Monday, October 28, 2013

ኢህአዴግ የዘራውን አጨደ፣ ተጠያቂው ማን ነው?


እሳት አስነሳችሁ በሚል እስሩ ቀጥሏል

fire
በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ተቃውሞ ቢያቀርቡም የኢህአዴግን ጆሮ ማግኘት ያልቻሉ ተበዳዮች ርምጃ ወሰዱ። ሕዝብ ወዶና ፈቅዶ ያልተቀበለው ኢንቨስትመንት ከዘረፋ ተለይቶ እንደማይታይ የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል። ውድመት የደረሰበት የህንድ ኩባንያ በልማት ባንክ ላይ ኪሳራ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋት አለ። ለደረሰው ጉዳት “ተጠያቂው ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ተነስቷል። በጥርጣሬ የሚታሰሩ መበራከታቸው በክልሉ ባሉ ተመሳሳይ የእርሻ ኢንቨስትመንት ባለቤቶችን ስጋት ላይ ጥሏል።
ሻይ ቅጠል ለማልማት የተፈጥሮ ጥብቅ ደን እንዲያወድም የተፈቀደለት ቬርዳንታ ሀርቨስት የተባለ ኩባንያ በከፍተኛ ወጪ ያለማውና ለመለቀም በደረሰ ምርት ላይ ማንነታቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች እሳት ለቀውበታል። ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓም ደረሰ በተባለው ቃጠሎ ኩባንያው የደረሰበት ሊሳራ እስከ 80 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ አስታውቀዋል።
አንጋፋ እድሜ ጠገብና ረዣዥም የተፈጥሮ ደን በመጨፍጨፍ ጣውላ እያመረተ ሲቸበችብ የነበረው ኩባንያ ሙሉ ንብረቱና ከፍተኛ መጠን ያለው የጣውላ ምርት ከተለያዩ ማሽኖች ጋር ወድሞበታል። የአካባቢው የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ኩባንያው ላይ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ ለመሰብሰብ የደረሰውን የሻይ ቅጠል ማሳ አጋይቶታል።
በጋምቤላ ክልል በመዠንግር ዞን፣ በጎደሬ ወረዳ በጉማሬና በካቦ ቀበሌዎች የሚገኝ 5000 ሄክታር በደን የተሸፈነ መሬት በኢንቨስትመንት ስም እንዲሸጥ መወሰኑን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ አሰምተው ነበር። በወቅቱ ውሳኔውን “በባዕድ ወራሪ ሃይል እንኳን የማይፈጸም” በማለት የተቹና ቅሬታቸውን የገለጹ ነበሩ።
ሙሉ በሙሉ በደን የተሸፈነ 3012 ሄክታር ድንግል ለም መሬት በሄክታር111 ብር ሂሳብ ለ50 ዓመት የሊዝ ኮንትራት የተሸጠለት ይህ ኩባንያ ጥብቅ ደኑን ከማውደሙ በፊት ውሳኔው እንዲጤን የአካባቢው ህዝብ በወኪሎቹ አማካይነት ለፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ጥያቄ አቀርበው ነበር። በወቅቱ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ድርጊቱን በመቃወም የሚከተለውን ጽሁፍ አትሞ ነበር። ሰሚ ባለመገኘቱ የተፈራው ደረሰ።
ጡረተኛው ፕሬዚዳንት ለአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የተፈጥሮ ደኑ ከመጨፍጨፉ በፊት ውሳኔው እንዲመረመርና እንዲጠና ሚያዚያ 28 ቀን 2002 ዓ ም ለክልሉ ደብዳቤ ልኮ ነበር። ሟቹ ጠ/ሚኒስትር በወቅቱ የአፍሪካ የተፈጥሮ ጥበቃና የአየር ንብረት ተሟጋች ነኝ ያሉበት ወቅት መሆኑንን በማስታወስ፣ የፕሬዚዳንቱን መመሪያ በመጠቆም ባለስልጣኑ የጻፈውን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የክልሉ ፕሬዚዳንት ህዳር 10 ቀን በተጻፈ ደብዳቤ ደመሰሱት። ከላይ የተጠቀሰው ኩባንያ የ50 ዓመቱን ውል ቅድሚያ ክፍያ የአንድ ዓመት 19 ሺህ ዶላር ስለከፈለ ቦታውን እንዲረከብ ዞኑንን አዘዙ።
የበላይና የበታቹ በማይታወቅበት የመለስ አወቃቀር ጥብቅ ደኑ ያለበት መሬት ለህንዱ ኩባንያ ተላለፈ። ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ እስከ ፕሬዚዳንቱ ያደረሱት ሊቀመንበር እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረው ከሃላፊነታቸው ተባረሩ። ህዝብ የኑሮው መሰረትና የህይወቱ ያህል የሚንከባከበው ደን ተጨፈጨፈ። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ደኑ ሲጨፈጨፍ የነበረው ሃዘን በቃል የሚገለጽ አልነበረም።timber log
ባገኘው ከፍተኛ የደን ምርት ጣውላ ማምረት የጀመረው ኩባንያ መጋዘን ገንብቶ የጣውላ ንግድ ውስጥ ገባ። አሁን ድረስ ንዴቱና የበደል ስሜቱ ያለቀቀቃቸው የአካባቢው ነዋሪዎች የተካሄደባቸውን ግፍ “ዝርፊያ” እያሉ ነው የሚጠሩት።
ህግን ጠብቀው ኢህአዴግን ያሳሰቡት የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም ቢሆን በእስርና በድብደባ በማሰቃየት ኢንቨስትመንትን /ነዋሪዎቹ ዝርፊያ ነው የሚሉት/ በክልሉ ቀጣይ ማድረግ አይቻልም። አስቀድሞ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ኢህአዴግና ኩባንያው ጆሮ ሰጥተዋቸው ቢሆን ኖሮ እንዲህ ያለ አደጋ ሊፈጠር እንደማይችል አስተያየት ሰጡ አሉ።
92 ሚሊዮን ብር በላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እዳ ያለበት የእርሻ ድርጅት፣ ንብረቱ በእሳት ከወደመ በኋላ የተሸከመው እዳ አጀንዳ ሆኗል። የደረሰበት ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ክልሉንና ኢህአዴግን ካሳ እንደሚጠይቅም ከወዲሁ ተሰምቷል። ዜናውን ያቀበሉ ክፍሎች “ህዝብ ላልተቀበለው ኢንቨስትመንት ካሳና የልማት ባንክ ላይ ለደረሰው ኪሳራ ተጠያቂው ኢህአዴግ ነው” የሚል ጥያቄ መነሳቱን አመልክተዋል።
ለአበባ እርሻ ላስቲክና ኬሚካል በማስያዝ ልማት ባንክን እያለቡ የተሰወሩ በርካታ ድርጅቶችና ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው ሸሪኮቻቸው መኖራቸውን በማስታወስ በጋምቤላ ተመሳሳይ ድርጊት ሊፈጸም እንደሚችል የዜናው ምንጮች ጠቁመዋል። ካራቱሪ በኪሳራ መንገዳገዱን፣ ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በ”ውክልና” ለሳዑዲ አረቢያ ቀለብ እንዲያመርት የተከሉት ሳዑዲ ስታርና ሌሎች የህወሃት ሰዎች ከተለያዩ የአገር ውስጥ ባንኮች ከፍተኛ ገንዘብ መበደራቸውን ገልጸዋል።
“ህዝብን ያለፈቃዱ በማፈናቀልና መሬቱን በመቀማት የሚከናወን ኢንቨስትመንት ሁሌም አደጋ ላይ መሆኑ አያጠራጥርም” በማለት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አኢጋን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ለጎልጉል ገልጸዋል። “ኢንቨስትመንት እንኳን ደህና መጣህ በሚል ህዝብ ካልተቀበለው ዘረፋ ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ “በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ ድምጹን ሲያሰማ ጆሮ ያጣ ህዝብ ተቃውሞውን ገለጸ” በማለት በደረሰው ውድመት ባይደሰቱም ለውድመቱ ተጠያቂው ኢህአዴግና ከኢህአዴግ ጋር ተሻርኮ ዝርፊያ ያከናወነው ድርጅት እንደሆነ አመልክተዋል።
ካሩቱሪና ሳዑዲ ስታርን ጨምሮ ህዝብ ላይ በተፈጸመ ግፍ ሃብት ለማፍራትና ለመበልጸግ የሚያስቡ ትልቅ ግንዛቤ ሊወስዱ እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ኦባንግ “ኢህአዴግ ዝርፊያና ኢንቨስትመንትን ለይቶ መሔድ ካልቻለ ስጋቱ እየጨመረ ይሄዳልና ከስህተት በመመለስ ህዝብ በሚፈቅደው መልኩ ማስተናገድ ግድ ነው” ሲሉ አሁንም ጆሮ የለውም ለሚባለው ኢህአዴግ ማሳሰቢያ አዘል ምክር ለግሰዋል። ባለሃብት የሚባሉትም ከዚህ ታላቅና አሳዛኝ ውድመት ሊማሩና ህዝብ “እንኳን ደህና መጣችሁ እንዲላቸው ህዝብ ከሚቃወመው ዝርፊያና አሰራር ራሳቸውን ሊያገሉ ይገባል” ብለዋል።
የክልሉ ፕሬዚዳንት ቃጠሎውን ማመናቸውን ሪፖርተር በእሁድ እትሙ ያስታወቀ ሲሆን አጣሪ ኮሚቴ ተቃቁሞ አደጋውን ያደረሱት እነማን ናቸው የሚለው እየተመረመረ እንደሆነ ጠቁሟል። የክልሉ የጎልጉል ምንጮች በርካታ ሰዎች እሳት አስነስታችኋል በሚል መታሰራቸውና በፌዴራል አንጋቾች እየተመረመሩ መሆኑን አረጋግጠዋል። እሳት ያስነሱትን ለማጋለጥ በሚል በየመንደሩ በሚደረግ ማዋከብ ነዋሪዎቹ መማረራቸውን ተናግረዋል። ለጊዜው የእስረኞች ቁጥር ባይታወቅም ወደ ማዕከል የተላኩ በርካታ እንደሆኑም ገልጸዋል። በማያያዝም ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ኢህአዴግም ሆነ ማንም ተጠቃሚ ስለማይሆን ህዝብን ማዳመጥ ሊቀድም እንደሚገባው ጠቁመዋል። (ፎቶ፡ ለማሳያነት ብቻ)
ምንጭ ጎልጉል

የአድዋዉ ልጅ አድዋ ገባ” የአርማጭሆ ልጅ የት ይግባ?!! (ናደዉ ከዋሽንግተን ዲሲ)


October 27, 2013

የአድዋዉ ልጅ አድዋ ገባ”

የአርማጭሆ ልጅ የት ይግባ?!!

እንደምን ከረማችሁ ዉድ የኢካዴፍ እድምተኞች “እስቲ ቂማችንን ጥቂት እናቆየዉ” በሚል ርእስ የጀመርኩትን መጣጥፍ “በአሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል” ቀጥዪ ከክፍል 1-7 ድረስ ይህ ድህረ ገፅ ለንባብ አብቅቶልኛል ክፍል 8-9 ግን ከአንድም ሁለቴ በአደራ ደብዳቤ ሳይቀር ልኬ ሚዛን ባለመድፋቱ ለንባብ አልበቃም(የቅርጫት ራት ሆኗል) ሚዛን የሚደፋ ፅሁፍ ለማቅረብ አስቤ ፅሁፎቼን ቆየት ማድረግ በወሰንኩ ማግስት ዛሬ October 24, ምሽት አንድ ወዳጄ ስልክ ደዉሎ ሰበር ዜና ጀባ አለኝ የአዉራምባዉ አምደኛ ተጋዳላይ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወደ ዘረኛ ግብረአበሮቹ ጉያ መሸጎጡን አጫወተኝ ከላይ በጠቀስኩት ርእስ እንደጠቀስኩት ይህ ሰላይ የትግራይ ጉጅሌ መልእክተኛ አዚህ ሰሜን አሜሪካ ኢሳትንና ሌሎች ጠንካራ ናቸዉ የሚባሉትን ተቃዋሚ ድርጅቶች የመሰለል ተልእኮዉን አጠናቅቆና የዳያስፖራዉን ተቃዋሚ ጓዳ ጎድጓዳ ሰልሎ የቃረማቸዉን የኦዲዮ ቪዲዮና ዳጎስ ያለ ጥራዝ ተሸክሞ አሜሪካ በገባበት አኳኋን ተመልሶ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በአራት ኪሎ ቤተመንግስት ገባላችሁ ቡራኬዉንም ተቀብሎ በአዲስ አበባዉ ሸራተን ሆቴል የወሬ ቅራቅምቦዉን ለህወሀት የዜና አዉታሮችና የስለላዉ መረብ ክፍል አለቆቹ እያጋታቸዉ መሆኑን ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ሹክ አሉን።
Dawit-Kebede-Awramba-Times-146x200
እዚህ ያለዉ አጃቢዉ ሆድ አደሩ የስዉር ስለላ መረብ ጓዱ የአርማጭሆዉ ጓዱ ወስላታ የደርግ ካድሬ ምርጫዉ ስንሻዉ ቀሪ የመበታተን አጀንዳቸዉን ለማስፈፀም የመመርያ የኪስ ማስታወሻዉን ዳጎስ ካለ የደም ገንዘብ ጋር ተረክቦ ቀጣይ ጥሪዉን ይጠባበቃል በቅርቡም የህወሃት አባልነት ደብተሩ ከምስጋና ጋር እጁ ይገባል።
ነገ አሱም አይኑን በጨዉ አጥቦ ሚስቱንና ልጆቹን እንደለመደዉ ጥሎ ይከተለዋል እስከዚያዉ በአዲስ መልክ በአዲስ መሠሪ ተልእኰ ራዲዮ ጣቢያ የጥላቻና የጋጠወጥ “ዘለፋ ስንቁ” የመንደር አደግ ራዲዮኑን ያገማናል። እኛም ሃይ አንለዉ እጆቻችንን ጉንጮቻችን ላይ አድርገን የገለማ ቀረርቶዉንና ቱማታዉን እናዳምጥለታለን።

ወገኖቼ ኢትዮጵያዉያን ጨካኝና አምባገነን ገዢዎቻችን አገራችንን ጥለንላቸዉ በስደት የመኖር መብታችንን እየከለከሉን ነዉ። ዛሬም እንደትናንቱ በተመሳሳይ ድራማ ያፌዙብናል። አለቆቼ በድለዉኛል አስጥሉኝ አይነት ቀልድ፥እኛም ቄጠማ ጎዝጉዘን ርችት ተኩሰን እንኳን ወደህሊናችሁ ተመለሳችሁ እንላቸዋለን ጓዳ ጎድጓዳችንን መዝብረዉ አላግጠዉብን ተመልሰዉ ይሄዳሉ። ዛሬም እደግመዋለሁ፦”እስቲ ቂማችንን ጥቂት እናቆየዉ”

Sunday, October 27, 2013

ስሜ ናፈቀኝ



October 23, 2013 at 11:11am
ዕቃ ለማውጣት ቦሌ ወደሚገኘው የካርጎ ተርሚናል ሄጃለሁ፡፡ መቼም ዘመድ ውጭ ሀገርያለው ሰው ደጋግሞ የሚሄደው አንድም ለወዳጁ እድሜ ከጤና ለመለመን ቤተ ክርስቲያን፣ አንድም የተላከለትን ዕቃ ለመውሰድ ካርጎተርሚናል፣ አንድም የዓመት በዓል ብር ለመቀበል ባንክ ቤት ነው፡፡
ወረፋውን ጠብቄ መስኮቱ ጋ ደረስኩና ስሜን አስመዘገብኩ፡፡ እስክትጠራ ጠብቅ ተብዬምወንበር ፈልጌ ተቀመጥኩ፡፡ ከጎኔ አንድ ጎልማሳ ተቀምጦ ይቁነጠነጣል፡፡ አንዴ ፀጉሩን አንዴ ዓይኑን ያሻል፡፡ ኩኩሉ እንደሚልአውራ ዶሮ አንገቱን ከወዘወዘ በኋላ ወደ እኔ ዞር አለና ‹‹ስምህ ናፍቆህ ያውቃል›› አለኝ፡፡

ገረመኝና ‹‹ስሜማ አብሮኝ ነው የሚኖረው፤ ምን ብሎ ይናፍቀኛል›› አልኩት፡፡

‹‹ስምህን ሰጥተህ አታውቅም፤ አሁን ስምህን አልሰጠህም እንዴ›› አለኝ፡፡
ይበልጥ ግራ ገባኝና ‹‹እና ወሰዱት ማለት ነው›› አልኩት ሳቅ እያፈነኝ፡፡

‹‹ታድያስ፤ አሁንኮ ወሳኙ እነርሱ ጋር ያስመዘገብከው ስምህ እንጂ አንተ ጋ ያለውስምህ አይደለም፡፡ አንተ እገሌ መሆንህ ቁም ነገር የለውም፡፡ እነርሱ    ‹እ-ገ-ሌ› ብለው ሲጠሩህ ነው ሕይወትህየሚንቀሳቀሰው፡፡ እኔ አሁን ስሜ ናፍቆኛል፡፡ ስሜ ሲጠራ መስማት፣ ስሜ ሲጠራ አቤት ማለት ናፈቀኝ፡፡››
የእርሱን ስሰማ እኔም ስሜ ይናፍቀኝ ጀመር፡፡ ‹‹ትጠራላችሁ›› አይደል ያሉን፤እውነትም ስማችንን ወስደውታል ማለትኮ ነው፡፡ ካልጠሩን ቁጭ ብለን መቅረታችን ነው፡፡ የተጠሩት ደግሞ እየተፍነከነኩ ወደመስኮቱ እየተጠጉ ነው፡፡ ሰልፉ ሲረዝም፣ ጊዜው ሲሄድ፣ መቀመጥም ሲሰለቻችሁ ደግሞ ስማችሁ ይበልጥ ይናፍቃችኋል፡፡

‹‹እዚህ ብቻ ነው ወይስ ሌላውም ቦታ ወረፋ አለው›› አልኩት፡፡

‹‹ምን እዚህ ብቻ ኑሮህኮ እንደዚሁ ነው፡፡ ስም ትሰጣለህ፣ ትጠብቃለህ፣ ስምህንትናፍቃለህ፣ እድለኛ ከሆንክ ትጠራለህ፣ አቤት ትላለህ፣ ወደ ሌላው ምእራፍ ትሻገራለህ፡፡ እዚያም ስም ትሰጣለህ፣ ስምትናፍቃለህ፣ ትጠራለህ፣ አቤት ትላለህ፣ እንዲህ እያልክ ትኖራለህ፡፡ አቤት ካላልክ ደግሞ ችግር ነው፡፡ ያልፍሃል፡፡ አሁን ያሰውዬ ስልክ እያወራ አለፈው፡፡ ‹አቤት› ማለት ነበረበት፡፡ አሁን እንደገና ስሙ እየናፈቀው ነው፡፡ ያኛው ደግሞ ስሙቢናፍቀው፣ ቢናፍቀው የሚጠራው አጥቷል፡፡እየደጋገመ ‹ጥሩኝ እንጂ› ይላል፡፡‹ቆይ እንጠራሃለን› ይሉታል፡፡ አሁን አንተንበስልክ ጠርተውህ ነው አይደል የመጣኸው? አሁን ይኼ ጋቢ ነገርየለበሰው ሰው ለምን አትጠሩኝም ብሎ ነው ከክፍለ ሀገር የመጣው፡፡ ስሙ ናፍቆት፡፡ ልጁ ደውላ ዕቃ ልኬልሃለሁ አለቺው፡፡ እርሱካሁን አሁን ስሜ በስልክ ይጠራል ብሎ ቢጠብቅ ቀረበት፡፡ ስሙ ሲናፍቀው መጣና ‹እባካችሁ ጥሩኝ› አለ፡፡ እነርሱ ደግሞ‹ሀገርህ ተመለስና ስንጠራህ ትመጣለህ› ይሉታል፡፡ ስሙ የናፈቀው ሰው መች እንዲህ በቀላሉ ይመለሳል፡፡››

‹‹እውነትምኮ ስም የሚያስናፍቁ አሠራሮች ሞልተዋል›› አልኩት ለመጎትጎት

‹‹ቤት ለማግኘት ትመዘገባለህ፣ ስምህ ይናፍቅሃል፡፡ ጋዜጣ ላይ ወጣ፣ ተለጠፈ፣በሬዲዮ ተነገረ በተባለ ቁጥር ስምህን ማየት ትናፍቃለህ፡፡ እዚያ ዝርዝር ውስጥ ስታጣው ቅር ይልሃል፡፡ ስኳር ለማግኘትትመዘገባለህ፣ ከሻሂው ሱስ ይልቅ ስምህን የመስማት ሱስ ይይዝሃል፡፡ ሥራ ለማግኘት ትመዘገባለህ፣ እንጠራሃለን ስትባልትጠብቃለህ፤ ከዚያ ስልክ ባቃጨለ ቁጥር እመር ብለህ ትነሣለህ፤ የሆነ ሰው ስምህን ሲጠራው፣ አንተም አቤት ስትል ለመስማትትናፍቃለህ፡፡ ጓደኛህ ደውሎ በቅጽል ስምህ ከጠራህ ትናደዳለህ፡፡ አንተ የምትጠብቀው ‹አቶ እንትና ነዎት› ተብሎ ሲጠራ መስማትነዋ፡፡ ››

‹‹ቆይ ግን ለምን ይመስልሃል ስማችን እስኪናፍቀን የምንደርሰው››

‹‹አንደኛ ለምዶብናል፡፡ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ስም ጠሪ መምህር ተመድቦ ስም መጥራትተለምዷል፡፡ ዕድር ላይ ይጠራል፤ ፍታት ላይ ይጠራል፤ ዕቁብ ላይ ይጠራል፤ ቡና ለመጠጣት ይጠራል፤ እሥረኛ ለመጠየቅ ይጠራል፤ቪዛ ለመጠየቅ ይጠራል፤ ስም መጥራት ባህላችን ሆኗል፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ስማቸው የሚጠራና የማይጠራ ስላሉ ነው፡፡ ስማቸውሊጠራ የሚችል፣ ስማቸው የማይጠራና ስማቸው ሳይጠራ እንደተጠራ የሚቆጠሩ አሉ፡፡ ስማቸው ሊጠራ የሚችለው እንደእኔና አንተ ያሉት ናቸው፡፡ ዕድል ካለህ ስምህ ይጠራል፡፡ ስማቸው የማይጠራው ደግሞ አንዳች ምክንያት የሚኖራቸው ናቸው፡፡ ስማቸውመጠራት የማያስፈልጋቸው ደግሞ ጉዳያቸው በውስጥ የሚያልቅላቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ስማቸው የወርቅ ቁልፍ ነው፤ ብዙቢሮዎችን ይከፍታል፤ ወይም ደግሞ የወርቅ ቁልፍ ያንጠለጠለ ስም የሚያውቁ ናቸው፡፡ አንዳንዴኮ ስምን መናፈቅ ይሻላል፡፡ ጭራሽስምህ ይጠፋልኮ››

‹‹አንተ ዋናው ክፉ አትሥራ እንጂ ስምህ ቢጠፋ ምን ችግር አለው? ከባሰ በሕግ መጠየቅ ነው››

‹‹ኖ ኖ ኖ ኖ ኖ እንደዚያ አይደለም፤ ስምህ ከነ ጭራሹ ከመዝገብ ላይ ይጠፋልእንጂ፤ ስምህ አልተመዘገበም፤ ‹ዳታ› ውስጥ የለም፡፡ ኮምፒውተር ውስጥ አልገባም፤ መዝገብ ላይ አልተገኘም፤ ፋይሉ ጠፍቷል፤ትባላለህ፡፡ አንዳንዱ ስምማ ይገርምሃል እንደ ቁልፍ ማንጠልጠያ ወልቆ የሚጠፋ ነውኮ የሚመስለው፤ በተመዘገበበት ቦታአታገኘውም፡፡ አሁን የእኔ ስም ዕድር ልከፍል ከሄድኩ አንደኛ ነው የሚጠራው፤ ስኳር ልወስድ ከሄድኩ ግን ጭራሽ ሳይጠራ ሊቀርይችላል፡፡ ለክፍያና ለመዋጮ ብቻ የታደሉ ስሞች አሉ፡፡ ለመቀበል ብቻ የታደሉ ስሞችም አሉ፡፡ ሁለቱንም ስሞች በየመዝገባቸውነው የምታገኛቸው፡፡ አንተ አንዴ እንኳን ስምህ አልጠራ ብሎህ እየናፈቀህ አንዳንድ ሰዎች ሁለትና ሦስት ጊዜ ስማቸው ሲጠራ ስታይ፣ስም የሌለህ ሁሉ ይመስልሃል፡፡››

‹‹ግን ለሥራና ለስም የታደሉ ሰዎች የሉም››

‹‹ሞልተው፤ አሁን እኛ ሀገር ሊቅ፣ ሳይንቲስት፣ እውነተኛ ነጋዴ፣ ባለሞያ፣ ሥራፈጣሪ፣ ገበሬ፣ ምናምን ለስም ያልታደሉ ናቸው፡፡ ስማቸውን የደመወዝ መክፈያና ግብር ሰብሳቢ ብቻ የሚያውቀው፤ አርቲስት፣ዘፋኝ፣ ቀልደኛ፣ ደግሞ ለስም የታደሉ፡፡ እስኪ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የአንድ ሳይንቲስት ቤት ዓመት በዓል ሲያከብር አይተህ ታውቃለህ? የአንድ የረዥም ርቀት አሽከርካሪ ቤት ገብቶ ኑሮውን ሲያስቃኝ አይተህ ታውቃለህ? እነዚህ ለስም ያልታደሉ ናቸው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ሥራውን የሠሩት፣ የደከሙት፣ የለፉትስማቸው ሳይጠራ መጨረሻ ላይ የሚጨመሩ ቅመሞች ስማቸው ሲጠራ ትሰማለህ፡፡›› 

ይህንን እያወራልኝ በድምጽ ማጉያ ስም መጥራት ተጀመረ፡፡ አምስት ሰዎች ተጠሩ፡፡አብሮኝ የነበረው ሰው ግን አልተጠራም፡፡ በድምጽ ማጉያው ‹መሐሪ ተሾመ› የሚል ስም ሲጠራ ከእኛ ፊት ለፊት ባለው ወንበር ላይየተቀመጠው ሰው ‹ወንድ ከሆንሽ መሐሪ አስቻለው ብለሽ አትጣሪም›› አለ፡፡

‹‹መሐሪ አስቻለው ብሎ መጣራት የወንድነት መለኪያ ሆነ እንዴ›› አልኩት

‹‹መሐሪ አስቻለው እኔ ነኛ››

©ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው

Saturday, October 26, 2013

በአፍሪካ ውስጥ በቅዠት የሚባንኑት እነማን ይሆኑ ?


Thursday, October 24, 2013 @ 01:10 PM Alma
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
ታላላቅ የአፍሪካ መሪዎች ህልም አላቸው፡፡ ቀሪዎቹ በቅዠት የተሞሉ ናቸው፡፡
በቅርቡ የአፍሪካ መሪዎች ቢያንስ በአፍሪካ ህብረት ስልጣን ያላቸውና የእነርሱ ጋሻ ጃግሬዎች ስለህግ ልዕልና፣ ስለዘር ማደን (ማሳደድ) የማያቋርጡ አስደንጋጭ የቅዠት ሪፖርቶች በገፍ እያቀረቡ ነው:: ቅዠታቸዉም የፍትህ ጎራዴ ስያሳድዳቸው በላብ ተጠምቀው ከንቅልፍ ይነቃሉ:: ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እንደ ታይም መጽሔት አገላለጽ “የኬንያውአንደኛ ሀብታም ሰው“ ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግስታት የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤትን ለማውገዝና ከስምምነቱ ለመውጣት በተጠራው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ በመገኘት ለመሰሎቹ በግልጽ እንደተናገረው በሌሊት ቅዠቶች በመሞላት እንቅልፍ ማጣቱን አሳውቆ እንዲህ ብሏል፣
“በአሁኑ ጊዜ በተለይም አገሬ እና እኔ እንዲሁም የእኔ ምክትል እንደግለሰብ እንቅልፍ ያሳጣንን ቅዠት ለእናንተ ክቡራትና ክቡራን ማሳወቅ ያለብኝ አይመስለኝም፡፡ የተባበሩት መንግስታት የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤትን የፍትህ ሂደት የሚዘውሩት የምዕራብ አገራት ኃያላን ናቸው፡፡ ኃያላኑ የዓለም አቀፍ የፍርድ ሂደቱን የሚጠቀሙበት ለማታለያና በኬንያ አመራር ላይ ጫና በመፍጠር የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎችን እነርሱ በሚፈልጉት መልክ ለማድረግ ነው፡፡ ሁልጊዜ የፍርድ ሂደቱን እንደማስፈራሪያ በመጠቀም ለእነርሱ አደግዳጊ አጎብዳጅ የሆኑ መሪዎች ወደ ስልጣን እንዲመጡ በማድረግ ለእነርሱ ምቹ የሆኑ ፖሊሲዎችና መርኃ ግብሮች እንዲተገብሩላቸው ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ በረቀቀ ዘዴ በአፍሪካ አገሮች የመንግስት ለውጥ እንዲመጣ ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ ለዚህም በብዙ መልኩ ተሳክቶላቸዋል፡፡ ከሁለት ሳምንታት በፊት ብቻ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዋና አቃቤ ህግ በኬንያውያን ፕሬዚዳንታዊ አስተዳደር ላይ ዴሞክራሲያዊና ህገመንግስታዊ ያልሆነ ማሻሻያ እንዲደረግ ሀሳብ አቅርቧል፡፡ እነዚህ በውስጣዊ የአገር ሉዓላዊነታችን ዘንድ የሚደረጉ ጣልቃገብነቶች ከምንታገሰው በላይ ሄደዋል፣ አነዚህ ድርጊቶች ለኬንያውያንና ለአፍሪካውይን ትልቅ ስድቦች ናቸው፡፡ የአፍሪካ ሉዓላዊነት ለተባበሩት መንግስታት የወንጀለኞች ፍርድ ቤትና ለደጋፊዎቹ  ጉዳያቸው አይደለም፡፡“
አንዳንድ ጊዜ ህይወት እንቆቅልሽና ግራ አጋቢ ይሆናል፡፡ ኡሁሩ ኬንያታ የኬንያ ፕሬዚዳንት የመሆን ህልሙን (በነገራችን ላይ አባቱ ጆሞ ኬንያታ የኬንያ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ነበሩ)  ባለፈው መጋቢት ወር በተደረገው ምርጫ በጠባብ ልዩነት 50.7% ድምጽ በማግኘት አሸናፊ ሆኖ የስልጣን እርካቡን ተቆናጧል፡፡ ኬንያታ ባለፈው ጊዜ በፈጸማቸው ወንጀሎች ሳቢያ በተደጋጋሚ በሚያስፈራ ሙት መንፈስ እየተጎበኘ አሁን ደግሞ “በዘር አዳኞች“ እየተፈለገ በአስቸጋሪ ሁኔታ የቅዠት ህይወትን በመግፋት ላይ ይገኛል፡፡ ኬንያታ እንዲህ ብሏል፣ “ህዝብ የአሁኑን ሁኔታ (የዓለም ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደትን) ‘ዘር አደና’ ብሎ ሰይሞታል፣ ድርጅቱ የያዘውን አቋም ስህተት ነው ብዬ ለማሳመን በከፍተኛ ችግር ላይ ወድቄ እገኛለሁ፡፡” ሳይኮሎጅስቶች እንደሚሉት በህዝብ ዘንድ በጣም የተለመደው ቅዠት በስሜት በተሞላ ምዕናባዊ ጭራቅ፣ አስፈሪ መንፈስ፣ ጠንቋይና በእብድ መሳደድ ነው፡፡ በኬንያታ ቅዠት ቀንድና የመጋዝ ጥርስ ያለው ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዋና አቃቢዎችና ዳኞች ላብ በላብ እስኪሆን እያሳደዱት እንደሆነ ይሰማዋል፡፡


አሁን ባለፈው ወር እንኳ ኬንያታ በሞይ ኤልዶሬት ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች ምረቃ በዓል ስነስርዓት ላይ በመገኘት ባሰማው ንግግር የሚከተለውን ብሎ ነበር፡፡ “እኔ፣ ዊሊያም ሩቶና ጆሹዋ ሳንግ ነጻ ሰዎች መሆናችንን የማያውቅ ማን ነው? እያንዳንዱ ዜጋ ቢያንስ ማን መዋጋትንና በማሳደድ ብጥብጥና ሁከት በዚህች አገር ውስጥ እንዲንሰራፋ እንደሚወድ ያውቃል፣ በመሆኑም እ.ኤ.አ በ2008 የተደረገውን ሀገር አቅፍ ምርጫ ተከትሎ በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሰውን የማስገደል ዕቅድ በእኛ በኩል እንዳልተደረገና እኛ አጃችን የሌለበት መሆኑን ህዝቡ ይመሰክርልናል፡፡ “ኬንያታ በተደጋጋሚና በኩራት “ጉዳዩ በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መታየት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ለእኔ ስሜን ለማደስ ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥርልኛል በማለት በሙሉ ልብ ለፍርድ ቤቱ ትብብሬን ሳደርግ ቆይቻለሁ፡፡ ከተመረጥኩ በኋላም ሙሉ በሙሉ ትብብር ማድረጉን ቀጥለንበታል፣ ለ5 ዓመታት የነበረውን ውጥረት በመቋቋም ሙሉ ትብብሬን ሰጥቻለሁ፡፡” ብሏል፡፡
አሁን ግን ኬንያታ መተባበር እንደማይችል ይናገራል፡፡ ከዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደማይኖረው ይገልጻል፡፡ እሱና (የእርሱ መሰል የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣን ተባባሪዎቹ) እስከሚያወቁት ድረስ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ገሃነብ  መሄድ ይችላል:: ኬንያታ አስረግጦ እንደተናገረው በምንም ሁኔታ ቢሆን ሄግ በተቋቋመው የፍርድ ሂደት ላይ እ.ኤ.አ ህዳር 12/2013 የእኔን ጉዳይ ለማየት በተያዘው ቀጠሮ ላይ አልገኝም፣ ምን ይመጣል? አሁን ሙሉ በሙሉ ነጻ መሆኑን በእርግጠኝነት የሚናገረውና ባለፉታ አምስት ዓመታትም ለፍርድ ሂደቱ ስኬት ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሙሉ ትብብር ሲያደርግ የቆየው ኬንያታ አሁን መንቀጥቀጥ፣ ስሜቱን መቆጣጠር ለምን አንዳቃተውና በላብ መዘፈቁ እንዲሁም ቀጥ ብሎ ለመሄድ አለመቻሉና በሀሰት በተቀነባበረ ክስ በሚለው ለስሙ፣ ለዝናውና ለክብሩ ሲል አለመታገሉ አስገራሚ ነው! የሸክስፒርን አባባል በመዋስ “እኔ እንደሚመስለኝ ብዙ ከንቱ ተቃውሞ አድርጓል፡፡”
ለመሆኑ የዓለም ወንጀለኞች ፍር ድ ቤት የማን ፍርድ ቤት ነው?
ኡሁሩ ኬንያታ፣ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ባሽርና ተባባሪዎቻቸው የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በቀልተኛና ዘረኛ “የነጮች ፍርድ ቤት“ መሆኑን አንድናምንላቸውና 70 በመቶ ያህሉን ገንዘብ የሚያገኘውም ከአውሮፓ ህብረት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የዓለም የወንጀለኞች ፍርድ ቤት 99 በመቶ የሚሆኑትን ኢላማ ያደረገው በአፍሪካውያን ላይ ስለሆነ ድርጅቱ “ዘር አዳኝ“ ነው በማለት አስደንጋጭ ክስ አሰምተዋል፡፡ (እ.ኤ.አ በ2010 በኢትዮጵያ በተደረገው አገር አቀፍ ፓርላሜንታዊ ምርጫ የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፓርቲ 99.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸናፊ ሆኗል፡፡) እውነታዎቹ ግን በተቃራኒው ይናገራሉ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የዓለም የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንዲቋቋም የሮምን ስምምነት ከፈረሙት 122 አገሮች ውስጥ 34ቱ ወይም 28 በመቶው ኬንያን ጨምሮ አፍሪካውያን ናቸው፡፡ ከድርጅቱ 18 ዳኞች 5ቱ ወይም 28 በመቶው አሁንም አፍሪካውያን ናቸው፡፡ የፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳንጂ ማሴኖኖ ሞናገን ከቦትስዋናና ፋቱአ ቤንሱዳ የዓለም የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዋና አቃቤ ህግ ከጋምቢያ የታወቁና በዓለም አቀፍ ህግ ችሎታቸው ዝናን ያተረፉ አፍሪካዊ ሴቶች ናቸው፡፡
የደቡብ አፍሪካው መንፈሳዊ ዴዝሞንድ ቱቱ ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ያልተቆጠበ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፣ እንዲህም ይላሉ “እስከ አሁን ድረስ ደካሞችን ከኃይለኞቹ ለመጠበቅ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ትልቅ እመርታ እያሳየ መሆኑን እያየሁ ስለሆነ ትልቅ ተስፋ እየሰጠን ነው፡፡ ስለሆነም የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አንዱ የተስፋችን የአክሊል ቀንዲላችን ነው” ብለዋል፡፡ እንዲሁም የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ጋናዊው ዋና ጸሀፊ ኮፊ አናን በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ የቀረበውን ስም አጥፊ ክስ በመቃወም እንዲህ ይላሉ፣ “የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ጸረ አፍሪካዊ ነው የሚለውን ሀሳብ አልጋራውም፡፡ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አፍሪካውያንን በክስ ላይ አላቆመም፣ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እየተዋጋ ያለው በሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀል የተዘፈቁትንና ከተጠያቂነት ለመሸሽ የሚጥሩትን አምባገነኖች ነው፡፡ እርግጥ ነው የአውሮፓ ህብረት ትልቁን የገንዘብ ድርሻ ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሊሰጥ ይችላል፣ ነገር ግን ብዙው የድርጅቱ ቦታ በአፍሪካውያን የተያዘ መሆኑ ሊካድ አገባም”!
ቅርጽና እውነታ፣ ኡሁሩ ኬንያታንና ግብረአበሮቹን ወደ ፍትህ ለማቅረብ በቂ ማስረጃ አለን?
የአፍሪካ መሪዎች ሀሳብን የማስቀየስ ጌቶችና የማታለል ንጉሶች ናቸው፡፡ የሚሰነዘሩባቸውን ትችቶች አቅጣጫ ለማስቀየስ እንዲሁም ከተጠያቂነትና ግልጽነት ለማምለጥ ሲሉ ሌላ ደንቃራ በማጀል የተካኑ ናቸው፡፡ በስሜቶቻችን ላይ እንደማሲንቆ ይጫወታሉ፣ የማሰብና ምክንያታዊ አቅማችንን በማሳነስ ንቀትን ያሳያሉ፣ የሞተውንና የተቀበረውን የኢምፔሪያሊዝምንና ቅኝ ገዥነትን ጭራቅነት በማንሳት ታሪካዊ ብሶታችንን ብቻ በየጊዜው እያነሳን ስሜቶቻችንን እንድናስጨንቅ ይጥራሉ፡፡ የኒዮኮሎኒያልና ኒዮሊበራል ህገወጥነትን በስሜቶቻቸን ላይ በማጀል እንድንፈራ ጥረት ያደርጋሉ:: ህሊናችን በሀሰት በተፈበረኩ የዘረኝነት ውርደት ስሜት እንዲጠመድ በማድረግ “ትልቁ ነጭ ዘር አዳኝ“ በአፍሪካ ላይ እያንዣበበ እንደሆነ ለማስረዳት ይፍጨረጨራሉ፣ ተፈጥሯዊ አዛኝነታችንንና ፍቅራችንን በመጠቀም እራሳቸውን ምንም ድጋፍ የሌላቸው በማስመሰልና በደል ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ በማድረግ ላይ ያለውን ድርጅት እንደ ጭራቅ እንዲቆጠር ይሞክራሉ፡፡ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እያንዳንዱን የአፍሪካ ዜጋ ለመከታተል እየመጣ እንደሆነ አድርገው ሊያሳምኑን ይሞክራሉ፡፡ በአጭሩ ከቁንጫ የበለጠ ዕውቀት እንደሌለን አድርገው ይቆጥራሉ፡፡
የኬንያታን የክስ ሁኔታ በአንክሮ ላልተመለከተና በቀረበው ስሜታዊነት ላይ በመመስረት ግንዛቤ የሚያደርግ ሰው ካለ ወደተሳሳተ አቅጣጫ ሊሄድ ይችላል፡፡ በተጨባጭ ያለው መረጃ እንደሚያሳያው ግን በኬንያታ ላይ የቀረበው የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ በማይረባና ሰውን ለመወንጀል ሲባል ሆን ተብሎና በሀሰት በተፈበረኩ መረጃዎች የተሞላ አይደለም፡፡
ኬንያታ የተከሰሰው በአስደንጋጭና በመረጃ በተደገፉ ሰነዶች በተረጋገጡ የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀሎች ነው፡፡ ብዙዎቹ ማስረጃዎች በነጻ አካል የተረጋገጡና በአግባቡ የተዘጋጁ ናቸው፡፡
የተራጋገጡ ውንጀላዎች በጣም ውስን ናቸው፡፡ ለምሳሌ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርደ ቤት ቅድመ ክስ ቻምበር (የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዋና አቃቤ ህግ ጉዳዩ ለፍትህ እንዲቀርብ ያጸደቀው) እንደወሰነው እ.ኤ.አ ጥር 3/2008 በናይሮቢ ክለብ በመገኘት ሚስተር ኬንያታ ከሙንኪጊ አባላት አንዳንድ ጊዜም “የኬንያ ማፍያ” እየተባሉ ከሚጠሩት ጋር በመዶለት ክስ የተመሰረተበትን ወንጀል እንዲፈጽሙ አዟቸዋል፡፡ የቀረበው መረጃ እንደሚያሳየው ኬንያታና ግብረአበሮቹ የተገኘወን አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም የቀድሞው የኪባኪ ናሽናል ዩኒቲ ፓርቲ አባላት በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ድርጅታዊ ፖሊሲ በመንደፍ እና ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱን ሳይቀር አንዳያስቆመው በማድረግ ከባድ ወንጀል ፈጽመዋል፡፡ መረጃው እንደሚያሳየው ኬንያታና ግብረ አበሮቹ በብርቱካናማው ዴሞክራቲክ ንቅናቄ (ኦዲኤም)  ደጋፊዎች ላይ ሰፊና የተቀነባበረ ጥቃት ለማድረስ የጋራ ስትራቴጅ በመንደፍ 1ኛ) የብቀላ ጥቃት እንዲፈጸምባቸው አድርጓል፣ 2ኛ) ሆን ተብሎ የብቀላ ጥቃቱ እንዳይቆም እርምጃ እንዳይወሰድ አድርጓል፡፡ አሁንም መረጃው እንደሚያሳየው ኬንያታ በናሽናል ዩኒቲ ፓርቲ (ፒኤንዩ) እና በሙንጊኪ የወንጀለኞች ድርጅት መካከል በመሆን የአስታራቂነት ሚና በመጫወት ከኖቬምበር 2007 ጀምሮ የፒኤንዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ፖለቲከኞች፣ የቢዝነስ ሰዎች እና የሙንጊኪ አመራሮች  እ.ኤ.አ በዴሴምበር 2007 ለሚደረገው ምርጫ መንግስትን በመደገፍ የሙንጊኪ እርዳታ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡ በድህረ ምርጫው ማግስት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ኬንያታና ሌሎች በኦዲኤም ደጋፊዎች ላይ በስምጥ ሸለቆ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ከሙንጊኪ ጋር ስብሰባዎችን በማካሄድ ከፕሬዚዳንቱ ቃለመሀላ በኋላ የፒኤንዩን ስልጣን በማጠናከር እገዛ አድርገዋል፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ኬንያታና ሌሎች የጋራ ዕቅድ በመንደፍና ተግባራዊ እንዲሆን በማገዝ የኬንያ ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ ጥቃቱን እንዳያስቆመውና ዋናዎቹ የጥቃቱ ተዋንያኖች ለህግ እንዳይቀርቡ አድርገዋል፡፡
ሁለተኛው የቅድመ ፍትህ ቻምበር ኬንያታና ግብረአበሮቹ የተባለውን ወንጀል መፈጸማቸውን በበቂ መረጃ በማረጋገጥ ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸው ወሰነ፡፡ የፈለገ በ155 ገጽ በዝርዝር የቀረበውን እና የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በአንቀጽ 61 (7) (a) እና (b) በኬንያታና በግብረ አበሮቹ ላይ የቀረበው ውንጀላ ለክስ የሚበያቃ መሆን አለመሆኑን በእልህ አስጨራሽና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ በዓለም አቀፉ የወንጅል ፍርድ ቤት ዋና አቃቤ ህግና በቅድመ ፍትህ ቻምበሩ የኬንያታን ፍትህ የማግኘት መብት ለመጠበቅ የተዘጋጀውን ማንበብ ብቻ በቂ ነው፡፡ በመሆኑም በአፍሪካ ስሜታዊ እራስ ወዳድ የእባብ ዘይት ሻጮች ለተሰነዘረው ክስ ማጎብደድ የለብንም፡፡
እንቅልፍ ማጣት በአፍሪካ፣
ሁልጊዜ ሌሊት የፍትህንና እረዳቷን ቅዠት የሚፈራውና እንቅልፍ አልባ የሆነው ኬንያታ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ጭምር ናቸው፡፡ የአፍሪካ መሪዎች “በአይሲሲ የሌሊት ቅዠት” (በሌሊት በላብ ተዘፍቀው የሚነቁ፣ ጥርሳቸውን የሚነክሱ፣ እራሳቸውን የሚያኩና ምንጣፋቸውን እያዩ ስለ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዋና አቃቤ ህግ ለማሰብ ልምድ ላላቸው የአፍሪካ መሪዎችን ለመግለጽ ያዘጋጀሁት) በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያው የይስሙላ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ላለፈው አንድ ዓመት የሟቹን ባለራዕይ ጠቅላይ ሚኒስትር ራዕይ እንደሚያሳካ ሲነግረን ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ በእርግጥ ራዕዩ “ትልቁ ነጭ አዳኝ“ የሌሊት “የዘር አደን“ ቅዠት ውስጥ ተዘፍቆ እናገኘዋለን፡፡ የሩዋንዳው ፓውል ካጋሜ “ኢምፔሪያሊስቶቸና ቅኝ ገዥዎች” በስውር እንደ ዳኛና አቃቤ ህግ ሆነው የአፍሪካ መሪዎችን ለመያዝና ለማሰር ወደ አፍሪካ በመመለሳቸው ቅዠት ውስጥ ገብቷል፡፡ የሱዳኑ ኦማር አልባሽር በቤተመንግስቱ ውስጥ መሽጎ የአይሲሲ ጭራቆች ሊይዙት እያንዣበቡበት መሆኑን አያየ ይቃዣል፡፡ የደቡብ አፍሪካው ታቦ ኢምቤኪ የምዕራቡ ዓለም አታላዮች፣ እምነተ ቢሶች በድብቅ በአፍሪካ ጨለማ እየተጓዙ ስለመጡ እያዘገመ የመጣውን ንቀታቸውን ለመከላከል አብረውት እንዲታገሉ ለአፍሪካ ምሁራን ጥሪ አስተላልፏል፡፡ የኡጋንዳው ዮሪ ሙሴቬኒ በ2003 ከልብ በመነጨ መልኩ በበጥባጭነቱ የሚታወቀውን ጆሴፍ ኮኒን ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለማስረከብ ተስማምቶ በ2013 ግን አይሲሲ መሰል ጓደኞቹን እየመረመረ መያዝ ሲጀምር በግልብና በእብሪት ቅዠት ውስጥ መዋኘት ጀመረ፡፡
ሌሎች ብዙ የአፍሪካ መሪዎች ተስፋ በመቆረጥ መልኩ የአይሲሲ ሙትምስል በፈረስ ላይ ሆኖ ገና ከአድማስ ጫፍ ሲመለከቱት በሰሩት የሰብአዊ መብት ረገጣ አንድ ቀን ተይዘው እንደሚጠየቁ በማሰብ በፍርሀት መራድ ጀመሩ፡፡ ከ60 የነጻነት ዓመታት በኋላ እንደ ኔልሰን ማንዴላ የመሳሰሉት የአፍሪካ መሪዎች ሰለአፍሪካ ያላቸውን ራዕይ ነበር ግዴታቸው: “በውስጧ ሰላሟ የተጠበቀ አፍሪካን እመኛለሁ፡፡“ ሰብአዊ መብት ረጋጮች ከፈጸሙት የሰብአዊ መብት ረገጣና ከተጠያቂነት ቅዠት ለማምለጥ የሚያደርጉት መፍጨርጨር በጣም የሚያስገርም ነገር ነው፡፡ ሆኖም ግን እውነተኛው ቅዠት — ህይወት ያለው ቅዠት — በአፍሪካውያን ህዝቦች ላይ ውጤት እያመጣ ነው፡፡ ከ2003 ጀምሮ አልባሽር በሱዳን በዳርፉር ክልል የማያቋርጥ የዘር ፍጅት በመፈጸሙ በተባበሩት መንግስታት መረጃ ግምት መሰረት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያለቀበትና ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ደግሞ የተፈናቀለበት ፖሊሲ በመንደፍ እልቂቱን አስፈጽሟል፡፡ በ2005 በኢትዮጵያ በመንግስት የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን ባቀረበው ሪፖርት መሰረት ድህረ ምርጫውን ተከትሎ 193 መሳሪያ ያልያዙ ሰላማዊ ተቃዋሚ ዜጎች ተገድለዋል፣ 763 ሰላማዊ ዜጎች በጥይት ተደብድበው ቁስለኞች ሆነዋል (ይህም በትንሹ የታየው ነው)፣ ቀደም ባለው ዓመት በጋምቤላ ክልል ከ400 በላይ ነዋሪዎች ተገድለዋል፡፡ በ2008 በኦጋዴን አካባቢ በታጣቂዎች በተከፈተ የእሩምታ ተኩስ  በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች፣ አካለ ጎደሎ፣ የሞቱና መፈናቀል የደረሰባቸው ሆነዋል፡፡
በ2007-2008 በተባበሩት መንግስታት ግምት መሰረት በኬንያ ለሳምንታት ለቀጠለውና በዴሴንበር 2007 እና ፌብሯሪ 2008 መካከል በተካሄደው ብጥብጥ ወደ 1200 የሚሆኑ ሰዎች ሲሞቱ፣ 600 000 የሚሆኑ ዜጎች ደግሞ ተፈናቅለዋል፡፡ በዚያ ብጥብጥ ኬንያታ ከደሙ ንጹህ ነኝ ምንም ጥፋት የለብኝም ሲል ቆይቶ ነበር በኋላ የአይሲሲ ዋና አቃቤ ህግ ያለምንም ጥርጣሬ ኬንያታ ድርጊቱን መፈጸሙን አስከሚያረጋግጥ ድረስ፡፡
በ2010 የኮትዲቯሩ ሎሬንት ባግቦ በመለያ ምርጫው በተቀናቃኙ ተሸነፎ ስልጣን አላስረክብም አለ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ባግቦ በሄግ በተሰየመው የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ፍርዱን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ (የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባግቦ ወደ ሄግ እንዲሄድ በተደረገው ጥረት የአፍሪካ መሪዎች ምንም ጆሮ አልሰጡም ነበር)፡፡ በተባበሩት መንግስታት ግምት መሰረት የድህረ ምርጫውን ብጥብጥ ተከትሎ በተቀሰቀሰው ሁከት 3000 ሰዎች ኮትዲቯር ተገድለዋል፡፡
በ2011 በሊቢያ የመጀመሪያዎቹ የአመጽ ቀናት ሞአማር ጋዳፊ በተቃወሙት በመቶዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ በቁጥጥር ስር የማዋል፣ የእስራትና የሞት ትዕዛዝ በማዘዝ አስፈጸመ፡፡ በ2012 ተገንጣይ የማሊን ሰሜናዊ ክፍል የተቆጣጠሩት አማጺያንና ሚሊሻዎች ለመግለጽ በሚያስቸግር መልኩ የሰበአዊ መብት ረገጣና የጦር ወንጀሎችን ፈጽመዋል፡፡ በ2013 በሩዋንዳ ኤም23 በሚደገፉት አማጺያንና በዴሞክራቲክ ኮንጎ ተፋላሚዎች መካከል በተካሄደ ጦርነት በምስራቅ ዴሞክራቲክ ኮንጎ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች አካለ ጎደሎ ሆነዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ ተገድለዋል፡፡ ይህ ከብዙ በጥቂቱ የአፍሪካ መሪዎች ቅዠት ነው፡፡
የአፍሪካ መሪዎች አይሲሲን በዓለም ህዝብ ሕሊና ፍርድ ቤት በማቅረብ የሌሊት ቅዠታቸውን ለማስወገድ ይፈልጋሉ፣
የአፍሪካ ህብረት አመራር አይሲሲን በዓለም ህዝብ ፊት ለፍርድ በማቅረብ የብልጣብልጥነት ታክቲክ በመጠቀም ቅዠታቸውን ለማስወገድ ይሞክራሉ፡፡ እስቲ ይታያችሁ በወንጀል የተዘፈቁት እነዚህ የሰብአዊ መብት ረጋጮች አቃቤ ህጉንና ዳኛውን በወንጀል ሊያስቀጡ ሲሞክሩ! የአፍሪካ ህብረት የህዝብ ግንኙነት ስትራቴጂ አይሲሲ ከአሜሪካው Seal Team 6 ወይም ከእንግሊዙ Special Air Service ከሚባሉት በድብቅ ከጠላት አገር ገብተው የተለየ አላማን ለማሳካት ከሚያከናውኑ ኃይሎች ጋር እኩል አስመስሎ ለማሳየት ነው፡፡ ለዚህም ነው ኬንያታ የምዕራቡ ኃያላን የአይሲሲ ሂደት ቁልፍ ዘዋሪዎች ናቸው ያለው፡፡ የህግ ሂደትን እንደማታለያ በመጠቀም የኬንያን አመራር በማስፈራራት የተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች በሌላ እንዲያዙ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ አይሲሲ በኬንያ ላይ የሚያንቀሳቅሰው “የጨለማው ኃይሎች” ክስ ምንም ትርጉም አይኖረውም፡፡ ኬንያ ለምዕራቡ ዓለም ሽብርተኝነትን ወይም በህንድ ውቅያኖስ የባህር ላይ ዘራፊዎችን በመዋጋት ዋና እረዳት እና ለደህንታቸው ማዕከል ናት፡፡ በ2013 ለአሜሪካ ኮንግረስ ተጠንቶ በቀረበው መረጃ መሰረት አሜሪካ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በየዓመቱ ለኬንያ አንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እርዳታ የምትሰጥ ሲሆን ይህም ከአሜሪካ እርዳታ ተቀባይነቷ ከዓለም በ10ኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል፡፡ በ2011 የበጀት ዓመት አሜሪካ ለኬንያ የሰጠችው እርዳታ 200 ሚሊዮን የምግብና ሌሎች ሰብአዊ እርዳታዎችን ጨምሮ 900 ሚሊዮን ደርሷል፡፡ በ2012 የበጀት ዓመት ኬንያ ከ700 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ እርዳታ ያገኘች ሲሆን 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደግሞ በሁለትዮሽ/በባይላተራል ስምምነት እንዲሁም 8 ሚሊዮን ዶላር የውጭ መጠባበቂያ ፈንድና ወደ 200 ሚሊዮን የሚጠጋ የሰብአዊ እርዳታ በተጨማሪም ለአሚሶን ወታደሮች ድጋፍ አድርጋለች፡፡ ለ2014 የበጀት ዓመት የአሜሪካ መንግስት መምሪያ ለኬንያ 564 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ላልሆነ እርዳታ እንዲያዝላት ጠይቋል፡፡ ይህም ለምግብ እርዳታ ወይም የተለዩ ለደህንነት የተያዘውን አያካትትም፡፡
ኬንያ ከአሜሪካ መንግስት መምሪያ በማያከራክር ሁኔታ ትልቁን የጸረ ሽብር አርዳታ  በጸረ ሽብር ስልጠና፣ በወታደራዊ መሳሪያና በደህንነት ጥበቃ ቴክኖሎጂ በሚሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር እርዳታ ተጠቃሚ ናት፡፡ አሜሪካና ኬንያ በጋራ ጸረ ሽብር ግብረ ኃይልና በጋራ የስለላ ልውውጥ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ እውነት ለመናገር አሜሪካ ለኬንያ ለጸረ ሽብር እርዳታ በገፍ እየሰጠች ለሰብአዊ መብት ረገጣው ግን አይታ እንዳላየች፣ ሰምታ እንዳልሰማች፣ መናገር እየቻለች እንዳልተናገረች ተደርጎ ከፍተኛ ትችት ይሰነዘርባታል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ጸረ ሙስና ላይ ትኩረት በማድረግ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማሻሻል፣ የፍትህ ስርዓቱ ተደራሽ እንዲሆን፣ ለምርጫና ለሲቪክ ኢዱኬሽን፣ ለአካባቢያዊ አስተዳደር፣ ለህግ ማሻሻያ፣ የሰብአዊ መብትን ለማስፋፋትና ለመጠበቅ፣ የፐብሊክ ሴክተሩን ለማሻሻል፣ ለተቋማዊና አቅም ግንባታ በርካታ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለኬንያ እርዳታ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ናይሮቢ በአፍሪካ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የልብ ትርታ በመሆን ለአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች አግልግሎት በመስጠት ላይ ትገኛለች፡፡ በናይሮቢ ከተማ ጊጊሪ በተባለው ቦታ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት ከኒዮርክና ከጀኔቫ በመቀጠል በዓለም ትልቁ አህጉራዊ የተባበሩት መንግስታት ማዕከል ነው ይባልለታል፡፡
እንዴት ኬንያታ ፊት ለፊት “የምዕራቡ ዓለም ኃያላን የፍትህ ሂደቱን እንደማታለያና በሚፈልጉት የኃላፊነት ቦታ ላይ እነርሱ የሚፈልጉተን ለማስቀመጥ ነው” ብሎ ይናገራል?  እስቲ እውነት እንነጋገር ኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ያለምዕራቡ ዓለም ምጽዋት መኖር ይችላሉን? ካለጭራቁ የዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ብድርና እርዳታ መቆየት ይችላሉን? ታላቁ የአሜሪካ የስራ ሰው ፈላስፋ ኤሪክ ሆፈር እንዲህ ብሏል፡፡ “የሚመግቧቸውን እጆች የሚነክሱ ሰዎች ሁልጊዜ የሚረግጣቸውን ጫማ ይልሳሉ::”
ቅዠቶች በየቦታው፣
በእርግጥ ማንም በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ከተናገሩት መሪዎች ውስጥ ስለረዳት የለሾች፣ ስለአቅመቢሶች፣ ስለተከላካይ የለሽ የዳርፉር ነዋሪዎች በአሁኑ ጊዜ በጃንጃዊድ (በፈረስ ጀርባ ላይ ያሉ ጭራቆች ማለት ነው) ሚሊሻዎች እየተሳደዱ ለመሀናቸው አውነተኛ ቅዠት የተናገረ የለም፡፡ በኢትዮጵያ በኦጋዴንና በጋምቤላ አካባቢዎች ህዝብን ፈጅተው የሰብአዊ መብት ረግጠው በቅዠት በሚኖሩ የሰብአዊ መብት ረጋጮች ላይ ማንም በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ የተናገረ መሪ አልነበረም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በዴሞክራቲክ ኮንጎ ላይ እየተካሄደ ስላለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀል ማንም ትንፍሽ ያለ መሪ አልታየም፡፡ በጥባጩን ጨፍጫፊ የኡጋንዳውን ጆሴፍ ኮኔ ለመያዝና ለፍርድ ለማቅረብ የተደረገ ጥረት ሪፖርት ማንም መሪ በስብሰባው ላይ አላቀረበም፡፡ በግድያ፣ በማሰቃይት፣ አካለጎደሎ በማድረግ፣ በአስገድዶ መድፈር፣ ዘረፋና ቅሚያ በመፈጸም በየቀኑ በመቃዠት ላይ ስላሉት ወንጀለኞች አንድም የአፍሪካ መሪ በስብሰባው ላይ ሲያልፍ እንኳን አልተናገረም፡፡
እውነት ለመናገር ቅዠቶች ለአፍሪካ መሪዎች፣ ለተጠቂዎች፣ ከጥቃት ለተረፉት ብቻ በሞኖፖል የተሰጡ አይደሉም፣ ሁላችንም ብንሆን ቅዠቶችን ለማየት ዕድሉን ላላገኘንና ምስክርነት ለመስጠት ባንችልም የነዚያ ጭራቅ ቅዠቶች እኛም ቅዠቶች አርጎናል፡፡ ምክንያቱም የአፍሪካ የፖለቲካና አማጺያን መሪዎች እንደዚያ ያለ አስቀያሚና አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት ይረግጣሉ ብለን እራሳችንን ለማሳመን ስለምንቸገር ነው፡፡ ሁላችንም በውል ባልታወቀ ቅዠት ውስጥ ተተብትበን እንገኛለን፡፡ ከእልቂት የተረፈው ኤሊ ዌይሴል “ጨለማ” በሚለው መጽሀፉ እንዲህ ይላል፣ “ከእኛ ብዙም ሳይርቅ ከጉድጓዱ የእሳት ነበልባል ይንቀለቀላል… ህጻናት! አዎ በአይኔ በብረቱ አየሁት… ፊቴን ቧጠጥኩ፣ ግን አሁንም በህይወት አለሁ? ነቅቸ ነበርን? ማመን አልችልም፣ አነርሱ እንዴት ሰውን፣ ህጻናትን ሊያቃጥሉ ቻሉ? እና ዓለምስ እንዴት ዝም አላቸው? አንዱም ቢሆን ይህ እውነት ሊሆን አይችልም፣ ቅዠት ነበር…“
በጥቂት ወራት ውስጥ እንዴት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሩዋንዳውያን በዘር ማጥፋት ፍጅት ያልቃሉ? ዓለምስ እንዴት ጆሮ ዳባ ልበስ አለ? ወይም ግማሽ ሚሊዮን ዳርፉራውያን ሲያልቁና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሲፈናቀሉ እንዴት ዓለም ዝም አለ? ከ200 ሺህ በላይ ሴራሊዮናውያን እና ላይቤሪያውያን ሲጋደሉና ሲተራረዱ አሁንም ዓለም ዝም? ከ50 ሺህ በላይ ኢኳቶሪያል ጊኒያውያን ሲዋረዱ፣ሲያልቁ አሁንም ዓለም ዝም? በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ማሰቃየት ሲፈጸምባቸው (በዚህ ባለፈው ሳምንት ሂዩማን ራይትስ ዋች ባወጣው ባለ 70 ገጽ ሪፖርት መሰረት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች፣ ህገወጥ የአጠያየቅ ዘዴዎች፣ ማዕከላዊ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት የታየው ደካማ የእስር ቤት አያያዝ እና ግድያ) ዓለም ዝም ማለቱ?
ኤሊስ ዌይልሴ የሚያስተምረን “ኢፍትሃዊነትን ለማስቆም አቅመቢስ የምንሆንበት ጊዜ ይኖራል፣ ነገር ግን ለማመጽ ጊዜ ልናጣ በፍጹ አንችልም“ ለዚህም ነው ድምጻችንን ከፍ አድርገን መናገር ያለብን፣ ማመጽ፣ መጮህና መቃወም፡፡ የኢፍትሀዊነት ሰለባ ለሆኑና ፍትህን ለሚፈልጉ ሁሉ ፍትህን ከመጠየቅ ወደ ኋላ ማፈግፈግ የለብንም፡፡
የአይሲሲን የፍርድ ሂደት ማዘግየት ቅዠቱን አያቆመውም፣ እንዲያውም እንዲራዘምና ጠንካራ እንዲሆን ያደርገዋል፣
ኬንያታ የአይሲሲን ሙዚቃ መጋፈጥ አልፈለገም፡፡ የፍርድ ሂደቱን በማዘግየት እሱና የእርሱ ምክትል ሩቶ የመንግስታዊ ስራቸውን ማከናወን ይፈልጋሉ፡፡ የአፍሪካ ህብረት መሪዎችና የኬንያታ የህግ ጠበቆች የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በሮም ስምምነት አንቀጽ  16ን መሰረት አድርጎ የኬንያታ ጉዳይ ለ12 ወራት እንዲራዘምና በቀጣይም እንዲራዘም የሚያሳስብ ነው፡፡ ማዘግየት የሚለው ማቆየት ለሚለው የገባ ቃል ሲሆን እንደ ወንጀልን መከላከል ህግ ከሆነ ማዘግየት የጥንቱ የማታለያ ዘዴ ነው፡፡ ጊዜ ባለፈ ቁጥር ለተከሳሹ ጠቃሚ ነው፡፡ ማዘግየት ሁልጊዜ ለወንጀለኛው የአሸናፊነትን ዕድል ይሰጣል፡፡ የወንጀል መከላከል የህግ ባለሙያዎቸ በሶስት የ’መ’ ኮዶች ይመራሉ፣ እነርሱም “ማዘግየት፣ መካድ፣ መከላከል” ናቸው፡፡ አንድ የክስ ጉዳይ ከዘገየ ብዙ ነገሮች ሊከተሉ ይችላሉ፣ ምስክሮች ቦታ ሊቀይሩ ይችላሉ፣ ወይም ሊሞቱ ይችላሉ፣ ወይም ቀደም ሊመሰክር የነበረውን ይቀይራል፣ ወይም የሀሰት ምስክርነት ይሰጣል፣ ወይም ደግሞ ምስክሩ በጊዜ ሂደት ዝርዝር ሁኔታውን ማስታወስ ይሳነዋል፣ በትልልቅ ጉዳዮች ላይ የህዝብ ሀሳብ ሊሰረቅና ህዝብም ዝምተኛ ሊሆን ይችላል፣ ወይም በፖለቲካና በዘር ላይ ያነጣጠረ ክስ አስመስሎ ለህዝብ በማቅረብ ድጋፍ አግኝቶ ለማምለጥ ይሞከራል፡፡ ጠንካራ አቃቤ ህግ በደካማና በግዴሌሽ፣ ፍትህ መስጠትን ወደ ጎን ትቶ ጉዳዩን በሰላም ለመፍታት ወይም ክሱን ለመሰረዝ በሚሞክር አቃቤ ህግ ሊተካ ይችላል፡፡
ነጸ መሆኑንና ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ለአይሲሲ መረጃ በመስጠት እገዛ ሲያደርግና በኩራትና በጩኸት ሲናገር የቆየው ኬንያታ እንዴት ፈጣን የፍርድ ሂደትን ሊጠላ እንደቻለ፣ እንዴት ማዘግየት እንደፈለገ ሲታሰብ አስገራሚ ነው፡፡ የዘገየ ፍትህ እንደታካደ መቆጠር ብቻ ሳይሆን ኢፍትሀዊነትን ማራዘም ጭምርም ነው፡፡ ሆኖም ግን በመከላከል ህግ እንደማውቀው ሁሉ የዘገየ ፍትህ እንደማምለጥ ወይም እንደማስወገድ ይቆጠራል፡፡
የኢፍትሀዊነት ቅዠትን ለማምለጥ ፍትሀዊነትን ማለም፣
የኬንያታን፣ የሩቶንና የአልባሽርን ሰለባዎች ቅዠት ከዚሁ ጎን ለጎን ሳያካትቱ የአምባገነኖቹን ቅዠት መቋጨት ተገቢ አይሆንም፡፡ ሰለባዎቻቸው ቅዠታቸው በፍትህ አደባባይ በግልጽ የ2007 ድህረ ምርጫ ማስረጃዎችና እውነታዎች ወጥተው ፍትህን አንዲያገኙ ያልማሉ፡፡ የተጎጂዎቹ የእውነት ነጸብራቅ በአሰቃቂ የእልቂት ወንጀሎች ላይ ሲፈነጥቅ ቅዠቶቻቸው ይጠፋሉ፡፡
ፕሬዜዳንት ኬንያታ፣ የአንተ ዝና፣ ጌታው! የአንተ ዝና ምንድን ነው?
በሮም ስምምነት አንንቀጽ 25 (3) (a) መሰረት ፕሬዚዳንት ኬንያታ በተዘዋዋሪ የወንጀል አስፈጻሚ ሆኖ የተገኘ ስለሆነ በሚከተሉት ወንጀሎች ተጠያቂ ነው፡፡ 1ኛ) ግድያ፣ አንቀጽ 7(1) (a) 2ኛ) ማጋዝ ወይም በኃይል ማፈናቀል፣ አንቀጽ 7(1) (d) 3ኛ) አስገድዶ መድፈር፣ አንቀጽ 7(1) (g) 4ኛ) ማሰቃየት፣ አንቀጽ 7(1) (h) 5ኛ) ሌሎች ኢሰብአዊ ድርጊቶች፣ አንቀጽ 7(1) (k)
እነዚህ ክሶቹ በሙሉ አስደንጋጭ ሰለሆኑ ቶሎ ወደ ፍትህ አደባባይ ቀርበው ቶሎ ብይን ሊሰጥባቸው ይገባል፡፡
ፕሬዚዳንት ኬንያታ በኩራት ሲናገር “ገና ከጅምሩ ጉዳዮች መታየት ሲጀምሩ ስሜን ለማደስ ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥርልኛል ስል ሙሉ በሙሉ ለፍርድ ቤት ተባባሪነቴን አሳያቻለሁ::” በአሁኑ ጊዜ ፕሬዚዳንት ኬንያታ በሸክስፒር ኦቴሎ ለተጠቀሰው አፍሪካዊ ጀኔራል አሳዛኝ ታሪክ የወጣቱ ካሲዮ ቃላትን   እንድናስብ ያደርጋል፡፡ ካሲዮ ታማኝና ጥሩ ወታደር በመሆን ያለውን ጥሩ ስም ተከትሎ ትልቅ እንቆቅልሸ ውስጥ በመግባት ሰው ካለ ጥሩ ስም አውሬ ነው የሚል ጥያቄ አነሳ፡፡ “ስሜን ስሜን ስሜን ኦ! ስሜን  አጥቻለሁ! የማይሞተውን እኔነቴን አጥቻለሁ! የቀረኝ አውሬነት ነው፡፡ የእኔ ስም! ኢያጎ ስሜ!” አለ ካሲዮ::
ሚስተር ኬንያታ ስሙ ለጠፋ ለጎደፈ ሰው ፕሬዚዳንት መሆን ምን ትርፍ ያስገኝለታል…! የማይሞተው እሱነቱ — ህያው ነፍሱ — በስሙ ፈንታ የብዙሃን ገዳይ፣ የብዙሃን አፈናቃይ፣ የብዙሃን አስገድዶ ደፋሪ: የብዙሀሃን አሰቃይ: ብሎ መታወቅ አያሳፍርም አይዘገነንም?! ሚስተር ፕሬዚዳንት! እንዲህ ስብዕና  አልባ ለሆነ ሰው እንግዲህ ምን ቀረው!?
ከሉዓላዊነት በፊት ሰብአዊነት!

የጀነራል መኮንኖች የምደባ ለውጥ ተካሄደ


ሜጀር ጀነራል አደም መሀመድ የአየር ሀይል አዛዥ ሆነው መሾማቸውንና የአዛዥ ጄነራሎች ላይም የምደባ ለውጥ መደረጉን ምንጮቻችን አመለከቱ፡፡ በአየር ሀይል አዛዥ በነበሩት ሜጀር ጀነራል ሞላ ሀይለማርያም ምትክ የተሾሙት ሜጀር ጀነራል አደም የአየር ሀይል ፓይለት የነበሩና በሱዳን አቢዬ ግዛት የሠላም አስከባሪ ሀይል 
ምክትል አዛዥነት ያገለገሉ እንዲሁም የመከላከያ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ነበሩ፡፡
 
በሌሎች የመከላከያ የስራ ምድብ ቦታዎች ላይ የአዛዦች የምደባ ለውጥ መደረጉን የተናገሩት ምንጮች፣ አዲስ የሀላፊነት ምደባ ከተሠጣቸው ውስጥ ሌተናል ጀነራል ሠአረ መኮንን፣ ሌተናል ጀነራል አበባው፣ ሜጀር ጀነራል ዮሀንስ ወልደጊዮርጊስ፣ ሜጀር ጀነራል ገብራት አየለ እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ ባለፈው አመት እና ዘንድሮ ከ60 በላይ ለሚሆኑ መኮንኖች የጀኔራልነት ሹመትና እድገት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

የሂውማን ራይትስ ዋች የሰሞኑ ዘገባ


October 26, 2013

ለወያኔ ፋሽስታዊ ግፍና የውገን ሰቆቃ ምላሽ መስጠት ይገባል

በኤፍሬም የማነብርሃን
በዓለም ታዋቂው የሰብዓ መብቶች ትሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች (Human Rights Watch) ሰሞኑን ባወጣው ዘገባ፡ የአፍሪቃ አንድነት ዋና ከተማ በምትባለው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ እያካሄደ ያለውን የግፍ ግፍ ለዓለም አጋልጧል፡፡ በዚች ደቂቃ ማዕከላዊ ፖሊስ ጣቢያ እየተባለ በሚጠራው የሰቆቃ ቦታ በንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ለኢትዮጵያዊነት ፍቅርና ክብር በሌለው የወያኔ ወንጀለኛ መንግስት ይህ ነው የማይባል ወንጀል እየተፈጸመበት ይገኛል። በ”ሕጋዊ” መንገድ እንዲሰሩ “ተፈቅዶላችው” የሕዝቡን ሰቆቃ በመስማትና የሚፈጸመው ግፍና በደል እንዲቀርና በሰላማዊ መንገድ በውድ አገራችን ላይ ደሞክራሲ እንዲለመልም እየታገሉ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ፤ የወያኔ ፋሽስታዊ መንግስት በአንድ ወገን ዓለምን ለማታለልና ዲሞክራሲ እንዳለ ለማስመሰል ፓርቲ ማቋቋም ይቻላል ብሎ ካስወራ በኋላ፤ ከዓለም እይታ በስተጀርባ ግን ይህ ነው የማይባል ፋሽስታዊ ጭካኔ በንጹኅን ኢትዮጵያውያን ላይ እያካሄደ አንደሚገኝ የመብት ትሟጋች ድርጅቱ አጋልጧል። እንዲህ ያለ ወንጀል በውዲቷ ዋና ከተማችንና በታላላቆች የሃይማኖት መጻሕፍት በቅድስናዋ ደጋግማ በምትጠቀሰው አገራችን ሲፈጸም እንዴት ዝም ብለን እናያለን? እያንዳንዱ እትዮጵያዊ ባለው ዐቅሙ ሊያደርግ የሚገባውን ለማድረግ ለምን አይረባረብም?
ይህ ግፍ በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸምባቸው የቆየ መሆኑን ከሥርዓቱ ተጠቃሚዎች በስተቀር ሁሉም የሚያውቀው ቢሆንም፡ እንደዚህ በዓለም ደረጃ ታውቆ በግላጭና ቁልጭ ብሎ መነገሩ ወያኔ አትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን፤ ከአሁን በኋላ የዓለምን ሕዝብ ጭምር አያታለለ ሊቆይ እንደማይችል ያስገነዘብው ዪመስለኛል። ለዚህም የሂውማን ራይትስ ዋችን በሚቻል ሁሉ መርዳትና ምስጋናችንንም ማቅረብ ይገባናል።
በተጨማሪም እያንዳንዱ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊ “አሁንስ በቃ በጋራ እንኳን ምንም ማድረግ ቢያቅት በግሌ ማድረግ የሚገባኝን ማድረግ አለብኝ” ብሎ መነሳትና ይህንንም የግል ውሳኔ በስራ ለመተርጎም መወሰን አለበት፡፡ የግፉ አይነት፡ ብዛት፡ እና የጭካኔው መጠን ውስጣችንን የሚረብሽና ሰላምን የሚነሳ እንደመሆኑ መጠን፤ ይህን የውስጥ ንዴታችንን ወደ ወደተጨባጭ ትግል ለመቀየር በኢትዮጵያ ላይ ይግፍ መረቡን ዘርግቶ የተቀመጠውን ይሕን እርኩስ መንግስት ባለን ዐቅም ፊት ለፊት ተጋፍጠን “በዚህማ ልትቀጥል አትችልም ፡ይብቃህ እርኩስ ኃይል ይብቃህ“ ማለት መቻል አለብን።
በአገሪቱ ዋና ከተማ መሃል ላይ እንዲሁም ስላልታወቀ ነው እንጂ በጣም በብዙ የአገሪቱ ከተሞችና መንደሮች ውስጥ ይህን የመሰለ የግፍ ግፍ እየተካሄደ እያለና ሕዝቡ የመከራ ገፈፉን እየቀመሰ ያለ መሆኑን ሁላችንም በልባችን እያወቅነው እንዴት ብለን ቁጭ እንላለን፤ እንዴትስ በልተን ጠጥተን እንውላለን አናመሻለን፤ እንዴትስ ተኝተን እናድራለን፤ እንዴትስ ቤተ ክርስቲያን አስቀድሰን፤ መስጊድ ተሳልመን ቤታችን እንገባለን፤ እንዴትስ አገር አለን ብለን ስለ አገር ዕድገትና ልማት እናወራለን፤ እንዴትስ ስለዚህ ወንጀለኛ መንግስት መልካምነት እንናገራለን።
ከሂውማን ራይትስ ዋች ሪፖርት ትንሽ ቀንጨብ አድርገን እንመልከት፡፡
“ በኢትዮጵያ ከ1997ቱ አወዛጋቢ ምርጫ በኋላ በሰላማዊ ተቃዎሞ ላይ የሚደረገው ጫና ተባብሷል። በማዕከላዊ ተይዘው ምርመራ የሚካሄድባቸው የመንግስት ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ሰዎች … በተለይ በምርመራ ጊዜ ታሳሪዎቹ በጥፊ፣ በእርግጫ እንዲሁም በብትር እና በሰደፍ በተደጋጋሚ እንደተመቱ … ሰውነታቸውን ለህመም በሚዳርግ ሁኔታ እንዲሆኑና በተለይም እጆቻቸውን ከግድግዳ ጋር ታስረው እንዲንጠለጠሉ ተደርጎ ለረጅም ሰዓታት ያለማቋረጥ እንደሚደበደቡ ተናግረዋል። ከኦሮሚያ ክልል የመጣ አንድ ተማሪ ብቻውን ተነጥሎና በሰንሰለት ታስሮ ለበርካታ ወራት እንዲቆይ እንደተደረገ ተናግሯል፡፡ ‘ለመቆም ስሞክር እቸገራለሁ፡ ለመቆም ጭንቅላቴን፣ እግሮቼን እና ግድግዳውን መጠቀም ነበረብኝ ፡፡ ምግብ ስመገብ እንኳ በሰንሰለት ታስሬ ነበር። ስመገብ እጆቼ በፊት ለፊት በኩል እንዲታሰሩ ይደረጋል ስጨርስ ደግሞ መልሰው ወደ ኋላ ያስሩኛል።’”
እንግዲህ ይህ መረጃ በአጋጣሚ ሕዝብ ዘንድ ወሬው ሊሰማ የቻለው ከእስር ወጥተው ለወሬ ነጋሪነት የበቁ ሰዎች ስለተገኙ ነው። ክዚህ ጀርባ እንዲህ ያልታወቁ፡ በድብቅ በአገሪቱ ዙርያ በወያኔ ነፍሰ ገዳይ ቡድኖች በወገኖቻችን ላይ የሚፈጸሙ ስፍር ቁጥር የማይገኝላቸው ወንጀሎች እንዳሉ መገመት አያዳግትም። ቤት ይቁጠረው። የወንጀለኞቹ መሪ መለስ ዜናዊ በተገኘበት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ወርቅነህ ገበየሁ በደህነነት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የተናገረውን ለመጥቅስ ወያኔ እንደ ልዩ የስራ ችሎታው አድርጎ የሚትቀምበት ዘዴ “በተቀናጀ ኦፐሬሽን ለረጅም ጊዜ ለመንግስት ሥጋት ሆነው የቆዩ ሰዎች እንዲወገዱ” ማድረግ መሆኑን ወርቅነህ በኩራት ሲገልጽ ሁሉም በስብሰባው የነበሩ የምክር ቤቱ አባላት ከመለስ ጭምር የዜናው አስፈሪነትና ከባድነት ለመቅጽበት እንኳን በመንፈሳችው ውል ሳይል ስብሰባውን ሲቀጥሉ ታይተዋል።
በቅንጅት መሪዎች በተልይ ደግሞ በእህት መሪያችን በወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ የተፈጸመውን ግፍና መከራ እንዲሁም በአሁኑ ውቅት በእስክንድር ነጋ፤ በአንዷለም አራጌ፤ ወዘተ በዚች ሰዓት የሚፈጸመውን ግፍና መከራ ሁሉም የሚያውቀው ነው ። በሞቱ የተገላገልነው መለስ ዜናዊና የወያኔ መንግስት በሃሰትና ውሽት ላይ የተመሰረተውን የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም በማሰብ፤ የቅንጅትን መሪዎችን ለዓመታት በእስር ቤት በማንገላታትና በማሰቃየት፤ በጨለማ ቤት ለወራት በማቆየት፤ ከጉልበትና ከማስፈራራት በተገኘ የሃሰት የእምነትቃል ላይ እንዲፈርሙ በማድረግ በኢትዮጵያ ሕዝብና በደጋፊዎቻቸው ዘንድ እነዲጠሉና የመሪነት ድጋፋቸው እንዲቀንስና እንዲናቁ ያደረጉትን ሙከራ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ነው።
ይህ የወንጀለኞች መንግስት በኢትዮጵያ ላይ በመሳርያ ኃይል ከተፈናጠጠ በኋላ አገሪቱን በዘር መከፋፈሉ፤ አገሪቱን ያለባሕር በር ማስቅረቱ፤ ለምለም የአገሪቱን መሬቶች ለሱዳን አሳልፎ መስጠቱ፤ የአንድን አናሳ ብሔረሰብ አባላትን የኢኮኖሚው፡ የቢሮክራሲው፡ የሚሊታሪው፡ የፍርድ ቤቶች፡ የቤት ንብረትና መሬት ይዞታዎች የበላይ አስተዳዳሪና ባለቤት ወዘተ ማድረጉ፤ የአገሪቱን ብርቅዬ መምህራን ከዩኒቨርሲቲ ማፈናቀሉ፤ ሕዝብን ለምርጫ ካልወጣህ ካለ በኋላ መሸነፉን ሲያውቅ በዲሞክራሲ የተመረጡትን መሪዎች ማስገደሉ ማሰሩና ንጹሃን ወጣትና ህጻናትን መጨፍጨፉ፤ ሰሞኑን ደግሞ የወንጀለኛ ድርጅት አባል ካልሆናችሁ ስራ፡ እድገት አታገኙም ማለቱ ወዘተ አልበቃው ብሎ አስከፊ በሆኑት አሥር ቤቶቹ ውስጥ መሪዎችንና አዛውንቱን ለዚሕ ለሚዘገንን መከራና ሰቆቃ መዳረጉ ምን ያሕል ሕዝቡን የናቀ መሆኑን ያሳያል።
እንዲያውም ከሁሉም በላይ ደግሞ የሚያበሳጨው መንግስቱ ኃይለማርያምን በኢትዮጵያውያን ላይ ትልቅ በደል ሰርቷል እያለ የሚያብጠለጥለው የወያኔ መንግስት፡ ከመንግስቱ ኃይለማርያም በማያንስ ጭካኔ ከፖለቲካ ልዩነት በቀር ምንም ያልሰሩ ንጹሃንን ይህን ለመሰለ ስቃይና መከራ የዳረጋቸው መሆኑ ነው። በተጨማሪም በመንግስቱ ኃይለማርያም የተጀመረው የዚህ ለመከራ የተዳረገ ሕዝብ ፍዳ በዚህ ዘረኝነት ባሰከረው የወንጀለኞች መንግስት በጣም በተራቀቀ ድርጊት መቀጠሉ “ያገር ያለህ” ወደሚያስብል ነጥብ ላይ አድርሶናል።
በተለይ ደግሞ በዚህ ኢንተርኔት፡ ተዟዟሪ ስልክ፡ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እና በአጠቃላይ የሚዲያ ቴክኖሎጂ በዓለም በተንሰራፋበት ዘመን የወያኔ መንግስት ኢትዮጵያውያን የዚህ ዕድገት ሙሉ ተካፋይና ተሳታፊ እንዳይሆኑ አፍኖ፡ የዓለምን ሕዝብ ይሉኝታ ሳይፈራ የጭካኔና የግፍ መረቡን በአገሪቱ ላይ ዘርግቶ በማናለብኝነት አስከፊ ሴራውን ሲያከናውን ለብዙ ኢትዮጵያውያን “አሁንስ አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም” የማያስብል ደረጃ የደረስን ይመስላል ። እስከመቼ ችለን ልናየውና የወያኔን የግፍ ቀንበር ተሸክመን ኑሮን መቀጠል እንደምንችል ማሰብና አስቸኳይ ውጤት ለማግኘት መረባረብ ይገባናል።
ይህን የሂዩማን ራይትስ ዋች ዘገባ ያነበብነውንና እንዲሁ እንደማንኛውም ዜና የምናልፈው መሆን የለበትም። ተጨባጭ የሆኑና የወንጀለኛው መንግስት እንዲሰማው የሚያስችሉ፤ ከባድ ያልሆኑ ነገርግን ተፈጻሚነት ሊያገኙ የሚችሉ፤ ሰላማዊ ዘዴና እርምጃዎች ላይ ተወያይተን በዝርዝር በማስቀመጥ በውጭ አገር ተቀማጭ የሆንነው ኢትዮጵያዊ ያን በስራ ልንተረጉማቸው ይገባናል። ለመነሻ፤ መወያያና መንደርደሪያ ያህል የሚከተሉት እነሆ።
1. ቢያንስ ለሶስት አለያም ለስድስት ወራትም ሆነ ለአንድ ዓመት የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላዎች ከኢትዮጵያውያን የሚያገኙትን ገቢ ለመቀነስ፤ እነደ ፓስፖርት የማሳደስ ቪዛ የማስመታት፤ የውክልና ሰነዶችን የማጻፍ፤ ቤትና መሬት ለማሰራትና ለመግዛት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ወዘተ የሚጠይቁ ሥራዎችን ወደነዚህ የመንግስት አውታሮች ዘንድ ሄዶ ወይም በፖስት ቤት አማካኝነት ልኮ አለማሰራት።
2. ቢያንስ ለሶስት አለያም ለስድስት ወራትም ሆነ ለአንድ ዓመት በውጭ አገር በሚገኙ በግልጽ በወያኔ ካድሬዎች በሚንቀሳቀሱ ወይም የወያኔን ካፒታልና ቢዝነስ በሚያንቀሳቅሱ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ በማድረግ ምንም ዓይነት የዕቃ ግዢ ወይንም የገንዘብ ልውውጥ እንዲህ ካሉ ሰዎች ጋር ከማድረግ መቆጠብ። ይህንን ዐቀብ በምናካሂድበት ወቅት እንቅስቃሴው በዘር ላይ ያልተመሰረተና ያለበቂ ማስረጃ በአንድ ብሔር ተወላጆች ላይ ያላነጣጠረ እንዲሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ወደዚያ ዓይነት የትግል አቅጣጫ ሊመሩ የሚፈልጉትን ግለሰቦች በሙሉ መምከርና ካልሆነም መገሰጽ ይገባል።
3. ቢያንስ ለሶስት አለያም ለስድስት ወራትም ሆነ ለአንድ ዓመት የመንግስት አውታር ለሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሆነ ሌሎች ባንኮች ገንዘብ ለሚያደርሱ እንደ ዌስተርን ዩኒየን የመሳሰሉ ወደ ወያኔ ካዝና የውጭ ምንዛሪ (ፎርን ኤክስቼንጅ) በሚያስገቡ ድርጅቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚላክ ገንዘብ አለመላክና የሚኖሩበትን አገር ሕግ ሳይጥሱ በሌላ ዘዴ አገር ቤት ለሚገኝ ወዳጅ ዘመድ ብር መላክ።
4. ቢያንስ ለሶስት አለያም ለስድስት ወራትም ሆነ ለአንድ ዓመት የወያኔን ዓላማ በግላጭ ከሚያስፈጽሙ የወያኔ ካድሬዎች ጋር በማንኛውም አጋጣሚ ድጋፋቸውን የሚሰጡት መንግስት በደምና ግፍ የተጨማለቀ መንግስት መሆኑን ባላሰልሰ በማስረዳት ላጭር ጊዜም ቢሆን ከጋራ ተሳትፎ ማግለል። ይህንን ዐቀብ በምናካሂድበት ወቅት እንቅስቃሴው በዘር ላይ ያልተመሰረተና ያለበቂ ማስረጃ በአንድ ብሔር ተወላጆች ላይ ያላነጣጠረ እንዲሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ወደዚያ ዓይነት የትግል አቅጣጫ ሊመሩ የሚፈልጉትን በሙሉ መምከርና ካልሆነም መገሰጽ ይገባል።
5. ቢያንስ ለሶስት አለያም ለስድስት ወራትም ሆነ ለአንድ ዓመት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አለመጠቀም። ወያኔ በአሁኑ ጊዜ የጭካኔና የግፍ ሥራውን ለማካሄድ ብዙ የገንዘብ ዐቅም ስለሚያስፈልገው ይህንን የገቢ ምንጩን መቀነስ ለትግላችን መፋጠን ይጠቅማል።
6. ወያኔ በኢትዮጵያ ውስጥ መልካም ሥራ እያካሄደ እንዳለ ሊናገሩ የሚፈልጉ ሞኝና ተላላዎች አገሪቱ በደም የተነከረችና የንጹሃን ሰቆቃ የሚጮህባት አገር እንደሆነች ባላሰለሰ በመንገር በእጅ አዙር የወያኔ ቱልቱላ ቃል አቀባዮች እንዳይሆኑ መምከርና የኢኮኖሚ ዕድገትም እውነትነቱም ሆነ ተፈጻሚነቱ ሊረጋገጥ የሚችለው የሰው ልጅ በሰውነቱ ሲከበርና ያች ሃገር የጥቂቶችና የዘረኞች ሳትሆን የሁሉ ኢትዮጵያዊያን በመሆኗ ጥቂቶች ዘረኞች የብዙዎችን መብት ረግጠው ላንተ እኛ ብቻ ነን የምናውቅልህ እያሉ የሚያናፍሱት ወሬ በሰለጠነው ዘመን ሊሰራና ሊቀጥል የማይችል ተራ ቱልቱላ መሆኑን እንዲገነዘቡ ማድረግ።
7. ወያኔ ሰሞኑን በዳያስፖራ የሚገኙትን የዋህ ኢትዮጵያውያን ገንዘባችውን ለመቀማት የያዘው ዘዴ “ኢትዮጵያ ውስጥ መሬትና ኮንዶ ለመሥራት ኢንዲያስችላችሁ 60/40 የሚባል ፕሮግራም ተዘጋጅቶላችኋል፤ 60 በመቶ (60%) በውጭ ምንዛሪ ካስቀመጣችሁ ቀሪዊን አርባ በመቶ (40%) በአነስተኛ ወለድ የሚከፈል ብድር አዘጋጅቼላችኋለሁ፤ ነገር ግን የውጭ ምንዛሪውን በቀጥታ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባችኋል” በማለት ኢትዮጵያውያንን በግፍ ቀንበሩ ለረጅም ጊዜ ሊይዝ የሚያስችለውን ሃብት ለመሰብሰብ ጥረት ኢያደረገ ስለሆነ ቢያንስ ለሶስት አለያም ለስድስት ወራትም ሆነ ለአንድ ዓመት ይህን ከመሰለ ለወያኔ የውጭ ምንዛሪ መሰብሰቢያ ማታለያ ዘዴ ውስጥ ከመውደቅ መቆጠብ።
እነኝህ ከላይ የተዘረዘሩት ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ መልስ ባጭሩ ለመስጠት የታቀዱ ናቸው እንጂ ሁሉንም ዘዴ አያካትቱም። የተለያዩ ኢትዮጵያውያን በዝርዝሮቹ ላይ ተጨማሪም ሆነ ማሻሻያ ወይም አዳዲስ ገንቢ ሃሳቦች ቢያቀርቡ ጥረታችን ውጤታማ ይሆናል የሚል ግምት አለኝ፡
የወያኔ የክፋት የጭካኔና የበደል ቀንበር አንድ ቀን ከኢትዮጵያውያን ጫንቃ ላይ ወድቆ ይፈጠፈጣል!!
የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ የማለቂያው ቀን ሩቅ አይደለም!!
ውድ አገራችን ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!