Friday, May 30, 2014

ግንቦት 20 ያለመለስ ስንት ይቆይ ይሆን?

ግርማ ሠይፉ ማሩ
girmaseifu32@yahoo.com

የተከበሩ ግርማ ሰይፉ
ሰሞኑን ልባችን እሰኪጠፋ የግንቦት 20 ፍሬዎች የተባሉት “ልማትና ዲሞክራሲ” በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እንዲሁም እየተከፈላቸው በማህበራዊ ድህረ ገፅ የስድብ ናዳ የሚያወርዱትን ስዶች ጨምሮ እንደ ፍራፍሬ እየበላን እንደ ወተት እየተጋት ነው፡፡ ሚዛናዊ ሆኜ ግንቦት 20 ያመጣልኝን ፍሬ ሳስብ የምር ግራ ይገባኛል፡፡ የእኔ ግርታ የሚመነጨው አሁን ያለንበት ደረጃ ለመድረስ በእርግጥ 23 ዓመት ያስፈልገን ነበር ወይ? የሚል ነው፡፡ በእኔ እምነት ግንቦት 20 የስርዓት ለውጥ የመጣበት ቀን እንደሆነ ለመቀበል አልቸገርም፡፡ ደርግን የተካው ዳግማዊ ደርግ በመባል
የሚታወቀው ኢህአዴግ ግን ከምን ከምን አንፃር ከደርግ እንደሚሻል ሊገባኝ አልቻለም፡፡

 እኔ በፍፁም የማላደርገው ኢህአዴግን ከደርግ ጋር ማወዳደር ነው፡፡ በሂሣብ ትምህርት ፍየልና በግ እንደማይደመረው ማለት ነው፡፡ ኢህአዴጎች ደስ የሚላቸው ሁሌም ውድድሩ ከደርግ ጋር እንዲሆን ነው፡፡ ሲያስፈልግም ከምኒሊክ ጋር መወዳደር የሚያሻቸው በተለይ ባቡርና ስልክ ሲነሳ ነው፡፡ ሊያፍሩበት በሚገባ ነገር ውድድር ይከጅላሉ፡፡ እኔ ኢህአዴግን እንዲመዘን የምፈልገው ስመዝነውም የሚቀልብኝ ከዓለም አቀፍ መለኪያ እንዲሁም እኛ ኢትዮጵያዊያን ከሚገባን ደረጃ አንፃር ነው፡፡

አፍቃሪ ኢህዴጎች “ኢህአዴግ ባይኖር ኖሮ ይህች ሀገር ትፈራርስ ነበር” ለማለት አፋቸውን እንኳን ያዝ አያደርጋቸውም፡፡ ይህንን
መፈራረስ የገታው ደግሞ “የኢህአዴግ የብሔር ብሔረሰብ ፖሊሲ ነው” ይሉናል፡፡ በእኔ እምነት የመፈራረስ ሟርትም ሆነ የሟርቱ
ማፍረሻ ፖሊሲ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ኢህአድጋዊያች ለዚህም ማሳያው የሚሉት በሽግግር ኮንፈረንስ ላይ ተሳታፊ ከሆኑት ውስጥ ከአስር በላይ የሚሆኑት መገንጠል አለብን የሚሉ ነበሩ በማለት ነው፡፡ ልክ ነው በዚህ ማህበር ውስጥ እንደዚህ ዓይነት ሃሣብ የሚያራምዱ ቢበዙ እንጂ የዚህ አቀንቃኞች ሊያንሱ አይችሉም፡፡ ህወሃትን ጨምሮ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ የመሳሰለሉት ከስማቸው ጭምር የመገንጠል ደቀ መዝሙሮች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ በእነርሱ ጋባዥነት የሚመጣ ድርጅት እንዴት አድርጎ ከዚህ የተለያ ሃሳብ ሊያራምድ ይችላል ተብሎ ይገመታል፡፡

ለዚያውም እነዚህ ጋባዦች በለስ ቀንቷቸው መሣሪያ ታጥቀው አራት ኪሎ ቁጭ ብለው ባሉበት ወቅት፡፡ ይህ ግን በፍፁም የኢትዮጵያ ህዝብ ለመገንጠል ዝግጁ ነበር የሚያስብል አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊያን ከኢህአዴግ በፊትም በቋንቋቸው ይናገራሉ፣ ይዘፍናሉ፣ ያለቅሳሉ፡፡ በኢህአዴግ ጊዜ የተጨመረልን “ቁቤ የሚበል” ፊደል እና ወጣቱ በተለይ በኦሮሚያ አካባቢ ኢትዮጵያዊ ራዕይ እንዳይኖረን መደረጉ ነው፡፡ የዚህ ፍሬ ምስራቹን በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ደርሶ ተመልክተነዋል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ችግር በኢትዮጵያ ጥላ ስር ይፈታል ጥቅሙም ይረጋገጣል ብዬ ነው የማምነው የሚለው ኦህዴድ፤ አባል የሚመለምለውና የሚያደራጀው በኦነግ ፕሮግራም እንደሆነ ያጋለጠ ክስተት ነበር፡፡

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒሰትር አሉት የሚባለው “ኦህዴድ ሲፋቅ ኦነግ ነው” የሚባው በዚህ ክስተት ኦህዴድ ሳይፋቅም ኦነግ ሆኖ ነው የተገኘው፡፡ ይህ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሀገራት ለውህደት በሚሰሩባት ዓለም የመገንጠል ጥያቄ በወጣቶች ላይ የዘራው ኦህዴድ/ኢህአዴግ ያሰገኘልን የግንቦት 20 ፍሬ ነው፡፡ ኢቲቪም ሆነ ተሳዳቢዎቹ የማህበራዊ ድህረ ገፅ ካድሬዎች ይህን የግንቦት 20 ፍሬ አያነሱትም፡፡ ዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በአንድ ሳምንት ተበጥብጦ የሚጠጣ አይደለም የሚል አዲስ መፈክር መጥቶዋል፡፡ በእኔ እምነት ሃያ ሶስት ዓመት ሙሉ ተዓማኒነት ያለው እና ተቀባይነት ያገኘ ምርጫ ማካሄድ ያለመቻልን የሚያክል ብቃት ማነስ በዓለም ያለ አይመስለኝም፡፡ ለነገሩ በብቃት ምርጫ ማጭበርበር እንደ ብቃት ከተወሰደ ደግሞ ገዢውን ፓርቲ የሚያሽልም ነው፡፡ ለልምድ ልውውጥም ብዙ አንባገነን መሆን የሚፈልጉ እንደ ጆርጅ ኦሩዌል መፅሃፍ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡

የዲሞክራሲ ስርዓት ገንብቻለው የሚል መንግሰት ዜጎች በምርጫ ለመወዳደር፣ አማራጭ ይዞ በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ፣ ምርጫን ያለስጋት መታዘብ፣ የመሳሰሉትን ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለመጠቀም በፍርሃት እየራዱ ብዙዎች “አታነካኩኝ ልኑርበት” የሚሉበት ሀገር ሲሆን፤ የዲሞክራሲ ስርዓት ለማስፈን ነው ትግሉ እየተባሉ በዱር በገደል ህይወታቸውን የሰዉ ሰማዕታት ድንገት ቀና ቢሉ ምን ምን ዓይነት መልስ እንደሚሰጧቸው መገመት ያስቸግራል፡፡ የሚያሳዝነው እራሳቸውን ለመስዋዕትነት አዘጋጅተው የነበሩ በአጋጣሚ በህይወት የተረፉት ይህ ነው ዲሞክራሲው ሲባሉ እሺ ብለው መቀበላቸው ነው፡፡

 ከመሰዋዕትነት መትረፋቸውን እንደ አንድ ትርፍ ቆጥረው በአንድ ወይም በሌላ የሚያገኙትን ጥቅም እያገኙ እነርሱም ቀሪ
ህይወታቸውን ማጣጣም ተያይዘውታል፡፡ በህይወት ለሚገኙ ኢህአዴግ ታጋዮች ፍሬው የእነርሱ በህየወት መትረፍ ሆኖወል፡፡
የሰመሃታቱን ቃል ኪዳን መብላት ግንቦት 20 ፍሬ ነው፡፡

የዛሬን ግንቦት 20 ለሃያ ሶስተኛ ጊዜ ተከብሮዋል፡፡ ዋና የቡድን መሪያቸውን አጥተው እውር ድንብር መሄድ ከጀመሩ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ያከበሩት ኢህአዴጎች ዛሬም ሃሳብን በነፃነት መግለፅን ማረጋገጥ አልቻሉም፡፡ ከዚህ በኋላ ስንት እንደሚቆዩ አይታወቅም፡፡ ለዚህ ነው ስንት ይቆዩ ይሆን ብዬ መጠየቅ ያማረኝ፡፡ ኢህአዴግ በእርግጥ የተሳካለት ይህን መብት መረጋገጡ ላይ ነው፡፡

በህገመንግሰት ውስጥ ወርቃማ ፃነቶችን ለማስቀመጥ ያልፈራው ኢህአዴግ በጠመንጃ ለማነጋገር ከተዘጋጁት ይልቅ በብዕራቸው ጉድለቱን ሊያሳዩት የሚጥሩትንጋዜጠኞች ዓይናችሁን ላፈር ብሎ እያሳደደ ነው፡፡ ኮምፒዩተር ላይ ቁጭ ብለው ሃሣባቸውን በነፃነት እዚህ ግባ ለማይባል ማህበራዊ ገፅ ተጠቃሚ ስላካፈሉ ብሩዕ ተሰፋ ያላቸውን ወጣቶችን እስር ቤት ያጉራል፡፡ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሽት ታዬ፣ እስክንድር ነጋ አንድም ጥይት የላቸውም፡፡ የሚያስገርመው ጠመንጃ ከያዙት ይልቅ ግን ገዢውን ፓርቲና መንግሰትን ያርበደብዱታል፡፡ “ዞን ዘጠኞች” በምን መለኪያ ነው ብጥብጥ የማስነሳት አቅም ያላቸው፡፡ የእነሱ አቅም የነበረው ሃሣብን በነፃነት ገልፆ በሰላም መተኛት ነው፡፡ ለነገሩ እነርሱም ወደ ሌላዞን ተዛወሩ እንጂ ሀገሪቱ እራሷ እስር ቤተ መሆኗን ለማመላከት ነው “ዞን ዘጠኝ” ብለው እራሳቸውን የሰየሙት፡፡ ኢህአዴግ እነዚህ ወጣቶች በሀገራችን ጉዳይ ያገባናል ብለው ስለተንቀሳቀሱ እስር ቤት አጎራቸው፡፡ በተቃራኒው ግን እነዚህ ወጣቶች በየካፍቴሪያው ተጎልተው ቢውሉ፣ በየጫት ቤቱ ሺሻ ሲያጨሱ ቢውሉ እና ዲቪ ሲሞሉ ወይም ከሀገር መውጫ መንገድ ሲቀይሱ ቢውሉ፣ ስለዚህች ሀገር አያገባንም ብለው ቢጦምሩ ጫፋቸውን አይነካም፡፡ ዝንባቸውን እሽ አይልም ነበር፡፡ የግንቦት 20 ፍሬያችን ከሃያ ሶስት ዓመት በኋላ ያገኘነው በግልፅ በህገ መንግሰት የተደነገገን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የማይከበርበት ስርዓት መገንባት ነው፡፡ የስርዓት ለውጥ ብቻ፡፡ ከደርግ ወደ ዳግማዊ ደርግ በመጀመሪያው ዘመናቸው ቡድናዊ አንባገነንነት፡፡ በኋላም ወደ ግለሰብ አንባገነንነት ማለትም ከመንግስቱ ሀይለማሪያም ወደ መለስ ዜናዊ መሸጋገር ነው፡፡ይህን ኢቲቪ ሊያሳየን አቅም የለውም፡፡ ተከፋይ የድህረ ገፅ ተሳዳቢዎችም አይሞክሯትም ለምን ቢባል እንጀራ ነው፡፡

ግንቦት 20 እንደ መሰከረም 2 ወደ መቃብር እንዳይወርድ በቀጣይ የሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ባህል ይሆን ዘንድ ግን ኢህአዴግ አሁንም እድል አለው፡፡ ሃያ ሶስት ዓመት ዘግይቶም ቢሆን ሰመዓታቱን ሊያስከብር የሚችለውን የዲሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ መሆን ይኖርበታል፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚመጥን የዲሞክራሲ ስርዓት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ነው፤ ይህንንም ለማሳካት እኛ ሰላሣ እና አርባ ዓመት መግዛት አለብን የሚለው ተረት ተረት ተቀባይነት የሌለው ብቻ ሳይሆን በዚህች ሀገር ሌላ አብዮት የሚጠራ ገፊ ምክንያት ነው፡፡

ይህ አብዮት ሲመጣ ደግሞ መሰከረም ሁለት እንደተፈነገለው ግንቦት 20 ይፈነገልናል ሌላ ከዓመቱ አንድ ቀን ሌላ የድል የለውጥ ቀን ይመጣል፡፡ ለዲሞክራሲ ለፍትህ ሲባል ሰማዕታት ለሆኑት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሲባል ግንቦት 20 የድል ቀን ሊሆን የሚችልበት እድል ያለው በኢህአዴግ እጅ ነው፡፡ በማንኛውም ምክንያት ኢህአዴግ በክብር ሳይሆን በውረደት ከወደቀ ግንቦት 20 የዓመቱ አንድ ቀን ከመሆን አልፎ የድል ቀን ሆኖ ሊከበርበት የሚችልበት አንድም ምክንያት አይኖርም፡፡ አሁን ባለው ሁኔት ያለፉት 23 ዓመታት ለኢህአዴጋዊያን የድል ቀን ሲሆን ለእኛ እንደማነኛውም የዓመቱ አንድ ቀን ሆኖ ተገደን ከሰራ የምንቀርበት ቀንም ጭምር ነው፡፡ እንደ አሁኑ ደግሞ አርብ ቀን ሲውል ለረዥም የሳምንት መጨረሻ ግብዓት ሆኖ ያገለግላል እንጂ በመጀመሪያው ግንቦት 20 ጠዋት የሰማነውን ለህዝብ ጥቅም ሲባል የተሰራ አንድም ድል አይሸተኝም፡፡

ዐፄ ሀይለስላሴ ሰማኒያኛ የልደት ባህላቸውን፤ ደርግ የኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዮት ያቀረበለትን የስልጣን ይልቀቁ ጥያቄ ገፍተው
እንደተዉት ሁሉ ኢህዴግም እሰከ ዛሬ ካሳለፋቸው እድሎች በተጨማሪ መቼ እንደሆነ በቅርብ ባይታወቅም እሩቅ ባልሆነ ጊዜ እድሉን ገፍቶ ይጥለዋል፡፡ በተለይ ደግሞ ከዋናው የቡድኑ መሪ መለስ ዜናዊ እልፈት በኋላ ለረዥም ጊዜ በሴራም በእውቀትም የሚመራው ሰው ያለው አይመስለኝም፡፡ ይህ ግን ከግምት በላይ ነው፡፡ ወንበሩን የወሰዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ይህን ፍንጭ አላሳዩንም ይልቁንም ሌጋሲ ማስቀጠል በሚል የወይን ፋብሪካ ምረቃን ጨምሮ ተቀባይነት የሌላቸው በምረቃ ስራ ተጠምደው መዋላቸው ለሌላ ሰትራቴጂክ ሰራ ጊዜ እንደሌላቸው የሚያሳብቅ ነው፡፡ እነዚህን ሁሉ ደምረን ስናይ ግንቦት 20 እንደ መስከረም 2 ሳይዋረድ ከመለስ እልፈት በኋላ ስንት ዓመት ይቀጥላል? ብለን እንድንጠይቅ የሚያስገድደን፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግንቦት 20 በግራዋ ዛፍ ላይ የበቀለ መራራ አፕል ነው፡፡

ቸር ይግጠም!!!!
ግርማ ሠይፉ ማሩ

የወያኔ ጥላቻ ፍሬ

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው።

የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤ ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህም በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤ አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ ‹‹ያመኛል›› ማለቱ ይገባኛል።

ወያኔ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ትግሬ ሁሉ ዕዳ አለበት ማለት እንደወያኔ ማሰብ ነው፤ ወንጀል በዘር አይተላለፍም፤ እያንዳንዱ ሰው ለሠራው ሥራ ሁሉ ኃላፊነትን ይወስዳል፤ ጊዜው ሲደርስ ውጤቱንም ለመቀበል ይገደዳል፤ ይህ የሚሆነው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ኃይል በጎ መንፈስ አድሮበት፣ አእምሮው በትምህርት ተገርቶ በትክክል ማሰብ ሲችል ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን በአለበት ሁኔታ በጎ መንፈስ የራቀው ይመስላል፤ አእምሮም ጭራሹኑ በእኩይ መንፈስና በጥላቻ እየዛገ ነው፤ ስለዚህ ያስፈራል፤ በደቡብ ሱዳን ሁለት መቶ ሰዎች በዘር ተለይተው ታረዱ ሲባል ያስፈራል፤ በናይጂርያ፣ በኮንጎ የሚካሄደውን የዘርና የሃይማኖት እልቂት ስንሰማ ያስፈራል፤ በ1997 ዓ.ም. መለስ ዜናዊና አዲሱ ለገሰ እንዳስታወሱን የሩዋንዳ የጎሣ እልቂት በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ አለ፤ የቅርብ ተኳሽ የሆነው የአግዓዚ ጦርም አድፍጦ መጠበቅ ያስፈራል፤ ሌላውም ይህንን አውቆ አድፍጦ መጠበቁ ያስፈራል፤ ሰማይ ጠቀስ የሠሩት፣ የሥልጣን ኃላፊነትን ችላ ብለው በሥልጣን የሚነግዱና የሚከብሩት፣ የማይኖሩበትን ሕንጻ የሚክቡት፣ ከሕዝብ ጋር ያላቸው የአይጥና የድመት ኑሮ ያስፈራል፤ አቶ አስገደ ወያኔ መደንገጡን ይነግረናል፤ መደንገጥ የማይቆጣጠሩት ፍርሃት ነውና አደጋ ያመጣል፤ አደጋው አደጋን ይጠራል፤ ይህም ያስፈራል።

በትግራይ ዙሪያ ያለው ምንድን ነው? የትግራይ ሕዝብ በየትኛው አቅጣጫ ነው አንደልቡ እየተዘዋወረ ለመሥራትና ለመኖር የሚችለው? ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ከሰሜን ከወገኑ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አቃብቶታል፤ በደቡብ-ምሥራቅ ከወሎ መሬት ቆርሶ የወሎን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ በደቡብ-ምዕራብ ከጎንደር መሬት ቆርሶ የጎንደርን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ የራስን ወገኖች አስቀይሞ ሱዳንን በመሬት ለመደለል የሚደረገው ጥረት ሁሉ ፋይዳ የለውም፤ ሱዳን ለራሱም ያልበጀ አገር መሆኑ እየታየ ነው፤ ወደፊት ደግሞ ይበልጥ ይታያል፤ በትግራይ ውስጥ ደግሞ ወያኔ የፈጠረው አፓርቴይድ የወያኔን የኑሮ ደረጃ ወደሰማይ ሲያስጠጋው፣ የቀረውን ወደአንጦርጦስ የደሀነት ገደል ውስጥ ከቶታል፤ በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከነልጆቻቸው እየተዘዋወሩ የሚለምኑ ሞልተዋል፤ ይህ ልመናም ለወያኔ ለመገበር ነው፤ ብዙዎቹ እንደሚናገሩት የሚለምኑት የማዳበሪያ ዕዳቸውን ለወያኔ ለመክፈል ነው።

ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ጥላቻ ወደንዴት፣ ንዴት ወደቁጣ ተለውጦ ሲገነፍል ምጽዓት ደረሰ ማለት ነው፤ ሁሉም ሰው ራቁቱን ይሆናል፤ አንደአውሬ ከጥፍሩና ከጥርሱ በቀር ሌላ መሣሪያ አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ በክፋት ወደአውሬነት ይለወጣል፤ ጠመንጃና ቦምብ አያገለግሉም፤ ሕንጻው ምሽግ አይሆንም፤ መኪናው፣ ባቡሩ፣ ታንኩ ከቆመበት አይነቃነቅም፤ የትም አያደርስም፤ ጭፍራ ሁሉ በየራሱ ፍዳ ታንቆ እንኳን ለሌላ ሊተርፍ ለራሱም የማይበቃ ይሆናል፤ ለነገሩ ጌታና ሎሌም የለም፤ ሁሉም በአውሬ እኩልነት የተፋጠጠ ነው፤ ርኅራኄ ተሟጦ፣ መግል ያዘለ ልብ ፈርጦ፣ ውይይትና ክርክር አብቅቶ፣ ጥርሱን ያገጠጠና ጥፍሩን የሳለ መንጋ በደም የሚራጭበት ሁኔታ ነው። ሌላ አገር እንዲህ አልሆነም፤ እዚያ አገር እንዲህ አልሆነም፤ የሚባል ነገር የለም፤ እኛ ዘንድ ሌላ ነው፤ የኢትዮጵያ ደሀዎች እንባ የእግዚአብሔርን ሰማይ አጨቀየው!

ክፋት እንደ እሳት ይቃጠላል፤ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፤ ጭፍቅየሆነውንም ዱር ያቃጥላል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዓምድ ይወጣል፤በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቁጣም ድር ተቃጥላለች፤ ሕዝቡም እሳትእንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ አይራራም፤ ሰው በቀኙ በኩልይነቅላል፤ ይራብማል፤ በግራም በኩል ይበላል፤ አይጠግብምም፤ እያንዳንዱምየ ክንዱን ሥጋ ይበላል፤ ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤ …ኢሳይያስ 9/18-21

ትንቢተ ኢሳይያስ ለሩዋንዳውያን ብቻ አይደለም፤ ጥላቻና ክፋት በተዘራበት ቦታ ሁሉ ውጤቱ ጥፋት ነው፤ ምናሴ ኤፍሬምን በልቶ አይቀርም፤ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላዋል።

Monday, May 26, 2014

የመጨረሻዉ ካርድ


አገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ሃያ ሦስት አመታት ያለፈችበትን የግፍና የመከራ ዉጣ ዉረድ ወደ ኋላ መለስ ብሎ መመለክት መፈጠርን የሚያስጠላና ልብን የሚያደርቅ እራሱን የቻለ ሌላ በጭንቅና በመከራ የተሞላ ዉጣ ዉረድ ነዉና አለመሞከሩ ይመረጣል። ሆኖም አገራችንን ከዚህ ሳትወድ በግድ እጇን ታስራ ከገባችበት የጥፋት ቁልቁለትና የመከራ አዘቅት ዉስጥ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ጎትቶ ለማዉጣት የግድ እዘህ ድቅድቅ ጨለማ ዉስጥ እንዴት ገባች ብሎ እራስን መጠየቅ ያስፈልጋልና ወደድንም ጠላን የሃያ ሦስቱን አመት ጉዟችንን ወደ ኋላ ዞር ብለን በጥሞና ማጤኑ አማራጭ የሌለዉ መንገድ ነዉ። የወያኔ ዘረኞች ፋሺስቱን ደርግ ጣልን ይበሉ፤ በ99.6 በመቶ ድምጽ ተመርጥን ይበሉ ወይም እድገት አመጣን ይበሉ የእነሱ ፍላጎት ምን ግዜም ቢሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ረግጦ መግዛት ነዉ እንጂ ህዝብን በጨዋነት ማስተዳደር አይደለም። አንድን ህዝብ ረግጦ ለመግዛት የሚያስፈልገዉ ደግሞ ጠመንጃና ባዶ ጭንቅላት ብቻ ነዉ፤ ጠመንጃና ባዶ ጭንቅላት በገፍ የሚገኝበት ድርጅት ነዉና ወያኔ ደግሞ በዚህ በፍጹም አይታማም። የወያኔ ዘረኞች ፍላጎት የኢትዮጵያን ህዝብ ከጣሊያን ፋሺስቶች ባልተለየ መንገድ እየረገጡ መግዛት ቢሆንም አንድን ህዝብ ዝንተ አለም ረግጦ መግዛት አንደማይቻል በሚገባ ያዉቃሉ፤ ለዚህ ነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ ኃይሉን እነሱ ላይ ለማሳረፍ በቆረጠ ቁጥር ህዝብን ከህዝብ የሚለያይና የሚያራርቅ ካርዳቸዉን እየመዘዙ ጸረ ህዝብና ጸረ አገር ጨዋታቸዉን የሚጫወቱት። በእርግጥም ወያኔዎች በስልጣን በቆዩባቸዉ ባለፉት ሃያ ሦስት አመታት የተለያዪ ካርዶችን መዝዘዋል – ፌዴራሊዝም እያሉ በፌዝራሊዝም ቀልደዉብናል፤ እድገትና ልማት እያሉ ጠብ ያለዉን ሁሉ እነሱ እራሳቸዉ እየዋጡ ሌሎቻችንን የበይ ተመልካቾች አድርገዉናል፤ በጎሳ ከፋፍለዉናል፤ በዘር አጥር አጥረዉናል። ዛሬ ደግሞ ለእነዚህ ተራ በተራ ለመዘዟቸዉ የክፋት ካርዶች አልታለልም ያለዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ካዝናቸዉ ዉስጥ የቀረችዉን የመጨረሻ ካርድ መዝዘዉ በጎሳና በዘር ከመለያየት አልፈዉ በዘር ለማጋጨትና ደም ለማፋሰስ ጉድ ጉድ እያሉ ነዉ።

ኢትዮጵያ ዉስጥ ማንም ኃይል በምርጫ ሥልጣን ያዝኩ ብሎ አፉን ሞልቶ ለመናገር ኦሮሚያና አማራ ክልል ዉስጥ ምርጫዉን ጉልህ በሆነ ብልጫ ማሸነፍ አለበት፤ ወይም አማራና ኦሮሚያ ዉስጥ ተሸንፎ ፓርላማ ዉስጥ አብዛኛዉን ወንበር ተቆጣጥሮ መንግስት መመስረት አይቻልም። ወያኔ ዛሬ ያንን የእንቅልፋሞች ፓርላማዉ ተቆጣጥሮ መንግስት ነኝ ብሎ የሚፏልለዉ ሁለቱን የአገራችንን ግዙፍ ብሄረሰቦች ለያይቶና አንዱ ሌላዉን በጥርጣሬ አይን እንዲመለከት አድርጎ ነዉ እንጂ ወያኔ በየቀኑ የሚያስራቸዉ፤ የሚደበድባቸዉ፤የሚያሳድዳቸዉና የሚገድላቸዉ የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች በፍላጎታቸዉ መርጠዉታማ አይደለም። ወያኔ ዛሬ ከሚታይበት የፖለቲካ ኪሳራና ህዝባዊ መተፋት አንጻር እንደቀድሞዉ ኦሮሞንና አማራን በመከፋፈልና በመለያየት ብቻ ስልጣን ላይ መቆየት እንደማይችል ስለተረዳ እነዚህ ሁለት የአገራችን ግዙፍ ብሄረሰቦች እርስ በርሳቸዉ ተጋጭተዉ እንዲተላለቁ የሚቻለዉን ሁሉ እያደረገ ነዉ። ወይም ቀለል ባለ አማርኛ ወያኔ ከጫካ ይዞት የመጣዉን የመጨረሻ ካርድ መዝዞ አገራችንን በቀላሉ ወደ ማትወጣዉ የዘርና የጎሳ ግጭት ዉስጥ ለመክተት ቁጭ ብድግ እያለ ነዉ።
ወያኔ የመሬት ባለቤትነትን ጉዳይ ህገ መንግስቱ ዉስጥ ሸንቁሮ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሬት የግል ንብረት የሚሆነዉ በእኔ መቃብር ላይ ነዉ ያለዉ አለምክንያት አይደለም። ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሬት የህዝብና የመንግስት ነዉ ይበል እንጂ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ትክክለኛዉ የመሬት ባለቤት ህዝብም መንግስትም ሳይሆን ህወሀት ወይም ወያኔ ነዉ። ይህንን ወያኔ የሚባል የዘረኞች ስብስብ ባስቸኳይ ጠራርገን በገዛ አፉ እንደተናገረዉ በወያኔ መቃብር ላይ የአገራችንን የተዛባና ጎታች የመሬት ይዞታ በፍጥነት ካልቀየርን ሁላችንም የወያኔ ገባር መሆናችን የማይቀር ነዉ:። ዛሬ ወደድንም ጠላን አገራችን ዉስጥ ልክ እንደፊዉዳሉ ዘመን መሬት እንደ ስጦታ ለዘመድና ለቤተዘመድ የሚሰጥ ደሃዉንና ሀብታሙን የሚለይ የመጨቆኛ መሳሪያ ነዉ። መሬት መብት መርገጫ ነዉ፤ መሬት አፍ ማስዘግያ ነዉ፤ መሬት ማማለያ መሳሪያ ነዉ፤ መሬት የማይወዱትናን የኛ አይደለም የሚሉትን ማግለያና መድረሻ ማሳጫ ነዉ። ባጠቃላይ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሬት የወያኔ ቂም በቀል መወጫ አይነተኛ መሳሪያ ነዉ። ወያኔ እኔን አይደግፈኝም ከሚለዉ ከማንም ሰዉ መሬት ቀምቶ ላሰኘዉ ሰዉ መስጠት ይችላል። ይህንን ለማረጋገጥ ደግሞ ብዙ መጓዝ አያስፈልግም፤ አዲስ አበባን ጨምሮ በየክልሉ አዳዲሶቹን የከተማ ቦታና ሰፋፊ የእርሻ መሬት ባለቤቶች እነማን እንደሆኑ መመልከቱ ይበቃል።
በቅርቡ አምቦ ዉስጥ በግፍ የተጨፈጨፉት የኦሮሞ ተማሪዎች እንደዚህ አይነቱን አግላይ የሆነ የወያኔ የመሬት ፖሊሲ የተቃወሙ ተማሪዎች ናቸዉ። ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ በልማት ስም በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ የኦሮሞ ገበሬዎችን እያፈናቀለ መሬቱን ለራሱ ወገኖች መስጠቱን በመቃወም አምቦ፤ ጅማ፤ ወለጋ፤ አዳማና ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ የሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ወያኔንና ደጋፊዎቹን ክፉኛ ያስደነገጠ ከፍተኛ የተቃዉሞ ሰልፍ ያደረጉትና ምትክ የሌለዉን ህይወታቸዉን የገበሩት ይህ እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ የወያኔ የመሬት ፖሊሲ ስለገባቸዉ ነዉ። በዚህ በተለያዩ ቦታዎች በተካሄደዉ የተቃዉሞ ስልፍ ላይ የኦሮሞ ተማሪዎች ያነገቡት አንድ ጥየቄ ብቻ ነበር፤ እሱም ህዝብን ያላካተተ ልማት የለምና ወላጆቻችንን እያፈናቀላችሁ መሬታችንን መከፋፈል አቁሙ የሚል ጥያቄ ነበር። ለዚህ የኦሮሞ ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ ላቀረቡት ጥያቄ ወያኔ የሰጠዉ መልስ እንደተለመደዉ በአግአዚ ነብሰ ገዳዮች ወጣቶችን በየአደባባዩ በጥይት መጨፍጨፍ ነበር – አዎ! የወያኔ ስራ ጥያቄ ሲጠይቁት መግደል፤ ምርጫ ሲሸነፍ መግደል፤ ለምን ጻፍክ ብሎ መግደል፤ ለምን ተናገርክ ብሎ መግደል ነዉ።
ወያኔ በሃያ ሦስት አመታት የስልጣን ዘመኑ እንደ ዘንድሮ ተገፍቶ ተገፍቶ ዳር የደረሰበትና እንደ ዘንድሮ መዉጪያና መግቢያዉ ጠፍቶበት አያዉቅም። እኛ ብናምንም ባናምንም ወይም ብናዉቅም ባናዉቅም ወያኔ የተከበበ አዉሬ ሆኗል፤ ግን ከዚህ በፊት አንዳደረገዉ ሁሉ የከበቡት ኃይሎች ፊት ለፊት የሚተያዩና አብረዉ የሚሰሩ ኃይሎች ባለመሆናቸዉ ወያኔ ከበባዉን ጥሶ ለመዉጣት እየሞከረ ነዉ። ከላይ ከፍ ሲል ለመጥቀስ እንደሞከርነዉ ወያኔ እንደ ዘንድሮ ተዋክቦና እንደዘንድሮ የመጨረሻዉ ሸትቶት አያዉቅም። ሆኖም እንድ መርሳት የሌለብን ነገር ቢኖር ወያኔ ከገጠመዉ ህዝባዊ ቁጣ ለማምለጥና ስልጣን እንደጨበጠ ለመቀጠል እንደዛሬ የዘር መለያየትና ማጋጨት ሴራዉን ተግባራዊ ያደረገበት ግዜም የለም። እዉነቱን ለመናገር በአንድ በኩል ምንም ጥርጥር በሌለዉ መልኩ ወያኔ ተከብቦ ህልዉናዉ አደጋ ላይ ወድቋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔ ከዚህ ተገፍቶ ከገባበት አደጋ ለመዳን አገራችን ዉስጥ ዘርና ጎሳ ለይቶ ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያባላ የእርስ በርስ ጦርነት ለመቀስቀስ ዝግጅቱን ጨርሷል።
የኦሮሞ ተማሪዎች ባካሄዱት የተቃዉሞ ሠልፍ ዉስጥ አልፎ አልፎ የተሰማዉ “የሚኒልክ ሃዉልት ይፍረስ” የሚለዉ ጩኸትና ጊምቢና በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች አማራ ይዉጣልን የሚለዉ ጥያቄ የህዝብ ጥያቄ ሳይሆን ወያኔ ሆን ብሎ ከትኩቶ ባሳደጋቸዉ ካድሬዎቹ አማካይነት ህዝብ ዉስጥ ይዞት የገባዉ የእርስ በርስ እልቂት መቀስቀሻ ጥያቄ ነዉ። ሁለቱ ዝሆኖች ሲጣሉ የሚሰቃየዉ ሳሩ ነዉ እንደሚባለዉ ወያኔ የአማራንና የኦሮሞን ብሄረሰቦች በማጋጨት እነዚህ ሁለት የአገራችን ብሄረሰቦች እርስ በርስ ሲፋጩና የኢትዮጵያ ህዝብ ሲሰቃይ እሱ የስልጣን ዘመኑን ማራዘምና የዘረፋ ተልዕኮዉን እንደገና ማደስ ይፈልጋል። ይህ “እኔ ከሞትኩ ስርዶ አይብቀል” አይነቱ የወያኔ ሴራ ለወደፊት ሊከናወን በዕቅድ የተያዘ ጥንስስ ሳይሆን ከአመታት በፊት ጫካ ዉስጥ ታቅዶ ዛሬ ተግባራዊ በመሆን ላይ ያለ የወያኔ ተንኮል ነዉ።
ወያኔ የኦሮሞና የአማራ ብሄረሰቦች እጅ ለእጅ ተያይዘዉ ከተነሱበት የስልጣን ዘመኑ በቀኖች እንደሚቆጠር በሚገባ ያዉቃል፤ በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ አብዛኛዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ያቀፉት ሁለት ግዙፍ ብሄረሰቦች በመካላቸዉ ስምምነት ከሌለና አንዱ ሌላዉ ላይ በቂም በቀል ከተነሳ ማንም በቀላሉ ከስልጣን እንደማያባርረዉ ጠንቅቆ ያዉቃል፤ ለዚህም ነዉ ባገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ እንዚህ ሁለት ብሄረሰቦች እንዲጋጩ ክብሪት የሚጭረዉ። አምቦ፤ ጊምቢ፤ አኖሌና ምስራቅ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተደጋጋሚ የተጫረዉ የዘር ግጭት መቀስቀሻ እሳት ወያኔ አማራዉንና ኦሮሞዉን ለማጋጨት ሆን ብሎ የለኮሰዉ እሳት ነዉ። ዛሬ የኦሮሞን ተወላጆች ስልጣን መድረክ አካባቢ እንዳይቀርቡ አድርጎ የኦሮሚያን መሬትና የመሬት ላይና ዉስጥ ኃብት በገፍ የሚዘርፈዉና የአገሪቱን እስር ቤቶች በኦሮሞ ተወላጆች የሞላዉ ወያኔ ነዉ እንጂ ግዑዙና የማይናገረዉ የምኒልክ ኃዉልት አይደለም። ኦህዴድ የሚባል ተለጣፊ ባቡር ሰርቶ የኦሮሞን ህዝብ የሚገድለዉና በገዛ መሬቱ ላይ ባይተዋር ያደረገዉ ወያኔ ነዉ እንጂ ከመቶ አመት በፊት ሞተዉ የተበሩት ዳግማዊ ምኒልክ አይደሉም። ስለዚህ የኦሮሞ ህዝብ ከአማራዉና ከሌሎቹ ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር ሆኖ ማፍረስ ያለበት የምኒልክን ኃዉልት ሳይሆን ወያኔንና ወያኔ የፈጠረዉን ዘረኛ ስርዐት ነዉ።
ባለፈዉ ወር አምቦ ላይ ያየነዉ የአግአዚ ጭፍጨፋ ወያኔ ከደገሰልን ጥፋት ጋት ሲነፃፀር እጅግ በጣም ትንሽ ነዉ፤ ወያኔ እያንዳንዳችንን በተናጠል በመታና በገደለ ቁጥር ቁጣችንን የምንገልጸዉና የምንከላከለዉ በተናጠል ከሆነ ወያኔ እያንዳንዳችንን በተናጠል እየገደለም ሆነ እያሰረ ጭጭ የማስደረግ ኃይል አለዉ። ይብዛም ይነስ የወያኔን ጥቃት ተቋቁመን ወያኔን ማስወገድ የምንችለዉ በጋራ አንድ ሆነን ስንቆም ብቻ ነዉ። እያንዳንዳችን ሺ ጠመንጃ ይዘን ወያኔን በተናጠል ብንገጥመዉ አናሸንፈዉም፤ ሁላችንም ተባብረን እንደ አንድ ሰዉ መቆም ከቻልን ግን ወያኔን ለማሸነፍ ጠመንጃም አያስፈልገንም። ስለዚህ ዛሬ ለኛ ለኢትዮጵያዉያን የትብብር ጥያቄ የትግል አማራጭ ሳይሆን በፍጹም ልናልፈዉ የማይገባን የህልዉና ጥያቄ ነዉ። እኛ ኢትዮጵያዉያን – ኑ አብረን እንታገል እያልን የትግል ጥሪ ስናስተላልፍ ወያኔ ደግሞ አገር እያፈረሰና ህዝብ እየገደለ ከሃያ አመት በላይ ተጉዘን ዛሬ ላይ ደርሰናል። የእኛ ጩኸት ከሃያ አመት በኋላ ዛሬም እንተባበር የሚል ነዉ፤ ሃያ አመት ሙሉ አገር ሲንድና ህዝብ ሲገድል የከረመዉ ወያኔ ግን ዛሬ የተቃወመዉን ሁሉ ቢቻል ለመግደል አለዚያም ለማሰር እየተንቀሳቀሰ ነዉ። እንደ አገርና እንደ ህዝብ በአንድነታችን ፀንተን ለመቀጠል ካሁን በኋላ ያለን ብቸኛ አማራጭ ጥቂቶች ታስረን፤ ጥቂቶች ተሰድደን ጥቂቶች ደግሞ ሞተን ወያኔን ማስወገድ ወይም በተናተል ሁላችንም ተራ በተራ መሞት ነዉ።
አባቶቻችን ያስተማሩንና እኛም በነጋ በጠባ እንደ ዳዊት የምንደግመዉ ይህንኑ ለእናት አገሬ እሞታለሁ የሚለዉን የአባቶቻችንን ትምህርት ነዉ።
ወገን ለኢትዮጵያ መሞት ካለብን ቀኑ ዛሬ ነዉ . . . . ኑና ለእዉነት ሞተን በህይወት እንኑር!

Ethiopia: Crimes Against University Students and Humanity



I am outraged beyond my ability to express my outrage in words. I grieve and ache for the students cut down by hails of bullets in the prime of their lives. They had an undeniable constitutional right to peacefully petition for grievances; because they exercised that right, we must now all grieve for them. I grieve for Ethiopia for it has lost its best and brightest children. I extend my deepest condolences to the families and friends of the victims of the massacre. 

I abhor massacres. I got involved in Ethiopian and African human rights advocacy following the post-2005 election massacres of unarmed protesters in Ethiopia. Prior to that time, I had virtually no involvement in Ethiopian politics. I did not know the name Meles Zenawi “from Adam’s off ox”. 
When troops under the personal control and command of the late Meles Zenawi massacred some 200 unarmed demonstrators and shot and wounded nearly 800 more (the actual figure is documented to be much more than that), I was hopping mad as hell. I just could not let Meles and his criminal gang get away with mass murder. For the past eight years, I have been advocating and promoting human rights in Ethiopia and Africa every single Monday without missing a single week. 



I am hopping mad as hell today over the massacre of the dozens of unarmed university and high school students in Ambo and elsewhere as I was in 2005 when hundreds of unarmed protesters were slaughtered. I am hopping mad as hell that no one is ever held accountable for massacring innocent people in Ethiopia. There is a long and shameful culture of impunity in Ethiopia. Mengistu Hailemariam committed mass murder and has not been held accountable. That mass murderer said he "did not hurt a fly" while he was in power. He did kill tens of thousands of innocent people. He is comfortably living out his twilight years in Zimbabwe writing fiction and fables about his time in office. 

Meles Zenawi received divine justice. His surviving disciples and comrades today thumb their noses at justice. The perpetrators of the massacres of 2005 today roam the streets free. Yet we know the names of each and every “federal police” thug who participated in the massacres. In a report entitled “Modernizing Internal Security in Ethiopia” counterterrorism expert Col. Michael Dewar, British Army (Rtd.) revealed that the Director General of the Ethiopian Federal Police Werkneh Gebeyehu told him that “as a direct result of the 2005 riots, he [had] sacked 237 policemen.” Not a single one of these  criminals who committed the massacres or the criminal bosses who ordered the massacres have been brought to justice.  Meles's own Inquiry Commission in 2007 damned Meles for the use of deadly force and absolved the peaceful unarmed protesters of any criminal or civil liability. 

In December 2003, Meles Zenawi’s troops in a series of attacks in Gambella killed 400 Anuaks and destroyed over 1000 homes. The Meles regime subsequently issued a statement “apologizing for not acting proactively and promised to stand on the side of the victims to see that justice is done.” At the time, the regime claimed to have identified dozens of suspects in the Anuak massacres. No soldier, police or security official has ever been prosecuted, held accountable or sanctioned for those crimes against humanity in Gambella. 

Sunday, May 25, 2014

ያለ በቂ ማስረጃ በሕገ ወጥ መንገድ ከአራት ሳምንት በፌት ከተያዙት ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በተጨማሪ በአንድ ጦማሪ አባል መኖሪያ ቤት ላይ ፖሊስ ለ7 ሰአት የቆየ ብርበራ አካሄደ

May 25, 2014

Zone 9 bloggers Zone9
ያለ በቂ ማስረጃ በሕገ ወጥ መንገድ ከአራት ሳምንት በፌት ከተያዙት ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በተጨማሪ በአንድ ጦማሪ አባል መኖሪያ ቤት ላይ ፖሊስ ለ7 ሰአት የቆየ ብርበራ አካሄደ፡፡

በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ በዞን ዘጠኝ ጦማሪና መስራች ሶልያና ሽመልስ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ፖሊስ ብርበራ ያካሄደ ሲሆን የጸረ-ሽብር ሕጉ ይፈቅድልናል የሚል ምክንያት ሰጥተው ያለ ፍርድ ቤት የብረበራ ማዘዣ ከካሜራ ቀራጭ ጋር የተገኙት ሰባት ፖሊሶች በጦማሪዋ ክፍል እና ሌሎች አስፈላጊ ነው ባሉዋቸው ክፍሎች ሲያካሂዱ ነበረውን ብርበራ ጨርሰው ይጠቅመናል ያሉትን የዶ/ር መረራ ጉዲና የመጨረሻ መጽሀፍ እና ሌሎች ወረቀቶች ወስደው ቤት ውስጥ የነበሩትን የጦማሪዋን ወላጅ እናት አስፈርመው ከጠዋቱ 4 ሰአት አካባቢ ቤቱን ለቀው ወጥተው ነበር፡፡ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተመልሰው በመምጣት ተጨማሪ ፍተሻ በዋናው መኖሪያ ቤት መካሄድ እንፈልጋለን ብለው ሁለተኛ ዙር ብርበራ በምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ እናካሂዳከን በሚል ሰበብ ትንሹ ክፍል ውስጥ የጦማሪዋን እናት እነዲወጡ በማግለል ከማቀዝቀዛውን አንቀሳቅሰው አፍታም ሳይቆዩ 19 ገጽ የግንቦት ሰባት ፕሮግራም አግኝቻለሁ ሲል አንዱ ፈታሽ ተናግሯል፡።
የጦማሪዋን ወላጅ እናት እነዲፈርሙ ያግባቡ ቢሆንም ወላጅ እናትዋ ከክፍሏ እና ሌላም ቦታ በመፈተሽ ስታገኙ ያየሁት ወረቀት ላይ ፈርሜያለሁ ይህ ግን ምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ ያልነበረ እና እዚህ ያልተገኘ ሌላ ወረቀት ነው ሲገኝም አላየሁም በማለት አልፈርምም ብለዋቸዋል፡፡ በመሆኑም ፈታሾች ተጨማሪ የሰው ሃይል ደውለው በማስጠራት ለማግባባት ቢሞክሩም ስላልተሳካላቸው ይዘዋቸው የመጡትን የራሳቸውን ሁለት ምስክሮች ብቻ አስፈርመው ባለቤትዋ ለመፈረም ፍቃደኛ አይደሉም ብለው ቤቱን ለቀው ሄደዋል፡፡ ከፓሊስ ጋር የመጡት ምስክሮች አንደኛው አድራሻቸው በብርበራ ምስክርነት ዶክመንቱ ላይ ያልተጻፈ መሆኑንም ለመረዳት ችለናል ፡፡
በብርበራው ወቅት በነበራቸው የ7 ሰአት ቆይታ የጦማሪዋን መጸሃፍት የጉዞ ትኬቶች የስልጠና ማንዋል እና የመሳሰሉትን ጥቃቅን ወረቀቶች የወሰዱ ሲሆን ማብሰያ ክፍል ከፍሪጅ ጀርባ አገኘነው ካሉት ወረቀት ግን ቤት ውስጥ ያልነበረና ፓሊሶች ራሳቸው ያመጡት በመሆኑ እናትዋ ተናግረዋል፡፡
የዞን ዘጠኝ ጦማሪ አባላት ከየትኛውም በፓርላማ በአሸባሪነት ከተፈረጀ የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆኑና ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው እነዲሁም አነዚህ ድርጅቶች ላይ በተለያየ አጋጣሚ ትችቶቻቸውን ሲያቀርቡና ሲቃወሙ የሚታወቁ ቢሆንም ሲሆን በተያዙት አባሎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው አስገድዶ ለሃሰተኛ መረጃ እንዲፈርሙ የማድረግ ተግባር ሳያንስ ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ለማያያዝ ማስረጃን እንደተገኘ አድርጎ የማቅረቡ ተግባር መንግሰት ይታማበት የነበረውን የፓለቲካ ውንጀላን በሽብር የመቀየር ክስ በተግባር እንድናይ ያስቻለን ነው ፡።
በመሆኑም አሁንም ቢሆነ ጦማሪ ጓደኞቻችን ሃሳባቸውን በነጻነት ከመግለጻቸው ውጪ ምንም አይነት የወንጀልም ሆነ ሽብር ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው እያስታወስን መንግስት ያሰራቸውን ጦማርያን እና ጋዜጠኞች አንዲፈታ አሁንም አንጠይቃለን፡፡
ምንጭ፦ ኢካዴፍ

Friday, May 23, 2014

ዞን 9 ጦማሪያን ይፈቱ/Free Zone 9 Bloggers



ዞን 9 ጦማሪያን ስለሃገራችን ያገባናል እንፅፋለን ብለው ብእርን መሳሪያቸው አድርገው እውነተኛ መረጃ በማሰራጨት ተግተው የሚሰሩ ከመፃፍ ውጪ ምንም ወንጀል ያልፈፀሙ የነገ ሃገር ተረካቢ ወጣቶች ናቸው። አምባገነኑ የወያኔ ስርአት የተማረና ስለ ሃገሬ ያገባኛል እውነቱ ይህ ነው ለምን ይዋሻል ብሎ እውነት የተናገረንና የፃፈን ሁሉ እንደአሸባሪ እየቆጠረ በየእስርቤቱ  እየከተተ ማሰቃየቱን ተያይዞታል። ሰዎች ሃሳባቸውን በነፃ መግለፅ ህገ መንግስታዊ መብታቸው ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊ መብታቸው መሆኑን የዘነጋው ወያኔ ዛሬ የዞን 9 ጦማሪያንን በመፃፋቸው ብቻ ሐገር እያሸበሩ ነው በሚል በአሸባሪነት ወንጀል በሐሰት ለመክሰስ ከላይ እታች እያለ ይገኛል።


ዞን 9 ጦማሪያን ያለምንም ወንጀል ዛሬም በእስር እየተሰቃየሚገኙ ቢሆንም የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችን ጨምሮ አለም ለእነኚ ወጣት ጦማሪያን ድምፁን እያሰማ ይገኛል እኛም ኢትዮጵያውያን በያለንበት ሁሉ ድፃችንን በማሰማት ከጎናቸው መቆም ይኖርብናል። አምባገነኑ ወያኔ እስከመቼ እያሰረና እየገደለ በሰዎች ስቃይ እያላገጠ እንዲኖር እድል እንደምንሰጠው ባይገባኝም ለነፃነት የሚደረገው ትግል ግን መፍጠን እንዳለበት ይሰማኛል። ሁላችንም ሃይላችንን ተጠቅመንን ይህንን መጥፎ ስርአት ከሐገራችን ማስወገድ ካልቻልን ማንም ሰው ሀሳቡን በነፃ መናገር ቀርቶ አየር በነፃ ለመተንፈስ መከልከላችን የማይቀር ነው።

የዞን 9 ጦማሪያን እና ሌሎች የፓለቲካና የህሊና እስረኞችን መታሰርን አጥብቄ እቃወማለሁ የዞን 9 ጦማሪያን በአስቸኳይ እንዲፈቱም ወያኔን እጠያቃለሁ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ሄለን ንጉሴ

Tuesday, May 20, 2014

ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ላለፉት ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን የአራተኛ ዙር ታጋዮችን አስመረቀ

የኢትዮጵያዊያንን ስቃይና መከራ ሊያቅብና እንባቸውን ሊየብስ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛው ሕወሃት የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደት ወደ ክብር ለመለወጥና የናቋትና ያዋረዷት በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ ዓላማየ ብሎ ምሎ ዱሩ ቤቴ ካለ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በቃሉ መሰረት አራተኛውን ዙር የታጋዮች የምረቃ በአል ሚያዚያ 26 2006 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ማክበሩን አስታወቀ። ይህ የአራተኛው ዙር ስልጠና በሰልጣኞች ቁጥርም ሆነ በስልጠናው ጥንካሬ ካለፉት ሶስት ዙሮች በእጅጉ የተለየ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም መረጃን መቀበልና ማስተላለፍን የጨመረም እንደነበር ተያይዞ ተጠቅሷል።

በሀገር ውስጥ ፋሽስት ወያኔ እያደረሰው ባለው መረን የወጣ ግፍ የተበሳጩና ሁሉም ልክ እንዳለው ለማሳየት ቆርጠው የተሰለፉት እነዚህ ምሩቅ ታጋዮች ከወታደራዊው ስልጠና በተጨማሪ የፖለቲካ፣ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ሌሎችንም ተያያዥ ክህሎቶችን በበቂ ሁኔታ እንደቀሰሙም ተጠቁሟል። ስልጠናው ታጋዮቹ ወደፊት ከሚያጋጥማቸው ጠንካራ ፈተናና ከሚሰለፉበት ጥብቅ ግዳጅ አንጻር በቀላሉ ተስፋ እንዳይቆርጡ ለማድረግ በአካልም ሆነ በመንፈስ ዝግጁ እንደሚያደርጋቸው የተገለጸ ሲሆን የተጀመረው ሕዝባዊ ትግል በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በጋራና በተቀነባበረ ሃይል ለድል እንደሚበቃና ይህን የጋራ ሃይል በጠነካራ እጆች ላይ ላመስቀመጥም የተሰጠው ስልጠና ከበቂ በላይ ነበር ተብሏል።
ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በሀገር ውስጥ እንደማእበል እየገነፈለ ያለውን የአታግሉን የሕዝብ ጣያቄ በተደራጀና በተቀነባበረ መንገድ በተገቢው መልኩ ለማስተናገድ እንዲችል እንደ ድርጅት ከመቼው በላይ ራሱን እያደራጀና እያጠነከረ እንደሚገኝና ምቹ አታጋይ ተቋም ሆኖ ለመውጣት ሌት ተቀን እየደከመ መሆኑም ተያይዞ ተጠቅሷል። በታጋዮች ስልጠና ወቅት የተገኙ አንዳንድ የክብር እንግዶች እንደጠቆሙትም ”ባሁኑ ሰአት በሀገር ውስጥ ያለው ሁኔታ ከመቼውም በላይ የተመቻቸ ነው” ካሉ በሗላ ”ሕወሃት የሚተማመንበት ወታደሩ እንኳ ቁጥሩ ካልሆነ በቀር ልቡም ሆነ መንፈሱ ከሕዝብ ጋር ነው፤ በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች እየሆነ ያለው ወያኔ በእርጅና ዘምኑ ማብቂያ ላይ መሆኑን ነው የሚያመለክተው። ስለሆነም በመረጃ መንቀሳቀስና በትብብር መስራት ባጭሩ ለድል ያበቃል። ለዚህ ደግሞ የዛሬ ምሩቅ ታጋዮች ያገኙት ስልጠና ለታሰበው ስኬት የሚያበቃቸው ነው” በማለት ትዝብታቸውን አጠቃለዋል።
በምረቃው ማብቂያ ላይ ራሱን ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ብሎ ከሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ለፋሽስት ወያኔ ከፍተኛ ስጋት እንደሆነ በማስረገጥ የጠቆሙት የሕዝባዊ ሃይሉ ሃላፊዎች፤ ከዚህ በፊት ፋሽስት ወያኔ በከፍተኛ ወጭና ጥንቃቄ ሕዝባዊ ሃይሉን ለማፈራረስና ለማትፋት በከፍተኛ ሁኔታ የሰራ ቢሆንም በሕዝባዊ ሃይሉ መረጃና ደህንነት ክፍል መክሸፉን አስታውሰው፤ ዓላማችንን ከዳር ለማድረስና የሕዝባችንን አርነት ለመመለስ ሀገራችንንም ከወያኔ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት በምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አስተላለፈዋል። ይህን ታሪካዊ ጥሪ ለመመለስና የሀገርና የትውልድ ጠላት የሆነውን ወያኔ ሕወሃትን ለማስወገድ አብረን እንቁም ሕዝባዊ ሃይላችንንም ተቀላቀሉ ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

Monday, May 19, 2014

ዘር ማጥራት ወይስ ኢህአዴግን ማፍረስ? (ተመስገን ደሳለኝ)




(ተመስገን ደሳለኝ) 
ኢህአዴግ ያነበረውን ቋንቋንና ዘውግን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም አደገኛነት በተመለከተ በርካታ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች… ሳያሰልሱ ለመምከርና ለማስጠንቅቅ መዋተታቸውን አልዘነጋሁም፡፡ እኔም ከ“ፍትህ” ጋዜጣ እስከ “ፋክት” መጽሔት ድረስ ችክ ያልኩበትም ሆነ ዛሬ በዚህ ተጠየቅ የተመለስኩበት ምክንያት ችግሩ እያደር እየተባባሰ በመምጣቱና ከምንጊዜውም በላይ አዘናግቶ ወደተፈራው የእርስ በእርስ እልቂት ሊዘፍቀን እየተንደረደረ በመሆኑ፣ ቅድሚያ ሰጥተን በሕብረ-ድምፅ ‘የሀገር ያለህ!’ ብለን መጮህ እንዳለብን ስለማምን ነው፡፡ 

አርባ አራት ዓመት ወደኋላ… 

 በኢትዮጵያ የዘውግ ጥያቄ ለአደባባይ የበቃው በ60ዎቹ መጀመሪያ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ከዘመነኞቹ የተማሪ እንቅስቃሴ መሪዎች ይህንን ጥያቄ አለቅጥ ለጥጦና አጋንኖ በማቅረብ ግንባር ቀደሙ ዋለልኝ መኮንን ነው፡፡ በ1962 ዓ.ም በአራት ገፅ 
ቀንብቦ ባዘጋጀው ታሪካዊ ጽሑፉ አማካኝነት “የብሔሮች ጥያቄ” ይፋ ሆኖ ለውይይት ከመቅረቡ በፊት፣ የተማሪው ዋነኛ የመታገያ አጀንዳ የመሬት ጉዳይ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ (በደብዛዛውም ቢሆን ይንፀባረቅ የነበረውን መደብ ተኮር መንፈስ ሳንረሳ)፡፡ ዋለልኝ የሀገሪቱን መንግስታዊ አወቃቀርም ሆነ ባሕልን በአማራና በትግሬ ተፅእኖ ስር ስለመውደቁ 
በተቸበት በዚያ “ዝነኛ” ጽሑፉ ላይ እንዲህ ይላል፡- 

“…ማንንም ሰው የኢትዮጵያውያን ቋንቋ ምንድን ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የኢትዮጵያውያን ሙዚቃ የቱ ነው ብላችሁ 
ጠይቁ፤ የኢትዮጵያውያን ባሕል የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ ብሔራዊ ልብሳችሁ የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የአማራ 
ወይም የትግሬ ይላችኋል፡፡” 

 ይህ ሀቲት በወቅቱ በአብዛኛው ተማሪ ዘንድ ቁጣ ከመቀስቀሱም በላይ ዋለልኝን በ‹ፀረ-አማራና ትግሬነት› አስፈርጆ 
ለውግዘት ዳርጎት ነበር፡፡ እራሱም ቢሆን በአንድ የዩንቨርስቲው መድረክ ላይ የተሰነዘረበት ከባድ ተቃውሞ በፈጠረበት 
ብስጭት ‹‹እኔም አማራ ነኝ፤ ያውም ከአማራ ሳይንት-ቦረና›› ማለቱ ይታወሳል (ቦረና በተለምዶ አማራ መጥቶበታል 
የሚባለው አካባቢ መሆኑን ልብ ይሏል)፡፡ ግና፣ ዋናው ጥያቄ የእርሱ አማራ መሆን ያለመሆን አይደለም፤ እዚህ ድምዳሜ ላይ 
የደረሰበት ምክንያት ከተጨባጩ እውነታ ጋ ምን ያህል ይዛመዳል? የሚል ነው፡፡ ሌላው ነገር ደግሞ ከዚህ ጽሑፍ በፊት 
ብሔር ተኮር ጎዳዮችን አንስቶ ካለማወቁም በዘለለ፣ ሌሎች ሲያነሱ ፅንፈኛ ተቃዋሚ ስለነበረ ነው፡፡ ለምሳሌ ተማሪ ኢብሳ 
ጉተማ (ኋላ ላይ የኦነግ መስራችና አመራር የሆነው) ‹‹ኢትዮጵያዊ ማነው?›› በሚል ርዕስ ባቀረበው ግጥም እጅግ ተናድዶ 
‹‹እንዴት እንዲህ አይነት ግጥም ታቀርባለህ? ዘረኛ ነህ፤ ኢትዮጵያውያንን የመከፋፍል ዓላማ ነው ያለህ?›› በማለት 
እስከመቃወም መድረሱ የክርክሩ አንዱ ጭብጥ ነው፡፡ 

 ታዲያ ዋለልኝ መኮንን ድንገት እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው ከምን የተነሳ ይሆን? በርግጥ ለዚህ ድንገቴ የአቋም ለውጥ ሶስት 
መላ-ምቶች ሲነገሩ ቆይተዋል፡፡ የመጀመሪያው ‹በአፄው ሥርዓት ላይ አሴረዋል› ተብለው ከተከሰሱትና ‹ኦሮሞ እየተጨቆነ 
ነው› የሚል እምነት ከነበራቸው ጄነራል ታደሰ ብሩ ጋር በታሰረበት ወቅት፣ በጄነራሉ ስብከት አመለካከቱ ተቀይሮ ሊሆን 
ይችላል የሚለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ‹‹መገንጠልን መደገፍ በመጨረሻ የማትገነጠል ሀገር እንድትኖር ያደርጋል›› 
በማለት ከተከራከረበት ከራሱ አቋም ጋር የሚያያዝ ነው፤ ሶስተኛው ‹የሻዕቢያ (ኤርትራውያን ተማሪዎች) አሊያም የአሜሪካኑ 
የስለላ ተቋም (ሲ.አይ.ኤ) መጠቀሚያ ሆኖ ነው› የሚሉት ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ይሁንና ከዋለልኝ ጀርባ ‹ስውር እጅ›ን ለመፈለግ 
ያስገደደው በጊዜው ብዙሁ ተማሪ ለሀገሪቱ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ‹የንጉሣዊው አስተዳደር ኋላቀርነት እና ስግብግበነት ነው› ብሎ 
ከማመኑም ባለፈ፣ ከፌዴራላዊ ይልቅ የቻይና ኮሙኒስታዊ ሥርዓት አድናቂ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የተማሪውን 
እንቅስቃሴ በመምራት በዘመኑ ከዋለልኝ የላቀ ተሰሚነት የነበረው ጥላሁን ግዛው ‹‹ጎሰኝነትን›› በአደባባይ አጥብቆ ይቃወም 
እንደነበረ፣ በ1968 እ.ኤ.አ የታተመው ‹‹Struggle›› ቅፅ 3፣ ቁጥር 1 መጽሔት ጋር ያደረገውን ቃለ-መጠይቅ መጥቀስ 
ይቻላል፡- 

‹‹በመጀመሪያ ደረጃ በጎሰኝነትና በሶሻሊዝም መካከል ያለውን ልዩነት ማሳየት እፈልጋለሁ፡፡ ጎሠኝነት በተወሰነ አካባቢ ብቻ 
የሚቀርና አካባቢ ቀመስ ነው፡፡ ሶሻሊዝም ግን ዓለም ዓቀፋዊ ነው፡፡ …እንደ ዩንቨርስቲ ተማሪነታችንና እንደ እጩ 
ምሁርነታችን የሕብረተሰባችንን አቋም ከመደብ አንፃር መተንተን እንጂ በጎሣ መከፋፈል አይገባም›› ማለቱ ይታወሳልና፡፡ 

የህወሓት-ውልደት 

Monday, May 12, 2014

በሜይ 8, 2014 በኦስሎ ከተማ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ

ሜይ 8, 2014
ሔለን ንጉሴ/ኖርዌ

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ተወላጆች ህፃናትን ጨምሮ በንፁሃን ዜጎች ላይ የፈፀመውን ግድያ በመቃወም በሜይ 8, 2014 በኦስሎ ከተማ ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ።


የዚህ ተቃውሞ ሰልፍ ዋና አላማ ህገመንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን ባቀረቡ ወገኖች ላይ የወያኔ መንግስት ምላሹ ጥይት መሆኑና ከ40 በላይ ሰዎች ህፃናትንና ተማሪዎችን ጨምሮ ጭካኔ በተሞላበት በጥይት ደብድቦ መግደሉ ነው። ይህ ደግሞ ዛሬ በኦሮሞ ህዝቦች ላይ ብቻ የተፈፀመ ሳይሆን ከዚህም በፊት በአማራ ህዝብ ላይ በበደኖና በአርባጉጉ እንዲሁም በአኙዋክ ህዝቦች ላይ የጅምላ ግድያ የተፈፀመ በመሆኑ ይህንን ግፍ በመቃወም የተደረገ ሰልፍ ነበር። 


ዝግጅቱ በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 15፡00 ለሞቱት ወገኖቻችን የህሊና ፀሎት በማድረግ የተጀመረ ሲሆን ሰልፉም በተለያዩ መፈክሮችና በኢትዮጵያ ባንዲራ ያሸበረቀ ነበር። ኢትዮጵያውያኑም በወገኖቻችው ላይ የደረሰውን ግፍ በመቃወም በቁጣና በእልህ መፈክሮችን እየተቀባበሉ በአደባባይ ሲያሰሙ ውለዋል። የሰልፉ መጠናቀቂያ ስፍራ በሆነው በኖርዌጅያን ፓርላማ ፊት ለፊት ከተለያዩ ድርጅቶች የተወከሉ ተናጋሪዎች ወያኔ በህዝባችን ላይ እየፈፀመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ግድያን ጨምሮ ሲያወግዙና ሲኮንኑ ተሰምተዋል። በስፍራውም የኖርዌጅያን ፓርላማ ተወካይ በሰልፉ መሃል በመገኘት ድብዳቤያችንን ተቀብለው ለፓርላማ ለውውይት እንደሚቀርቡ ተናግረዋል። ሰልፈኛውም ኖርዌ በልማት ስም ለወያኔ የምትለግሰው ገንዘብ ህዝብ ለመጨቆኛና ለማፈኛ እንዲሁም የሰው ህይወት ማጥፊያ በመሆኑ የሚሰጠው እርዳታ እንዲቆም ጥያቄ አቅርበዋል።

በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ሊቀመንበር የማጠቃለያ ንግግር ሲያሰሙ ወያኔ በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ድርጅታቸው የሚያወግዘው መሆኑን የሚገልፅ የአቋም መግለጫ በማቅረብና ለሞቱ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተው የታሰሩ የኦሮሞ ተማሪዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱና ይህንን ድርጊት የፈፀሙ አምባገነኖች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀው ስብሰባው በተያዘለት ሰአት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።




ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

Sunday, May 11, 2014

ማርች 11, 2014 በተደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተደረገ ንግግር

ማርች 11, 2014
ሄለን ንጉሴ

ዛሬ እዚህ የሰላማዊ ሰልፍ እያደረግን የምንጮህው ዋናው ዓላማ የወያኔ ቡድን በሃገር ቤት እያደረገ ያለው አፈናና ጭቆና እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥሰት ሳያንሰው ድንበር ተሻግሮ በስደት በምንኖርበት ምድር የስለላ መረቡን ዘርግቶ እየሰለለ የሚገኝ በመሆኑ በኖርዌ የሚገኙ የወያኔ ሰላዮችን መቃወምና ነው።

ሐገራችን ኢትዮጵያ በወያኔ የጭቆና አገዛዝ ስር ከወደቀችበት ጊዜ አንስቶ ህዝቦችዋ ሆን ተብሎ በዘር በሃይማኖት እንዲከፋፈሉ ተደርገዋል፣ ለድህነትና፣ ለጉስቁልና ተዳርገዋል፣ የተማሩና ሃገር ማስተዳደር የሚችሉ ምሁሮቻችን ሃገር ለቀው እንዲሰደዱ ተደርገዋል፣ ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እንዲሁም ግለሰቦች የመናገርና የመፃፍ መብታቸው ተነፍገው በአሸባሪነት እየተፈረጁ በየእስርቤቱ እየተንገላቱ ይገኛሉ። ወጣት ሴት እህቶቻችን በፓለቲካ አመለካከታቸውና በመቃወማቸው በየጊዜ ይታሰራሉ። ይህ አልበቃ ብሏቸው የሐገራችን ህዝብ የሚበላው አጥቶ በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ እንዲሁም ሃገራችን መናጢ ደሃ ከሚባሉት ሃገሮች ተርታ ተደርድራ እያለች ወያኔ የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የሐገሪቷን አንጡራ ሃብት በመዝረፍ ከፍተኛ የሆነ ውስብስብ የስለሳ ሶፍትዌር ከዌስተርና ከሌሎችም ሃገራት በመግዛት የተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎችን እና ነፃ የሚዲያ ተቋማትን ሳይቀር በከፍተኛ ደረጃ በማሰለል ስራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል።  

ወያኔ ድንበር ዘለል ስለላውን በሶፍት ዌር ብቻ ሳይሆን ሰላዮችን በየሃገራቱ በማሰማራት በዲያስፖራ የምንኖር ተቃዋሚዎችን እያሰለለ ይገኛል። እዚህ በምንኖርበት በኖርዌ ምድር ላይ እንኳን በርካታ ጀሌዎቹን በማሰማራት በሃገራችን እንዲመጣ የምንፈልገውን የዲሞክራሲያዊ ትግል እንቅስቃሴ እንድናቆም በማስፈራራት በየሶሻል ሚዲያዎች እና በስልክም በአካልም ጭምር ሳይቀር ለማስፈራራት ይሞክራሉ ፎቶ ግራፎችን እና ቪዲዮዎችን እያነሱ መረጃ እንደሚያስተላልፉ እኛ ፈጥረን የምናወራው ሳይሆን የኖርዌ የደህንነት ክፍል ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎች በኖርዌ እንደሚሰለሉና ወያኔ በኖርዌ ሰላዮች እንዳሉት መረጃው እንዳላቸው በ2011 ዓመተ ምህረት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በቅርቡም ይህንኑ በማጠናከር የኖርዌ ትልቁ ጋዜጣ እንዲሁም በተጨማሪ የሂውማን ራይትስ ዋች በ2014 ባወጣው ሪፖርት ወያኔ ተቃዋሚዎችን እንደሚሰልል መረጃ እንዳላቸው አጋልጠዋ።

ይህ የሚያሳየው ወያኔ ምን ያህል የተቃዋሚ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ሰጋት ውስጥ እንደከተተው ነው። በመሆኑም እኛም የተቃዋሚ ድርጅቶች ወያኔ እኛን እንደሚሰልለን ሁሉ እኛም በልጠን በመገኘት መሰለልና ክፉ ስራቸውን በማጋለጥ መረጃ ከነርሱ መንጠቅ  መቻል አለብን ትግላችን ውጤት እንደሚያመጣ ሳንጠራጠር በአላማችን ፀንተን እስከመጨረሻው መቀጠል እንዳለብንና ወያኔን ማሸነፍ እንደምንችል የነሱ ፍርሃት ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል።

ባጠቃላይ የሐገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በምናይበት ጊዜ የህዝቡ ኑሮ ከእለት ወደ እለት እያሽቆለቆለ በልቶ ለማደር ከፍተኛ ችግር ውስጥ በመግባቱ እናቶች ልጆቻቸውን ለማሳደግ በልመና ስራ ተሰማርተዋል በሃገሪቱ ላይ መብራት የለም፣ ውሃ የለም፣ መንገድ የለም፣ ትራንስፖርት የለም፣ ኔትወርክ የለም ስራ የለም እጅግ በጣም ብዙ ነገር የለም እንግዲህ በትንሹ ሰዎች ለመኖር የሚያስችላቸው መሰረታዊ ፍላጎቶች ባልተሟሉበት ሁኔታ በሐገሪቱ ውስጥ መንግስት አለ ለማለት አይቻልም አለ ቢባልም እንኳን የዚህ አይነቱ አስተዳደር የተበላሸ በመሆኑ ወይም ለሐገር እድገት የማይጠቅም ስለሆነ ስርአቱ ለውጥ ያስፈልገዋል ባጠቃላይ ሃገሪቱን የሚያስተዳድሩት የወያኔ አምባገነኖች ማስተዳደር እንዳልቻሉና ብቃቱ እንደሌላቸው የሚያሳይ በመሆኑ በቃ ልንላቸው ይገባል።

በመጨረሻም ለማለት የምፈልገው ወያኔ እዚህ በስደት የምንኖርበት ድረስ ሰላዮቹን ልኮ በመሰለሉ ማናችንም ልንፈራ  አይገባንም ደግሞም አንፈራም ስለላን ለወያኔ ብቻ የሰጠው ማን ነው እኛስ ለምን አንሰልላቸውም ይሄ ሁሉ የሚያሳየው የተቃዊሚዎች መጠንከር ወያኔን ያብረከርከዋል እና ሁላችንም በአንድነት በሃገራችን ፍትሃዊ አስተዳደር እስከምናመጣ ሙሉ ሃይላችንን ተጠቅመን የሃገራችን ጠላት የሆነውን ወያኔን ለመጣል እንነሳ እላለሁ እኔ የመጣሁ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት የሴቶች ክፍልን ወክዬ በመሆኑ ሴቶች በዚህ ትግል ውስጥ እያበረከትን ያለነው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ በሐገራችን ዲሞክራሲያዊ መንግስት ለመመስረት እና የህግ የበላይነት እንዲከበር እንዲሁም የዜጎች እኩልነትና መብት እንዲረጋገጥ በሚደረገው ሁለ ገብ ትግል ሁሉ የሃገራችን ጉዳይ ከማንም በላይ ያገባናልና እንታገላለን እላለሁ።

እግዚአብሄር ሐገራችንን ይባርክልን

አመሰግናለሁ

Tuesday, May 6, 2014

Mr. Secretary where is this man?

John Kerry's picture with Ethiopian blogger Nathaniel Feleke
John Kerry with Nathaniel Feleke one of arrested Zone –nine bloggers
Mr. Secretary, last year when you went to Ethiopia, for the 50th anniversary of the OAU/AU, many Ethiopians including myself expected that your stay in Addis Ababa (other than the jubilee celebration) will include important issues such as human right abuse, torture, freedom, democracy and good governance in Ethiopia. In fact, most of us wanted to see you voice your disagreement with the dreadful human rights record of Ethiopia, or at least rebuke Ethiopia’s dictators whom your department annual report depicts as enemies of liberty, justice and democracy year after year. Mr. Secretary, I remember, in your speech to the AU leaders, you said the following words:
The United States joins with so many other nations – the Secretary General, Russia, many other friends that are here – all to applaud the remarkable accomplishments, to work together and solve peace, security challenges, trade, defense, democracy, good governance, and human rights
Mr. Secretary, when I read your government’s promise of working together with others to solve peace, democracy, good governance, and human rights challenges in Africa, I was elated and my expectation grew by the day because I know for sure these are the problems that plagued my native country Ethiopia. In May 2013, I was also moved when I saw your , one of the founders of the renowned Zone –nine bloggers. Mr. Secretary, last week when you went back to Ethiopia, Nathaniel Feleke whom you gave a big hug with chanting smile was being tortured inside the notorious Makelawi prison.
Mr. Secretary, a week ago, a journalist who actually happens to be a friend of Nathaniel Feleke asked you the following very important question: Is your concern about press freedom real or “just lip service” Here is how you addressed the question: “I make clear to Ethiopian officials that they need to create greater opportunities for citizens. To be able to engage with their fellow citizens and with their government by opening up more space for civil society. And we shouldn’t use the anti-terrorism proclamations as mechanisms to be able to curb the free exchange of ideas” Well, Mr. Secretary, if this is not lip service then what? Besides, what about if the Ethiopian officials are not willing to create greater opportunities for citizens, and instead they keep on arresting and killing innocent citizens like they have been doing since 1991?
Mr. Secretary, a week before your recent visit to Ethiopia started, the Ethiopian regime arrested Blue Party leaders and members. As if this was not enough, just days before your scheduled arrival to Addis, Ethiopia arrested journalists and bloggers, and on April 30 2014 when you were in Addis, the regime killed more than 30 demonstrators and wounded and arrested undetermined number peaceful demonstrators. Mr. Secretary, I still have to hear your public statement on this “In your face” act of the Ethiopian regime that your government has been baby-sitting for more than two decades?
Mr. Secretary, the US government has always been the first to condemn indiscriminate killings by totalitarian regimes around the globe for a long time. In addition to this, the department you lead (the US Department of State), has exposed dictators and human rights violators through its annual human rights reports. But, the US government has abnormally been silent when the TPLF regime has been killing peaceful citizens throughout its twenty two years stay in power. I wonder how many Ethiopians should die before the US government goes beyond publishing annual reports and starts condemning and holding responsible the killing machine in Addis Ababa!
Mr. Secretary, the most recent killing in Ethiopia that ended the life of more than 30 innocent people took place while you were in Addis having good time with the very people that ordered the killing. Millions of Ethiopians who thought your visit will bring at least a temporary change of heart were staggered by the savage killing. Mr. Secretary, It is not just the killing that took millions of Ethiopians by surprise, it is the calculated timing of the arrest and the killing immediately before and after you set your foot on the soil of Ethiopia. Mr. Secretary, this is a deliberate move by the TPLF leaders who are seeking a divorce from the US and looking for another partner in Asia.
Mr. Secretary, while the people of Ethiopia were mourning their death, we heard that you met with PM Hailemariam Desalegn and Foreign Minister Tedros Adhanom to discuss efforts to advance peace and democracy in the Horn of Africa. Mr. Secretary, to me this is like teaming up with Cuba to advance democracy in Latin America. It’s also ironic that the United States Secretary of State meets with vicious killers to discuss efforts to advance peace and democracy in the Horn of Africa, in a country where more than thirty people were killed by government forces. I have never seen and I don’t think I would ever see again or hear such insensitivity for a loss of humans, especially from a country that reacts vigorously when animals are mistreated by humans.
I remember, during the 2009 Iranian protest, President Obama condemned the violence against the protesters and said the following two statements that have been travelling around the globe ever since he said them: “It would be wrong for me to be silent” – “The protesters in Iran will be ‘on the right side of history’ ”. Mr. Secretary, does the President’s silence when more than 30 Ethiopians were killed by the Ethiopian regime mean that – it would be right for him to be silent? What about the protesters in Ethiopia? Are they in the wrong side of history?
Dear Mr. Secretary, its geopolitical location, large population size (Christian & Moslem) and diverse ethnicity has made Ethiopia a strategically placed country in the Horn of Africa. If Ethiopia plays its hand wisely, it can be a critical force for good in the region. Unfortunately, ruthless dictatorships that ruled over Ethiopia for the past 23 years have darkened the fate of their own people let alone playing a positive role in democratizing the Horn of Africa.
We believe the relationship between Ethiopia and the United States has to be reconstituted on the basis of shared values of freedom, democracy, and promotion of mutual interests. To realize this, the United, and other democratic countries need a strong democratic partner in the Horn of Africa. The Horn of Africa is a volatile region characterized by political instability, and it is no secret that the TPLF dictators are one of the architects of instability in the Horn of Africa.
Dear Mr. Secretary, from all of its actions, particularly since 2005, it is clear that the TPLF regime has closed all avenues for a peaceful democratic opposition and is determined to stay in power by force including committing the most heinous crimes against its own people. The extra judicial killings in different parts of the country, the 2005 massacre, and the genocide in Gambella are glaring examples of crimes committed by a regime which once was praised as the “Hope” of Africa. Today, it is obvious that Ethiopia’s is not and cannot provide a trusted leadership and the democratic credentials to be a credible partner to the United States and the international community at large. The TPLF regime has become an embarrassment to its own people and to the international community. It is high time for the United States and the international community to embrace change in Ethiopia.
ebini23@yahoo.com

Swiss reject Ethiopia's request to extradite co-pilot

Hailemedhin Abera

Hailemedhin Abera, 30, hijacked an Ethiopian Airlines passenger plane that was on an Addis Ababa-Rome route and landed it safely in the Swiss city, thereby requesting a political asylum. The 202 passengers and crew onboard the Boeing 767 plane were not harmed


The VOA quoted a spokesperson of the Swiss Federal Justice Ministry as saying that criminal proceedings were underway for charges as Ethiopia's. For this reason, the spokesperson said, it was decided not to extradite the person to Ethiopia.

Ethiopia and Swistzerland don't have an extradition treaty.



Monday, May 5, 2014

UN human rights chief condemns crackdown on journalists in Ethiopia


High Commissioner for Human Rights Navi Pillay. UN Photo/Paulo Filgueiras
2 May 2014 – The United Nations human rights chief today condemned the crackdown on journalists in Ethiopia and the increasing restrictions on freedom of opinion and expression in the Horn of Africa nation.
The comments by High Commissioner for Human Rights Navi Pillay follow the recent arrest and detention of six members of the blogging collective Zone Nine and three journalists in the capital, Addis Ababa.
“I am deeply concerned by this recent wave of arrests and the increasing climate of intimidation against journalists and bloggers prevailing in Ethiopia,” she stated in a news release.
The nine people arrested last week remain in custody. On 27 April, they appeared before the Arada Court of First Instance. Although the exact charges against each of them remain unclear, the UN human rights office has received information that they were arrested for “working with foreign human rights organizations and inciting violence through social media to create instability in the country.”
They reportedly are being held incommunicado and some of their family members who tried to bring them food over the weekend were denied access.
Since January 2012, a number of journalists have been convicted under the Anti-terrorism Proclamation to sentences ranging from 5 years to life imprisonment. Two journalists arrested in July 2012 and January 2013 under the same law are currently in detention, awaiting their trial.
“The fight against terrorism cannot serve as an excuse to intimidate and silence journalists, bloggers, human rights activists and members of civil society organizations. And working with foreign human rights organisations cannot be considered a crime,” said the High Commissioner.
“Over the past few years, the space for dissenting voices has been shrinking dramatically in Ethiopia,” she added.
Ms. Pillay stressed that in its efforts to combat terrorism, the Ethiopian Government must comply at all times with its human rights obligations under international law. The country is party to the International Covenant on Civil and Political Rights and the African Charter on Human and Peoples’ Rights, both of which guarantee the right to freedom of expression.
The High Commissioner urged the Ethiopian Government to release all bloggers and journalists currently in detention for simply exercising their right to freedom of expression. She also reiterated her appeal for there to be a review of current anti-terrorism and civil society legislation to ensure its conformity with international human rights standards.
The human rights chief’s call comes on the eve of World Press Freedom Day, observed annually on 3 May. The Day is an opportunity to celebrate the fundamental principles of press freedom; assess the state of press freedom throughout the world; defend the media from attacks on their independence; and pay tribute to journalists who have lost their lives in the line of duty.

News Tracker: past stories on this issue

Sunday, May 4, 2014

የብሶት ፅዋ ሞልቶ ሲገነፍል!!


የሰው ልጅ የብሶቱ መጠን ከጥግ ሲደርስ አዳማጭ፤ አማራጭ ሲያጣ፤ ግራ ሲገባው ሁሉም ነገር ከአቅሙ በላይ ሲሆን ሲያቅተው፤ የብሶቱ ፅዋ ሞልቶ ሲገነፍል የሚያሰማው የመጨረሻ የጣር ድምፅ እሪታ ነው። እሪታ የሰው ልጆች ከፍተኛ በደል ሲፈፀምባቸው የሚያሙት ድምፅ በመሆኑ በቸልታ ሊታይ የማይገባ እጅግ በጣም ከባድና አደገኛ ነገር መሆኑንም እሪታ ሰሚዎቹ ቢያስተውሉና የህዝቡን ድምፅ ቢሰሙ የተሻለ ይሆናል። ሐገራችን ላለፉት ሃያ ሶስት አመታት በአምባገነኖች አገዛዝ ስር በብሶት ሰንሰለት ታስሮ የኖረው ህዝብ ዛሬ ሚያዝያ 26, 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ የእሪታ ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰምቷል የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ!!











በሐገራችን እጅግ በርካታ እሪ የሚያስብሉ ከፍተኛ ችግሮች ያሉ ቢሆንም እንደምሳሌ አድርገን ጥቂቶቹን እንኩዋን ብንወስድ የኑሮ ውድነቱ ከሰዎች አቅም በላይ በመሆኑ እናቶች ልጆቻቸውን መመገብና  ማስተማር ባለመቻላቸው በልመና ስራ ተሰማርተው ይገኛሉ፤ ወያኔ የመብራት አቅርቦት በሃገር ውስጥ ሳያዳርስ ከተሞች መብራት በፈረቃ እያገኙ ለነጅቡቲ የመብራት አቅርቦት ስምምነት ማድረጋቸው በራሱ ለህዝቡ ያለውን ንቀትና ምን ያህል ለሃሪቷ ጥላቻ እንዳላቸው ያስመሰከሩበት ነው። በሌላ በኩል የሰው ልጅ ያለ ውሃ አቅርቦት እንዴት ህይወቱን ይገፋል ብለው እንዳሰቡ ባናውቅም ውሃ በሃገሪቱ ውስጥ የለም ቢኖርም እርሱም እንደ መብራቱ ሁሉ በፈረቃ በአስራ አምስት ቀን አንድ ቀን ወይንም በሳምንት አንድ ቀን እንደሚመጣ ነዋሪዎች ይናገራሉ ውሃ ፍለጋ ሰው ጀሪካን ይዞ ሲንከራተት ቀኑን ሙሉ እንደሚውልና ውሃ ጥበቃ ህዝቡ እንቅልፍ መተኛት እንዳቃተው ይታወቃል ሌላው መንገድና ትራንስፖርት ለአንድ ሃገር እድገት መሰረታዊ ነገሮች ቢሆኑም ገዢው ፓርቲ ያለፕላንና ያለረዢም ጊዜ እቅድ በሚሰራቸው መንገዶችና በሚያፈርሳቸው መንገዶች በልማት ሰበብ ህዝቡ ለመንገድና ለትራንስፖርት ችግር በማጋለጥ እንዲማረር አድርገውታል።

መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ በህገ መንግስቱ በግልፅ ተደንግጎ የተቀመጠ ቢሆንም ገዢው ቡድን እጁን በማስረዘም የሃይማኖት ተቋማቱን ደጅ በመድፈር ጣልቃ እየገባ ካድሬዎቹን በሃይማኖት ተቋማቱ በማሰማራት ክርስቲያን ሙስሊሙን እያሸበረ ይገኛል። ሌላው እጅግ በጣም የሚገርመው ወያኔ ለትምህር የሚሰጠው ዋጋ ዜሮ መሆኑ ነው ዜጎች በከፍተኛ ተቋማት በዮኒቨርሲቲ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው ኮብልስቶን ድንጋይ መንገድ ላይ እንዲያነጥፉ ይገደዳሉ ያው ተምረው የቀን ሰራተኛ ይሆናሉ ማለት ነው ለስርአቱ አባልና ታማኝ እስካልሆኑ ድረስ መማር ዋጋ እንደሌለው እና ስራ የማግኘት እድላቸው ህልም እንደሆነም ተማሪዎቹ ይናገራሉ። የተማረ ሃይል የሃገር ሃብት በሆነበት በዚህ ዘመን ወያኔ በተቃራኒው የተማረ መጥላቱ አለመማሩንና የተማረ ዜጋ በሃገሪቱ እንዳይኖር እያደረገ ያለውን ጥረት ያሳየናል በአንፃሩ የነሱ ልጆች የሚማሩበትን ደግሞ ከሁላችንም የተሰወረ አይደለም ይሄ በዘር ላይ ያተኮረ ፖለቲካ የትም የማያደርስ መሆኑንም ማወቅ አላባቸው።

ሌላውና አደገኛው የሰው ልጆች የመፃፍና ሃሳብን በነፃነት የማንሸራሸር ችሮታ ከመንግስታት የሚሰጥ ስጦታ ወይንም መመሪያ ሳይሆን እንዲሁ በፀጋ ተፈጥሮ  የቸረችን  ልዩ ችሮታችን ነው ወያኔ ይህንን የእግዜር ስጦታ ሳይቀር በመገደብ እኔ የምለውን ብቻ እንደገደል ማሚቱ አስተጋቡልኝ እንጂ እናንተ የምትናገሩትም ሆነ የምታስቡት ሁሉ ወንጀል ነው በማለት የሰዎችን ነፃ አስተሳሰብ የሚያስተናግደው በማእከላዊና በቅሊንጦ፤ በዝዋይ እስርቤቶች ከሆነ አስርተ አመታት ተቆጥረዋል። ሃሳባቸውን በነፃነት በብእር ያሰፈሩ ደግሞ እንዲሁ የመፃፍ መብታቸው ተገድቦ ብዙዎች በየእስርቤቱ እየማቀቁ ይገኛሉ።

በቅርቡ ወጣት የዞን9 ጦማሪያን ስለሚያገባን እንጦምራለን ብለው የሀገራቸውን ጉዳይ ቢጦምሩ በደረሰባቸው የደህንነቶች ወከባና ማስፈራሪያ መጦመራቸውን ለሰባት ወራት ካቆሙ በኋላ እንደገና እንጦምራለን ብለው ብእራቸውን ማንሳታቸውን ባሳወቁ ማግስት ሁሉም ከያሉበት በተመሳሳይ ሰዓት በደህንነቶች ተይዘው ሃገር የማሸበር ስራ እየሰራችሁ ነው ለሁከት እና ለአመፅ ህዝብ እያነሳሳችሁ ነው በሚል ክስ ተመስርቶባቸው አሰነባበታቸው እንዴት እንደሆነ ባናውቅም ከታሰሩ ሰነባብተዋል።

ባጠቃላይ ይህንን ሁሉ ግፍና በደል በጫንቃችን ተሸክመን እሹሩሩ እያልን ለሃያ ሶስት አመታት ስናባብል የኖርን የኢትዮጵያ ልጆች ዛሬ ያጎበጠንን የወያኔ ቀንበር ከላያችን ለማውረድ የእሪታ ቀን አውጀን እሪ ብለን በአደባባይ ድምፃችንን ማሰማቱ ሲያንሰን ነው ሁላችንም የበደሉ ተጋሪዎች በመሆናችን እኛም በያለንበት ለሃገራችን ትንሳኤና መልካም አስተዳደር ለማምጣት በሚደረገው ሰላማዊም ትግልም ሆነ ሁለገብ ትግል በአንድነት በመነሳት አጋርነታችንን ለወገኖቻችን ለማሳየት እና አምባገነኖችን ከሃገራችን ለማስወገድና ለፍርድ ለማቅረብ በሚደረገው ትግል ሁሉ በጋራ እንታገል እያልኩ እኔም ብሶቴን እሪሪሪሪሪሪ በማለት አሰማለሁ እሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪ

ሄለን ንጉሴ/ኖርዌ