Monday, October 7, 2013

ዶ/ር ሙላቱ ታደሰ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ሆነው ተሾሙ

ኦክቶበር 07, 2013
ሄለን ንጉሴ

ዶ/ር ሙላቱ ታደሰ ከ1998 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለፕሬዘዳንትነት እስከታጩበት እለት በቱርክ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት  ሲሆን ባለ ትዳርና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ናቸው እንዲሁም የኦሮምኛ፤ አማርኛ፤ ፈረንሳይኛ፤ እንግሊዘኛ እና ቻይንኛ ቋንቁዎችን መፃፍና ማንበብ ጭምር እንደሚችሉ ተነገሮላቸዋል። በመሆኑም ለሚቀጥሉት ስድስት አመታት የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሆነው ማገልገል እንደሚችሉ ምክርቤቱ አምኖበት በእጩነት ያቀረባቸው ሲሆን፤

ዶ/ር ሙላቱ በዛሬው እለት የተወካዮች ምክር ቤት ያለምንም ተቃውሞ ፕሬዘዳንትነታቸውን በሙሉ ድምፅ ያፀደቀ በመሆኑ ከቀድሞው ፕሬዘዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ስልጣን ተረክበው ቃለ መሃላም ፈፅመዋል ለሚቀጥሉት ስድስት አመታት የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ሆነው ተሹመዋል። 

ለአዲሱ ፕሬዘዳንትም መልካም ምኞቴን እየገለፅኩ ለሚቀጥው የስራ ዘመናቸው የማንንም ራእይ አስፈፃሚ ሳይሆኑ የተሰጣቸውን የህዝብ አደራ በቅንንነት እንጂ በቀቀን ሆነው በሙት መንፈስ እንዳይመሩ አምላክ የሰጣቸውን አይምሮ በመጠቀም በማስተዋል እራሳቸውን ሆነው ሃገሪቷን በቅንነት እንዲያገለግሉ  መልክቴን አስተላልፋለሁ፡፡ 


No comments:

Post a Comment