በአለፉት ሃያ ሁለት አመታት
ውስጥ በሀገራችን ላይ እየደረሰ ያለው ችግርና መከራ እየጨመረ መምጣቱ እና የአንድ ብሄር የበላይነት ነግሶ ሌላውን ብሄር በገዛ
ሃገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ በመቁጠር በዘርና በሀይማኖት በመከፋፈል የህዝቦችን የመናገርና የመፃፍ መብት በመገደብ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ
ፓርቲ አመራሮች በእስር ቤት መንገላታት እንዲሁም የሴቶች እህቶቻችን በየአረብ ሃገራቱ ሞትና እንግልት እያስቆጨንና እያስቆጣን ያለ
መሆኑ ይታወቃል።
ይህ ሳያንሳቸው በቅርቡ
ደግሞ የአማራ ተወላጅ ወገኖቻችን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀሙ እና በገዛ ሀገራቸው ሀብት ንብረት ካፈሩበት ተጋብተው ከተዋለዱበት
ወዳጅ ዘመድ ካፈሩበት ቀያቸው ያለምንም ሀብትና ንብረት የሚበሉትና የሚጠጡት እንዲሁም ያለ አንዳች መጠለያ ተፈናቅለው ሜዳ ላይ
ወጥተው እንዲጣሉ ተደርገዋል። ከዚያም በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን
በየሃገሩ ባሰሙት ጩህት ወደ ነበሩበት ስፍራ እራሳቸው ትራንስፖርታቸውን ከፍለው እንዲሄዱ ከተደረጉ በኋላ ወደ ቤታቸው ሳይገቡ አሁንም
ወገኖቻችን በሜዳ ላይ ይገኛሉ ለህይወታቸውም ዋስትና እንደሌላቸው እየተናገሩ ይገኛሉ።
በመሆኑም የህዝባችንን ችግርና
ሰቆቃ ከስር መሰረቱ ለማቆም ይህንን ዘረኛና አምባገነን መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከስልጣን አውርደን ለመጣልና ኢትዮጵያ
ሀገራችንን ነፃ ለማውጣት ሁላችንም በግላችን የሚጠበቅብንን ሁሉ በማድረግ ትግሉን በፍጥነት ወደፊት ለማራመድ ለዲሞክራሲና ለፍትህ
እንዲሁም ለነፃነት ከሚታገሉ ወገኖቻችን ጋር ተባብረን በመስራት ይህንን ነብሰበላ መንግስት ባስቸኴይ ማስወገድ ይኖርብናል።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም
ትኑር
ሄለን ንጉሴ
ኤፕሪል 18. 2013 ኖርዌ
No comments:
Post a Comment