Wednesday, February 19, 2014

የፍርድ ቤት ያለህ


የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ
Girma-Seifuበታሕሳስ ወር አጋማሽ አንድ የፌዴራል ፖሊስ መኮንን ችሎት በመድፈር ተከሰው አሁንም ጉዳይ በፍርድ ሂደት ላይ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ፖሊሶቹ አድመው አሁንም ማን እንደሆነ አላወቅንም ብለው አለቃቸው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ አስደርገዋል፡፡ አሁን አላውቅም ድሮ የመኮንን ማዕረግ የሚሰጣቸው ሰዎች ከፖሊስነቱ በተጓዳኝ የህግ ትምህር እውቀት እንደነበራቸው ለማንም ግልፅ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ድፍረት መዳፈር አይቻልም፡፡ ይህን ጉዳይ ያነሳሁት በመፅሔት ላይ በተሰጠ አስተያየት ተደፍርኩ ያለ ችሎት አቶ አስራት ጣሴን የአምስት ወር የእስር ቅጣት በሁለት ዓመት ገደብ መወሰኑን ታዝቤ ነው፡፡ ከአምስት ወሩ ይታሰብ አይታሰብ ባይታወቅም ለአስር ቀን በወህኒ ቤት እንዲቆዩም ተደርጎዋል፡፡ ለህግ ልዕልና ሲባል ፍርድ ቤት እንዲከበር ከዚህ የበለጠ መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጀን ሰው ችሎት ደፍረሃል ማለት ግን ጠብ ያለሽ በዳቦ ነው፡፡
ለማንኛውም መኮንኑ ይግባኝ ስለጠየቁ በሚል በገንዘብ ዋስትና ከእስር ያሰፈቱት የፌዴራል የመመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንት አቶ አስራትን ግን ሊያስፈቱ አልቻሉም፡፡ ከሲቪል ሰርቪስ የሚሰበሰቡት ዳኞች የፖለቲካ ታማኝነት እንጂ የህግ እውቀታቸው ዝቅተኛ ነው የሚል እምነት አለን፡፡ ስለዚህ ለገዢው ፓርቲ ያዳላሉ ማለት እንዴት ሆኖ ነው ችሎት መድፈር የሚሆ ነው? በቅርቡ የፍትህ ስርዓቱን የመልካም አስተዳደር መርሀ ግብር በቀረበበት ወቅት አቅመቢስ ያለውን ፍርድ ቤት እኛስ ብንለው ምን ይለዋል? አቅም የሌላቸው ዳኞች ተገቢውን ፍትህ ይሰጣሉ ብለን አለማመን መብታችን ነው፡፡
የፖለቲካ ትግል ውስጥ የገባነው ትክክለኛ የፍትህ ስርዓት እንዲዘረጋ ጭምር ነው፡፡ መንግስትን ፍርድ ቤት ገትረን መብታችንን የሚጠብቅልን ፍርድ ቤት ቢኖር በእውነት ወደ ፍርድ ቤት እንጂ የፖለቲካ ትግል ምን አመጣው፡፡ የዚህ ጊዜ ፖለቲካ የሚሆነው መሪ ለመሆን ዕጩ ሆኖ መወዳደር ብቻ ነው፡፡ ትግል የታባቱ፡፡
የፀረሙስና እና ስነምግባር ኮሚሽን ባስጠናው ጥናት ተዓማኒነት ከጎደላቸው ተቋማት አንዱና ዋነኛው ፍርድ ቤቶች እንደሆኑ ገልፆዋል ይህን ተቋም ትክክለኛ ፍትህ ሊሰጠኝ አይችልም ብዬ ማመን በምን መንገድ ነው ችሎት መድፈር የሚሆነው፡፡ በግሌ በፍርድ ቤት ላይ እምነት ቢኖረኝ ኖሮ ያለ ስሜ የአሸባሪነት ዶክመንተሪ መስሪያ ስሆን በማግሰ ስቱ ነበር ፍርድ ቤት የምገትራቸው፡፡ ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ከፖለቲካ ጥቅሻ ነፃ ነው ብዬ ስለማላምን አላደረኩትም፡፡ አንድ ቀን እንዳውም በዚሁ ዶክመንተሪ እኔው ልከሰስ እችላለሁ፡፡ ፍርድ ቤትም ጥፋተኛነህ ተከላከል ብሎ ዕድሜ ልክ ሊፈርድ ይችላል፡፡
በአቶ አሰራት ጣሴ ክስ መነሻ ዳኛዋ በሌላ ክስ የማይፈለጉ ከሆነ ልቀቋቸው ብለው ለፖሊስ ሲያዙ፤ ፖሊሱ ያለ ምንም ማንገራገር አለቅም ሲል ደነገጥኩ፡፡ ፖሊሱ ይዞት የመጣውን እሰረኛ የሚለቅበት ስርዓት ቢኖርም ክብርት ዳኛ ማዘዣው በፅሁፍ ሲደርሰን በህጉ መሰረት እንፈፅማለን የሚል ለፍርድ ቤት የሚገባን ክብር የማይስጥ ፖሊስ ይህን እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ፍርድ ቤት ነፃነኝ ቢለኝ መብቱ ቢሆንም፤ እኔ ደግሞ አይመስለኝም ነፃ አለመሆናችሁን ብዙ ምልክት አለ ማለት መብቴ ነው፡፡
የፌዴራል የሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽነር አሊ ሱሌይማን እንደ ተናገሩት “በአሁኑ ወቅት ጠበቃ የሚመረጠው በሙያ ብቃትና በምስጉን ስነምግባሩ ተከራክሮ እውነት ያወጣል በሚል ሳይሆን ምን ያህል ደላላ አለው? ዳኛና ባለስልጣናትን ያውቃልን? በሚል መስፈርት ነው” ብለዋል፡፡(አዲስ ዘመን ጋዜጣ የካቲት 2/2006) ይህ አስተያየት ጠበቆችን ለመዝለፍ ቢመስልም ትክክለኛው ግን ደላሎች የሚያገናኙት ዳኞች፣ በባለስልጣን ጥቅሻ የሚሰሩ ዳኞች መኖራቸውን ነው፡፡ የጠበቃ፣ የዳኛ እና የባለስልጣናት ህገ ወጥ ግንኙነት የሰፈነበት የፍትህ ስርዓት ትክክለኛ ፍትህ አይሰጠንም ብሎ ማመን እንዴት አድርጎ ነው ችሎት/ፍርድ ቤትን መድፈር የሚሆ ነው፡፡
“ፍትህ ከኢህአዴግ ፍርድ ቤቶች ይገኛል ተብሎ ሳይሆን ለታሪክ ምስክርነት ነው” ብሎ ጥርጣሬን መግለፅ ነው ወይስ “በደላላና በባለሥልጣን ጥቅሻ ይስራል” ማለት፡፡ ሁለቱም እውነት ከሆነ እውነት ነው፡፡
ሌባ ዳኞች ብለው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በምክር ቤት ሲሳደቡ እረ በህግ ማለት ያልቻለ ፍርድ ቤት ዛሬ ደግሞ ችሎት በአንድ መጣጥፍ ውስጥ በተሰጠ አሰተያየት ተደፈረ ማለት እንዴት ነው ነገሩ፡፡
- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=6301#sthash.B7Yh6TEm.dpuf

No comments:

Post a Comment