የተፈናቃዮቹ ድምፅ
 |
የተፈናቃዮቹ ድምፅ |
የአማራ ተወላጆች ዛሬም ተሰደው በአንድነት ፓርቲ ፅህፈት ቤት ይገኛሉ። በአምቦ ከአስራ ዘጠኝ ዓመታት በላይ ከኖሩበት ምድር ልጆች ወልደው ካሳደጉበት ሃብት ንብረት ካፈሩበት ምድር መንግስት ሆን ብሎ ሽብር በማስነሳት በገጀራና በዱላ እየተደበዱ ህይወታቸውን እስከማጣት ድረስ ደርሰዋል የአማራ ተወላጅ በመሆናቸው ብቻ ግፍ እየተፈፀመባቸው ይገኛል ክልሉ የናንተ አይደለም ወደ ክልላችሁ ሂዱ በሚል ሰበብ የዜግነት መብታቸው እየተነፈጉ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየደረሳባቸው ይገኛሉ። እነዚሁ ተፈናቃዮች ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ጀምሮ በተዋረድ ላሉ ባለስልጣናት ችግራቸውን ቢያስረዱም ምንም አይነት መፍትሄ ባለማግኘታቸው የሚሰሩ እጆች ምፅዋተኛ ለመሆን ተገደዋል ኧረ ጎበዝ ምን ይሻላል መላ እንበል ሙሉውን ለመከታተል እዚህ ሊንኩን ያጫኑ
No comments:
Post a Comment