
በዓዲግራት ከተማ በደረሰን ድብደባ በጣም አዝኛለሁ። ህወሓቶች በተግባራቸው ሊያዝኑ ይገባል። ህዝብን ፖለቲካ እንዲያውቅና ራሱ ከጭቆና እንዲከላከል ለማገዝ በምንሞክርበት ግዜ መንግስት ወደ ተራ የሽፍትነት ተግባር መሰማራቱ የሚያስደምም ነው። ህወሓት ከሽፍታ በላይ ነው። ምክንያቱም ሁሉም ሽፍቶች ሰለማዊ ሰውን ላይበድሉ ይችላሉና።
እኛ ለህዝብ ነፃነት ነው የምንታገለው። ትግላችን ሰለማዊ ነው። ወታደርና ፖሊስም የለንም። እኛ ያለን ህይወት ነው። ያለችንን ህይወት ለህዝብ ደህንነት ስንል መስዋእት አድርገናል። በህዝብ ፊት ተደብድበናል። በፖሊስና አስተዳዳሪዎች ፊት ተደብድበናል። እኛ መክፈል ያለብን ህይወትን ነው።
የድብደባው ዓላማ (አንድ) ከህዝብ ጋር እንዳንገናኝ፣ (ሁለት) ስንበትነው የነበረው የዓረና አጀንዳ ስሜት ኮርኳሪ ስለነበር፣ (ሦስት) የዓዲግራት ህዝብ ጥሩ አቀባበል ስላደረገልንና ህወሓቶች ስለሰጉ (አራት) እኛ ተስፋ ቆርጠን ቀጣይ ስብሰባዎቻችን እንድንሰርዝ ለማስገደድ ነበር።
ትግሉ ይቀጥላል። ቆርጠን ተነስተናል። ከዓዲግራት ድብደባ የባሰ ሊመጣ አይችልም። በዓዲግራት መስዋእት ሁነናል። የዓዲግራት ድብደባ የትግላችን አስፈላጊነት አረጋግጦልናል።
ተስፋ መቁረጥ የለም። ወደ ኋላ አንድም ኢንች ፍንክች አልልም። በዓዲግራት’ኮ ሙቻለሁ። አልቅሻለሁ። ሐዘኔን ጨርሻለሁ። ሁለተኛ ሞት የለም። ስለዚህ ካሁን በኋላ ሞት የለም። ትግሉ ይቀጥላል። ሰው ሁሉ ለነፃነቱ ይነሳ። ህወሓት ለማንም ሊሆን እንደማይችል አረጋግጠዋል።
(የዓድግራት ድብደባ ዝርዝር ጉዳይ እፅፋለሁ። አሁን ትንሽ ድካም ይሰማኛል)።
ምንጭ፡ ECADF
No comments:
Post a Comment