Monday, December 30, 2013

በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ መቃብር ተገኘ



December 30, 2013
ሁኔ አቢሲኒያዊ
ነገሩ የተከሰተው አርብ እና ቅዳሜ እለት ነው ከስድት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ(በቀድሞ ስሙ ሦስተኛ ሻለቃ) ግቢ ውስጥ በትንሹ ወደ 6 የሚጠጉ አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተገኝተዋል! አስከሬኖቹ ሊገኙ የቻሉት ለመንገድ ስራ የጦር ካምፑ ግቢ አጥር ወደ ውስጥ ፈርሶ መቆፈር ነበረበት፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ነው እንግዲህ በስካቫተር ሲቆፈር በመጀመሪያ ሁለት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለሉ፡፡ በዚህ የተደናገጡት ሰራተኞች ለጊዜው ስራቸን ያቋረጡ ሲሆን በበነጋው ቅዳሜ እለት ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫ ቁፋሮ ሲያደርጉ በዛም በኩል እዲሁ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ አራት አስከሬኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ከአፈሩ ዉስጥ ተገኙ፡፡
A mass grave in Addis Ababa, Ethiopia
በዚህ መሃል ከጦር ካምፑ አካባቢ የተወሰኑ መኮንኖችና ከፍተኛ ማዕረግ(ጄነራሎች)በትከሻቸው ላይ ያለባቸው ሰዎች ወደ ቦታው በመምጣት ስራው እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን በአካባቢው የነበረውንም ሰው ከቦታው አባረው በትነዋል፡፡ በስፋራው ተገኝተው ሁኔታውን ሲከታተሉ እና በስራው ላይም ተሳታፊ የነበሩ ለሰማያዊ ፓርቲ ቅርብ የነበሩ ሰዎች ፎቶ ለማንሳት ጥረት ቢያደርጉም በወታደሮቹ ተመናጭቀዉ ክልከላ ደርሶባቸዋል፡፡ እንደምንጮቻችን እና የምስል ማስረጃዎች ከሆነ አስከሬኖቹ የተጠቀለሉበት ብርድልብስ አንዳችም ሳይቀደድና ሳይበሰብስ ከነአዲስነቱ መገኘቱ ጅምላ ግድያው በቅርቡ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬን አሳድሯል! በጉዳዩ ላይ ማጣራት ለማድረግ ሙከራ ያደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ አባሎችንም ፊት እንደተነሳቸውና ለማናገርም ፈቃደኛ የሆነ ሰው አለማግኘታቸዉንም እንዳዉም ቦታውን ባስቸኳይ እንዲለቁ ከሀይለ ቃል ጋር መታዘዛቸውንም ጨምረውተናግረዋል፡፡
ከወታደሮቹ መሀከል የሆነ አንድ ስምና ሀላፊነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ምናልባትም የግቢው አዛዥ ሊሆን የሚችል ሰው ይህ ግቢ ሶስት ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ሰዎች በመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው ብሎ ትእዛዝ ሲሰጥ የሰሙ የአይን ምስክሮች ለምንጫችን ስለሁኔታው አስረድተዋል! በሁኔታው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በእጅጉ ያዘኑና የተደናገጡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላትና መንግስት ይህን ጉዳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አስተያየት ሲሰጡም ተደምጠዋል! በአሁኑ ሰዓት በስፍራው ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ አካባቢውም በቆርቆሮ ተከልሏል፡፡
ተጨማሪ ብርድልብሱ ደብረ ብርሃን ሲሆን ዲዛይኑ በኢህአዲግ ዘመን በቅርብ የተጀመረው ነው!
ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ

በጀግኖች አባቶቻችን ደም የተቦካው ሉአላዊ ግዛታችን ላይ የሚደረገውን ስውር ሴራ ያለማወላወል በፅናት እንታገለዋለን (ሰማያዊ ፓርቲ)


December 30, 2013

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ታኅሣሥ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. (December 30, 2013)
Statement from Semayawi party of Ethiopia, regarding Nile issue.የኢትዮጵያንና የሱዳንን ድንበር የማካለሉ ሥራ ከመስከረም 29 ቀን 2002 ዓ.ም. (October 9, 2009) ጀምሮ እየተከናወነ እንደሆነ፣ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተመው ዕለታዊ የሱዳን ጋዜጣ ሱዳን ትሪቢውን (Sudan Tribune) በመስከረም 8 ቀን 2002 ዓ.ም. (September 18, 2009) መዘገቡ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ጉዳይ ያንገበገባቸው ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥና በውጪ የሚኖሩት ዜጎቻችንም ራሳቸውን በተለያዩ “ኮሚቴዎች” እና “ግብረ ሃይሎች” በማደራጀት ለጉዳዩ ክፈተኛ ትኩረት እንዲሰጠው ሲጥሩ ቆይተዋል፡፡ ፓርቲያችን (ሰማያዊ)፣ ለነዚህ ሀገር ወዳድ ዜጎች ያለውን ከፍተኛ አክብሮት ለመግለጽ ይወዳል፡፡

ሆኖም፣ የነዚህን ሀገር ወዳድ ዜጎችና አፍቃሪ-ኢትዮጵያውያን ጥሪና መግለጫዎች ከቁብም ካለመቁጠር፣ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ሥውር የሥልጣን ማራዘሚያ ደባዎችን እየሸረበ እንደሚገኝ አጋልጠዋል። ወያኔ ራሱ ያቋቋመው “የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር ኮሚቴ” አባላት ራሳቸው በተለያዩ ቃለ-ምልልሶች እንዳጋለጡት፣ ወያኔ በአባቶቻችን ደም ተላቁጦ ለተቦካውና የበርካታ ሰማዕታትን ህይወት ላስከፈለው የኢትዮጵያ ድንበርና የግዛት ሉዓላዊነት ግዴለሽነቱን በተግባር አሳይቷል፡፡ የኢትዮጵያንም ሉዓላዊ ግዛትና ድንበር “በጫካ ውሎችና ስምምነቶች” እያመካኘ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ጠላቶች አሳልፎ መስጠቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡
ይህንንም ከፍተኛ የሆነ የሃገር ክህደትና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ለማስተባበል በመገንዘብ፣ የወያኔ-ኢህአዲግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ-ገጹ ላይ በመስከረም 2002 ዓ.ም መጨረሻ ላይ አንድ የማደናገሪያ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ከዚህም የማደናገሪያ መግለጫ ውስጥ የሚከተሉትን ሦስት(3) አበይት ጉዳዮች መገንዘብ ይቻላል። እነርሱም፦
1ኛ. የኢትዮጵያና ሱዳን የፖለቲካ ኮሚቴ (Ethio-Sudan Political Committee) ተብሎ የሚጠራ ከፍተኛ አካል መኖሩንና የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ ድንበር ኮሚቴም (Ethio-Sudan Joint Boundary Committee) በፖለቲካው ኮሚቴ ሥር እንደሚሠራ አረጋግጧል፤ የዚህ የኮሚቴ መዋቀርና የአሰራር ሂደቱም ለረጅም ዓመታት ከኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ተደብቆ የቆየ እንደሆነና፣ ወያኔ-ኢህአዲግም በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ክትትል መጋለጡን ሲያውቅ ተጨንቆ ያወጣው ምስጢር ነበር።
2ኛ. የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ የድንበር ኮሚቴም (Ethio-Sudan Joint Boundary Committee) ከጥቅምት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. (October 15, 2009) እስከ ግንቦት 2002 ዓ.ም.(May 2010) ድረስ የኢትዮጵያና ሱዳን ድንበርንና አካባቢውን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀይስና ቅኝት እንደሚያደርግም ገልጾ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ወያኔ ሲጋለጥ ያወጣው ሌላው ምስጢር ሲሆን፣ (ሱዳን ትሪቢውን ያወጣውን ዜና የሚያጎለምስ) እና የሱዳን ሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ድንበሩን ለማካለል የሚያደርገውን ዝግጅት የሚያስተጋባ ነው።
3ኛ. የድንበር ክለላው ከግንቦት 2002 ዓ.ም. ( May 2010) በኋላ እንደሚደረግና ከዚህም ጋር አያይዞ ወያኔ-ኢህአዲግ ያለፉት የኢትዮጵያ መንግሥታት አምነው የተቀበሉት የድንበር ክልል እንዳለ አስምስሎ ለማቅረብም ጥረት አድርጎ ነበር፡፡ በመሆኑም፣ ወያኔ-ኢህአዲግ አሁን የሚያካሂደው “የድንበር-ክለላ ሂደት” ዳግም ድንበርን የመከለል ተግባር ( re-demarcation ) እንደሆነ መግለጹ ለመግለጽ ሞክረዋል፡፡ ይህ ማደናገሪያና ተራ ልፈፋ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማወናበድና ግዛቱን በጫካ ውሎችና ስምምነቶች አማካይነት አሳልፎ ከመስጠት የዘለለ ኢምንት እውነታ የለውም፡፡ ይሄንን በተመለከተም ያጠኑት ሊቃውንትንና በግዛቱ ላይ የሚኖሩትን ዜጎች ምስክርነት ሊያገኝ አልቻለም፤ አይችልምም፡፡
የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት “ያለፉት የኢትዮጵያ መንግሥታት የተቀበሉት የድንበር ክልል” የሚለው ሀተታ፤ ሜጀር (ሻለቃ) ጉዊን የተባለው የእንግሊዝ ጦር መኮንን በ1902 ዓ.ም. (እ.አ.አ.) “አስምሬአለሁ” የሚለውን የወሰን ክልል ነው። ይሁንና አንድ በእንግሊዝ የቅኝ-ገዥነት አባዜ የሰከረ ሻለቃ ያሰመረውን መስመር መሠረት አድርጎ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ሉዓላዊነትን የወያኔ-ኢህአዲግ ገዢ ቡድን “ለሱዳን ይገባታል” ብሎ መሟገቱ የፖለቲካ ቅጥፈት እንጂ ታሪካዊ ማስረጃ የለውም፡፡ የሚከተሉትም ታሪካዊ ዳራዎች የወያኔን ሙግት ውድቅ ያደርጉታል፦
1ኛ.ሻለቃ ጉዊን መሬቱን አካልያለሁ ሲልና በወረቀት ሲያሰምር፤ በኢትዮጵያ በኩል አንድም ተወካይ ስለአልነበረ የጉዊን የድንበር ማካለል ተግባር ከቅኝ ገዢዎች ማንአለብኝነት ተለይቶ የማይታይና የውል አፈጻጸም ሥርዓት የማይከተል በመሆኑ የተነሳ ተቀባይነት የለውም፡፡
2ኛ. የ1896 ዓ.ም.(እ.አ.አ.) የአድዋ ጦርነት ድል በቅኝ ገዥዎች ላይ በፈጠረው ከፍተኛ መደናገጥ ምክንያት 1902 ዓ.ም. (እ.አ.አ.) አካባቢ እንግሊዝና ጣሊያን በጋራ በመመሳጠር የሰሜንና የምዕራብ ኢትዮጵያን ድንበር ለመግፋት የፈፀሙት ሴራ ስለሆነ፣ የሻለቃ ጉዊን ተልዕኮም ከዚያ ሴራ ተነጥሎ ሊታይ አይችልም፡፡ ስለሆነም ተቀባይነት የለውም፡፡
3ኛ. ከአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት በፊትም ይሁን ከዚያ በኋላ፣ ይህ ሻለቃ ጉዊን ከለለው የሚባለው መሬት ምን ጊዜም ቢሆን ከኢትዮጵያ ይዞታ ውጭ ሆኖ አያውቅም፡፡ ይባስ ብሎም፣ በአፄ ቴዎድሮስና በአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ግዛት አሁን ሱዳን ተብሎ ከሚጠራው ሃገር በጣም ወደ ውስጥ የገባ ነበር፡፡ ስለሆነም፣ የግዛት ጥያቄ ሲነሳ የይገባኛል ታሪካዊ መሠረት ያላት ኢትዮጵያ መሆኗን ለማስተባበል አዳጋች ነው፡፡
4.አሁን የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት በመጋቢት 22/2006 ዓ.ም ገደማ March 30, 2014 ለሱዳን ለመስጠት ቅድመ-ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ምንም አይነት ግልጽነትና ተጠያቂነትን መርሆው ያላደረገው የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት ግን አንዳችም መረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳያገኝ የተለመደ አፈናውን ገፍቶበታል፡፡ በመሆኑም፣ በእልፍ-አዕላፍ ድንበር ጠባቂ ኢትዮጵያዊያን ደምና አጥንት ተጠብቆ የኖረውን ዳር ድንበር፣ ወያኔ በተለመደ “የደጃዝማቾች ፈረስ መጠጫና ጉግዝ መጫወቻ ነው” በሚል ንፍገት አሳልፎ ለሱዳን ሊሰጠው ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሰፊ ውሃ-ገብና ለም ሉዓላዊ መሬት፣ የታሪክ ማስረጃዎችንና የኢትዮጵያውያንን መስዋዕትነት በማናናቅ ለባዕዳን ሊሠጥ አይችልም፡፡
ስለዚህ ከላይ በተጠቀሱት ማስረጃዎችና በዓለም-አቀፍ የአሠራር ደንብ መሠረት፤ ወያኔ-ኢህአዲግ ከሱዳን ጋር የሚያደርገው የድንበር ክለላ ስምምነት ህገ-ወጥ ነው። ከዚህም ባሻገር፤ ከዋናው ባለጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በስተጀርባ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ስምምነት ይሁን የድንበር ክለላ ተግባር ምንም ዓይነት ተቀባይነት አይኖረውም።
ከዚህም ሌላ፣ ወያኔ-ኢህአዲግ የተወሰኑ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ መሬት ቆርሶ በመስጠት ሥልጣኑን በጎረቤት አገር ሱዳን ለማስባረክ ብሎ የሚያደርገው ሽር-ጉድ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የለውም፡፡ ውጤቱም “ታግዬላቸዋለሁ የሚላቸውን ብሄሮችና ብሔረሰቦች” ከማዳከምና ብሎም ለማፈራረስ የተጠቀመበተ ዘዴ የቅኝ ገዢዎች ለራሳቸው ጥቅም ማስጠበቂያ ያሰመሩትን የድንበር መስመር በመቀበልና የቅኝ ገዢ ጠበብትን እንደ ምስክር በመጠቀም ነው። ይህም ተግባሩ፣ቀድሞውንም በቋፍ የነበረውን የወያኔ-ኢህአዲግን መንግሥት የፖለቲካ ቅቡልነት የሚያሳጣው መሆኑን ለማስታወስ እንፈልጋለን፡፡ አልፎ-ተርፎም በዚህ ተግባሩም ዛሬም የቅጥረኛ ሥራ እያከናወነ እንደሆነ ህዝቡ እንዲያውቀው እንፈልጋለን፡፡
ይህ የወያኔ-ኢህአዲግ ገዢ ቡድን ተግባር የሃገራችን ኢትዮጵያን ዓለም-አቀፍአዊ ክብር የሚጎዳ ስለሆነ ከተግባሩ እንዲታቀብ እናሳስባለን፡፡ በተጨማሪም፣ ለጉዳዩ ባለቤት ለሆነው ለኢትዮጵያ ህዝብ፣ ዝርዝር መረጃና ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበትም ልንገልጽ እንወዳለን፡፡ ይህን ሳያደርግ ቢቀር ግን፣ ፓርቲያችን የተጣለበትን የአባቶቻችንን ክብርና የሀገራችንን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት መቼም ቢሆን ያለምንም ማወላወል የምንወጣ መሆናችንን ለጉዳዩ ባለቤት ለኢትዮጵያ ኅዝብ በድጋሚ እናረጋግጣለን፡፡
ሰላም፣ ተስፋ፣ ፍትህና እኩልነት በዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች በተከበሩባት ኢትዮጵያ ዕውን ይሆናል!!!

በቁም እስር ላይ ያሉት ብጹእ ኣቡነ ማቲያስ አምጸዋል!!!



ከአሜሪካን መልስ በደህንነት ቢሮ ለ72 ሰአታት ታስረው ነበር::
2013-12-29_015319“ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊ አሸባሪ የለም::” ብጹእ አቡነ ማትያስ“ከኦሮሞ እና አማራ ጳጳሳት ጋር ትፈተፍታላችሁ::” አቶ ጸጋዬ በርሄ ..የአፋኝ ደህንነቶች ሹምበጳጳሳቶች እና በፌዴራሉ ሚኒስትሮች መካከል በስብሰባ ላይ በተነሳው አለመግባባት እና የጳጳሶቹ ድምጽ በደል እና ግፍን በማስተጋባቱ እንዲሁም ለመጣው ችግር ሁሉ ተጠያቂው የኢሕኣዴግ መንግስት ነው:ማለታቸውን ተከትሎ እንዲሁም ጳጳሱ አሜሪካን ተጉዘው ከመጡ በኋላ የሚያሳዩትን የቁጥብነት ባሕሪ ተከትሎ እንዲሁም በቤተክህነት ውስጥ የሚወስዱትን አስተዳደራዊ እርምጃ ያልጣመው ኢሕኣዴግ በአቶ ጸጋዬ በርሄ የሚመራው የአፈና እና የቶርች ቡድን ብጹእ አቡነ ማትያስን ለ72 ሰአታት በደህንነት ቢሮ በቁጣ እና በስድብ በማስጠንቀቂያ አሰቃይተው እና አንገላተው ወደ መኖሪያቸው እንደመለሱዋቸው ከደህንነት ቢሮ ምንጮቻችን ገልጸዋል::ጻጻሱ ለ72 ሰአታት ከመኖሪያቸው ሲታጡ በጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ካድሬ ቄሶች አቡኑ ለህክምና ውጪ አገር ሂደዋል የሚል ወሬ ሲያስወሩ ነበር::
ብጹ አቡነ ማትያስ በደህንነት ቢሮ ውስጥ በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ መሰረት ከአገሪቱ የመንግስት አካልት ጋር እንዲሁም ከጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ካሉ የትግራይ ተወላጆች ጋር በቅርበት እንዲሰሩ የተነገራቸው ሲሆን በዙሪያቸው ያሉ የሲኖዶስ አባላትን ፊት እንዳይሰቷቸው እና አማራ እና ኦሮሞ ጳጳሳቶች እንቅስቃሴያቸው ሁሉ ከአቡነ መልከጻዲቅ እና ከተቃዋሚ ሃይላት መሆኑ አውቀው ጥንቃቄ እንዲወስዱ እንዲሁም አስተዳደራዊ ስራዎችን ለንብረዑድ ኤልያስ አብርሃ እንዲያስረክቡ ተነግሯቸዋል:: ከሳቸው ጋር በረዳትነት አቡነ ሳሙኤል እንዲሰሩ መመሪያ የተሰጣቸው መሆኑ ታውቋል::
ብጹእ አቡነ ማቲያስ በደህንነት ቢሮ የአቶ ጸጋዬ በርሄ ቡድን ማስፈራሪያ ሲሰጣቸው ፊታቸውን ቅጭም አድርገው በሃዘን እና በቁጭት ስሜት ያዳምጡ እንደነበር ታይተዋል:: መልስ ሲሰጡ የነበሩት እጅግ ዘግይተው በትካዜ እንደነበር ታውቋል::አሸባሪዎችን መዋጋት አለብዎ ሲባሉ በኢትዮጵያ ምድር ኢትዮጵያዊ አሸባሪ የለም ብለው የመለሱት አቡኑ አብዛኛው መልሶቻቸው “…እስኪ ካላችሁ ይሁን እግዛብሄር እንደፈቀደው…’ የሚል እንደነበር የደህንነት ቢሮ ምንጮች ጠቁመውናል::
በዚህም መሰረት አቡነ ማትያስ የፖለቲካ ፍጆታ በሚያስፈልጋቸው መንፈሳዊ ስብሰባ ላይ አይገኙም:: በተገኙበትም ቦታ ደሞ ስለ ልማት ካልሆነ በቀር ስለ አስተዳደራዊ ጉዳይ እና ስለ ብሶት ቀስቃሽ ንግግር እንዳያደርጉ ተነግሯቸዋል:: በአሁኑ ወቅት ማንኛውም የአገር ውስጥ እንቅስቃሴያቸው በደህንነት አይን ስር ያለ ሲሆን የቁም እስር ላይ ናቸው::
እግዛብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቃት

Saturday, December 28, 2013

ይድረስ ለብአዴን አባላት


በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ ወደ ባህር ዳር አቅንተው ነበር። መቸስ በረከት ስምዖን አማራ ካልሆንኩ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ አለመንደሩ የአማራ ህዝብ መሪ እኔ ነኝ ብሎ ከአማራ ህዝብ ፊት ሲቆም አለማፈሩ ያስገርማል። አዲሱ ለገሰም እንደ በረከት ራሱን የአማራ ህዝብ ወኪል እኔ ነኝ ይላል።እነዚህ ሁሉት ህወሃት የሠራቸው ፍጡራን ባህር ዳር እንዲወርዱ ያደረጋቸው ብአዴን ተዳክሟል ተብሎ መታሠቡ ነበር።
እንግዲህ በእንበረከት የአስተሳሰብ ደረጃ ብአዴን ተዳከመ ሲባል ምን ማለት ይሆን?
ከጥቂት ደካማ ካድሬዎች በቀር ሌሎች እንደ ሰው ማሰብ የሚችሉ የብአዴን አባላት አገሪቷ እየሄደች ያለችበት መንገድ ያሳስባቸዋል። ህወሃት በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ የሚያንገበግባቸው በርካታ ናቸው። ጉርፋርዳ እና ቤንሻንጉል አገራችሁ አይደለም ተብለው አማሮች ከኖሩበት ቀየ ተፈናቀለው ሜዳ ላይ የመውደቃቸው ድርጊት የእግር እሳት ሁኖ የሚለበልባቸው ብዙዎች አሉ። በዚህ ሁኔታ ያዘኑና የተቆጡ የብአዴን ካድሬዎች ድርጅቱ ቆሜለታለው የሚለው ፍትህ የት አለ፤ እኩልነትስ ከወዴት አለ፤ ኢትዮጵያስ የሁላችን አገር ነች የምትባለው መገለጫው ምንድ ነው እያሉ ይጠይቃሉ። እነዚህ ጥያቄዎች በካድሬዎች መካከል መመላለስ ሲጀምሩ ድርጅቱ ተዳክሟል ተብሎ ግምገማ ይካሄዳል።
በረከት እና አዲሱ ነፃነትን ሳያውቁ ራሳቸውን ነፃ አውጪ አድርገው የሚቆጥሩ የህወሃትን ዙፋን ከመጠበቅ የዘለለ ምንም ሚና የሌላቸው ያልሆኑትን ለመሆን የሚውተረተሩ ደካሞች መሆናቸውን እናውቃለን። እነዚህ ግለሰቦች ስለ አማራ ህዝብ ነፃነትና ክብር ይሠራሉ ብሎ ማሰብ የሚቻልበት ሁኔታ የለም። በረከትና አዲሱ በህዝብ መካከል እየኖሩ የህዝብ ፍቅር የሌላቸው፤ ከህዝቡ ጋር መኖርንም የማያውቁ፤ እለት ዕለት በሚፈጥሩት የፍርሃት አረንቋ ውስጥ የሚኖሩ እና ሠላም የራቃቸው ግለሰቦች ናቸው። ከእነዚህ ግለሰቦች እውነትን ፈልጎ ማግኘት፤ ነፃነትን ጠይቆ መቀዳጀት፤ ለፍትህ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የሚቻል አይደለም። የአማራ ህዝብ ከጉራፋርዳ እንዲወጣ የተደረገበት ምክንያት ምንድ ነው ተብለው ሲጠየቁ የጠባቦች ጥያቄ ብለው ይሳደባሉ። አያቶቻችን በደምና አጥንታቸው ያቆዩልንን ድንበር አፍርሳችሁ ለባእዳን ለምን ትሰጣላችሁ ሲባሉ የጦርነት ናፋቂ ጥያቄ እያሉ ይዘባበታሉ። እንደምን ሁኖ ከሁለት ሚሊዮን በላይ አማራ ከቁጥሩ ጎድሎ ተገኘ ሲባሉ የትምክህተኞች ወሬ እያሉ ይሳለቃሉ። አዎን እነበረከት ስምዖን የሚፈልጉት ዜጎች ስድባቸውን ተሸከመው እንዲኖሩላቸው እንጂ እውነትን፤ ፍትህን እና እኩልነትን እንዲጠይቁ አይደለም።
የሰሞኑ የባህር ዳር አስቸኳይ ስብሰባ ምክንያትም በብአዴን ካድሬዎች መካከል የፍትህ፤ የነፃነት እና የእኩልነት ጥያቄዎች ሥር እየሰደዱ መምጣታችው ነው። በካድሬዎቹ መካከል እንደ እሳት ሰደደ እየተሰራጩ ላሉ የፍትህ፤ የነፃነት እና የእኩልነት እጦት ጥያቄዎች ከህወሃት መራሹ “መንግስት መሰል” አካል በቀላሉ መልስ ማግኘት የሚቻል አይደለም። ይሄ ቡድን ነፃነትን ሳያውቅ ነፃ አወጣኋችሁ ማለትን ብቻ የሚያውቅ፤ራሱ ለሠራው ህግ መገዛትን ሳይወድ ስለ ህገ-መንግስት የበላይነት የሚሰብክ፤ ራሱ ከሁሉ በላይ እኔ ነኝ ብሎ ሲያበቃ ስለ እኩልነት ለመስበክ የማያቅማማ የነውረኞች ስብሰብ ነው። በረከትና አዲሱም የዚህ ነውረኛ ቡድን አካል እንጂ የአማራ ህዝብ አካል ናቸው ለማለት ለአማራ ህዝብ የሠሩት በጎ ነገርን ፈልጎ ማግኘት አይቻልም።
የብአዴን ካድሬዎች ሆይ !
ብአዴን ከተመሠረተ በኋላ ከሁለት ሚሊዮን በላይ አማራ መጥፋቱን በፓርላማ ሪፖርት መደረጉን ሰምተችኋል።ለመሆኑ ከሁለት ሚሊዮን በላይ አማራ የት ጠፋ? በአገሪቷ ካሉ ብሄረ ብሄረሰቦች መካከል እንደምን ሁኖ የአማራ ቁጥር ብቻ ሊቀንስ ቻለ? ከአማራ ክልል ወጥተው በሌላ ክልል የሚኖሩ አማሮች ይሄ አገራችሁ አይደለም፤ ወደ አገራችሁ ሂዱ ተብለው የሚባረሩት ለምንድ ነው? ኢትዮጵያ አገራቸው ካልሆነች የእነዚህ አማሮች አገር ወደየት አለች? ከጉራፈርዳ እና ከቤንሻንጉል ተነቅለው ሜዳ ላይ እንዲወድቁ የተደረጉ አማሮች በደላቸው ምንድ ነው? ለነዚህ ጥያቄዎች አማራ ካልሆንን ሞተን እንገኛለን የሚሉት በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ መልስ አይሰጡም። እነርሱ የቆሙት በህወሃት “የትግራይ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት አማራ ነው” ተብሎ የተያዘውን እምነት በተግባር ለማስፈፀም እንጂ ለአማራ ህዝብ ደህንነት እንዳለሆነ ምግባራቸው ህያው ምስክር ነው።
ብአዴን ከተመሠረተ ዘመን ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰውን ግፍ እናውቃለን። የአማራን ቅስም መሰበር፤ ትምክህቱን ማስተንፈስ፤ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ማዋረድ የሚሉት የእነበረከት ስምዖን ዋነኛው መፈክሮቻቸው ናቸው።በዚህ መፈክር መሪነት ከሁለት ሚሊዮን በላይ አማሮች ጠፍተዋል፤ኢትዮጵያ አገራችሁ አይደለችም ተብለው ከጉራፈርዳ እና ከቤንሻንጉል ውጡ ተብለው ሜዳ ላይ ተጥለዋል። ከንግዱ አምባም ሳይቀር ቀስ በቀስ አማሮች እንዲጠፉ ተደርገው ሥፍራቸውን ለሌላ እንዲለቁ ሁነዋል። ከፕሮፌሰር አሥራት ጀምሮ ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምልክት እና ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ አማሮች ቀስ በቀስ እንዲጠፉ መደረጋቸውን በአይናችን አይተናል በጆሮአችንም ሰምተናል። ብአዴን የተባለው ድርጅት በአማራ ስም ቢቋቋምም አማሮችን ከውርደትና ከሚደርስባቸው በደል ሊታደጋቸው አልቻለም።እንዲያውም ግፉንና በደሉን ለማስፈፀም የተወከለ ድርጅት ሁኗል።
እንግዲህ የብአዴን ካድሬዎች ሆይ እናንተም ከበረክተ ስምዖንና ከአዲሱ ለገሰ ጋር ተሰልፋችሁ ህዝባችሁን ትወጉ ዘንድ አይገባም። ዙሮ መግቢያችሁ ዛሬ እንወክለዋለን ያላችሁት ግን ደግሞ በአሣር በመከራ ውስጥ ያለው ህዝብ እንጂ ሌላ ዙሮ መግቢያ እንደሌላችሁ እወቁ። የወከላችሁት ህዝብ ሲረገጥ የለም ህዝቤን አትበድሉ ማለት ይጠበቅባችኋል። አማራ ከቁጥሩ ጎደለ ሲባል ምን ሆኖ እንደጎደለ በመጠየቅ የችግሩን ምንጭ ማወቅ ሥራችሁ ነው። አማራ ወደ “አገርህ” ሂድ ተብሎ ከኖረበት ሲነቀል ኢትዮጵያ አገሩ ካልሆነች የአማራ አገሩ የት ነው ብላችሁ መጠይቅ አለባችሁ።
ዛሬ እናንተን ትምክህተኞች እያለ የሚገመግማችሁ በረከት ስምዖን አያሌው ጎበዜን አስነስቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንዲተካ አድርጓል። የአያሌው መሄድና የገዱ መምጣት ለአማራ ህዝብ ነፃነት እና ክብር የሚፈይደው አንዳችም ቁም ነገር የለም። አያሌውም ሆነ ገዱ ለቆሙለት ህዝብ ይቅርና ለራሳቸውም ክብር የሌላቸው ደካሞች መሆናቸው የታወቀ ነው። ለራሱ ክብር ያለው የህዝብ ወኪል እወክለዋለው የሚለው ህዝብ ከኖረበት ቀየ እየተነቀለ ሜዳ ላይ ሲጣል አይቶ ዝምታን አይመርጥም። አያሌውና ገዱ ከአማራ ህዝብ አብራክ ወጥተው ደሃውን አማራ በሙሉ ነፍጠኛ፤ ትምክህተኛ፤ ሌላም ሌላም እያሉ እየሰደቡ ለሳዳቢ አሳላፈው የሰጡ ደካሞች ናቸው። ካድሬ ሆይ ስማን! የገዱ በአያሌው መተካት የተዋረደውን ክብርህን አይመልሰውም። ያጣኸውን ነፃነት መልሶ አያቀዳጅህም። ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠውን በአያቶችህ ደምና አጥንት የቆየውን መሬትም አይመልስልህም። የብአዴን ካድሬዎች ሆይ ስሙ ለክብራችሁ፤ ለማንነታችሁ፤ ለነፃነታችሁ ቀናዒ እንድትሆኑ ሁኑ እንጂ የህወሃትን ትርፍራፊ የምትለቃቅሙ አትሁኑ።
በብአዴን ውስጥ ያላችሁ የንቅናቄያችን አባሎች ሆይ !!
የህወሃት ስንቅና ትጥቁ ጥላቻ መሆኑን ታውቃላችሁ። ህወሃት “አማራ የትግራይ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነው” ብሎ የሚያምን ቡድን ነው። ከዚህ ቡድን ፍትህ፣ እኩልነትና ነፃነት ያለመስዋእትነት እንደማይገኝ መዘንጋት አያስፈልግም። እስከ አሁን የንቅናቄያችንን መሠረት ለማሲያዝ ያደረጋችሁት አስተዋፅኦ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በህወሃት የተነጠቀው ነፃነታችን፤ የተዋረደው ክብራችንና ማንነታችን በቀላሉ እንደማይመለስ መገንዘብ ይኖርብናል። ትግሉ መራራ የሚሆንበት ግዜ መጥቷል። ለነፃነትና ለማንነት የሚከፈል መሥዋእትነት ደግሞ አስፈላጊ መሥዋዕትነት ነው።ጥቂት ዘረኞች አንገታችንን አስደፍተው በማንነታችን ላይ ተሳልቀው፤ ህዝባችንን አጎሳቁለውና ረግጠው ሲገዙ በአይናችን እያየንና በጆሮአችን እየሰማን ተንጋለን ለመተኛት አልተፈጠርንም። እንዲህ ዓይነቱን ሥንፍና ከቀደሙት ከኩሮዎቹ አያቶቻችንና አባቶቻችን አልተማርንም።
በአውሬው መረብ ውስጥ ሁናችሁ የለውጥ ኃዋሪያ ለመሆን መነሳታችሁ የሚደነቅ ነው።የለውጥ ኃዋሪያነት ትልቅ ሸከም ያለው ነው።ጥላቻን ወደ ፍቅር የሚቀይር፤ ለይቅርታ ራስን ማዘጋጀት፤ ከግዜያዊ ጥቅም ይልቅ ትውልድን አሻግሮ የማየት ራዕይን የሚጠይቅ ነው። ህወሃት አገሪቷን እያፈረሰ ያለው ከፍቅር ይልቅ በጥላቻ ስለተሞላ፤ ከይቅርታ ይልቅ በበቀል ልቦና የሚመላለስ በመሆኑን፤ ትውልድን አሻግሮ ከማየት ይልቅ የስግብግብነት ስሜቱ ያየለበት ሆኖ በመገኘቱ ነው። ንቅናቄያችን ይህን ከመሰለ አገር አጥፊ አስተሳሰብ በላይ ነው። ንቅናቄያችን ሁል ግዜ ለይቅርታ የተዘጋጀ ልቦና አለው። ይሄ ሲባል ግን የበቀለኞችን ሠይፍ ለመመከት ራሱን አያዘጋጅም ማለት አይደለም። እንዲያውም ሰይፋችን ከእነርሱ ሠይፍ በላይ የሳለ መሆኑን ያውቁት ዘንድ እንወዳለን። ንቅናቄያችን ትውልድን አሻግሮ የሚያይ ባለ ረዥም ራዕይ ነው። እንደ ህወሃት ለዘረፋ የተሠለፈ፤ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል የሚል አይደለም። ዘራፊውንና እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይበቀል የሚለውን ሁሉ ነቅሎ ሥፍራውን ለማስለቀቅ ሳያቅማማ በፅናት የሚሠራ ነው።
በብአዴን ውስጥ ያላችሁ የንቅናቄው አባላት ሆይ!!
የገዱ በአያሌው መተካት የሚያመጣው ለውጥ የለም።አያሌው ሄደ ገዱ መጣ ሁለቱም ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ደካሞች ናቸው። ገዱ የነፃነትን፤የፍትህንና የእኩልነትን ዋጋ የሚያውቅ አይደለም። ገዱ ሲሊኩት ወደየት፤ ሲጠሩት አቤት ከማለት የዘለለ ለዚያች አገር ለውጥ የሚፈይደው አንዳችም ነገር እንደማይኖር እወቁ። ስለሆነም የተጀመረውን ትግል ከዳር ለማድረስ ሳታቅማሙ በፅናት ቁሙ። ፍርሃትን ግደሉት። ከፍርሃት አርነት የሚያወጣን ነፃነት፤ ፍትህና እኩልነት ብቻ ነው። እነዚህ ለሰው ልጆች መሠረታዊ ቁም ነገሮች በአገሪቷ ሰፍነው ዜጎች ሁሉ እፎይ እሰከሚሉ ድረስ የሚከፈለውን መሥዋ ዕትነት ለመክፈል ወደ ኋላ እንዳትሉ። በእኛም በኩል አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ለመክፈል የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። የጀመርነውንም ትግል ሳናቅማማ እና ሳናፈገፍግ እንቀጥላለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

Friday, December 27, 2013

ትግሉ የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅበት ወሳኝ ምእራፍ ላይ ደርሷል



ራሱን የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ብሎ የሚጠራው ድርጅት በከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ ገብቷል። የህወሃትን ዙፋን ከመጠበቅ ባለፈ ምንም ሚና የሌላቸው የብአዴን አመራሮች ያለፉትን ሶስት ወራት በተለያዩ መንገዶች የድርጅቱን አባሎች ሲገመግም ከርመዋል። በግምገማዎች ላይ እንደተረጋገጠው ብአዴን የህወሀትን ዙፋን ሊሸከሙ የሚችሉ ወጣቶችን ኮትኩቶ ለማሳደግ አለመቻሉ ነው። በብአዴን ውስጥ ለሚታየው የውስጥ ትርምስ በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙ የግንቦት7 አባላትና ደጋፊዎች እየተጫወቱት ያለው ሚና በሌሎች ድርጅቶች ውስጥ ላሉ የንቅናቄው አባላት ጥሩ ትምህርት የሚሰጥ ነው። የንቅናቄው አባሎችና ደጋፊዎች በድርጅቱ ውስጥ የታቀፉ ወጣቶችን የፖለቲካ ግንዛቤ ከማሳደግ ጀምሮ ፣ የንቅናቄውን መረብ እስከ ወረዳዎች በመዘርጋት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ናቸው። ሰሞኑን በገሀድ በየግምገማዎች ላይ ሲነገር እንደነበረው ብአዴን እወክለዋለሁ ከሚለው የአማራ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ተነጥሎ በአየር ላይ የተነሳፈፈ ድርጅት ሆኗል።

ይህን እውነታ ዘግይተው የተረዱት የብአዴን ዙፋን ጠባቂ አመራሮች የሚይዙትን የሚጨብጡትን በማጣት የተለያዩ ውሳኔዎችን እያሳለፉ ነው። ታማኝ የሚሉዋቸውን ካድሬዎች በየወረዳዎች በመላክ በግንቦት7 የሚጠረጠሩትን ወይም የግንቦት7 አባሎች ናቸው ተብለው ከሚገመቱ ሰዎች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት አላቸው ተብሎ የሚታሰቡትን ሰዎች በመያዝና በማሰቃየት ሌላው ወጣት ንቅናቄውን እንዳይቀላቀል ለማድረግ እቅድ ነድፈው ለመንቀሳቀስ አስበዋል። እንዲሁም አንድ ለአምስት የተባለውን አደረጃጀት በመስሪያ ቤቶች፣ በቤተሰብ፣ በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ ተቋማት ላይ በስፋት በማውረድ፣ የሰውን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አልመዋል። ወጣቱ አካባቢውን እየለቀቀ ግንቦት7ን ለመቀላቀል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የአካባቢ ፖሊሶችንና የድንበር ጠባቂዎችን በማጠናከር ለመቆጣጠር ውሳኔ አሳልፈዋል።
በድርጅቱ ውስጥ የግንቦት7 ደጋፊዎች ናቸው ተብለው የሚጠረጠሩትን ወይም ዝንባሌ አላቸው የሚባሉትን ሁሉ ነቅሶ በማውጣት ለብአዴን ነፍስ ለመዝራት ሙከራ እየተደረገ ነው። እነዚህን ውሳኔዎች ያስፈጽማሉ የተባሉ በጭካኔያቸው ፣ በጎጠኝነታቸውና በንቅዘታቸው የሚታወቁትን የእነሱ ታማኝ ካድሬዎችን ወደ ፊት ለማምጣት በማሰብ ሰሞኑን ሹም ሽር አድርገዋል። ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም እንደሚባለው የሰዎች መለዋወጥ የብአዴንን ህልውና ከክስመት የሚታደገው አይሆንም።
ለመሆኑ ብአዴን የህወሀትን ዙፋን ከመጠበቅ በስተቀር ባለፉት 22 አመታት እወክለዋለሁ ለሚለው ህዝብ ምን ሰራ? ብአዴን ባለፉት 22 ዓመታት ከሰራቸው አሳፋሪ ስራዎች መካከል ሰፊው የአገራችን መሬት ለሱዳን ተላልፎ ሲሰጥ የስምምነት ፊርማውን ማስቀመጡ ነው። ከዚህ በተጨማሪ እወክለዋለሁ የሚለው የአማራ ህዝብ ከቦታ ቦታ ሲፈናቀል፣ ለአመታት ህዝቡ በኤድስና በወባ እንደቅጠል ሲረግፍ ፣ ወጣቱ ስራ አጥቶ በአደገኛ እጾች ደንዝዞና ተስፋ ቆርጦ የወጣትነት እድሜውን በከንቱ ሲያሳልፍ ብአዴን ዞር ብሎ ለማየት ፈቃደኛ አልሆነም።
የብአዴን ዙፋን ጠባቂነት የሰለቻቸው የድርጅቱ አባላት በተለያዩ ጊዜያት የውስጥ ትግል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ብዙዎች በህወሀትና በተላለኪው ብአዴን የጸጥታ ሀይሎች ተገድለዋል፣ አንዳንዶች ድርጀቱን ለቀው ወጥተዋል፣ አንዳንዶች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብአዴን ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላ አገራችን ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ፈቃደኝነታቸውን አሳይተው በግንቦት7 ስር ታቅፈው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉት ወጣት አባላት የቀድሞ አባሎች የጀመሩትን ትግል በተደራጀና ስርአት ባለው መልኩ ለማስኬድ የጀመሩት ትግል ንቅናቄው በትኩረት የሚከታተለው ነው። ይህ ትግል ተጠናክሮ በሌሎች ድርጅቶችም ተግባራዊ እንዲሆን ግንቦት7 በተለያዩ የኢህአዴግ ድርጅቶች ውስጥ ላሉ አባሎቹ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ግንቦት7 መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ከዘረኛው፣ ዘራፊውና ራዕይ አልባው የህወሀት ጎጠኛ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመገላገል እና በምትኩ የሁሉም የምትሆን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት የጀመረውን ትግል ከመቼውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህ ወሳኝ የትግል ምእራፍ ወቅት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ብሎ ንቅናቄው እንደሚያምን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። በተለይም በኢህአዴግ ድርጅቶች ውስጥ ታቅፈው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ እውነተኛ የስርአት ለውጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ ሀይሎች የብአዴን ወጣት የግንቦት7 አባላት እያሳዩት ካሉት እንቅስቃሴ ልምድ በመውሰድ በውስጥ የሚያደርጉትን ትግል አጠንክረው እንዲገፉበት ንቅናቄያችን ጥሪውን ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

የጁነዲን ባለቤት በድርድር ተፈቱ !!/ከኢየሩሳሌም አርአያ/


የቀድሞ የኦህዴድ/ኢህአዴግ አመራር አባልና ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት በውስጥ በተደረገ ድርድር ከእስር እንዲለቀቁ መደረጉን የቅርብ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ። « ከሳኡዲ ኤንባሲ ገንዘብ ተቀብለው ሲወጡ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል» በሚል በሽብርተኝነት ወንጀል እንዲከሰሱ የተደረጉትና ለአንድ አመት የታሰሩት የአቶ ጁነዲን ባለቤት ወ/ሮ ሃቢባ መሐመድ ከሕወሐት መሪዎች በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ እንዲፈቱ መደረጉን የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ይህ ሊሆን የቻለው በስደት ከሚገኙት አቶ ጁነዲን ሳዶ ጋር በተደረገ ምስጢራዊ ድርድር ላይ “መንግስት ከዚህ ቀደም በወሰዳቸው እርምጃዎች፣ ፖለቲካዊ ምስጢራዊ ጉዳዮችና ገዢውን ፓርቲ የሚመለከቱ ማንኛውም ነገሮች በየትኛውም ቦታ ላለማጋለጥ፣ ላለመናገር፣..” ከጁነዲን ጋር ከስምምነት ከደረሱ በኋላ ባለቤታቸው እንዲፈቱ መደረጉን አስታውቀዋል። በሙስና የተጨማለቁት አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ደ/ፂዮንና ፀጋዬ በርሄ ከጁነዲን ጋር እንደተደራደሩ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። 
መጀመሪያም ወ/ሮ ሃቢባ የሰሩት ወንጀል ኖሮ አይደለም የታሰሩት ያሉት ምንጮቹ አቶ ጁነዲን ከስልጣን ለማንሳት ሲባል ብቻ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ገልፀዋል። ጁነዲን ባለቤታቸው ከታሰሩ በኋላ በስልጣን ላይ እያሉ እንዲያውም ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ሚሚ ስብሃቱ በምታዘጋጀው ራዲዮ ጣቢያ « ጁነዲን መታሰር አለባቸው፤ መንግስት እስከ አሁን እርምጃ የማይወስደው ለምንድነው?..ባለቤታቸው አሸባሪ ናት» በማለት የፍ/ቤትን ነፃነት ጭምር በሚጋፋ መልኩ ቅስቀሳ ይካሄድ እንደነበረ ምንጮቹ አስታውሰዋል። አቶ ጁነዲን ከአገር ከወጡ በኋላ እውነቱን እያወቁ መደራደራቸውና ባለቤታቸውን በማስፈታት ሌሎች ንጹሃን የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች ላይ በተዘዋዋሪ በመፍረድ የኢህአዴግና ካንጋሮው ፍ/ቤት ተባባሪ መሆናቸው አሳዛኝ ነው ብለዋል ምንጮቹ። አቶ ጁነዲን ምናልባትም « ባለቤቴ በፍ/ቤት ነፃ ተባለች» በሚል በኢትዮጲያ የፍትህና የፍ/ቤት ነፃነት እንዳለ አስመስለው ሊናገሩ እንደሚችሉ ማረጋገጫ የለም ያሉት ምንጮቹ አክለውም ጁነዲን ምንም አሉ ምን በስልጣን እያሉ ለፈፀሙት ወንጀል መጠየቃቸው እንደማይቀር መታወቅ አለበት ብለዋል።
source: harartubes.com

Thursday, December 26, 2013

ሰበር ዜና ሪያድ መንፉሃ ውስጥ፡ ማምሻውን ውጥረት ነግሷል ! በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ኢትዮጵያውያኑ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ወረቀት በትኗል!








ሰበር ዜና ሪያድ መንፉሃ ውስጥ፡ ማምሻውን ውጥረት ነግሷል ! በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ኢትዮጵያውያኑ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ወረቀት በትኗል! 
=====================================================
ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቋጣጠር ከቀትር 6 ሰዓት ጀምሮ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው የሃበሾች መንደር ከ 15 ሺህ በሚበልጡ ቆመጥ፡ እና አሜሪካ ሰራሽ ኦዚ በታጠቁ የሳውዲ ኮማንዶዎች መከበቡን የሚናገሩ የአካባቢው ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መታፈሳቸውን ይገልጻሉ ፡፤ በአካባቢው ውጥረት መስፈኑንን የሚገልጹ የአይን ምስክሮች ማንኛውም ሰው ወደተጠቀሰው መንደር መግባት እንጂ መወጣት እንዳማይችል ይገልጻሉ። 

ይህን ተከትሎ ማምሻውን አያሌ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል የተፈጸመው አይነት ጭፍጨፋ ይፈጸምብን ይሆን የሚል ስጋት ውስጥ እንደሆኑ የሚናገሩ ምንጮች ዛሬ አመሻሹ ላይ መንፉሃ ዳግም ወደ ጦር ቀጠናነት መለወጡ ያስደነገጣቸው የሃበሻ ሱቆች እና ምግቤቶች በግዜ ለመዝጋት መገደዳቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያኑን ነዋሪ ለበለጠ ጭንቀት እንደዳረጋቸው ይናገራሉ። የፀጥታ እስከባሪዎቹ ማመዘኛ ህጋዊ መሆን ያለመሆን ነው የሚሉ ምንጮች የሌላ ሃገር ዜጎች መንፉሃ ውስጥ፡በነጻነት ሲንቀሳቀሱ መታየታቸውን ጠቅሰው በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ይህ ሁለተኛ ዙር የሳውዲ መንግስት እርምጃ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውንም ጭምር ፈቃዶቻቸውን እይቀደዱ ከሃገር ለማባረር እቀድ መኖሩን ማሳያ ነው ብለዋል ። 

በተለይ ታህሳስ 7 ቀን 2006 ዓም በተሰጠው የምህረት ግዜ ውስጥ፡የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ ለማስተካከል ጀምራችህ ላልጨረሳችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በሚል ረዕስ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ባወጣው ማስታወቂያ ተጭበርብረናል የሚሉ ወገኖች « የጀመራችሁትን የማስተካከል ሂደት ማጠናቀቅ እንድትችሉ ሚሲዮኑ ለሳውዲ አረቢያ መንግስት ጥያቄ ለማቅረብ እንዲቻል ከታትህሳስ 9 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተገኝታችሁ እንድተመዘገቡ እናስታውቃለን » በሚል አያሌ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፈቃድ እና የፓስፖርት ቁጥሮቻቸውን የሪስፖንሰር « የከፊል » ቴልፎን ቁጥሮቻቸውን እና ኢትዮጵያውያኑ ሪያድ መንፉሃ ነሲም ነስሪያ ኡመልሃማም እና አካባቢዎ የሚኖሩበትን የመኖሪያ አድራሻ ዲፕሎማቱ እንደመዘገቡ የሚናገሩ ታዛቢዎች ጉዳያችን በኤንባሲ በኩል ታይቶ እልባት ያገኛል ብለው የተስፋ የጣሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በህገወጥነት ተፈርጀው ስም ዝርዝር እና የመኖሪያ አድራሻዎቻቸው ለሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች መተላለፉ ዲፕሎማቱ ከህዝብ ያልተፈጠሩ እርጉም አረመኔ መሆናቸውን ማስያ ነው ብለዋል። 

በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ሰሞኑንን በልማት ማህበራት በኩል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሶስት ወር ግዜ ውስጥ የሳውዲን ምድር ለቆ እንዲወጣ በተላላኪዎቻችቸው አማካኝነት መለዕክት ሲያስተላለፉ በነበሩበት ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠማቸው የሚናገሩ ምንጮች እንደማንኛውም የወጭ፡ሃገር ዜጋ ህጋዊ ለመሆን የሚያስችሉን ነገሮች አሞልተን እያለን በኢትዮጵያዊነታችን ብቻ ሳውዲ ውስጥ የመኖር መብታችን መታገዱ ከጀርባው ድብቅ አጀንዳ እንዳለው ይገልጻሉ ። በተለይ ኢትዮጵያውያኑ ቀደም ብለው ህጋዊ ለመሆን የሚያስችላቸውን ጉዳዮቻቸውን ለማስፈጸም በሳውዲ ኢሜግሬሽን ስደተኞች ጉዳይ መ/ቤት ተጸኖ እይተደረገባቸው መሆኑንን በማውሳት በተደጋጋሚ ብሷታቸውን በጽሑፍ እና በአካል ለኢትዮጵያ ኤንባሲ ቢያቀርቡም ጆሮ ዳባ ተብለው ከርመው ዛሬ በኤንባሲው አንደበት ህግወጥ ትብለው በመፈረጅ ለባዕዳን ተላልፈው መሰጠታቸው በህዝብ ዘንድ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ቁጣን ይቀሰቅሳል ተብሎ ይሰጋል። 
በኢንባሲው ህግወጥ ትብለው የተፈረጁት ኢትዮጵያውያን ጥያቂያቻቸውን በማጠናከር 
1/ነፃ የሙያ ቅየራ /profishinal change/ ይፈቀድልን ።
2/ የመኖሪያ ፈቃዶቻችንን ከግለሰብ ወደ ተለያዩ መ/ቤቶች እንድናደርግ ይፈቅድልን ።
3/ ያለ ምክንያት ሚደረግ የመኖሪያ ፈቃድ በላግ ይቁምልን ።
4/ፖሊሲ ባልተፈፀመ ወንጀል ይዞ ማሰር ያቁምልን ።
5/ለዕድሳት የሚሰጡ የመኖሪያ ፈቃዶቻችን በጊዜ ታድሰው ይመለሱልን ።

ይህ ሁሉ የማይቻል ከሆነ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን የተከበረው ኤምባሲ መሉ የኢቃማ ወጪያችውን ከነ ሞራል ካሳ የሳውዲ መንግስትን ጠይቆ በሰላማዊ መንገድ ወደ ሐገራቸው የሚመለሱበትን ሆነታ ሊያመቻችላቸው ይገባል የሚሉ ወገኖች የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ካርታ አሲዘው አሊያም ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቻቸውን ሸጠው ሳውዲ አረቢያ ሰርቼ እለወጣለሁ በሚል ተስፋ ከ 1 መቶ ሺህ እስከ 2 መቶ ሺህ ብር አውጥተው የገዙትን መኖሪያ ፈቃዶቻቸውን ሰርዘው ሃገር እንዲገቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ እያሰማ ያለው ጩኽት ወገናዊነት የጎደለው በመሆኑ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ከፍተኛ ተቋውሞ መቀስቀሱን አክለው ገልጸዋል።





ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቋጣጠር ከቀትር 6 ሰዓት ጀምሮ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው የሃበሾች መንደር ከ 15 ሺህ በሚበልጡ ቆመጥ፡ እና አሜሪካ ሰራሽ ኦዚ በታጠቁ የሳውዲ ኮማንዶዎች መከበቡን የሚናገሩ የአካባቢው ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መታፈሳቸውን ይገልጻሉ ፡፤ በአካባቢው ውጥረት መስፈኑንን የሚገልጹ የአይን ምስክሮች ማንኛውም ሰው ወደተጠቀሰው መንደር መግባት እንጂ መወጣት እንዳማይችል ይገልጻሉ። 

ይህን ተከትሎ ማምሻውን አያሌ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል የተፈጸመው አይነት ጭፍጨፋ ይፈጸምብን ይሆን የሚል ስጋት ውስጥ እንደሆኑ የሚናገሩ ምንጮች ዛሬ አመሻሹ ላይ መንፉሃ ዳግም ወደ ጦር ቀጠናነት መለወጡ ያስደነገጣቸው የሃበሻ ሱቆች እና ምግቤቶች በግዜ ለመዝጋት መገደዳቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያኑን ነዋሪ ለበለጠ ጭንቀት እንደዳረጋቸው ይናገራሉ። የፀጥታ እስከባሪዎቹ ማመዘኛ ህጋዊ መሆን ያለመሆን ነው የሚሉ ምንጮች የሌላ ሃገር ዜጎች መንፉሃ ውስጥ፡በነጻነት ሲንቀሳቀሱ መታየታቸውን ጠቅሰው በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ይህ ሁለተኛ ዙር የሳውዲ መንግስት እርምጃ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውንም ጭምር ፈቃዶቻቸውን እይቀደዱ ከሃገር ለማባረር እቀድ መኖሩን ማሳያ ነው ብለዋል ። 

በተለይ ታህሳስ 7 ቀን 2006 ዓም በተሰጠው የምህረት ግዜ ውስጥ፡የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ ለማስተካከል ጀምራችህ ላልጨረሳችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በሚል ረዕስ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ባወጣው ማስታወቂያ ተጭበርብረናል የሚሉ ወገኖች « የጀመራችሁትን የማስተካከል ሂደት ማጠናቀቅ እንድትችሉ ሚሲዮኑ ለሳውዲ አረቢያ መንግስት ጥያቄ ለማቅረብ እንዲቻል ከታትህሳስ 9 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተገኝታችሁ እንድተመዘገቡ እናስታውቃለን » በሚል አያሌ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፈቃድ እና የፓስፖርት ቁጥሮቻቸውን የሪስፖንሰር « የከፊል » ቴልፎን ቁጥሮቻቸውን እና ኢትዮጵያውያኑ ሪያድ መንፉሃ ነሲም ነስሪያ ኡመልሃማም እና አካባቢዎ የሚኖሩበትን የመኖሪያ አድራሻ ዲፕሎማቱ እንደመዘገቡ የሚናገሩ ታዛቢዎች ጉዳያችን በኤንባሲ በኩል ታይቶ እልባት ያገኛል ብለው የተስፋ የጣሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በህገወጥነት ተፈርጀው ስም ዝርዝር እና የመኖሪያ አድራሻዎቻቸው ለሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች መተላለፉ ዲፕሎማቱ ከህዝብ ያልተፈጠሩ እርጉም አረመኔ መሆናቸውን ማስያ ነው ብለዋል። 

በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ሰሞኑንን በልማት ማህበራት በኩል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሶስት ወር ግዜ ውስጥ የሳውዲን ምድር ለቆ እንዲወጣ በተላላኪዎቻችቸው አማካኝነት መለዕክት ሲያስተላለፉ በነበሩበት ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠማቸው የሚናገሩ ምንጮች እንደማንኛውም የወጭ፡ሃገር ዜጋ ህጋዊ ለመሆን የሚያስችሉን ነገሮች አሞልተን እያለን በኢትዮጵያዊነታችን ብቻ ሳውዲ ውስጥ የመኖር መብታችን መታገዱ ከጀርባው ድብቅ አጀንዳ እንዳለው ይገልጻሉ ። በተለይ ኢትዮጵያውያኑ ቀደም ብለው ህጋዊ ለመሆን የሚያስችላቸውን ጉዳዮቻቸውን ለማስፈጸም በሳውዲ ኢሜግሬሽን ስደተኞች ጉዳይ መ/ቤት ተጸኖ እይተደረገባቸው መሆኑንን በማውሳት በተደጋጋሚ ብሷታቸውን በጽሑፍ እና በአካል ለኢትዮጵያ ኤንባሲ ቢያቀርቡም ጆሮ ዳባ ተብለው ከርመው ዛሬ በኤንባሲው አንደበት ህግወጥ ትብለው በመፈረጅ ለባዕዳን ተላልፈው መሰጠታቸው በህዝብ ዘንድ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ቁጣን ይቀሰቅሳል ተብሎ ይሰጋል። በኢንባሲው ህግወጥ ትብለው የተፈረጁት ኢትዮጵያውያን ጥያቂያቻቸውን በማጠናከር 
1/ነፃ የሙያ ቅየራ /profishinal change/ ይፈቀድልን ።
2/ የመኖሪያ ፈቃዶቻችንን ከግለሰብ ወደ ተለያዩ መ/ቤቶች እንድናደርግ ይፈቅድልን ።
3/ ያለ ምክንያት ሚደረግ የመኖሪያ ፈቃድ በላግ ይቁምልን ።
4/ፖሊሲ ባልተፈፀመ ወንጀል ይዞ ማሰር ያቁምልን ።
5/ለዕድሳት የሚሰጡ የመኖሪያ ፈቃዶቻችን በጊዜ ታድሰው ይመለሱልን ።
ይህ ሁሉ የማይቻል ከሆነ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን የተከበረው ኤምባሲ መሉ የኢቃማ ወጪያችውን ከነ ሞራል ካሳ የሳውዲ መንግስትን ጠይቆ በሰላማዊ መንገድ ወደ ሐገራቸው የሚመለሱበትን ሆነታ ሊያመቻችላቸው ይገባል የሚሉ ወገኖች የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ካርታ አሲዘው አሊያም ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቻቸውን ሸጠው ሳውዲ አረቢያ ሰርቼ እለወጣለሁ በሚል ተስፋ ከ 1 መቶ ሺህ እስከ 2 መቶ ሺህ ብር አውጥተው የገዙትን መኖሪያ ፈቃዶቻቸውን ሰርዘው ሃገር እንዲገቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ እያሰማ ያለው ጩኽት ወገናዊነት የጎደለው በመሆኑ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ከፍተኛ ተቋውሞ መቀስቀሱን አክለው ገልጸዋል።

Wednesday, December 25, 2013

ኢኮኖሚያችን ሲያድግ የህዝቡ ኑሮ ለምን አሽቆለቆለ?


December 25, 2013
ማስተዋል ደሳለው
ላለፉት 8 እና ዘጠኝ ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሁለት አሃዝ አያደገ ነው ሲባል እንሰማለን፤  የእድገት ፍጥነቱ  ላይ የሚነሱ በርካታ ጥያቄውች  ቢኖሩም መንግስት  የመንገድ ግንባታ ፣ የኃይል ማመንጫ ግንባታወችን እና መሰል ነገሮችን  በመጥቀስ እድገት እንዳለ አስረግጦ ይከራከራል::  በሌላ በኩል የኢኮኖሚ እድገቱ ተመዘገበ በሚባልባቸው ዓመታት በዋጋ ንረት የህዝቡ ኑሮ ከጊዜ ወደጊዜ እያሽቆለቆለ  እንደሆነ በግልፅ የሚታይ ነገር ነው:: ታዲያ  የኢኮኖሚ እድገት አለ በተባለባቸው ዓመታት የህዝቡ ኑሮ ለምን አሽቆለቆለ? ይህን ጥያቄ ከ 7 ዓመት በፊት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ  ተጠይቀው የሰጡት መልስ የዋጋ ንረቱን የኢኮኖሚ እድገቱ እራሱ የፈጠረው ጉዳይ ነው ነገር ግን ቀስ በቀስ እድገቱ ሲቀጥል ራሱ እድገቱ ችግሩን ይፈታዋል ብለው ነበር፤ ነገር ግን ከሰባት ዓመት በዃላም እንኩአን ሊሻሻል  የህዝቡ የኑሮ ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየባሰበት ሂዷል::  ችግሩ የተለያዩ  ምንጮች ቢኖሩትም በዋናነት በ 2 ከፍሎ ማየት ይቻላል::
፩. የኢኮኖሚ እድገቱ ምንጭ
፪. የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መዋቅር
የኢኮኖሚ እድገት ማለት በአጭሩ ኢኮኖሚዉ ዉስጥ ተጨማሪ ሀብት መፍጠር ማለት ነው::  በመጀምሪያ ላለፉት 8  እና ዘጠኝ ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ  የተፈጠሩት ተጨማሪ ሀብቶች ምንድን ናቸው ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል ፤  በአብዛኛዉ ሀገሪቱ ዉስጥ የተፈጠሩት ሀብቶች ከመንገድ ፣ ከሕንፃ እና ከ ከኃይል ማመንጫ ከግንባታ ጋር የተያያዙ ናቸው:: በመቀጠልም የዚህ ሀብት የገንዝብ ምንጭ ምንድን ነው ብሎ ማየት ያስፈልጋል፤ የገንዘቡ ምንጭ በዋናነት ከብድር እና እርዳታ የተገኘ ሀብት ነው ፣ በተለይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ 1998 ዓም ጀምሮ በሶማሊያ በመጀመሪያ የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረት በመቀጠልም የአልሻባብ እንቅስቃሴ መጠናከር ለኢትዮጵያ ትልቅ ሲሳይ ይዞ ነው የመጣው:: በሶማሊያ ያለዉን ሁኔታ  ለመቆጣጠር ምዕራባዉያኑ የሚያደርጉትን ጥረት በመደገፍ  በዋና አጋርነት የተሰለፈችዉ ኢትዮጵያ ላለፉት ስምንት ዓመታት በየዓመቱ በቢልየን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ በእርዳታ መልክ ከምዕራብ ሃገራት እንድታገኝ አድርጓታል:: ይህም ማለት ሀገሪቱ ዉስጥ የጎላ  የኢኮኖሚያዊ መዋቅር ፣ የአሰራር ስርዓት  እና የቴክኖሎጅ ለውጥ ሳይኖር ከፍተኛ ገንዘብ ወደኢኮኖሚው ፈሰስ እንዲሆን አድርጓል:: በሌላ አገላለፅ  የቆየው የሀገሪቱ  ኢኮኖሚ የጎላ የምርት ጭማሪ ሳይኖረው ከዉጭ የተገኘ ብድር እና እርዳታ ኢኮኖሚዉ ዉስጥ ተጨመረ እና የኢኮኖሚዉ መጠን አደገ ማለት ነው::  ስለዚህ የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ እና የሀገሪቱን ተወዳዳሪነት ሊያሻሽል የሚችል የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ የጎላ  ለዉጥ ሳይታይ ለመሠረት ልማት ኢኮኖሚዉ ዉስጥ ፈሰስ የተደረገው ገንዝብ የገንዘብ አቅርቦትን (Money Supply) በመጨመር እና  የአገልግሎት ዘርፉ ( Service sector) ከሌሎቹ የኢኮኖሚ ዘርፎች ተነጥሎ እንዲለጠጥ እንዲሁም ዋጋ እንዲንር በማድረግ አብዛኛዉን ሕዝብ ለችግር አጋለጠ ::
ከብድር እና እርዳታ የተገኘው ገንዘብ መሰረተ ልማት ላይ ሲዉል ከላይ የተገለፀው ችግር ቢኖርበትም በአንፃሩ የመሰረተ ልማት መስፋፋት የማምረቻ ወጭ ( cost of production) እንዲቀንስ በማድረግ የሚያስገኘው ጥቅም አለ ፤ በተጨማሪም ገንዘብ ገንዘብን ይፈጥራል “ money creats money” በሚለው የኢኮኖምክስ  መርህ መሰረት ኢኮኖሚዉ ዉስጥ የተረጨው ገንዘብ በአብዛኛዉ አገልግሎት ዘርፉ ላይ የፈጠረው ተጨማሪ ሀብት አለ:: ነገር ግን ይህ የተፈጠረ ተጨማሪ ሀብት በጠንካራ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መዋቅር ስላልተመራ ወደጥቂት ሰወች እጅ እንዲገባ ሁኗል::  ሃብቱ እጃቸው የገባ ሰወችም የኢኮኖሚዉን መዋቅር ሊለዉጡ የሚችሉ እንደኢንዱስትሪ አይነት ዘርፎች ላይ ከመሰማራት ይልቅ ከሙሰኛ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለዉን የከተማ ቦታ በኢንቨስትመንት እና በሊዝ ስም በመዉሰድ ህንፃ በመገንባት እየተለጠጠ ላለው የአገልግሎት ዘርፍ በማከራየት በአቁአራጭ ከፍተኛ ገቢ ለመሰብሰብ ተጠቀሙበት::
በሌላ በኩል የሀገሪቱ የመሬት አስተዳደር ስርዓት በሙስና የተጨማለቀ እና ወጥ ስላሆነና አዳዲስ ብቅ ለሚሉ ባለሀብቶች መሬት ማግኘት ከባድ ስለሆነ ሀገሪቱ አሁን ባለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ወሳኝ ሀብት (strategic resource) የሆነዉን የከተማ ቦታ ቀድመው የያዙ ባለሀብቶች የገቢያ ዉድድሩን ሚዛናዊ እንዳይሆን በማድረግ አዲስ የሚፈጠሩ ተወዳዳሪያቸውን በቀላሉ ከገቢያ ያስወጣሉ:: በተጨማሪም እንደነዚህ አይነቶቹ  ባለሀብቶች በአብዛኛው የፖለቲካዉ እና የግዥዉ ፓርቲ ጥገኛ ስለሆኑ የሚጠበቅባቸዉን ያክል  ግብር እና ታክስ አይከፍሉም:: ሥራቸዉን ስለሚያውቁም በሀገሪቱ በረጅም ጊዜ ሊከሰት ይችላል ብለው የሚፈሩትን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ስለሚሰጉ የሚያገኙትን ትርፍ ወደዉጭ ያሽሻሉ ፤ በጎን ሙሰኛ ባለስልጣናትም የሚዘርፉትን ገንዘብ ከሀገር ያሸሻሉ:: ከዚህ ላይ ፋይናንሽያል ትራንስፓረንሲ ኳሊሽን  ያወጣዉንና ኢትዮጵያ በህገወጥ የገንዘብ ፍሰት (illicit financial flow) በፈረንጆቹ ከ 2000 እስከ 2009 ያጣችዉን 11. 7 ቢልየን ዶላር ልብ ይሏል::
ለማጠቃለል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኖ እንዲያድግ ከተፈለገ ከላይ የተጠቀሱት  የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ መዋቅር ድክመቶች መስተካከል የሚገባቸዉ ሲሆን ፤ በዉጭ ብድር እና እርዳታ ላይ መንጠልጠሉን ቀንሶ ከሀገር ቤት በፍትሃዊነት ከሚሰበሰብ ግብር ሊሆን ይገባል:: ከዉጭ የሚገኘዉን ሀብትም  በብዛት መሰረተ ልማት ላይ ብቻ ማዋሉ የሚያስከትለዉን ችግር ጥልቅ ጥናት በማካሄድ  መመርመር እና  ገንዘቡ ከመሰረተ ልማቱ ጎን ለጎን የኢንዱስትሪው እና የእርሻዉን ዘርፍ መዋቅር ወደተሻለ ደረጃ እንዲደርስ ለማስቻልም መሰራት አለበት:: ከሁሉም በላይ ግን የኢኮኖሚ ነቀርሳ የሆነዉን ሙስና ለማስወገድ ከአንድ ፓርቲ የበላይነት ወደ መድብለ ፓርቲ ስርዓት መሸጋገር እንዲሁም ተጠያቂነትን ሊያጠናክሩ የሚችሉ እንደገለልተኛ ፍርድ ቤቶች ፣ የግል መገናኛ ብዙሃን  የመሳሰሉትን ተቋማት መፍጠር ያስፈልጋል:: ይህ ካልሆነ ግን ሀገሪቱ ሽህ ጊዜ ብታድግ የኢኮኖሚውን ፍሬ ጥቂቶች እየበሉ የአብዛኛዉ ሕዝብ  ኑሮ ማሽቆልቆሉ ይቀጥላል::

Monday, December 23, 2013

ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ጻፉ


December 22, 2013

ክንፉ አሰፋ
ፀሃይ አሳታሚ ድርጅት በታኅሣሥ 16, 2006 ዓ/ም (Dec. 25, 2013)  የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስን ‘እኛና አብዮቱ’ የሚል መጽሃፍ  ለገበያ እንደሚያበቃ አስታወቀ። ሻምበል ፍቅረሥላሴ እንደ ደርግ አባልነታቸው በጋራ ያመኑበትን፣ የተማከሩትን፣ የወሰኑትን፣ የሰሩትን፣ የገጠማቸውንና በቅርብ በዓይን ምስክርነት ያዩትን ተንትነው በ‘እኛና አብዮቱ’ ያስነብቡናል። የራሳቸውን ዕይታ ያካፍሉናል።
New book by Fkreselase Wegderes
ልጅ ሆነን አንድ አባባል እሰማ ነበር።”አበላል እንደ ደርግ አባል። አለባበስ እንደ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ!” – የሚል። በተለይ በኔ ትውልድ ያለን ሰዎች፣ ከዚህ ውጭ ስለኝህ ሰው የምናውቀው ብዙም ነገር አልነበረም። ግና እኝህ ሰው በልባቸው መክሊት ለአመታት የቋጠሩትን መረጃ ጀባ ሲሉን፤”… አጻጻፍም እንደ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ” የሚያሰኝ ሆኖ አገኘሁት።
ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ለአስራ አምስት ዓመታት አብዮቱን ሲመሩ ቆይተው ወደ መጨረሻው ከሥልጣን በጡረታ ስም እንዲሰናበቱ ተደርገዋል። ደርግን በጣለው በወያኔ መንግሥትም ለ፳ ዓመታት ታስረው፣ የሞት ፍርድ የተበየነባቸውና በመጨረሻ ፍርዱ ወደ ዕድሜ ልክ ተዛውሮላቸው ከእሥር ቤት በአመክሮ የወጡ ግለሰብ ናቸው።
ጸሃፊው በድራማ መልክ በመጽሃፋቸው ካሰፈሩዋቸው እውነታዎችና ግለ-ሂሶች ውስጥ አንዳንዶቹን ለአንባቢያን ማካፈሉ አይከፋም።  ደርጎች መፈንቅለ መንግስት አድርገው ሲያበቁ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘንድ ቀርበው ከንጉሱ የገጠማቸውን አስገራሚ ምላሽ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ  በመጽሃፋቸው እንዲህ ሲሉ አስፍረዋል።
የፖለቲካ እሥረኞች በሙሉ እንዲፊቱ የሚለው ጥያቄ እንደተነበበ ንጉሡ ጣልቃ ገብተው “ለመሆኑየፖለቲካ እሥረኞቹ እነማን ናቸው?” የሚል ጥያቄ አቀረቡ። “በእርግጥ የምናውቃቸው የፖለቲካእሥረኞች ባይኖሩም ማንኛውም የፖለቲካ እሥረኛ እንዲፈታ ነው የምንጠይቀው” አሉ ሻለቃ ተስፋዬገብረኪዳን። ንጉሡ ራሳቸውን ነቅነቅ አድርገው ጽሑፉን የሚያነበውን የደርግ አባል እየተመለከቱአልገባችሁም!” ብለው ዝም አሉ። በእርግጥም አልገባንም። ተማሪዎችና የተለየ ዓላማ የነበራቸውየተማሩ ሰዎች የሰነዘሩትን መፈክር ብቻ ነበር ይዘን ንጉሡ ፊት የቀረብነው። በፖለቲካ እሥረኝነትስም በከፍተኛ ደረጃ ለጣሊያን ወራሪ መንግሥት በባንዳነት አድረው አገራችንን የወጉ፣ ለቅኝተገዥነትም የዳረጉትን እንደ ኃይለሥላሴ ጉግሳ ያሉ ወንጀለኞች የፖለቲካ እሥረኞች ተብለው ከግዞትናከእሥር ቤት አስወጥተን እንደ ጀግና ራሳቸውን እንዲቆጥሩ አደረግናቸው።
የነ ጄነራል ተፈሪ በንቲ ጉዳይን አስመልክቶ የሰፈረው ታሪክ ደግሞ እንዲህ ይነበባል።
“በሊቀመንበርነት ስብሰባውን የሚመሩት ጄነራል ተፈሪ ‘የቋሚ ኮሚቴው’በዛሬው ቀን የሚወያይበትንጉዳይ አስመልክቶ የመቶ አለቃ ዓለማየሁ የደርጉ ዋና ፀሐፊ ይገልጽልናል’ ብለው ስብሰባውመጀመሩን ካበሰሩ በኋላ ዓለማየሁ በአጀንዳው ላይ አጭር ገለጣ ማድረግ ሲጀምር ስልክ ተደወለ።ስልኩ /ኮሎኔል መንግሥቱ አጠገብ ስለነበር ወዲያው ቅጭል እንዳለ መነጋገሪያውን በማንሳት ሃሎአሉ። ከሌላው ጫፍ ማን እንደደወለ አላወቀንም። በኋላ እንደታወቀው /ኮሎኔል ዳንኤል ነበርየደወለው። ምን እንደተነጋገሩ አልተሰማም። /ኮሎኔል መንግሥቱ ብቻ “እሺ እሺ” ብለው ስልኩንዘጉት። ስልኩን እንደዘጉ “ይቅርታ ስልኩ የተደወለው ከጎንደር ነው። ጎንደር ውስጥ ችግር አለ።እናንተ ቀጥሉ” ብለው ከጀርባቸው ባለው በር በኩል ውልቅ አሉ። በዚህን ጊዜ ዓለማየሁና ሞገስጥርጣሬ የገባቸው መሰለ።  ዓለማየሁ ንግግሩን አቋርጦ በመስኮት በኩል ውጭ ውጭዉን መመልከትጀመረ። ዓይኖቹ አላርፍ አሉ። ግራና ቀኝ ይመለከታል። አጠገቡ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በጥርጣሬተመለከተ። ሻምበል ሞገስም በር በሩን ይመለከታል። ከአሁን አሁን አንድ ችግር ይከሰታል የሚልፍርሃት ያደረበት ይመስላል። ሁሉም የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች ፈርተዋል። እንደፈሩት አልቀረም/ኮሎኔል መንግሥቱ ከወጡ ሁለት ደቂቃ እንኳን አልሞላም ከበስተጀርባ ባለው ኮሪደር የወታደሮችንእርምጃ ሰማን። ወታደሮች ሲንቀሳቀሱ በፊት ለፊታችን ባሉት መስኮቶች በኩል ተመለከትን። በዚህንጊዜ ፍስሐ ደስታ “ተከብበናል” አለ። ወዲያው ሁለቱም በሮች በኃይል ተበረገዱ። ሁላችንም ደነገጥን፣ቀልባችን ተገፈፈ፣ እጢአችንም የወደቀ መሰለን። ድርቅ ብለን በተቀመጥንበት ቀረን።…
ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ሰለ ልጅ ሚካኤልን አስተዋይነት ሲያስታውሱ እንዲህ የሚል ግለሂስም ያስነብቡናል።
እኛ በችኮላ ውሳኔ መስጠታችን፣ ሕዝቡን በደንብ አለማወቃችን፣ ሰፊ የሕዝብ አመራር ልምድማጣታችን፣ የአገርና የውጭውን ፖለቲካ ውስብሰባዊ ግንኙነት አለመገንዘባችን፣ የመንግሥትን አሠራርደንብና ሥርዓት አለመረዳታችን፣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጥመርታዊ ግንኙነትን መመልከት አለመቻላችን፣የተለያየ ገንቢም ሆነ አፍራሽ ተልዕኮ ያላቸው ኃይሎች ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩብ ያለማጤናችን፣በየዋህነትና በቅንነት ብቻ እንደምንሠራ በመገንዘባቸው ሊሆን ይችላል ልጅ ሚካኤል ከእኛ ጋር መቆየትየሚችሉት ለአጭር ጊዜ ብቻ እንደሚሆን የጠቆሙት…
በወቅቱ ስለ ህዝቡ የእርስ በርስ መጨካከንና መወነጃጀል ባሰፈሩት ክፍል ውስጥ እንዲህ የሚል ታሪክ እናገኛለን።
Former Ethiopian Official Fkreselasie Wegderes..የሥራ ዕድገት የተከለከለ፣ በሌብነትም ሆነ በስካር ወይምበሌላ ጥፋት የተቀጣ፣ በግል ጉዳይም ሆነ በመንግሥት ሥራከአለቃው ጋር የተጣላ፣ በአጋጣሚው ተጠቅሞ አዲስ ሹመትወይንም ዕድገት ለማግኘት የሚፈልግ ሁሉ ጠቋሚ፣ ወንጃይ፣ከሳሽ፣ ተበዳይ ነው።
የተወሰነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ሌላውን ለመጉዳት ብለውኢትዮጵያ ትቅደምን ይቃወማል፣ ከታሠሩት ባለሥልጣናትወይም ሚኒስትሮች የቅርብ ዝምድና አለው። ስለሆነም ሥራይበድላል፣ ሠራተኛውን ያጉላላል፣ ውሳኔ አይሰጥም” በማለትአለቆቻቸውን የሚከሱ፣ የሚወነጅሉ በርካታ ናቸው። ለደርግአባላት ቤታቸው ድረስ በመሄድ በማስረጃ የተደገፈ ቢሆንምባይሆንም ተቆርቋሪ በመምሰል የክስ ማመልከቻ የሚያቀርቡምነበሩ። እንታሠራለን ብለው በፍርሃት የተደበቁ ባለሥልጣናትንየቅርብ ዘመዶቻቸው ወይም አሽከሮቻቸው ወይምጎረቤቶቻቸው ደርግ ጽሕፈት ቤት ድረስ በመምጣትያጋልጧቸው ነበር። የመሥሪያ ቤቶችን ሰነዶች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ወይም ሰነዱን እንዳለ ከፋይሉአውጥተው በማቅረብ “በመንግሥት ንብረት፣ ሀብት ወይንም ገንዘብ ላይ አላግባብ ተወስኗል” ብለውጥቆማና መረጃ የሚያቀርቡም ነበሩ። ሠራተኞች አሠሪዎቻቸውን ይከሳሉ፣ ይወነጅላሉ። ገበሬዎችለዘመናት በደል አደረሱብን የሚሏቸውን የአካባቢ ባለሥልጣናት ይወነጅላሉ። ውንጀላው በርካታነው።
አሽከሮች፣ ዘበኞች፣ ገረዶች… መረጃ ይሰጣሉ፣ ይጠቁማሉ። የተደበቀ የጦር መሣሪያ፣ የተደበቀ ገንዘብ፣ወደሌላ ቦታ የተወሰደ ወይም የሸሸ ሀብት እንዳለም የሚጠቁሙን እነሱ ናቸው። በአንድ ቦታ በርከትያሉ ሰዎች ተሰብስበው ምሽት ከአሳላፉ “ሲያድሙ ነበር” ብለው ከነስም ዝርዝራቸው መረጃውን ደርግጽሕፈት ቤት ድረስ ያመጣሉ። “እኛ እስከዛሬ የበይ ተመልካች ነበርን ዛሬ ዕድሜ ለእናንተ እንጀራሊወጣልን ነውከእናንተ ጎን ተሰልፈን አቆርቋዦቹን እንታገላለንበማንኛውም ጊዜ ትዕዛዝ ብትሰጡንለመፈጸም ዝግጁ ነን!” እያሉ ታማኝነታቸውንና ተባባሪነታቸውን የሚገልጡም ብዙዎች ነበሩ። በጣምየሚያስደንቀው አባቶቻቸውን፣ ልጆቻቸውን፣ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውን፣ ባሎቻቸውን፣ሚስቶቻቸውን በመክሰስ፣ በመወንጀል፣ በማጋለጥ፣ በመጠቆም ብሎም በማሳሰር ጉዳት ያደረሱበርካቶች መሆናቸው ነው።
እንግዲህ ስለ አዲሱ ‘እኛና አብዮቱ’ መጽሃፍ ይህንን ካልኩ ቀሪውን ለአንባቢ መተው ይበጃል። ሁሉም ሰው መጽሃፉን አንብቦ የራሱን ፍርድ ይስጥ።
ህይወት በሩጫ ትመሰላለች። የተፈጥሮ ህግጋት ነውና የሰው ልጅ እስትንፋሱ እስኪቋረጥ ይሮጣል።  ከዚያም ሩጫውን ይጨርሳል። ሩጫውን ሳይጨርስ በልቡ ቋጥኝ የያዘውን እምቅ ቋጠሮ የሚተነፍስ ደግሞ እድለኛ ነው።  በአንጻሩ ደግሞ በአእምሮውየቋጠረውን የእውቀት ምስጢር ሳያካፍል የሚያልፍ ሁሉ ያሳዝናል። ያለውን የወረወረ ንፉግ አይደለምና መንቀፍም ካለብን የሚወረውረውን ሳይሆን የማይወረውረውን ነው። መተቸት ካለብነም ሃሳቡን እንጂ ግለሰቡን ባይሆን ይመረጣል። በሃሳብ ላይ መወያየትና መተሻሸት ደግሞ አዋቂነት ነው።
በመጨረሻም የመጽሃፉ አርታኢ ኤልያስ ወንድሙ በመግቢያው ላይ ባሰፈረው መልእክት ጽሁፌን ልቋጭ።
የተማረ፣ ያወቀና ያደገ ትውልድና ዜጋ ምልክቱ የተጻፈን ማንበቡ፣ ያነበበውን ማብላላቱና ካነበበው ውስጥ ስንዴውን ከእንክርዳዱ መለየቱ ሲሆን፤ እራሱም አስተውሎና አገናዝቦ መጻፉ ደግሞ መማሩን ብቻ ሳይሆን መመራመሩንና ማወቁን የሚያሳይ ታላቅ ተግባር ነው። ለዚህም ደግሞ ግላዊ ነጻነት ያስፈልገዋልና ጫንቃው ላይ ያሉትን ግላዊና ታሪካዊ ቀንበሮች የሰበረ ነጻ ሰው መሆን ይጠበቅበታል። ትምህርትና ዕውቀት አስተዋይነትንና ጥልቀትን ከራስ በላይ ለትውልድ አሳቢነትን የሚያመለክት ታላቅ ኃላፊነት ነው። ለዚህም እንደ ትናንቱ ‘የተማረ ይግደለን’ ሳይሆን፤ የተማረ ያስተምረን፣ ያስተዳድረን ብሎም ይምራን በምንልበት ዘመን ከምናነብበው ውስጥ ያልተስማማንበትን በጨዋነት የመቃወም፣ የፈቀድነውን እንደ ስሜታችን የመደገፍና ተሳሳተ የምንለውን ለእርማት መጠቆም ግላዊ መብታችን ነው።…
* ፀሃይ አሳታሚ ድርጅት ከዚህ በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምን፣ የቀድሞውን የህወሃት መሪ ዶ/ር አረጋዊ በርሄን፣ የቀድሞውን የኢህአፓን አመራር አባል የዶ/ር መላኩ ገኝን፣ የቀድሞው ሚንስትር  የአቶ ተካልኝ ገዳሙን መጽሃፍትና  ከስልሳ በላይ የሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክና ጥናት ላይ ያተኮሩ መጽሃፍትን ማሳታሙ ይታወሳል። ‘እኛና አብዮቱ’ የሚለው ይህ አዲስ መጽሃፍ በwww.tsehaipublishers.com ድረገጽና በቀርቡ በየሱቁ አንደሚገኝ ከሎስ አንጀነሰ የደረሰን ዘገባ  አስታውቋል። ሁላችንም ገዘተን እናንብብ።
መጽሃፉን አንብቤ እንደጨረስኩ በሂሳዊ ግምገማ እመለስበታለሁ።