Monday, March 17, 2014

አልቀይዳ ወደ ፊት ከሚያጠቃቸው ሀገሮች ዝርዝር ወስጥ ኢትዮጵያን አካተተ




Ethiopia included in al Qaeda's next target: terror organization's ...








ልቀይዳ ወደ ፊት ከሚያጠቃቸው ሀገሮች ዝርዝር ወስጥ ኢትዮጵያን ማካተቱን የሽብር ድርጅቱ በሚያሳትመው ኢንስፓየር መፅ ሔት ገለፀ።

የአሜሪካው abc ዜና አውታር እንደዘገበው በአልቀይዳ በሚታተመው መፅሔት ባለፈው መስከረም በ ኬንያ እና በ 2010 በአዑጋንዳ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት በማስምልከት ከሁለቱ ሀገሮች ስም አጠገብ ምልክት (ቼክ ማርክ) አድርገዋል።
ይህም የጥቃት እቅዳቸውን ማሳካታቸውን ለማመላከት ይሆናል ተብሏል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ጅቡቲን፣ቡሩንዲ እና ሴራልዮን ስም አጠገብ ደግሞ ምልክት አለማድረጋቸው ወደፊት የአልቀይዳ ጥቃት ኢላማ ውስጥ መግባታቸውን ማመላከቻ ሊሆን ይችላል ተብሏል።
ከዚህ ሌላ መፅሔቱ በዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ለተገደሉት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው አባሎቹ ሰፊ ሽፋን ሰጥቷል። እንዴት በቤት ወስጥ ቦምብ መስራት እንደሚቻል እና በአሜሪካ የሚኖሩ ሰዎችን ማጥቃት እንደሚቻል መመሪያ ማውጣቱን የአሜሪካ የሽብር-አፀፋ መላሽ ክፍል ኃላፊ ለabc ዜና አውታር ተናግረዋል።



No comments:

Post a Comment