቦአል።
WASHINGTON, DC - OCTOBER 1: Ethiopian Emperor Haile Sellassie I (C) and his granddaughter Princess Ruth Desta are welcomed by U.S President John F. Kennedy and his wife Jackie (2d L) 1st October 1963 in Washington. After having led the revolution in 1916 against Lij Yasu he became regent and heir to the throne, westernizing the institution of his country. Settled in England after the Italian conquest of Abyssinia, he was restored in 1941 after the British liberation. In the early 1960s he helped to establish the Organization of African Unity. The disastrous famine of 1973 led to economic chaos, industrial strikes, and mutiny among the armed forces, and he was deposed 12 September 1974 in favour of the Crown Prince. He die in 1975. (Photo credit should read STAFF/AFP/Getty Images)
ኢትዮጵያ በጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ዘመነ ሥልጣን ከዩኤስ አሜሪካ ጋር ጥሩ የወዳጅ ነት ግንኙነት እንደነበራት ቢታወቅም ጆኔፍ ኬኔዲ በተለይ ከኢትዮጵያዉ ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንደነበራቸዉ ዘገባዎች ያመላክታሉ። በዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪ የሆኑት የንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ልዑል ኤርምያስ ሳህለ ስላሴን በስልክ አግኝተን ጠይቀናቸዉ ነበር፤
የ 53 ዓመቱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ልዑል ኤርምያስ፤ የልዑል ሳህለ ስላሴ እና የልዕተ ማህፀንተ ሃብተማርያም ብቸኛ ልጅ ናቸዉ። እንደ ልዑል ኤርምያስ፤ በጆኔፍ ኬኔዲ ዘመን ስልጣን፤ አንዳንድ ዘመናዊ ስልጣኔ ገብቶአል፤
በጆኔፍ ኬኔዲ የስልጣን ዘመን እድሜም የደረሰ ስለነበር ብዙ ነገሮችን አአስታዉሳለሁ ያሉን በተመድ 28 ዓመታት ያገለገሉት እና በጡረታ ላይ የሚገኙት አቶ ኪዳኔ አለማየሁ፤ ቀደም ሲል ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አሜሪካንን ብዙ ግዜ ቢጎበኙም፤ እንደ ጆኔፍ ኬኔዲ በደማቅ አቀባበል አልተደረገላቸዉም ሲሉ ይገልጻሉ፤
የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸዉን ኢትዮጵያ እንደተከታተሉ የሚገልፁት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ልዑል ኤርምያስ፤ በኢንግሊዝ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸዉን በመቀጠል፤ በዩናይትድ ስቴትስ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን እንደተከታተሉ ተጠቅሶአል። ልዑል ኤርምያስ ጃንሆይ ጆኔፍ ኬኔዲ ሊገደሉ አንድ ወር በፊት አሜሪካን እንደነበሩ ገልፀዉልናል።
የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸዉን ኢትዮጵያ መከታተላቸዉ የተመለከተዉ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ልዑል ኤርምያስ፤ በኢንግሊዝ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸዉን በመቀጠል፤ በዩናይትድ ስቴትስ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን እንደተከታተሉ ተጠቅሶአል። ልዑል ኤርምያስ ጃንሆይ ጆኔፍ ኬኔዲ ሊገደሉ አንድ ወር በፊት አሜሪካን እንደነበሩ እንዲህ ያስታዉሳሉ።
ቀድሞ በተመድ ሰራተኛ የነበሩት አቶ ኪዳኔ አለማየሁ፤ በበኩላቸዉ ምንም እንኳ በዚያ ወቅት የጆን ኤፍ ኬኔዲ እና የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ወዳጅነት የጠነከረ ቢሆንም ቅሉ፤ ጃንሆይ ለሀገራቸዉ ያስፈልገኛል ያሉት ርዳታን ከአሜሪካ አላገኙም ሲሉ ተናግረዋል።
USA _Präsident John F. Kennedy und Kaiser Haile Selassie von Äthiopien im Weißen Haus. Fahrzeugkolonne durch Washington, Oktober 1 1963 
Titel: In Memory of 50th Anniversary of JFK 
Autor/Copyright: Prince Ermias Sahle-Selassie 2013(der Enkel von Kaiser Haile Selassie von Äthiopien lebt in USA)
Rechte geklärt, via: DW/Azeb Tadesse Hahn
ከአሜሪካዉያን ደስ ያለኝ ነገር፤ ያለፉትን የታሪክ ሰዎች ማስታወሳቸዉ ነዉ የሚሉት ልዑል ኤርምያስ ሳህለ ስላሴ፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተገቢዉን ክብር እንዲሰጣቸዉ ምኞቴ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።
ጆን ኤፍ ኬኔዲ በጀርመን ሀገርም እጅግ ተወዳጅ ናቸዉ። ፕሬዝዳንት ኬኔዲ የዛሬ 50 ዓመት ምዕራብ በርሊንን በጎበኙበት ወቅት በጀርመንኛ ICH BIN EIN BERLINER „በርሊናዊ ነኝ“፤ነፃ ሰዎች ሁሉ የትም ይኑሩ የት የበርሊን ዜጎች ናቸው። እናም እንደ አንድ ነፃ ሰው ICH BIN EIN BERLINER „በርሊናዊ ነኝ“ ስል ኩራት ይሰማኛል ሲሉ በተናገሩት በዚህ አባባላቸው ዘወትር ይታወሳሉ።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

ሰበር ዜና በሰሜናዊ ኢትዮጵያ በሁመራ ቃፍታ ወረዳ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የሰነዘረውን ጥቃት ከመንግስት አካል በኩል ተረጋገጠ



በሰሜናዊ ኢትዮጵያ በሁመራ ቃፍታ ወረዳ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የሰነዘረውን ጥቃት የወረዳው የፀጥታ ኃላፊ ገዛይ ዳኘው ለአካባቢው ራድዮ ማመናቸውን ቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ዛሬ ህዳር 18/2006 ዓም አስታወቀ።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሽምቅ ውግያ ሂደቶች ከሰሜናዊ ኢትዮጵያ በኩል እየተሰማ ነው።

''የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል'' እና ''የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር'' ያሰለጠኗቸውን ሰራዊቶች ማስመረቃቸውን በእዚሁ በያዝነው ህዳር ወር ላይ ማስታወቃቸው ይታወቃል።በእዚሁ ወር ኢሳት ለወራት በኢህአዲግ-ወያኔ ሲቀናበር የነበረ ኤርትራ በሚገኙ  በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አመራሮች ላይ ግድያ ለመፈፀም የተሸረበ ሴራ መጋለጡ መዘገቡ ይታወቃል።የሴራው ሂደትም ኢህአዲግ-ወያኔ በቁጥር አንድ ያስጨነቀው ጉዳይ ወደ ትጥቅ ትግል የገቡ ኃይሎች መሆናቸውን ያመላከተ አይነተኛ ማስረጃ መሆኑን ብቻ ሳይሆን የአሁኑ ሂደት ከእዚህ በፊት ከነበሩት ሁኔታዎች የተለየ ነባራዊ ሁኔታ መኖሩን ብዙዎች ይስማማሉ።

ዛሬ ቪኦኤ የመንግስት መዋቅር የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ ውግያውን ማመናቸውን ለአካባቢው ራድዮ መናገራቸውን ከመግለፁም በላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ኑር ጀባን ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዋል።አርበኛ ኑር ጀባ ስለውግያው ሲናገር  በ24ኛ ክፍለ ጦር ላይ ጉዳት ማድረሱን እና በርካታ ቀላል እና ከባድ የጦር መሳርያዎችን መማርኩን ገልጧል።በነገራችን ላይ ኢሳት በትናንትናው እለት ቀደም ብሎ ዜናውን ማወጁ ይታወቃል።በውቅቱም ጦርነቱ የተደረገው ህዳር 13/2006 ዓም መሆኑ ተዘግቦ ነበር።ከእዚሁ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ በሌለበት ፍርድ ቤት ተከሶ የነበረው በአሁኑ ወቅት የግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ኃይል አመራር ካሴ ዘመነ ''ከወያኔ ጋር ከአሁን በኃላ የምንገናኘው ቃሊቲ ወይም እስር ቤት ሳይሆን ጦር ሜዳ ነው እዝያው እንገኛኛለን'' ያለውም በእዚሁ በያዝነው ሳምንት ነው።
ጉዳያችን ህዳር 19/2006 ዓም

Wednesday, November 27, 2013

Saudi Arabia is buying Western Medias



November 27, 2013
by Tedla Asfaw
I followed roundtable discussion among Adissu, Tizita and Henok regarding the Saudi humanitarian crisis Ethiopians facedonVOA’s this past Sunday program.The Western Media’s absence is not because of lack of the organizers reach to them. It is because of the “Saudi Arabia factor “.
Ethiopians deported to Yemen secretly by the Saudi government.
The American medias downplayed the 9/11 Terrorist attack Saudi’s origin knowing that 18 out of 19 were Saudis citizens. This is because of the Saudi Arabia Huge Money in companies owning the major medias.
There were not any protest against Saudi Arabia following 9/11 even if the 18th terrorist were Saudis. Osama Bin Laden recruited 18 Saudis to kill 3000 innocent citizens. The Saudi regime has involved in world affairs that brought war in Afghanistan, Pakistan, Iraq, Libya, Somalia and currently in Syria.
The Saudi Royals friendship with America brought us the war in Middle East and beyond. No wonder the American medias are not interested in anything that antagonized the Saudi Kingdom because they do not want to destroy their investment interest amounting to hundreds of billions of dollars.
Who destroyed the Egypt Revolution ? It is Saudis Money. The Western media never say a word about that.In fact Saudi is not happy with Obama not embracing the coup in Egypt that is paid by them.
The America medias ignoring the protest in Washington DC, NY and other states by Ethiopians condemning Saudi Kingdom for rape,killing, beating and jailing is not unexpected.
Our protest message had reached the King. Killing of our citizens in public has stopped. The Arab racist propaganda had toned down. Our people in camps are saying thank you.
The American public knew their alliance with Saudi had cost them more than trillion dollar and huge amounts of American lives. That is why Saudis next war to topple Bashar for his barbaric war against his own people is not merely for Syrians but to put Saudis favorite in Damascus like they did in Iraq, Bahrain and Egypt.
One thing we Ethiopians did but the Arabs failed to do is expose the long term ally of USA Saudi Arabia in US soil calling it, ” Saudi Arabia, Kingdom of Shame”. We are proud of that and the American pubic cheered us in our rallies. Job Well done.

ተዋርደን አንቀርም!! ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)


November 26, 2013

Interview Eng. Yilkal Getnetሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡

ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡
አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው“ብለዋል፡፡መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ሆኖም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ ያዙን፣እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል አልሰጡንም፡፡
ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡በቃለ-መጠይቁ ሰላማው ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
ሁለተኛ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹ እየተደፈሩ፣በማጎሪያ ካምፕ በረሀብና በውሃ ጥም፣ሌላው ቢቀር መጸዳጃ ቤት እንኳ ተከልክለው ፍጹም ከሰውነት ክብራቸው ወርደው እየተበደሉ፣እየተገደሉ ባለበት ወቅት ገና ለገና ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በሚንጸባረቅ ጥላቻና ተቃውሞ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል ብለን መናገር እንችላለን?ሌላው ይቅር አንድ ክፉና ደጉን የለየ ሰው የሚያስበው ጤነኛ ሃሳብ ነው ማለትስ ይቻላል?
ከእገዳው ባሻገር የሚደንቀው ነገር ደግሞ በፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ላይ የተደረገው ድብደባ ነው፣የሆነ ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ያለ ይመስላል፡፡የጭካኔያቸውን መጠን እንድናውቅ የሚደበድቡት አቅመ-ደካሞችን፣ሽማግሌወችንና ሴቶችን እየመረጡ በፍጹም አረመኔነት ነበር፡፡ይህን ተግባራቸውን ስመለከት የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ መታዘብ ችያለው፡፡ከፖለቲካ ልዩነትም፣ከአምባገነንነትም በላይ ሰወቹ እንደታመሙ ነው ለመረዳት የቻልኩት፣ስር የሰደደ የቁስ ሰቀቀንና የስልጣን ጥም የተጣባቸው፣ለዚያ ሲሉም የትኛውንም አይነት ውርደት ለመቀበል የቆረጡና የሞራል ልዕልናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎች ናቸው፡፡ስነ-ልቦናቸው ክፉኛ ተቃውሷል እንጂ ሀገር እመራለው የሚል ቡድን እንዲህ ያለ ተግባር ይፈጽማል ለማለት እቸገራለው፡፡በአባላቶቻችን ላይ ክፍኛ ድብደባ ተፈጽሟል፣እስከዛሬም እግሮቻቸው መራመድ የማያስችላቸው፣የሚያነክሱ ሰዎች አሉ፡፡እውነት ለመናገር ይሄ እብደት ነው፡፡አንዲት እራሷን መከላከል የማትችል ሴትን ለሶስት መደብደብን ከዚህ በተሸለ ልገልጸው አልችልም፡፡
አንድ ማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ለኛ ዋነው ጉዳይ የዜጎቹ ህጋዊነት ወይም ህጋዊ ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡በምንም አይነት መንገድ ሴቶች እየተደፈሩ፣ወንዶች በየስርቻው እንደ ውሻ ተቀጥቅጠው እየተገደሉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ታጉረው ይህን ሁሉ መከራ መቀበላቸውን ልንታገሰው፣ወይም ከህጋዊነት አንጻር እየተራቀቅን ልንመለከተው አንችልም፣ስለ ህግም ከተወራ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ጭፍጨፋው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባላቸው ላይ ጭምር ሲፈጸም እንደነበር አምኗል፡፡
ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የአንዱ ሀገር ዜጋ ካለ ሀገሩ መገኘት አገር ይያዝ የሚያስብል አይደለም፡፡መውጣት ካለባቸው ጊዜ በመስጠት፣ከመንግስታቸው ጋር በመነጋገር በዘዴ ነገሩን መከዎን እየተቻለ አንድ ሀገርና መንግስት በሰዎች ላይ እንዲህ የጭካኔ ጥግ የሆነን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለ አስከፊ ጊዜ የለም፣እውነቱን ለመናገር ለአገዛዙ ሰዎች የነበረኝ ጭላንጭል ተስፋም አፈር ተደፍቶባታል፣እንዲህ ግልጽ የሆነ ጭፍጨፋ እየደረሰብን እንኳ በድፍረት ለመናገር አልፈለጉም፡፡ስለ ኢትዮጵያውያን መገደል ለማውራት ሲፈልጉ ሌላ ሀገር ይጠቅሱና እነሱም እኮ እየተገደሉ ነው ይላሉ፣ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል፡፡

ለምሳሌ ኢቲቪ ስጉዳዩ ሲያወራ ህገ ውጥ ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡ተመልከቱ! እንዴት ያለ ባዕድነት ነው?ኢትዮጵያውያን በድህነትም ውስጥ እንኳ ለክብራችን የመሞት ባህሪ አለን፣ይሄ ከቀደሙት አንጡራ ኢትዮጵያውያን የወረስነውና ዛሬም ያለን ሀብታችን ነው፡፡
ትናንት ፍየል ጠባቂ የነበረ በረኸኛ ይህን ክብራችንን ገፍፎ እንደውሻ ቀጥቅጦ ስርቻ ሲጥለን ያልተቆጣ መንግስት ኢትዮጵያዊ ነው?ከዜጎቹ የወጣና ለህዝቡ የቆመ እውነተኛ መንግስት ከዚህ የበለጠ የሚቆጣበት ጉዳይ ከወዴት ይመጣል? እውነተኛ መንግስት ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ካምፓኒዎችን በሰአታት ውስጥ ማባረር፣ኢምባሲውን ዘግቶ አምባሳደሩን ማሰናበትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችን ያሳልፉ ነበር፡፡የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፣የድፕሎማሲ ግንኙነቴ ሊበላሽ ይችላል ብሎ እኛ ድምጻችን እንዳናሰማ ደበደበን፣አፈነን፡፡በግልጽ እንደሚታየው የጥቅም ትስስሩ ነው አፋቸውን ያዘጋቸው፣ይህች ጥቅማቸው እንዳትቋረጥ በዜጎች ህይዎት መደራደርን መርጠዋል፡፡
ስነ ልቦናቸው የተቃወሰ በመሆኑና ተራ ስስታሞች በመሆናቸው እንጂ ኢንቨስትመንትም ሆነ ዲፕሎማሲ ግብአትነታቸው ለሰው ልጅ ነው፣እንደ አህያ ሲያፈጋ ከርሞ ሬሳቸውን ለላከ መንግስት እንዴት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመመለስ ይገዳል?እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊትና ለአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት የሆነች ሀገርን እየመሩ እንዴት ትናንት የነዳጅ ዘይት ባቆማቸው እረኞች ስትዋረድ ዝም ይላሉ?!::
እንዴት!በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም፣ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ታሪክ ለመጥቀስ ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግኝም፡፡የቅርብ የሰሜን አፍሪካ አምባገነኖች የከፋ ፍጻሜ አለና፡፡ኢትዮጵያውያን ፍቅርም ጸብም እናውቃለን፣ሳውዲወችም የፈጸሙትን ግፍ ማወራረዳቸው አይቀርም፡፡በዚህ ክፉ ጊዜ ስለስብአዊ መብት ቆመናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው እውነተኝነታቸውን ለመመርመር ጥሩ እድል ይሰጠናል፡፡
መንግስት ቢኖረን ኖሮ ይሄ ሁሉ ውርደት ይፈጸምብን ነበር ብየ አላስብም፡፡በዚህ ሰአት ርዕሰ-መንግስት ብሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ድርጅት እንደመሆኑ፣ወደየትኛውም ሀገር የሚደረገውን ጉዞ አቋርጨ ዜጎቸን ማስወጣትን አስቀድም ነበር፡፡ያሄ ጥቂት ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ሊያመጣብን ቢችልም ከከፋው የዜጎች ስቃይ ጋር ግን በአንድ ሚዛን ላይ አይቀመጥም፡፡የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡በዜጎቻችን ላይ ጎርፍና ድርቅ ሲመጣ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው? ይሄም ሰው ሰራሽ አደጋ ነው ሙሉ ሀይሉን ወደዚህ አዙሮ ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር፡፡
እርግጥ ነው ባቀድነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ጩኸቱ ግን ይቀጥላል……ባለን አቅም ሁሉ አፈናውንም፣ወከባውንም ተቋቁመን ለዜጎቻችንና ለኢትዮጵያዊነት እንታገላለን፡፡
አገዛዙ ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያፍን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድ መልእክት አስተላልፏል፣ይህን መልእክት እንዲያስትላልፍ ማስገደዳችንም ለኛ ትልቅ ስኬት ነው፡፡የሳውዲ መንግስት ያሻውን ያደርግ ዘንድ የፈቀድኩት እኔ ነኝ፣በመሆኑም እሱን በመቃወም ግንኙነቴን አታበላሹ ብሎ እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ የነገሩ ቁልፍ የት እንዳለ፣የአጥቂወቹ በራስ መተማመን ምን ላይ እንደቆመ በጠራ ሁኔታ ለመመልከት እንዲችል ሆኗል፡፡
ይሄ ሁሉ ነገር እየተፈጸመ የተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ እውነተኛ ማንነታቸው፣እውነተኛ በአገዛዙ ውስጥ ያላቸውን ቦታ ያሳየን ክስተት ነው፡፡እንደሚታወቀው እሳቸው በኢህአዲግ እንጂ በኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ኢህአዲግ የሚናገረው ከሌለ እርሳቸው የሚሉት አይኖርም፡፡እንደ አንድ ሀገርና ህዝብ መሪ ግን የመኮነንም ሆነ የማጽናናት ቃል ይጠበቅባቸው ነበር፡፡
ባሉበት ቦታ ያስቀመጣቸው ህወሀት ነው፤ድርጅቱ ደግሞ ይሄን አቋም አልወሰደም፡፡ስለዚህ እንደሚቆጣቸው ስለሚያውቁ ዝምታን መረጡ፣ቸልታንም አስበለጡ፡፡በሀገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ከዚህ በላይ ሽንፈት ያለ አይመስለኝም፡፡
(ይህ ጽሁፍ በፋክት መጽሄት ተስተናግዷል፣ነገር ግን መጽሄቱ ላልደረሳቸው ሰዎች ይደርስ ዘንድ እዚህ ለማስተናገድ ወደድኩ፡፡)
Source. ECADF

ይድረስ ለኢህአዴግ ደህንነት ክፍል


በመጀመሪያ ደረጃ የከበረ ሰላምታዬን አቀርባለሁ። በውስኗ አቅሜ ይህችን ደብዳቤ ለመፃፍ ስነሳ በውስጤ ብዙ ነገሮችን እያወጣሁና እያወረድኩ ነው። በወንድምና በእህቶቼ ላይ የምትፈፅሙት ኢሰብአዊ ድርጊት በእጅጉ ስላሳዛነኝና ዝምብዬም ማየት ስላላስቻለች ይህችን ደብዳቤ ልፅፍላችሁ ወደድኩ። የዚህች አጭር ደብዳቤዬ አላማ እናንተ ወንድምና እህቶቼ በሌሎች ወንድምና እህቶቼ ላይ የምትፈፅሙትን ኢሰብአዊ ድርጊት እንድታቆሙ ለማሳሰብና ከህዝብ ጎን ለመሰለፍ ግዜው እንዳልረፈደባችሁ ለመጠቆምም ጭምር ነው።


በቅድሚያ ግን ራሴን ስላላስተዋወኳችሁ ራሴን ላስተዋውቅ። ሙሉ ስሜ ኢዮኤል ፍሰሀ ዳምጤ ይባላል። የሀያ ሁለት አመት ወጣት ነኝ። አቅሜ በፈቀደው መጠን ሀሳቦቼን በሶሻል ሚዲያው ላይ የምሰነዝር ጦማሪ በእናንተ አጠራር “ሽብርተኛ” ነኝ። ብእር ያነሳን ሁላ ሽብርተኛ አይደል የምትሉት ፤ ይህች ደብዳቤዬ ብዙ ስያሜ ልታሰጠኝ ብትችልም ለእናንት ከመፃፍ ግን አልቦዘንኩም። በደብዳቤዬ መጀመሪያ ላይም ይድረስ ለኢህአዴግ የደህንነት ክፍል ያልኩበት ምክንያት የአንድ ድርጅት ደህንነት (ኢህአዴግ) እንጂ የኢትዮጲያውያን ደህንነት ስለማያስጨንቃችሁ ነው። በእውነት ለኢትዮጲያውያን በሙላ የቆማችሁ ቢሆን ኖሮ እኔም ይህችን ደብዳቤ መፃፌ ባላስፈለገ ነበር። ድርጊታችሁ እንደሚያሳብቀው የሚያስጨንቃችሁ ነገር የድርጅታችሁ ደህንነት ብቻ ነው።

 የሚገዳደራችሁን ወይም መብቱን ለማስነካት ፈቃደኛ ያልሆነ ዜጋ ሲያጋጥማችሁ በተደጋጋሚ የምታሰሟት አንድ የተለመደች አባባል አለቻችሁ። ወንድ ከሆንክ ጫካ አትገባም! ወንድነት እናንተ ቤት የሚለካው ጫካ በመግባት ነው። ሀያአንደኛ ክፍለዘመን ላይ ሆናችሁ ከጫካ አስተሳሰብ አለመላቀቃችሁ ግን በእጅጉ ያሳፍራል። የዶ/ር መረራን ኢህአዴግ ከጫካ ወጣ እንጂ ጫካው ከኢህአዴግ አልወጣም የሚለውን አባባል እኔም በእጅጉ እጋራለሁ። ወንድሞቼ ያለነው እኮ በሀያአንደኛ ክፍለዘመን ላይ ነው። ዓለም በቴክኖሎጂው መስክ ትልቅ እድገት እያሳየ በሚገኘበት ዘመን ላይ እንዴት ስለጠመንጃ ትልቅነት ይሰበካል።

በሀሳብ የተለያችሁንስ እንዴትስ ለምንስ እንደ ጠላት ትቆጥሩታላችሁ። እኔ በበኩሌ ከእናንተ ጋር የሀሳብ ልዩነት ቢኖረኝም እናንተን እንደ ጠላት መመልከት በእጅጉ ይከብደኛል። እናንተ ግን በሀሳብ ከእናንተ የተለየውንና በድርጅታችሁ ላይ ትችት የሚሰነዝረውን ሁላ አሳድዶ በማንበርከክ ስራ ላይ ተጠምዳችኋል። የሀሳብ ልዩነት መኖሩ እኮ ችግር ሊሆን አይገባም። ምክንያቱም ሁሉም ሰው አንድ አይነት ሀሳብ እንዲያመነጭ አይጠበቅምና ፤ አንድን ሰው በሀሳብ ስለተለየ ብቻ ዛቻና ማስፈራሪያ ፣ ድብደባ ፣ እስር ፣ እንግልት የመሳሰሉበት እንዲደርስበት ማድረግ  ኢሰብአዊ ድርጊት ነው። ከአለቆቻችሁ በተላለፈላችሁ ትዕዛዝ ሰውን በየፖሊስ ጣቢያውና በተለያዩ ቦታዎች ደህንነቶች ነን በማለት እየወሰዳችሁ የምትፈፅሙት ኢሰብአዊ ድርጊት ዛሬ ባያስጠይቃችሁ እንኳ አንድ ቀን ትጠየቁበታላችሁ። አላማችሁ ዜጎች በሀገራቸው ሀሳባቸውን እንዳይገልፁና ሰጥ ለጥ ብለው እንዲገዙ ማድረግ እንደሆነ እሙን ነው። ይህ ግን በጠመንጃ ሊሳካ አይችልም። ምንም አይነት የሀይል እርምጃ ብትወስዱ አንድን ሰው ከፈጣሪ የተሰጠውን መብቱን ልትወስዱበት አትችሉም።

በቅርቡ በእናንተ የደህንነት ሀይሎች ድብደባ የተፈፀመበትን አንድ ወዳጄን አግኝቼ አናግሬው ነበር። ወዳጄ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት አባል ወጣት ዮናስ ከድር ነው። እዚህ ፅሁፌ ላይ በወጃጄ ላይ የፈፀማችሁትን የመብት ጥሰት ለአብነት ላነሳው ወደድኩ። ምክንያቴ ደግሞ አጋጣሚው የእናንተን ማን አለብኝነትና እብሪት በሚገባ እንደሚያንፀባርቅ ስላመንኩ ነው።

 ወጣት ዮናስ ደብደባው እንዴት እንደተፈፀመበት ከጅምሩ በማንሳት እንዲህ ብሎ አወጋኝ “ከላንቻ ፓሊስ ጣቢያ ስልክ ተደውሎልኝ እንደምፈለግ ተነገረኝ። በመቀጠል ወደ ፓርቲዬ ፅ/ቤት አምርቼ ከፓሊስ ጣቢያው ለሌሎች ጓደኞቼ ስልክ ተደውሎላቸው እንደሆነ ጠየቋቸው። እነሱም ስልክ እንዳልተደወለላቸው ነገሩኝ። ይህን ግዜ እኔን ብቻ እንደፈለጉኝ ተረዳሁ። በመቀጠል ከፓርቲያችን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጋር በመሆን ወደ ላንቻ ፓሊስ ጣቢያ አመራን። ፓሊስ ጣቢያው እንደደረስን የፈለጉኝ ፓሊሶቹ ሳይሆኑ ከዚህ በፊት ተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያስከትልብኝ የነበረ አንድ ደህንነት ነው”።

ደህንነቱ ዮናስን አንድ ክፍል ውስጥ ይዞት ከገባ በኃላ ድብደባና ዘለፋ ያከታትልበት ቀጠለ። ደህንነቱ ወደ  ክፍሉ ይዞት ሲገባ በአካባቢው የነበሩት ፓሊሶች እንግዲህ ድብደባ ሊፈፀምበት ነው ሲሉ ማዳመጡን ዮናስ አጫውቶኛል። ድብደባው ሲፈፀም የነበረውም ፓሊሶቹ ቢሮ ወስጥ ነው። ሶስት ሰአት ከፈጀ ድብደባና ዘለፋ በኃላ ዮናስ ድብደባው ፣ ማስፈራሪያውና ዛቻው ከተፈፀመበት ክፍል በመውጣት ላይ እንዳለ ደህንነቱ ከእኛ ጋር መስራት ይኖርብሀል። እዚህ የተፈፀመብህን ነገር ደግሞ ለማንም ትንፍሽ እንዳትል በተለይ ሶሻል ሚዲያው ላይ አንዲት ነገር ማየት አልፈልግም ሲል ማስፈራሪያውን አከለ። ወጣት ዮናስ ወደ ሶስት ሰአት የዘለቀው ደብደባ ፣ ዘለፋና ተግሳፅ ሲካሄድበት የነበረው በወለሉ ላይ ተንበርክኮ እንዳለ ነው። እኔ ወንጀለኛ አይደለሁም ወንጀለኛ ከሆንኩም ክስ ተመስርቶብኝ በፍርድ ቤት ልዳኝ እችላለሁ ሲል ምላሹን ለደህንነቱ የሰጠው ዮናስ ከደህንነቱ በኩል ፍርድ ቤት የማን ሆነና ነው እንዲህ የምትለው ፍርድ ቤት እኮ የእኛ የኢህአዴጎች ነው የሚል ምላሽ እንደተሰጠው አጫውቶኛል። ከላይ በደህንነቱ የተጠቀሰው ፍርድ ቤት እኮ የእኛ የኢህአዴጎች ነው የሚለው ንግግር እናንተ የምታገለግሉት ኢህአዴግን እንጂ የኢትዮጲያን ህዝብ እንዳልሆነ በሚገባ ያመላክታል። ከዛም በተጨማሪ ምን አይነት እብሪትና ድንቁርና በውስጣችሁ እንዳለም ፍንትው አድርጎ ያሳያል። አንድ የደህንነት ባልደረባ ነኝ የሚል ሰው በዚህ ደረጃ ሲናገር መስማት በእጅጉ ያሳፍራል። ታዲያ ይህ የደህንነት ባልደረባ የኢህአዴግ ደህንነት እንጂ የሌላው ሰው ደህንነት ያስጨንቀዋል? ይህ የደህንነት ባልደረባ ነኝ የሚለው ግለሰብ በእንደዚህ አይነት እብሪት ተወጥሮ የሚናገረው የግል አቋሙን ብዬ ለመናገር ይከብደኛል። ይህ የአብዛኞቻቹ ደህንነት ነን የምትሉ ሰዎች አቋም ይመስለኛል።

 በዮናስ ላይ የደረሰውን ለአብነት አነሳሁት እንጂ ደህንነት ነን የምትሉ ሰዎች ሁላ ከዚህም እጅግ የከፍ አፀያፊ ተግባርን ነው የምትፈፅሙት። በቅርቡ እንኳ በአንድነት ፓርቲ ምክር ቤት አባል አቶ አበበ አካሉ ላይ የፈፀማችሁት እጅግ ዘግናኝ የሆነ ኢሰብአዊ ድርጊት ይታወሳል።

ዘመኑ የመረጃ ዘመን በመሆኑ እያንዳንዱ የምትሰሩት ግፍ ተደብቆ አይቀርም። ግዜውን እየጠበቀም ይወጣል። በዘረጋችሁ የአፈና መረብና ባነገታችሁት ጠመንጃ ተኩራርታችሁ አለቃዎቻችሁን ለማስደሰትና ከእነሱ የሚወረወርላችሁን ፍርፋሪ ለመልቀም ኢሰብአዊ ድርጊት መከወኑን ትገፉበት ይሆናል። አንድ ነገር ግን እርግጥ ነው። በምትፈፅሙት ኢሰብአዊ ድርጊት የተነሳ የህሊና እረፍት የላችሁም። የህሊና እረፍት የሌለው ሰው ደግሞ በውስጡ ሰላም የለም። በእርግጥ ዛሬ ህሊናችሁ ጥያቄ አንስቶባችሁ አያውቅ ይሆናል። ጥያቄ ያነሳለት ግን እረፍት አይኖራችሁም። ባሪያ ሆኖ ዘወትር ፍርፋሪ ከመልቀም የአንድ ቀን የህሊና እረፍት ፍፁም ሰላምን ይሰጣል። ውድ የኢህአዴግ ደህንነት ክፍል ባልደረቦች ሆይ በዜጎች ላይ የምትፈፅሙትን ኢሰብአዊ ድርጊት በማቆም ከኢትዮጲያ ህዝብ ጎን ለመሰለፍ ጊዜው አልረፈደም። ጊዜው ሳይረፍድ ፈጥናችሁ መርከቧ ላይ በመሳፈር ከህዝብ ጎን ተሰለፉ።

የግንቦት7 እና አክራሪ የእስልምና ሀይሎች በኢህአዴግ አባላት ስም ፓርላማውን በመቆጣጠር ኢህአዴግን ሊጎዱት ይችላል ሲሉ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ተናገሩ


ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ይህን የተናገሩት ” በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና” በሚል ርእስ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባቀረቡት ጽሁፍ ነው።
ኢሳት የሚኒስትሩን  ሙሉ ንግግር የያዘ ሰነድ የደረሰው ሲሆን፣ በሰነዱ ግርጌ ላይ ” ለመደበኛ አባላት የማይነገር፣ ለከፍተኛ አመራሮች ብቻ” የሚል ተጽፎበት ይታያል።  በዚህ ርእስ ስር ደግሞ ” ቀጣዩ የምክር ቤት አባላት ምርጫ የግንቦት ሰባት እና አክራሪ እስልምና ሀይሎችን የሚያስቀጥሉ አባላት ወንበሩ በኢህአዴግ አባላት ስም ሊነጠቅ ይችላል። ” ብሎአል። ሚኒስትሩ ለዚህ አስተሳሰባቸው የምርጫ 97ትን ሁኔታ እንደማጠቃሻ ተጠቅመዋል። ” የ97 የቅንጅት አሸናፊት አካሄድ ስልት ማለትም የተቃዋሚ አባላት ሁነው በህቡእ ተደራጅተው በኢህአዴግ የአባላትን ካርድ ሙሉ በሙሉ ፓርቲውን ሊጎዱት ይችላሉ” ሲሉ ሚኒስትሩ ጽፈዋል።
ሚኒስትሩ በዚህ ጽሁፋቸው፣ ቅንጅት በ97 ምርጫ ማሸነፉን እንዲሁም የኢህአዴግ አባላት ሆነው ለቅንጅት በውስጥ ይሰሩ የነበሩ ሰዎች እንደነበሩ ጠቅሰዋል። በክርስትና እና በእስልምና ሀይማኖት ሽፋን የሚካሄደውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሚኒሰትሩ በዝርዝር አቅርበዋል።

Dr. Berhanu Nega speaking the media importance and TPLF Photoshop (ESAT Live)



Dr. Berhanu Nega talk about the importance of media in the government and society also he mentioned the recent TPLF poor Photoshop story.

Friday, November 22, 2013

ዲፕሎማቱ በትዕዛዝ ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች ወዳልታወቀ ስፍራ ሰደዱ


12ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ 200 ስደተኞች የደረሱበት አልታወቀም

saudi ethio11
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ይገኙ የነበሩ 12 ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ ከ 200 በላይ ስደተኞች በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ ወዳልታወቀ ስፈራ ተወሰዱ ።
በሪያድ ልዩ ስሙ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ሰሞኑንን የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ አያሌ ወግኖቻችን መገደላቸው እና በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወቃል። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ወገኖቻችን ህይወት አስከፊ ገጽታ ላይ ባለበት ሁኔታ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ ከአንድ አመት በላይ ተጠልለው እንደቆዩ የሚነገርላቸው እነዚህ ወገኖች ወዳልታወቀ ስፈራ መወሰዳቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል።
አሰሪዎቻቸው ከሚፈጽሙባቸው ግፍ እና በደል ራሳቸውን ለመታደግ ቀደም ብለው ወደ ኮሚኒቲው ግቢ እንደመጡ የሚነገርላቸው እኚህ ወግኖች፤ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ጉዳዩቻቸውን ተከታትለው ሊያስፈጽሙላቸው ባለመቻሉ በተጠቀሰው የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በሚገኝ አንድ ኮንቴነር ውስጥ ሲሰቃዩ መኖራቸውን የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል። ከ12 በላይ ነፍሰጡሮች እና የአእምሮ በሽተኞችን ጨምሮ ከ200 በላይ ስደተኞች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ያለምንም የህክምና እርዳታ ሲሰቃዩ ከከረሙት እህቶቻችን ውስጥ 3ቱ በሞት መለየታቸውንና 5ቱ ለአእምሮ ጭንቅት መዳረጋቸው ከኢትዮጵያ ህዝብ ልብ የማይጠፋ መሪር ሃዘን መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች ሰሞኑንን መንፉሃ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ እንደ ገባ ለሚነገርለት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ልኡካን ቡድን ገበናችንን ያጋልጣሉ በሚል ስጋት ዲፕሎማቱ እነዚህን ወገኖቻችንን ወደ አልታወቀ ስፍራ በአውቶብስ ጭነው መውሰዳቸው ታውቆል።
ስደተኞቹ ያሉበት ሁኔታ እስካሁን በውል እንደማይታወቅ የሚናገሩት የሪያድ ምንጮች ምናልባት ወደ አገራቸው ለመግባት ለፖሊስ እጅ ሰጥተው በየጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ከሚሰቃዩ ወገኖቻችን ጋር ቀላቅሎዋቸው ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ያጠናክራሉ። ዲፕሎማቱ የሚፈሩት ነገር ከሌለ በቀር እነዚህ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ኮኔትንር ውስጥ ላለፉት ወራት ያሳለፉትን የችግር እና የመከራ ጊዜያቶች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ጉዳዩቻቸውን ባሉበት በማስፈጸም ወደ ሃገር በመላኩ ረገድ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ይገልጻሉ። ዲፕሎማቱ የፈጸሙት ድርጊት ወገናዊነት የጎደለው መሆኑን የሚገልጹ ምንጮች የተጠቀሱት እህቶቻችን ኮሚኒቲው መጠለያ ግቢ ውስጥ በነበሩባቸው ጊዜያቶች አንዳንድ እህቶቻችን ተመርጠው በዲፕሎማቱ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ በሚል ሽፋን ማታ ማታ ከማደሪያ ኮንቴነር ክፍላቸው እየተጠሩ እዛው ኮሚኒት ግቢ ውስጥ በሚገኝ አንድ ጽ/ቤት ውስጥ ለሰአታት ቆይተው ይወጡ እንደነበር በማስታወስ በእህቶቻችን ላይ ጾታዊ ጥቃት ሳይፈጸምባቸው እንደማይቀር ጥርጣሬያቸውን ይገልጻሉ።
እንዲህ አይነት አስጸያፊ ድርጊት አልፎ አልፎ የሚሰማ መሆኑንን የሚገልጹ ወገኖች በሪያድ አንዲት ኢትዮጵያዊት ወጣት ላይ መከስቱን ተከትሎ ኮሚኒቲው አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ወጀለኛውን ፍ/ቤት በማቆም 60 ሺህ ሪያል ካሳ እንዲከፍል ማስወሰናቸውን የሚያወሱ አንድ አባት፤ ጉዳዩን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከታትሎ እንዲያሰፈጽም አደራ ቢሰጡም ሃላፊነቱን በብቃት ሳይወጣ በመቅረቱ ወንጀለኛው ከእስርቤት ተለቆ ተበዳይ እህት ሰሞኑንን ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር ወዳልታወቀ ስፍራ እስከተወስደችበት ጊዜ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቴ ግቢ ውስጥ በህመም ስትሰቃይ እንደነበር እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በሚገኙ እህቶቻችን ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መሞከሩን የሚናገሩ የአካባቢው ምንጮች አንዲት ወጣት በቆንስላው ጽ/ቤት ዘበኛ ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞባት ጉዳዩ ፍ/ቤት ደርሶ እንደነበርና በቆንስላው የመንግስት ባለስልጣኖች ተድበስበሶ መቅረቱ የሚያስታውሱ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ጊቢ ይኖሩ ከነበሩ ስደተኞች ውስጥ የ12ቱ ነፍሰ ጡር እህቶቻችን ጉዳይ ሳይጣራ ሰሞኑንን በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ ከኮሚኒቲው ግቢ ባስቸኳይ እንዲለቁ መደረጉ የአካባቢውን ማህበረሰብ ጥርጣሬ የበለጠ ያጠናክረዋል ብለዋል።
Ethiopian Hagere በፌስቡክ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከጅዳ በዋዲ የላኩት

ሰማያዊ ፓርቲ፣ የዜጎችን ሰቆቃ እና በደል ችላ ማለት ከግፈኞች ጋር እንደመተባበበር ይቆጠራል!!


November 22, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የሳውዲ መንግስት እያደረሰ ያለውን እስራት፣ ስቃይ እና ግድያ በመቃወም እና ህይወታቸው ላለፈ፣ ለተደበደቡ እንዲሁም የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ህዝቡ ሃዘኑን እንዲገልጽ በመጪው እሁድ በሚደረገው ታላቁ ሩጫ ላይ የሚሮጡ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ ጥሪ ማስተላለፉ የሚታወቅ ነው፡፡
ይሁን እንጂ የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች ይህንን ጥሪ እንደሚቃወሙት እና በፕሮግራሙም ላይ ጥቁር ሪቫን ያሰረ ተሳታፊን እንደተሳታፊ እንደማይቆጥሩ መናገራቸው ፓርቲያችንን እጅግ አሳዝኖታል፡፡ ፓርቲያችን ይህንን ጥሪ ሲያስተላልፍ አላማው ፍጹም ፖለቲካዊ አንድምታ የሌለው ሲሆን ጥያቄውም በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እና ግድያ እንዲቆም እና ፍትሃዊ እርምጃም እንዲወሰድ ለመጠየቅ ብቻ እና ብቻ እንጂ ሌላ አላማ እንደሌለው እየታወቀ የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች ግን ጉዳዩ ከፖለቲካ ጋር ለማያያዝ መሞከራቸው የሚያስተዛዝብ እና ህዝባዊ ወገንተኝነታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው፡፡

ስፖርት ሰላማዊ ነገር የሚሰበክበት እንዲሁም እኩይ ተግባራት የሚወገዙበት መድረክ ነው፡፡ በአለማችን ላይ በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱ አሰቃቂ ሰው ሰራሽ አደጋዎች በተለያዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶች ላይ ሲወገዙ እንዲሁም ለሰለባዎች ሃዘን የመግለጽ ስነ ስርዓትና የህሊና ጸሎት ሲደረግ መመልከት የተለመደ ነው፡፡ ታዲያ በጠራራ ፀሀይ በአደባባይ እናት ልጆችዋ ፊት እንዲሁም ሴት ልጅ ቤተሰቦችዋ ፊት ስትደፈር ከማየት የዘለለ ምን እኩይ ተግባርስ ሊኖር ነው? ታዲያ ስፖርት ይህንን ካላወገዘ ምንን ሊያወግዝ ነው?
በመጨረሻም የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች የፓርቲውን ጥሪ መቃወማቸው ፓርቲያችንን ያሳዘነ እና ያስቆጣ መሆኑን እየገለጽን አሁንም ፓርቲያችን በድጋሜ በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ እየጠየቀ ጥቁር ሪቫኖችን ማግኘት ለማትችሉ በሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተገኝታችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡


ክብር ለዜጎቻችን ይሁን!!

Thursday, November 21, 2013

ኢትዮጵያ፣ በህዳርና በ… ሁልጊዜ አስታውሳለሁ!! (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም)


November 21, 2013
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የህዳር ወር በኢትዮጵያውያን በአሰቃቂነቱ ሁልጊዜ ሲታወስ ይኖራል፡፡
እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2013 ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በቃላት ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ሰቆቃ የተፈጸመበት ወር ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ፣ በሚሰሩና የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጥረት በማድረግ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲሰነዘር ቆይቷል፡፡ እንዲያውም በግል በሚኖሩበት ቤት እምነታቸውን በማራመዳቸው ብቻ ኢትዮጵያውያኑ/ቱ ዜጎች ላይ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፣ እንዲጋዙም ተደርጓል፡፡
Ethiopia November Victims never again, Alemayehu G. Mariam
እ.ኤ.አ 2011 የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ (Human Rights Watch) ዘገባ የሳውዲ አረቢያ ፖሊስ “ህገወጥ ስብሰባ በሚል ሰበብ 35 የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያወያንን/ትን“ “በአንድ ኢትዮጵያዊ የክርስትና እምነት ተከታይ የግል መኖሪያ ቤት በእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ዋዜማ ተሰባስበው ጸሎት በማድረግ ላይ እንዳሉ” በፖሊስ ቀጥጥር ስር ውለዋል” ይላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ ጥገኝነት በሚፈልጉ እና ሌሎች ስደተኛ ኢትዮጵያውያት የቤት ሰራተኖች ላይ በሚደረገው ሰብአዊ መብት ረገጣ ምክንያት ምንጊዜም የማያቋርጥ ትችት እየተደረገ መሆኑን መግለጽ ማጋነን አይሆንም፡፡ በዚህ ወር በዕየለቱ በሚባል መልኩ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች፣ የደህንነት ኃላፊዎችና ተራ የሳውዲ ዜጎች በየመንገዱ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ያድናሉ፣ ይደበድባሉ፣ ያሰቃያሉ፣ አንዳንድ ጊዜም ይገድላሉ፡፡ የሳውዲ ፖሊሶች ኢትዮጵያውያንን ሲያሰቃዩ የሚያሳየው የቪዲዮ ቅርፅ ለህሊና የሚሰቀጥጥ ነው፡፡ የሳውዲዎች ኢትዮጵያውያንን በየመንገዱ የማባረር ሁከት፣ ጥቃት የመሰንዘርና የመግደል ድርጊት ምንም ዓይነት ማብራሪያ አያስፈልገውም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ የሚያሳየው የፎቶግራፍ ምስል አስደንጋጭና ከሰለጠነ የሰው ልጅ አስተሳሰብ በእጅጉ የዘለለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አስተዳደር 200 ሺ እና ከዚያ በላይ የሚሆኑትን በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን/ት ለማገዝ ምን እያደረገ ነው? ምንም!!! እራሱ አምኖ በተቀበለው መሰረት ገዥው አስተዳደር ምን ያህል ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ እንደሚኖሩ እንኩዋን አያውቅም፣ ሆኖም ግን ተጨባጭነት በሌለው መልኩ ኢትዮጵያውያንን/ትን ከሳውዲ አረቢያ ሙሉ በሙሉ በተቻለ መጠን ወደ ኢትዮጵያ እመልሳለለሁ የሚል ቃል ገብቷል፡፡
የወባ ተመራማሪው “የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር”፣ ቴዎድሮስ አድሃኖም የሳውዲ መንግስት በግዛቱ በሚገኙት ስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ሰራተኞች ላይ የፈጸመውን አረመኒያዊ የኃይል እርምጃ “መንግስቱ አውግዘዋል፡፡ ይኸ በፍጹም ተቀባይነት የለውም፡፡ ይህን ጉዳዩ የሳውዲ መንግስት እንዲያጣራ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ እዚያ በነበሩበት ጊዜ በክብር መያዝ የነበረባቸውን ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስም ደስተኞች ነን፡፡ ተቀባይነት የለውም” የሚለውን አባባል ገዥው አስተዳደር እንደ አስፈሪ የጭካኔ ድርጊቶች፣ ያለመሰልጠንነትና ዘግናኝ ጨካኝነትና ወንጀለኛነት የሚሉትን ቃላት ለመግለጽ የሚጠቀምበት የውግዘት ቃል ነው፡፡ አልጄዚራ እንደዘገበው ከሆነ በተፈጸመው ድርጊት ተበሳጭተው የነበሩ ኢትዮጵያውያን/ት አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ለማሰማት በሄዱበት ጊዜ የገዥው አስተዳደር ፖሊስ በቁጥጥር በማዋል  ድብደባ ፍጽሞባቸዋል፡፡ “ፖሊሶች ከመጡ በኋላ ደብድበውናል፣ እና በአሁኑ ጊዜ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በእስር ቤት ይገኛሉ” በማለት የተቃዋሚው የሰማያዊ ፓርቲ ነባር አባል ጌትነት ባልቻ ገልጿል፡፡ ጌትነት በመቀጠልም “የፓርቲው ሊቀ መንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከታሰሩት ውስጥ ይገኙበታል” በማለት ሀሳቡን አጠቃሏል፡፡
ሆኖም ግን ኢትዮጵያውያን/ በሀዳር ወር መጎዳትና መጎሳቀል ለምን ይደንቀን? እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2005 ያለው የገዢ አስተዳደር ለመናገር በሚዘገንን መልኩ የጭካኔ ድርጊት በአትዮጵያኖች ላይ ፈፅሞአል:: በዚያው ዓመት የፓርላማውን ምርጫ ተከትሎ በግንቦት ወር በጠራራ ፀሐይ የተዘረፈውን የህዝብ ድምጽ በመቀወም ድምጻቸውን ባሰሙ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች እራሱ መለስ ዜናዊ ያቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን 193 ያልታጠቁ ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች በአዲስ አበባ መንገዶች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በመግለጻቸውና እና ሌሎች በከፍተኛ ደህንነት በእስር ቤት የሚገኙ እስረኞችን ሆን ተብሎ በጥይት ደብድበዋል፣ ሌሎች 763 የሚሆኑት በጽኑ ቆስለዋል፡፡
እ.ኤ.አ ከ2007 ጀምሮ በየጊዜው በህዳር ወር እ.ኤ.አ የ2005 ምርጫን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጨዋና ያልታጠቁ ሰልፈኞች ተኩስ በመክፈት ገደሏቸው፣ አካለ ጎደሎ አደረጓቸው፡፡ እኔም ያንን ጊዜ ለማስታወሰ ስል መጻፌን ቀጥየ ነበር፡፡
በመጀመሪያው የማሰታወስ ጽሁፌ እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2005 እና በጁን 2005 የተከፈለው መስዕዋትነት ለዘላለም ይታወሳል! ለአንባቢ ዎቼም ሳስታዉስ በህይወት ላሉትና ለሞቱት ምስክርነት መስጠት እንዳለባችሁ የሞራል ግዴታ ተጥሎባችኋል ብዬ ነበር፡፡ ኤሊ ዌይሰል የዕልቂቱ ተራፊና የኖቬል ተሸላሚ በክብር እንዳስቀመጠው “ማስታዋስ አለብን ምክንያቱም የጋራ ትውስታችን የሆኑትን ያለፉ ድርጊቶች የወደፊቱን ትውልድ መብት መከልከል ስለማንችል ነው መርሳት መጥፎ ነገር ብቻ አይደለም ነገር ግን ስድብም ነው፡፡ የሞቱትን መርሳት ሁለተኛ ከመግደል እኩል ነው፡፡”
በ2005 ያለቁትን መርሳት ማለት በእነርሱ ላይ የተፈጸሙትን ግፎች መርሳት እንዲህም ያሉትን አረመኔአዊ ወንጀል መርሳትማለት ነው፡፡ እልቂቱን መርሳት ማለት ወንጀለኞች ተጠያቂ እንዳይሆኑ የልብ ልብ መስጠት ማለት ነው፣ ምክንያቱም ወንጀሎቹ ተረስተዋል፡፡ በመጨረሻም መርሳት ማለት በስልጣን ላይ ያሉ ወንጀለኞች እንደገና እና እንደገና የወንጀል ደረጃውን ከፍ በማድረግና ተጠያቂነት የሌለበትን ሁኔታ በመፍጠር ወንጀል እንዲሰሩ ማበረታታት ማለት ነው፡፡
አስታውሳለሁ! በምንም አይነት አልረሳምም፣ በፍጹም!!!
አስታውሳለሁ ምክንያቱም እኔ ካላስታወስኩ ማን ያስታዉሳል? አስታውሳለሁ ምክንያቱም የምረሳ ከሆነ ወንጀሎችና ወንጀለኞች ይረሳሉ፡፡ የምረሳ ከሆነ ታሪክ እንዴት ሊያስታውስ ይችላል? ታሪክ ሊያስታውስ የሚችለው ሌላ ሊያስታውስ የሚችል ሰው ሲኖር ነው:: በህዳር፣ በታህሳስ፣ በጥር፣ በየካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዝያ… ዛሬ ለኢትዮጵያ ወጣቶችና ነገ ለሚወለዱ ህጻናት አስታውሳለሁ፡፡
የእኔን ስራ በማድነቅና ለበርካታ ዓመታት ሲደግፉ ሲቆዩ ሌሎች ደግሞ ሲተቹ ሲቃወሙ የሚኖሩ አሉ። እኔ በኢትዮጵያውያን ሰበአዊ መብቶች ችኮ ነው ይሉኛል:: በኢትዮጵያውያን ሰበአዊ መብቶች ችኮ መሆን ለኔ ታላቅ ክበር ነው::
የ2005 ዕልቂትን አስታውሳሁ፡፡ እያንዳንዱን በግፍ የተገደሉትን አስታዉሳለሁ፡፡ አስታውሳለሁ ወጣት ሴቶች ወደፊት እናት ላይሆኑ፣ ወጣት ወንዶችን የአራዊቱን  ጭፍረኞች ገዳዮችን አልረሳም  ወደፊት አባት ላይሆኑ፣ ወላጅ የሌላቸውን ወላጆቻቸው የተገደሉባቸውን አስታውሳለሁ፡፡ ልጆቻቸው የተገደሉባቸውን እናቶችንና አባቶችን አስታውሳለሁ::
ወንጀለኞችን አልረሳም፣ ተንኮል የሰሩትን 237ቱን የፖሊስ አባላት አስታውሳለሁ፣ የወንጀለኞችን ቁንጮና መሪ የነበረዉን አራዊትን  አልረሳም:: የአራዊቱን  ጭፍረኞች ገዳዮችን አልረሳም::
አስታውሳሁ፣ መቼ ረሳለሁ: ሁልጊዜ  ህዳርን፣ ታህሳስን፣ ጥርን፣ የካቲትን፣ መጋቢትን፣ ሚያዝያን….አልረሳም፡፡
.
ስም
ጾታ
እድሜ
ስራ

መግለጫ
1
ሬቡማ ኢርጋታ
34
ግንበኛ
2
መለሳቸው አለምነው
16
ተማሪ
3
ሀድራ ኦስማን
22
አይታወቅም
4
ጃፋር ኢብራሂመ
28
ቢዝነስ
5
መኮንን
17
አይታወቅም
6
ወልደሰማያት
17
7
ባህሩ ደምለው
አይታወቅም
8
ፈቀደ ነጋሽ
25
መካኒክ
9
አብርሀምይልማ
17
ታከሲ ነጂ
10
ያሬድ እሸቴ
23
ቢዝነስ
11
ከበደ ገ/ህይወት
17
ተማሪ
12
ማቴዎስ ፍልፍሉ
14
ተማሪ
13
ጌትንት ወዳጆ
48
ቢዝነስ
14
ቃሰም ራሽድ
21
መካኒክ
15
ሸውሞሊ
22
ቢዝነስ
16
አሊየ ኢሳ
20
የቀን ስራ
17
ሣምሶን ያዕቆብ
23
የህዝብ ማመላ
18
አለባለው አበበ
18
ተማሪ
19
በልዩ ዛ
18
ትራንስ. ረዳት
20
ዩሱፍ ጀማል
23
ተማሪ
21
አብርሃም አገኘሁ
23
ትራንስ.ረዳት
22
መሀመድ በቃ
45
አርሶ አደር
23
ረዴላ አወል
19
የታክሲ ረዳት
24
ሀብታሙ ኡርጋ
30
ቢዝነስ
25
ዳዊት ፀጋዬ
19
መካኒክ
26
ገዛኸኝ ገረመው
15
ተማሪ
27
ዮናስ አበራ
24
አይታወቅም
28
ግርማ ወልዴ
38
ሾፌር
29
ደስታ ብሩ
37
ቢዝነስ
30
ለገሰ ፈይሳ
60
ቢዝነስ
31
ተስፋዬ ቡሽራ
19
ጫማ ጠጋኝ
32
ቢንያም ደገፋ
18
ስራ አጥ
33
ሚሊዮን ሮቢ
32
ትራንስ.ረዳት
34
ደረጀ ደኔ
24
ተማሪ
35
ነብዩ ሃይሌ
16
ተማሪ
36
ምትኩ ምዋለንዳ
24
ዶመስቲክ ሰራተኛ
37
አንዋር ሱሩር
22
ቢዝነስ
38
ንጉሴ ዋብግነ
36
ዶመስቲክ ሰራተኛ
39
ዙልፋ ሀሰን
50
የቤት እመቤት
40
ዋስይሁን ከበደ
16
ተማሪ
41
ኤርሚያስ ከበደ
20
ተማሪ
42
00428
25
አይታወቅም
43
00429
26
አይታወቅም
44
00430
30
አይታወቅም
45
አዲሱ በላቸው
25
አይታወቅም
46
ደመቀ አበበ
አይታወቅም
47
00432
22
አይታወቅም
48
00450
20
አይታወቅም
49
13903
25
አይታወቅም
50
00435
30
አይታወቅም
51
13906
25
አይታወቅም
52
ተማም ሙክታር
25
53
በየነ በዛ
25
አይታወቅም
54
ወሰን አሰፋ
25
አይታወቅም
55
አበበ አንተነህ
30
አይታወቅም
56
ፈቃዱ ኃይሌ
25
አይታወቅም
57
ኤሊያስ ጎልቴ
አይታወቅም
58
ብርሃኑ ዋርካ
59
አሸብር መኩሪያ
አይታወቅም
60
ዳዊት ሰማ
አይታወቅም
61
መርሀጽድቅ ሲራክ
አይታወቅም
62
በለጠ ጋሻውጠና
አይታወቅም
63
ብኃይሉ ተስፋዬ
20
አይታወቅም
64
21760
18
አይታወቅም
65
21523
25
አይታወቅም
66
11657
24
አይታወቅም
67
21520
21
አይታወቅም
68
21781
60
አይታወቅም
69
ጌታቸው አዘዘ
45
አይታወቅም
70
21762
75
አይታወቅም
71
11662
45
አይታወቅም
72
21763
25
አይታወቅም
73
13087
30
አይታወቅም
74
21571
25
አይታወቅም
75
21761
21
አይታወቅም
76
21569
25
አይታወቅም
77
13088
30
አይታወቅም
78
እንዳልካቸው ገብርኤል
27
አይታወቅም
79
ኃይለማርያም አምባዬ
20
አይታወቅም
80
መብራቱ ዘውዱ
27
አይታወቅም
81
ስንታየሁ በየነ
14
አይታወቅም
82
ታምሩ ኃይለሚካኤል
አይታወቅም
83
አድማሱ አበበ
45
አይታወቅም
84
እቴነሽ ይማም
50
አይታወቅም
85
ወርቄ አበበ
19
አይታወቅም
86
ፈቃዱ ደግፌ
27
አይታወቅም
87
ሸምሱ ካሊድ
25
አይታወቅም
88
አብዱዋሂደ አህመዲን
30
አይታወቅም
89
ታከለ ደበሌ
20
አይታወቅም
90
ታደሰ ፌይሳ
38
አይታወቅም
91
ሶሎሞን ተስፋዬ
25
አይታወቅም
92
ቅጣው ወርቁ
25
አይታወቅም
93
ደስታ ነጋሽ
30
አይታወቅም
94
ይለፍ ነጋ
15
አይታወቅም
95
ዮሀንስ ኃይሌ
20
አይታወቅም
96
በኃይሉ ብርሀኑ
30
አይታወቅም
97
ሙሉ ሶሬሳ
50
አይታወቅም
98
የቤት እመቤት
አይታወቅም
99
ቴዎድሮስ
23
አይታወቅም
100
ጫማ ሰሪ
ጫማ ሰሪ
101
በኃይሉ ብርሃኔ
30
አይታወቅም
102
ሙሉ ሶሬሳ
50
የቤት እመቤት
103
ቴዎድሮስ ኃይሌ
23
ጫማ ሻጭ
104
ደጄኔ ይልማ
18
መጋዝን ጠባቂ
105
ኡጋሁን ወልደገብርኤል
18
ተማሪ
106
ደረጀ ማሞ
27
አናጺ
107
ረጋሳ ፈይሳ
55
ላውንድሪ ሰራተኛ
108
ቴዎድሮስ ገብረዎልድ
28
የግል ንግድ
109
መኮንን ገ/እግዚአብሄር
20
መካኒክ
110
ኤሊያስ ገ/ጊዮርጊስ
23
ተማሪ
110
አብርሀም መኮንን
21
የቀን ሰራተኛ
111
ጥሩወርቅ ገ/ጻድቅ
41
የቤት እመቤት
112
ሄኖክ መኮንን
28
አይታወቅም
113
ጌቱ ምሀትተ
24
አይታወቅም
114
ክብነሽ ታደሰ
52
አይታወቅም
115
መሳይ ስጦታው
29
የግል ንግድ
116
ሙሉአለም ወይሳ
15
አይታወቅም
117
አያልሰው ማሞ
23
አይታወቅም
118
ስንታየሁ መለሰ
24
የቀን ሰራተኛ
119
ጸዳለ ቢራ
50
የቤት እመቤት
120
አባይነህ ሰራሴድ
35
ልብስ ሰፊ
121
ፍቅረማርያም ተሊላ
18
ሾፌር
122
አለማየሁ ገርባ
26
አይታወቅም
124
ጆርጅ አበበ
36
የግል ትራንስፖርት
125
ሀብታሙ ዘገየ
16
ተማሪ
126
ምትኩ ገ/ስላሴ
24
ተማሪ
127
ትዕዛዙ መኩሪያ
24
የግል ንግድ
128
ፈቃዱ ዳልጌ
36
ልብስ ሰፊ
129
ሸዋጋ ወ/ጊዮርጊስ
38
የቀን ሰራተኛ
130
አለማየሁ ዘውዴ
32
የቴክስታይል ሰራተኛ
131
ዘላለም ገ/ጻድቅ
31
የታክሲ ሾፌር
132
መቆያ ታደሰ
19
ተማሪ
133
ሀይልየ ሁሴን
19
ተማሪ
134
ፍስሀ ገ/ጻድቅ
23
የፖሊስ ተቀጣሪ
135
ወጋየሁ አርጋው
26
ስራ ፈላጊ
136
መላኩ ከበደ
19
አይታወቅም
137
አባይነህ ኦራ
25
ልብስ ሰፊ
138
አበበች ሆለቱ
50
የቤት እመቤት
139
ደመቀ ጀንበሬ
30
አርሶ አደር
140
ክንዴ ወረሱ
22
ስራ ፈላጊ 141
141
እንዳለ ገ/መድህን
23
የግል ንግድ
142
አለማየሁ ወልዴ
24
መምህር
143
ብስራት ደምሴ
24
መኪና አስመጭ
144
መስፍን ጊዮርጊስ
23
የግል ንግድ
145
ወሎ ዳሪ
18
የግል ንግድ
146
በሀይሉ ገ/መድህን
20
የግል ንግድ
147
ሲራጂ ኑሩ ሰይድ
18
ተማሪ
148
እዮብ ገ/መድህን
25
ተማሪ
149
ዳንኤል ሙሉጌታ
25
የቀን ሰራተኛ
150
ቴዎድሮስ ደገፋ
25
የጫማ ፋብሪካ ሰራተኛ
151
ጋሻው ሙሉጌታ
24
ተማሪ
152
ከበደ ኦርቄ
22
ተማሪ
153
ለሊሳ ፋጤሳ
21
ተማሪ
154
ጃገማ ባሻ
20
ተማሪ
155
ደበላ ጉታ
15
ተማሪ
156
መላኩ ፈይሳ
16
ተማሪ
157
እልፍነሽ ተክሌ
45
አይታወቅም
158
ሀሰን ዱላ
64
አይታወቅም
159
ሁሴን ሀሰን ዱላ
25
አይታወቅም
160
ደጀኔ ደምሴ
15
አይታወቅም
161
ዘመድኩን አግደው
18
አይታወቅም
162
ጌታቸው ተረፈ
16
አይታወቅም
163
ደለለኝ አለሙ
20
አይታወቅም
164
ዩሱፍ ኡመር
20
አይታወቅም
165
መኩሪያ ተበጀ
22
አይታወቅም
166
ባድሜ ተሻማሁ
20
አይታወቅም
167
አምባው ጌታሁን
38
አይታወቅም
168
ተሾመ ኪዳኔ
65
የጤና ባለሙያ
169
ዮሴፍ ረጋሳ
አይታወቅም
170
አብዩ ንጉሴ
አይታወቅም
171
ታደለ በሀጋ
አይታወቅም
172
ኤፍሬም ሻፊ
አይታወቅም
173
አበበ ሀማ
አይታወቅም
174
ገብሬ ሞላ
አይታወቅም
175
ሰይዴ ኑረዲን
አይታወቅም
176
እንየው ጸጋዬ
32
እረዳት ትራንስፖርት
177
አብዱራህማን ፈረጅ
32
የእንጨት ስራ ባለሙያ
178
አምባው ብጡል
60
የቆዳ ፋብሪካ ሰራተኛ
179
አብዱልመናን ሁሴን
28
የግል ንግድ
180
ጅግሳ ሰጠኝ
18
ተማሪ
181
አሰፋ ነጋሳ
33
አናጺ
182
ከተማ ኡንኮ
23
ልብስ ሰፊ
183
ክብረት እልፍነህ
48
የጥበቃ ሰራተኛ
184
እዮብ ዘመድኩን
24
የግል ንግድ
185
ተስፋዬ መንገሻ
15
የግል ንግድ
186
ካፒቴን ደበሳ ቶሎሳ
58
የግል ንግድ
187
ትንሳኤ ዘገየ
14
ልብስ ሰፊ
188
ኪዳና ሹክሩ
25
የቀን ሰራተኛ
189
አንዷለም ሺበለው
16
ተማሪ
190
አዲሱ ተስፋሁን
19
የግል ንግድ
191
ካሳ በየነ
28
ልብስ ሽያጭ
192
ይታገሱ ሲሳይ
22
አይታወቅም

የጸጥታ ኃይሎች እርስ በእርስ ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ በጥይት የተገደሉ ሰዎች፣

193
ነጋ ገብሬ
194
ጀበና ደሳለኝ
195
ሙሊታ ኢርኮ
196
የሃንስ ሶሎሞን
197አሸናፊ ደሳለኝ
198
ፈይሳ ገ/መንፈስ
በመቶዎቹ የሚቆጠሩትን የግድያ ሰለባዎች፣ አካለ ጎደሎዎች፣ ቁስለኞች፣ በኃይል የተመቱትንና ሰውነታቸው በጥይት የተበሳሱትን ሁሉ አስታውሳለሁ፡፡
..ኖቬምበር 2/2005ከቃሊቲእስርቤትለማምለጥሲሞክሩበታጣቂዎችበተከፈተተኩስበጥይትተደብድበውያለቁሰዎችስምዝርዝር፣
.
ስም
ጾታ
የተከሰሱበት ጥፋት፣
1
ጠይብ ሸምሱ መሀመድ
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
2
ሳሊ ከበደ
ምንም ዓይነት ክስ አልተጠቀሰም
3
ሰፊው እንድሪስ ታፈሰ
በአስገድዶ መድፈር
4
ዘገዬ ተንኮሉ በላይ
በዝርፊያ ወንጀል
5
ቢያድግልኝ ታመነ
የተወነጀሉበት ያልታወቀ
6
ገብሬ መስፍን ዳኘ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
7
በቀለ አብርሃም ታዬ
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
8
ጉታ ሞላ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
9
ኩርፋ መልካ ተሊላ
በማስፈራራት ወንጀል
10
በጋሻው ተረፈ ጉደታ
የህዝብን ሰላም በማደፍረስ ወንጀል
12
አብደልወሃብ አህመዲን
በዘርፊያ ወንጀል
13
ተስፋዬ አብይ ሙሉጌታ
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
14
አዳነ ቢረዳ
በነፍስ ማጥፋት ወንጀል
15
ይርዳው ከርሴማ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
16
ባልቻ አለሙ ረጋሳ
በዝርፊያ ወንጀል
17
አቡሽ በለው ወዳጆ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
18
ዋለልኝ ታምሬ በላይ
በአስገድዶ መድፈር
19
ቸርነት ኃይሌ ቶላ
በዝርፊያ ወንጀል
20
ተማም ሸምሱ ጎሌ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
21
ገብየሁ በቀለ አለነ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
22
ዳንኤል ታዬ ለኩ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
23
መሀመድ ቱጂ ቀኔ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
24
አብዱ ነጂብ ኑር
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
25
የማታው ሰርቤሎ
በአስገድዶ መድፈር
26
ፍቅሩ ናትናኤል ሰውነህ
በማስፈራራት ወንጀል
27
ሙኒር ከሊል አደም
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
28
ኃይማኖት በድሉ ተሸመ
ጽንፈኝትን በማራመድ
29
ተስፋዬ ክብሮም ተኬ
በዥርፊያ ወንጀል
30
ወርቅነህ ተፈራ ሁንዴ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
31
ሲሳይ ምትኩ ሁነኛ
በማጭበርበር ወንጀል
32
ሙሉነህ አይናለም ማሞ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
33
ታደሰ ሩፌ የኔነህ
በማስፈራራት ወንጀል
34
አንተነህ በየቻ ቁበታ
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
35
ዘሪሁን መርሳ
በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ወንወጀል
36
ወጋየሁ ዘሪሁን አስፋው
በዝርፊያ ወንጀል
37
በከልካይ ታምሩ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
38
የራስወርቅ አንተነህ
በማጭበርበር ወንጀል
39
ባዝዘው ብርሀኑ
ግብረሰዶም በመፈጸም ድርጊት
40
ሶሎሞን እዮብ ጉታ
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል
41
አሳዩ ምትኩ አራጌ
በማስፈራራት ወንወጀል
42
ጋሜ ኃይሉ ዘገዬ
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
43
ማሩ እናውጋው ድንበሬ
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል
44
እጂጉ ምናለ
በግድያ ሙከራ ወንጀል
45
ኃይሉ ቦስኔ ሀቢብ
የተቀደሰን ቦታ በማራከስ
46
ጥላሁን መሰረት
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
47
ንጉሴ በላይነህ
በዝርፊያ ወንጀል
48
አሸናፊ አበባው
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
49
ፈለቀ ድንቄ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
50
ጀንበሬ ድንቅነህ ቢለው
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
51
ቶሎሳ ወርቁ ደበበ
የዝርፊያ ወንጀል
52
መካሻ በላይነህ ታምሩ
የህዝብን ሰላም በማደፍረስ
53
ይፍሩ አደራው
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
54
ፋንታሁን ዳኘ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
55
ጥበቤ ዋቀኔ ቱፋ
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
56
ሶሎሞን ገብረአምላክ
የህዝብን ሰላም በማደፍረስ
57
ባንጃው ቹቹ ካሳሁን
በዝርፊያ ወንጀል
58
ደመቀ አበጀ
በግድያ ሙከራ ወንጀል
59
እንዳለ እውነቴ መንግስቴ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
60
አለማየሁ ጋርባ
እ.ኤ.አ በ2004 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አመጽ ጋር በተያያዘ መልኩ በቁጥጥር የዋሉ
61
ሞርቆታ ኢዶሳ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
ለምዘገባ፣ በዚህ እልቂት ላይ ተዋንያን የነበሩ 237 የተረጋገጠ የፖሊስ እና የደህንነት አባላት ዝርዝርን የያዘ ሰነድ ተቀምጧል፡፡
የኔሰው ገብሬን አስታውሳለሁ!
Yenesew Gebre from Dawro-Waka Ethiopia
የኔሰው ገብሬ
እ.ኤ.አ በ11/11/11 የኔሰው ገብሬ የተባለ የ29 ዓመት መምህር እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች በደቡብ ኢትዮጵያ በዳውሮ ዞን በተርጫ ከተማ ከህዝብ መሰብሰቢያ ዳራሽ ፊት ለፊት እሳት በመለኮስ እራሱን በእሳት አያይዟል፡፡ ለሶስት ቀናት ቆስሎ ከቆየ በኋላ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ እራሱን በእሳት ከማያያዙ በፊት የኔሰው ከህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውጭ ለተሰበሰበ ህዝብ እንዲህ የሚል ንግግር አሰምቶ ነበር፣ “በእኩልነት ላይ ባልተመሰረተ አስተዳደር እና ፍትህ በሌለበት እንዲሁም የሰብአዊ መብት በማይከበርበት አገር ውስጥ እራሴን ለመስዋዕትነት አቀርባለሁ፣ ይህንንም በማድረጌ ወጣቱ ትውልድ ነጻ ይወጣል፡፡” የአትዮጵያ ጀግናዉ የእኔሰው ገብሬን አስታውሳለሁ
“ገዳዮችን አስታውሳለሁ፣ የግድያ ሰለባዎችንም አስታውሳለሁ፣ ለትግሌ የሚያግዙ አንድ ሺ እና ከዚያ በላይ ያሉ አሳማኝ ምክንያቶች እና ተስፋ ቢኖረኝም፡፡ ባስታወስኩ ቁጥር ተስፋየ ይሟጠጣል፣ ያንን ድርጊት ባስታውስኩ ቁጥር ደግሞ ተስፋቢስነቴን የማስወገድ ኃላፊነት እንዳለብኝ እገነዘበላሁ፣ ተስፋ ከተስፋቢስነት በላይ ነው፡፡“ ይላል ኤሊ ዊሴል!
**ለጥቃቱ ሰለባዎች ተጨማሪ መረጃ ይሆን ዘንድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት ያሬድ ኃ/ማርያም እ.ኤ.አ ሜይ 15/2006 በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ  ወንጀል በኢትዮጵያ፣ የጁንና ኖቬምበር 2005የአዲስ አበባው ዕልቂት በሚል ርዕስ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላሜንት ለልማትና ውጭ ጉዳዮች እና ለሰብአዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ አስቸኳይ ጥምር ጉባኤ የቃረቡትን ምስክርነት ይመለከቷል፡፡
***የመርማሪ ኮሚሽኑ ሪፖርት ሙሉ በሙሉ የጥቃቱ ሰለባዎችን ነጻ ሲያወጣ አጠቃላይ ኃላፊነቱን ግን በፖሊስና ታጣቂ ኃይሎች ላይ ደፍድፎታል፡፡ መርማሪ ኮሚሽኑ አስተያየቱን በመቀጠል እንደሚከተለው አጠቃሎታል፣ “በተቃዋሚዎቹ የተጎዳ ንብረት የለም፣ በመንግስት በሞኖፖል በተያዘው መገናኛ ብዙሀን እንደተለፈፈው ጥቂት ተቃዋሚዎች የእጅ ቦንቦችንና ጠመንጃዎችን ታጥቀዋል እንደሚለው ሳይሆን በተቃራኒው የእጅ ቦንብ እና ጠብመንጃ የታጠቀ አንድም የተቀዋሚ አባል የለም፣ በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች የተከፈተው ተኩስ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ለመበተን ሳይሆን በተቃራኒው የሰልፈኞችን ጭንቅላትና ደረት ለመበርቀስ ዒላማ ያደረገ ነበር፡፡” የመርማሪ ኮሚሽኑ የ193 የእልቂቱ ሰለባዎችን ስም ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚያካትተው እ.ኤ.አ ከጁን 6 – 8 እና ከኖቬምበር 1- 4/2005 በዚህ ጊዜ ብቻ ያለውን ድርጊት እንዲያጣራ ለአጣሪ ኮሚሽኑ የተሰጠው ስልጣን ነበር፡፡ አጣሪ ኮሚሽኑ ግን በፓርላማው ከተሰጠው የጊዜ ገደብ ውጭ ከህግ ውጭ በመንግስት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች የተፈጸሙ ግድያዎችን ስም ዝዝዝር ያገኘ ቢሆንም እነዚህ ግድያዎች ኮሚሽኑ እንዲያጣራ ተለይቶ ከተሰጠው ጊዜ ውጭ በመሆናቸ ለህዝብ ይፋ ሳያደርገው ቀርቷል፡፡