Thursday, October 10, 2013

የባለ ስልጣናት ልጆች የኤርትራውያን ስደተኞችን እድል እየተጠቀሙ ወደ አውሮፓና አሜሪካ እንደሚወጡ ተጠቆመ

ኦክቶበር 10, 2013
ሔለን ንጉሴ/ኖርዌ

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮምሽን በኢትዮጵያ የኤርትራዊያን ስደተኞች ቁጥር ሰባ ባት ሺህ መሆኑን ይናገራል። እነኚህ ስደተኞች እድል እየተነፋጋቸው በስደተኛ መጠለያ ጣቢያው ውስጥ ለረጅም አመታት ከመቆየታቸው የተነሳ በመሰልቸትና  ተስፋ በመቁረጥ በህገወጥ መንገድ እየተሰደዱ በርካታ ኤርትራውያን ህይወታቸው እንዳለፈ ስደተኞቹ ይናገራሉ። አሁን በቅርብ በጣሊያን በተከሰተው አደጋ የብዙ ኢትዮጵያውያን እና በርካታ ኤርትራዊያን ስደተኞች ህይወታቸው ማለፉ አለምን እያስደመመ ያለ ዜና ነው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ከሟቾቹ ውስጥ በኢትዮጵያ በስደተኞች ኮምሽን ስር ተመዝግበው እድል የተነፈጋቸው በህገወጥ መንገድ በመሄዳቸው ህይወታቸውን ያጡ ስደተኞችም መኖራቸውን የስደተኞች ኮምሽን ገልፅዋል።

ሰሞኑን ታዲያ በኢቲዮጵያ  የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ወደ ሌላ ሃገር እንስፈር በሚል ለስደተኛው ኮምሽን ባነሱት ጥያቄ በስደተኞቹ ጣቢያ ውስጥ ውጥረት ነግሶ፤ ግጭት ፈጥሮ በግጭቱም የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ውጥረቱም ለተከታታይ ሶስት ቀናት መቆየቱን እንዲሁም ስደተኞቹ በኢትዮጵያ ለተባበሩት የስደተኞች ኮምሽን ጥያቄዎቻቸውን በመግለፅ የኢትዮጵያ መንግስት በመካከላቸው ያስቀመጣቸውን ሰላዮች ከመካከላቸው እንዲያወጣና እንዳይሰለሉ በተጨማሪም ወደ አውሮፓና አሜሪካ በኤርትራዊያን ስደተኞች ስም የሚላኩት እና እድላቸውን እየወሰዱ ያሉት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ልጆች እንጂ ኤርትራውያን ባለመሆናቸው የስደተኛ ኮሚሽኑ ስደተኞቹን ወደ ሌላ ሃገር እንዲያሰፍራቸው ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። 

እንደሚታወቀው ገዢው ፓርቲ የባለስልጣናቱን ልጆች እና ጀሌዎቻቸውን በኤርትራውያን ስም ወደ አውሮፓና አሜሪካ በመላክ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ለመሰለል የስለላ መረባቸውን በመዘርጋት እንደፈለጉ በአውሮፓና በአሜሪካ እየኖሩ ወደ ሃገር ቤት በመመላለስ የስለላ ስራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ። በሃገር ቤት በየመንደሩና በየቤተሰቡ የስለላ መረባቸውን ዘርግተው ሰው እርስ በራሱ እንዳይተማመንና አንዱን ባንዱ እያሰለሉ ህዝብ እያስጨነቁና እያስፈራሩ እንደሚኖሩ ይታወቃል ወያኔም የራሱን ዜጎች በማሰለል የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም ከፍተኛ የሃገሪቱን ሃብት እያወደመ ይገኛል።

የወያኔ ሆድ አደር ጀሌዎች እዚህም በስደት በምንኖርበት ነፃ ምድር እንኳን ሳይቀር ይሰልሉናል ሊያስፈራሩንም ይሞክራሉ ነገር ግን በምንኖርበት ሃገር የሰዎች የመናገርና ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት በሽበሽ ስለሆነ በፍርሃት ተሸማቆ ድምፁን ለማሰማት ያልቻለውን የህዝባችንን ድምፅ ወያኔ ከስልጣን እስከምናወርድ ድረስ ጮክ ብለን እናሰማለን አንፈራም፡፡ የወያኔ ጀሌዎችም እዚህም እዚያም እንደልብ የሚኖሩበት ዘመን ሊያበቃና ወንጀለኞች ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜም ቅርብ መሆኑን እንዲያውቁት መግለፅ እወዳለሁ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ውድቀት ለሆድ አደር ወያኔዎች

No comments:

Post a Comment