አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) አስቸኳይ ስብሰባውን ከትናንት ምሽት ጀምሮ በባህር ዳር ያካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉን ርእሰ መስተዳድር ሾሟል።
ምክር ቤት ለስምንት ዓመት ተኩል ክልሉን ያገለገሉት አቶ አያሌው ጎበዜን በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተክቷል።
አቶ ገዱ ክልሉን በምክትል ርእሰ መስተዳድርነትና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
ለምክር ቤቱ የስንብት ንግግር ያቀረቡት አቶ አያሌው ጎበዜ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።አቶ አያሌው ለአዲሱ ርዕሰ መስተዳድርም መልካም የስራ ዘመንን ተመኝተዋል።
No comments:
Post a Comment