ማርች 11, 2014
ሄለን ንጉሴ
ዛሬ እዚህ የሰላማዊ ሰልፍ
እያደረግን የምንጮህው ዋናው ዓላማ የወያኔ ቡድን በሃገር ቤት እያደረገ ያለው አፈናና ጭቆና እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥሰት ሳያንሰው
ድንበር ተሻግሮ በስደት በምንኖርበት ምድር የስለላ መረቡን ዘርግቶ እየሰለለ የሚገኝ በመሆኑ በኖርዌ የሚገኙ የወያኔ ሰላዮችን መቃወምና
ነው።
ሐገራችን ኢትዮጵያ በወያኔ
የጭቆና አገዛዝ ስር ከወደቀችበት ጊዜ አንስቶ ህዝቦችዋ ሆን ተብሎ በዘር በሃይማኖት እንዲከፋፈሉ ተደርገዋል፣ ለድህነትና፣ ለጉስቁልና ተዳርገዋል፣ የተማሩና ሃገር ማስተዳደር የሚችሉ ምሁሮቻችን ሃገር ለቀው እንዲሰደዱ ተደርገዋል፣ ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት
መሪዎች እንዲሁም ግለሰቦች የመናገርና የመፃፍ መብታቸው ተነፍገው በአሸባሪነት እየተፈረጁ በየእስርቤቱ እየተንገላቱ ይገኛሉ። ወጣት
ሴት እህቶቻችን በፓለቲካ አመለካከታቸውና በመቃወማቸው በየጊዜ ይታሰራሉ። ይህ አልበቃ ብሏቸው የሐገራችን ህዝብ የሚበላው አጥቶ
በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ እንዲሁም ሃገራችን መናጢ ደሃ ከሚባሉት ሃገሮች ተርታ ተደርድራ እያለች ወያኔ የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም
በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የሐገሪቷን አንጡራ ሃብት በመዝረፍ ከፍተኛ የሆነ ውስብስብ የስለሳ ሶፍትዌር ከዌስተርና ከሌሎችም ሃገራት
በመግዛት የተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎችን እና ነፃ የሚዲያ ተቋማትን ሳይቀር በከፍተኛ ደረጃ በማሰለል ስራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል።
ወያኔ ድንበር ዘለል ስለላውን በሶፍት ዌር ብቻ ሳይሆን ሰላዮችን በየሃገራቱ
በማሰማራት በዲያስፖራ የምንኖር ተቃዋሚዎችን እያሰለለ ይገኛል። እዚህ በምንኖርበት በኖርዌ ምድር ላይ እንኳን በርካታ ጀሌዎቹን
በማሰማራት በሃገራችን እንዲመጣ የምንፈልገውን የዲሞክራሲያዊ ትግል እንቅስቃሴ እንድናቆም በማስፈራራት በየሶሻል ሚዲያዎች እና በስልክም
በአካልም ጭምር ሳይቀር ለማስፈራራት ይሞክራሉ ፎቶ ግራፎችን እና ቪዲዮዎችን እያነሱ መረጃ እንደሚያስተላልፉ እኛ ፈጥረን የምናወራው
ሳይሆን የኖርዌ የደህንነት ክፍል ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎች በኖርዌ እንደሚሰለሉና ወያኔ በኖርዌ ሰላዮች እንዳሉት መረጃው እንዳላቸው
በ2011 ዓመተ ምህረት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በቅርቡም ይህንኑ በማጠናከር የኖርዌ ትልቁ ጋዜጣ እንዲሁም በተጨማሪ የሂውማን ራይትስ
ዋች በ2014 ባወጣው ሪፖርት ወያኔ ተቃዋሚዎችን እንደሚሰልል መረጃ እንዳላቸው አጋልጠዋ።
ይህ የሚያሳየው ወያኔ ምን
ያህል የተቃዋሚ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ሰጋት ውስጥ እንደከተተው ነው። በመሆኑም እኛም የተቃዋሚ ድርጅቶች ወያኔ እኛን እንደሚሰልለን
ሁሉ እኛም በልጠን በመገኘት መሰለልና ክፉ ስራቸውን በማጋለጥ መረጃ ከነርሱ መንጠቅ መቻል አለብን ትግላችን ውጤት እንደሚያመጣ ሳንጠራጠር በአላማችን ፀንተን
እስከመጨረሻው መቀጠል እንዳለብንና ወያኔን ማሸነፍ እንደምንችል የነሱ ፍርሃት ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል።
ባጠቃላይ የሐገራችንን ወቅታዊ
ሁኔታ በምናይበት ጊዜ የህዝቡ ኑሮ ከእለት ወደ እለት እያሽቆለቆለ በልቶ ለማደር ከፍተኛ ችግር ውስጥ በመግባቱ እናቶች ልጆቻቸውን
ለማሳደግ በልመና ስራ ተሰማርተዋል በሃገሪቱ ላይ መብራት የለም፣ ውሃ የለም፣ መንገድ የለም፣ ትራንስፖርት የለም፣ ኔትወርክ የለም ስራ
የለም እጅግ በጣም ብዙ ነገር የለም እንግዲህ በትንሹ ሰዎች ለመኖር የሚያስችላቸው መሰረታዊ ፍላጎቶች ባልተሟሉበት ሁኔታ በሐገሪቱ
ውስጥ መንግስት አለ ለማለት አይቻልም አለ ቢባልም እንኳን የዚህ አይነቱ አስተዳደር የተበላሸ በመሆኑ ወይም ለሐገር እድገት የማይጠቅም
ስለሆነ ስርአቱ ለውጥ ያስፈልገዋል ባጠቃላይ ሃገሪቱን የሚያስተዳድሩት የወያኔ አምባገነኖች ማስተዳደር እንዳልቻሉና ብቃቱ እንደሌላቸው
የሚያሳይ በመሆኑ በቃ ልንላቸው ይገባል።
በመጨረሻም ለማለት የምፈልገው
ወያኔ እዚህ በስደት የምንኖርበት ድረስ ሰላዮቹን ልኮ በመሰለሉ ማናችንም ልንፈራ አይገባንም ደግሞም አንፈራም ስለላን ለወያኔ ብቻ የሰጠው ማን ነው እኛስ
ለምን አንሰልላቸውም ይሄ ሁሉ የሚያሳየው የተቃዊሚዎች መጠንከር ወያኔን ያብረከርከዋል እና ሁላችንም በአንድነት በሃገራችን ፍትሃዊ
አስተዳደር እስከምናመጣ ሙሉ ሃይላችንን ተጠቅመን የሃገራችን ጠላት የሆነውን ወያኔን ለመጣል እንነሳ እላለሁ እኔ የመጣሁ የዲሞክራሲያዊ
ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት የሴቶች ክፍልን ወክዬ በመሆኑ ሴቶች በዚህ ትግል ውስጥ እያበረከትን ያለነው አስተዋፅኦ ከፍተኛ
በመሆኑ በሐገራችን ዲሞክራሲያዊ መንግስት ለመመስረት እና የህግ የበላይነት እንዲከበር እንዲሁም
የዜጎች እኩልነትና መብት እንዲረጋገጥ በሚደረገው ሁለ ገብ ትግል ሁሉ የሃገራችን ጉዳይ ከማንም በላይ ያገባናልና እንታገላለን እላለሁ።
እግዚአብሄር ሐገራችንን
ይባርክልን
አመሰግናለሁ
No comments:
Post a Comment