Friday, May 23, 2014

ዞን 9 ጦማሪያን ይፈቱ/Free Zone 9 Bloggers



ዞን 9 ጦማሪያን ስለሃገራችን ያገባናል እንፅፋለን ብለው ብእርን መሳሪያቸው አድርገው እውነተኛ መረጃ በማሰራጨት ተግተው የሚሰሩ ከመፃፍ ውጪ ምንም ወንጀል ያልፈፀሙ የነገ ሃገር ተረካቢ ወጣቶች ናቸው። አምባገነኑ የወያኔ ስርአት የተማረና ስለ ሃገሬ ያገባኛል እውነቱ ይህ ነው ለምን ይዋሻል ብሎ እውነት የተናገረንና የፃፈን ሁሉ እንደአሸባሪ እየቆጠረ በየእስርቤቱ  እየከተተ ማሰቃየቱን ተያይዞታል። ሰዎች ሃሳባቸውን በነፃ መግለፅ ህገ መንግስታዊ መብታቸው ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊ መብታቸው መሆኑን የዘነጋው ወያኔ ዛሬ የዞን 9 ጦማሪያንን በመፃፋቸው ብቻ ሐገር እያሸበሩ ነው በሚል በአሸባሪነት ወንጀል በሐሰት ለመክሰስ ከላይ እታች እያለ ይገኛል።


ዞን 9 ጦማሪያን ያለምንም ወንጀል ዛሬም በእስር እየተሰቃየሚገኙ ቢሆንም የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችን ጨምሮ አለም ለእነኚ ወጣት ጦማሪያን ድምፁን እያሰማ ይገኛል እኛም ኢትዮጵያውያን በያለንበት ሁሉ ድፃችንን በማሰማት ከጎናቸው መቆም ይኖርብናል። አምባገነኑ ወያኔ እስከመቼ እያሰረና እየገደለ በሰዎች ስቃይ እያላገጠ እንዲኖር እድል እንደምንሰጠው ባይገባኝም ለነፃነት የሚደረገው ትግል ግን መፍጠን እንዳለበት ይሰማኛል። ሁላችንም ሃይላችንን ተጠቅመንን ይህንን መጥፎ ስርአት ከሐገራችን ማስወገድ ካልቻልን ማንም ሰው ሀሳቡን በነፃ መናገር ቀርቶ አየር በነፃ ለመተንፈስ መከልከላችን የማይቀር ነው።

የዞን 9 ጦማሪያን እና ሌሎች የፓለቲካና የህሊና እስረኞችን መታሰርን አጥብቄ እቃወማለሁ የዞን 9 ጦማሪያን በአስቸኳይ እንዲፈቱም ወያኔን እጠያቃለሁ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ሄለን ንጉሴ

No comments:

Post a Comment